The Christian News
5.37K subscribers
3.08K photos
29 videos
730 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
#የአዲስ አበባ ጎዳናዎች #ላይ #ለምን #ወንጌል እንሰብካለን? ለምን አዲስ አበባ #ብቻ?

ወንጌል መስበክ ከተፈለገ ወንጌል ያልደረሰባቸዉ ሌሎች የሃገራችን ክፍል ለምን አንሔድም ?

#ዝርዝር #መረጃ ይዘን እንመለሳለን እስከዛዉ የየራሳችሁን ምልከታ ማስፈር ትችላላችሁ።
በመዲናችን #አዲስ አበባ እጅግ ብዙ #ወንጌል የተሰራ ብዙዎች በወንጌል የተደረሱ ይመስላችኋል?

የአዲስ አበባ ጎዳናዎች በተለይም #መገናኛ#ሜክሲኮ#ፒያሳ#ጀሞ#አያት እና ሌሎች አከባቢዎችን ስንመለከት ከተማዋ በወንጌል የተጥለቀለቀች ይመስላል።

#ነገር #ግን ይመስላል #ነው #እንጂ እውነታው #እጅግ ከዚህ የራቀ እንደሆነ በቅርብ #ጊዜ በአንድ መድረክ አስደንጋጭ ሪፖርት ወጥቷል።

#ከተማ ተኮር የወንጌል አገልግሎት በሚል በቀጠና #ሙሉ ወንጌል አጥቢያ #ቤተክርስቲያን ጥናታዊ ጽሁፍ ቀርቦ ነበር።

ታዲያ #ይህ ጥናት ሲቀርብ ከ700 በላይ የሆኑ የአብያተ ክርስቲያናት መሪዎች መጋቢዎች #እና አገልግዮች በቦታው ተገኝተው ነበር።

ጥናቱ #ኢትዮጵያ #ውስጥ የሚገኙ ተለቅ ተለቅ ያሉ 11 ከተሞችን የሚዳስስ የነበረ ቢሆንም እኛ ግን ለጊዜዉ የመዲናችንን አዲስ አበባ #ብቻ የተወሰነ እንበል።

ይህም ጥናት አዲስ አበባ ላይ በወንጌል የተደረሰው ሕዝብ 6 በመቶ ብቻ እንደሆነ ያሳያል።

ይህም በወንጌል ካልተደረሱ የአለማችን ከተሞች መካከል አንዷ አዲስ አበባ እንድትሆን አድርጓታል።

#እንደ ጥናቱ ከሆነ የአዲስ አበባ ከተማ እድገት እጅግ ፈጣን እና ከሌሎች የአለም ከተሞች ጋር ተወዳዳሪነት ባለው መልኩ በፈጣን እድገት ውስጥ የምትገኝ ከተማ እንደሆነች ተጠቅሷል ነገር ግን ይህቺን ከተማ መድረስ በሚችል መልኩ አገልጋዮቻችን ግን ለዚህ ዝግጁ እንዳልሆኑ ጠቁመዋል።

ይህንን ለመድረስ እጅግ ቅንጅት የሚፈልግ ቢሆንም በከተማችን የሚገኙ አገልጋዮች ግን ወደዚህ መስመር ለመግባት ገና ብዙ ስራ እንደሚጠይቅ ተጠቁሟል።

ምናልባት ይህንን ለመቅረፍ የቤት ስራ ተወስዶ በየአመቱ ለመሰብሰብ እና ለመነጋገር ቀጠሮ ቢያዝም ውጤቱን ግን ለወደፊት የምናየው ይሆናል።
#ፍትህ ግን ምንድነው? 🤔 የትስ #ነው ያለው? 🤔
#እኛ ጥያቄያችን #አንድ እና ግልጽ  ነው።

#የቤተክርስቲያናችን_ንብረት_ይመለስልን!!! 🙏🙏🙏

37 ዓመታት በእንባ እና በጸሎት የጸሎት ቤቷን ለማስመለስ ፍትሕን ፍለጋ የተነከራተተችው #ቤተክርስቲያን ዛሬም ፍትህን ፍለጋ ላይ ነች።

የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ከ1950ዎቹ #መጀመሪያ ጀምሮ በተለይ ትምህርትን ከማስፋፋት አንጻር #ለሀገር እና #ለሕዝብ ጥቅም ላበረከተችው አስተዋጽዖ በወቅቱ የነበረው የመንግስት ስረዓት ከምስጋና ይልቅ ት/ቤቶቻችንና ጸሎት ቤቶቻችንን መውረስ ቀሏቸዋል።

በደርግ #መንግስት በግፍ የተወረሰው የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የኦሎምፒያው ጸሎት ቤታችን በአዲስ አበባ የመጀመሪያው የመሰረተ ክርስቶስ የማምለኪያ ስፍራ ነው።

#ይህ የመሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ንብረት #ማለት የሙሉ #ወንጌል ምዕመን እና የሙሉ ወንጌል ቤ/ክ ንብረት ማለት ነው። የመካነ ኢየሱስ ማለት ደግሞ የቃለ ሕይወት ነው። የቃለ ሕይወት ማለት የሕይወት ብረሃን የሕይወት ብረሃን ማለት የገነት የገነት ማለት የጉባኤ እግዚአብሔር ... በአጠቃላይ የወንጌል አማኞች #በሙሉ ነው።

ይህ ከ66 ዓመት በላይ የተሻገረው የጸሎት ስፍራ ንብረት ብቻ አይደለም ይልቁንም ለወንጌል የተሰደዱ ፤ ለወንጌል ዋጋ የከፈሉ የወንጌላውያን አማኞች #ታሪክ እና ቅርስም ጭምር ነው።

በ1943ዓ.ም የተመሰረተችው የመሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ከቀደምት የወንጌል አማኞች ቤተዕምነት መካከል አንዷ ብቻ ሳትሆን እውነተኛው የክርስቶስ ወንጌል ለአዲሱ #ትውልድ  እንዲሸጋገር ከ70 ዓመት በላይ #በኢትዮጵያ በሚመችም በማይመችም ሁኔታ #ውስጥ ስትሰራ ቆይታለች።

#ዛሬ ላይ መዲናችን #አዲስ አበባ ከሌሎች #አለም ላይ ከሚገኙ ከተሞች መካከል ለመወዳደር ሌት ተቀን እየተጋች ትገኛለች። በዚህ ውስጥ ታዲያ በከፊሉ አዳዲስ ሲገነባ በከፊሉ ለተቸገሩት ሲደረስ በሌላ አቅጣጫ ግን እንሳኩን ያልተመለሱ #ብዙ ጥያቄዎች እንዳሉ የአደባባይ ሚስጥር ነው።

ታዲያ በመዲናችን #ዛሬም ፍትህን ከሚጠይቁ ተቋማት መካከል አንጋፋዋ የመሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አንዷ ነች።

ስለዚህ ህጋዊ የሆነው የቤተክርስቲያን ታሪክ ፤ ቅርስ እና ንብረታችን የሆነው የጸሎት ቤቶቻችን ይመለሱልን የማያቋርጥ ጥያቄያችን ነው!!!

ይህ #መልዕክት የሚደረሳችሁ ምዕመናን እና ኢትዮጵያውያን በሙሉ የቤተክርስቲያናችን ንብረት እስኪመለስ ድረስ ሁላችንም #SharePost በማድረግ ለሁሉም እናድርስ!!!

The Christian News - የክርስቲያን ዜና በዚህ ዙሪያ ተጨማሪ ዘገባዎችን በተለያየ ጊዜ ይዘን የምንመለስ ይሆናል።

#share #share #share #share
በርግጥ ወንጌላውያን #በዚህ ደረጃ ፍትሕ ተጓድሎባቸዋል ?

#ይህንን #ጥያቄ #ለምን በተደጋጋሚ ማንሳት አስፈለገ ?

ሁላችሁም መልሱን አዘጋጁ #እኛ #ግን የራሳችንን ሃሳብ እንሰነዝራለን።

በትላንትናዉ ዕለት #የኢትዮጵያ #ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካዉንስል በወንጌላዊያን አማኞች እና አብያተክርስቲናት ላይ እየደረሰ ስላለዉ ፍትህ መጓደል ለሚዲያዎች ጋዜጣዊ #መግለጫ ሰጥቷል።

በካውንስሉ ጠቅላይ ጽሐፊ አማካኝነት በተሰጠዉ መግለጫ #ላይ በዋናነት ከ 6 በላይ .. የሆኑ (የደረሱ የፍትሕ መጓደል) የሚያሳዩ ነጥቦች ተጠቅሰዋል።

1. በደርግ #ዘመን የተወረሱ የቤተክርስቲያን ይዞታዎች በኢሕአዴግ ዘመን በከፊል ቢመለሱም እስካሁን ያልተመለሱ የኦሎምፒያ መሰረተ #ክርስቶስ ፣ የአዲስ ከተማ ገነት፣ የኢትዮጵያ ወንንጌላዊት #ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ብረት የሆነው የጉድ ሼፐርድ ማዕከል ፣ቄራ አካባቢ ያለው የብርሃነ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን አዳራሽ፣እና ሌሎች እስካሁን ያልተመለሱ ይዞታዎች ሲሆኑ እነዚህ ይዞታዎች የቤተክርስቲያን ንብረት በመሆናቸዉ እንዲመለሱ ተጠይቋል።

2 የድሬዳዋ መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን #በአንድ ወር #ጊዜ ዉስጥ ይዞታዋን ለቃ እንድትነሳ የከተማዉ አስተዳደር የወሰንኑ ቢሆንም የከተማዉ አስተዳደር እና የቤተክርስቲያኒቱ መሪዎች እንዲሁም የካውንስሉ አመራሮች ሰፊ ዉይይት አድርገዉ የከተማዉ አስተዳደር ጉዳዩን እየመከረበት ይገኛል። የከተማዉ አስተዳደር የደረሰበትን ደረጃ በአጭር ጊዜ ግልፅ እንዲያደርግ ተጠይቋል።

3 የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር የሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን ይዞታ ነጥቆ የራሱ ጽህፈት #ቤት አድርጎት ይገኛል። እንዲሁም የቃለ #ህይወት ቤተክርስቲያን ይዞታ የሆነዉን የኩሪፍቱ የጸሎት ማዕከል በተመለከተም በማእከሉ #ምንም አይነት የልማት #ስራ ቤተ ክርስቲያን እንዳታከናወን በማገድ የቤተክርስቲያኑን ይዞታ ለመንጠቅ እንቅስቃሴ ላይ እንደሚገኝኝ ተገልጾ የቢሾፍቱ #ከተማ አስተዳደር ከዚህ ህገወጥ ድርጊቱ እንዲቆጠብ እና የወሰደዉን የቤተክርስቲያን ንብረት እንዲመልስ ተጠይቋል።

4. በአዲስ አበባ ዙሪያ ባለችው የሸገር ከተማም የፈረሱ የወንጌላዊያን የእምነት ተቋማት ይዞታቸዉ እንዲመለስ እንዲሁም በከተማዋ ለ23 አብያተክርስቲያናት ከካቢኔ #ቦታ ተወስኖላቸዉ ቦታቸዉን መረከብ ላልቻሉ በአፋጣኝ ካቢኔ የወሰነዉ ዉሳኔ ተግባራዊ እንዲሆን ተጠይቋል።

5 የመቃብር ስፍራን ጥሶ በመግባት እየተደረገ የሚገኘዉ አግባብ ያልሆነ ተግባር በአስቸኳይ እንዲቆም

6 በምዕራብ ኢትዮጵያ በቄለም ወለጋ ዞን በጊዳሜ ወረዳ ዘጠኝ ምእመናንን የአምልኮ ስነስርአት እየፈፀሙ ካሉበት ሌሊት ላይ ተወስደዉ መረሸናችው #እጅግ #አሳዛኝ እንደሆነና ለነዚህ ንፁሃን ፍትህ እንዲሰጥ ተጠይቋል።

በአጠቃላይ #ይህ #ሁሉ እየሆነ ያለዉ የታችኛዉ የመንግስት አካል የመንግስትን ስልጣን በመጠቀም ጥቂት ግለሰቦች የግል አጀንዳ ይዘዉ የሚፈፅሙት ተግባር ነዉ።

የፌደራል መንግስት ጣልቃ በመግባት ፍትህ ሊያሰፍን ይገባል ሲል የኢትዮዽያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት #ካዉንስል በመግለጫዉ አስታዉቋል።

#ታዲያ ይህ ሁሉ የፍትህ ጥያቄ አለ #ማለት መጀመሪያላይ ለጠየኩት ጥያቄ ትክክለኛ ምላሽ በርግጥም ወንጌላውያን በግልፅ በአደባባይ #ፍትሕ ተነፍገዋል የሚል ነዉ።

ይሄንን ጥያቄ በዚህ ሰዓት ለምን ማንሳት አስፈለገ ከተባለ ደግሞ ከዚህ በፊት ለበርካታ አመታት ምላሽ ያላገኙ እና ፍትህ ያልተሰጣቸው ጥያቄዎች ባለበት ዛሬም ሌላ በደል እየደረሰ ስለሆነ ማንሳት አስፈላጊ ነዉ።

The Christian News - የክርስቲያን ዜና የወንጌላውያን ድምፅ በመሆን ለበርካታ ጊዜያት ሲያገለግል ቆይቷል። አሁንም ገና ለቤተክርስቲያን ፍትህ ካልተሰጠ በስተቀር ጥያቄያችንን ማስተጋባታችን ይቀጥላል።

ፍትሕ ለወንጌላዉያን ቤተክርስቲያን
#አስደሳች #ዜና ለወንጌል አማኞች #በሙሉ

#በመስቀል #አደባባይ የንስሐ፣ የምልጃና የምስጋና ፕሮግራም መዘጋጀቱ ተገለጸ።

በዛሬው እለት #የኢትዮጵያ #ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል መሪዎች በአዲስ አበባ በመስቀል አደባባይ የንስሐ፣ የምልጃና የምስጋና ፕሮግራም መዘጋጀቱን ለሚዲያዎች መግለጫ ሰጥተዋል።

በተሰበረ #ልብ፣ በንስሐ መቅረብ የመጀመሪያ ተግባራችን መሆን እንዳለበት የጠቀሱት መሪዎቹ “#ወደ ደጆቹ በመገዛት ወደ አደባባዮቹም በምስጋና ግቡ፣ አመስግኑት፣ ስሙንም ባርኩ” (መዝ 100)፤4 በሚለው ቃለ #እግዚአብሔር መሠረት መጋቢት 8 ቀን 2016 ዓ/ም ከቀኑ 7፡00 ጀምሮ #በአዲስ አበባ #መስቀል አደባባይ የንስሐ፣ የምልጃና የምስጋና በዓል ለማካሄድ አስፈላጊው ዝግጅት #ሁሉ ተጠናቋል ብለዋል።

አሁንም የእርስ በርስ መጠፋፋቱ አልቆመም ያሉት መሪዎቹ መደማመጥና መከባበር በመካከላችን እንዲኖርና ለይቅርታና ለፍቅር ልባችን የቀና እንዲሆንና ፀጋውንም እንዲያበዛልን #እግዚአብሔርን የምንማጸንበት #ጊዜ ይኖራል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በፕሮግራሙ የሚካፈለው የሕዝብ #ብዛት እጅግ ብዙ ስለሆነ ስብሰባው የሚካሄደው በመስቀል አደባባይ ነው፡፡

በመሆኑም መላው የወንጌል አማኝ በነቂስ ወጥቶ #በእግዚአብሔር ፊት የንስሐ፣ የምልጃና የምስጋና ፕሮግራሙ ተካፋይ እንዲሆን ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

The Christian News - የክርስቲያን ዜና በስፍራው ተገኝተን ዝርዝሩን አሰናዳንላችሁ።

#photo Christian tube - ክርስቲያን ቲዩብ

ዝርዝር መረጃ ምሽት ላይ በቪዲዮ ይዘንላችሁ የምንመለስ ይሆናል።
https://www.youtube.com/channel/UCeHRJCDJ0wUDaBfAFmuMa7A?sub_confirmation=1
#ኑ #የእግዚአብሔርን #ቤት በጋራ እንስራ!!!

ለብዙዎች መጠለያ የሆነችው እና ለአርሲ ዩንቨርስቲ አሰላ ካምፓስ ክርስቲያን ተማሪዎች ህብረት ማምለኪያ የሆነችው የአሰላ አርዱ ቁጥር 2 #ሙሉ #ወንጌል ቤተክርስትያን #ዛሬ የሁላችንን እገዛ ትፈልጋለች።

#አሁን የምትገኝበት የማምለኪያ አዳራሽ የአምልኮ ፕሮግራም ለመካፈል የሚመጡትን አማኞች መያዝ ስላልቻለ እና እንዲሁም የአሁኑ አዳራሽ እየፈረሠ ስለሚገኝ ከአጥቢያዋ በረከት የተካፈላችሁ በዓለም ዙሪያ እንዲሁም በሃገር ውስጥ የምትገኙ የአሰላ አርዱ ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን ቤተሰቦች ወዳጆች እንዲሁም #የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ለዚህ ስራ እጆቻቸሁን እንድታበረቱ ስንል በጌታ ፍቅር እንጠይቃለን።

ከዚህም ጋር ተያይዞ ከመጋቢት 6 እስከ 8/2016 ዓ.ም በአጥቢያዋ የተዘጋጀ #ልዩ ኮንፍራንስ ስላለ በቦታው በመገኘት በዚህ የወንጌል ስራ እንድትሳተፉ #በጌታ #ፍቅር እንጠይቃለን።

በተጨማሪም በቦታው መገኘት የማትችሉ ከታች በመተቀመጠው የቤተክርስቲያኒቷ አካውንት እጆቻችሁን ትዘረጉ ዘንድ በጌታ ፍቅር እንጠይቃለን።

1000515969962 ንግድ ባንክ
1600860054837 ብርሃን ባንክ

የአሰላ አርዱ ሙሉ ወንጌል #ቤተክርስቲያን
#መንገድ #ዝግ #ነዉ

#የኢትዮጲያ #ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል በመስቀል አደባባይ የሚያከናውኑት የፀሎት ፕሮግራም ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የተወሰኑ መንገዶችን ለተሸከርካሪ ዝግ እንደሚደረጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ

አሽከርካሪዎች እንደ ተለመደው ለትራፊክ ፖሊሶች ትዕዛዝ ተባባሪ እንዲሆኑ ተጠይቋል፡፡

#ነገ ዕሁድ መጋቢት 8 ቀን 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ በመስቀል አደባባይ ከሰዓት በሗላ ከቀኑ 7፡30 እስከ 12፡00 ሰዓት ድረስ የኢትዮጲያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል የፀሎት መርሐ-ግብር ስለሚያከናውኑ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚደረጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

አሽከርካሪዎች መረጃው አስቀድሞ ኖሯቸው ሌሎች አማራጭ መንገዶችን በመጠቀም ለትራፊክ ፖሊስ አባላት ትዕዛዝ ተባባሪ እንዲሆኑ ፖሊስ ጥሪውን እያስተላለፈ፡-

• ከቅዱስ ኡራኤል አደባባይ #ወደ መስቀል አደባባይ ለሚጓዙ ተሽከርካሪዎች ኡራኤል አደባባይ ላይ

• ከቦሌ ጌቱ ኮሜርሻል አቅጣጫ ወደ መስቀል አደባባይ ኦሎምፒያ አደባባይ በታች እና በላይ እንዲሁም ግራና ቀኝ

.የቀድሞው አራተኛ ክፍለጦር (ጥላሁን አደባባይ ላይ )

• ከለገሀር መብራት ወደ መስቀል አደባባይ ለሚጓዙ ለገሀር መብራት ላይ

• ከሀራምቤ መብራት ወደ መስቀል አደባባይ ሃራምቤ መብራት ላይ

• ከብሔራዊ ቤተ መንግስት ወደ መስቀል አደባባይ ብሔራዊ ቤተ መንግስት አጠገብ ዕሁድ መጋቢት 8/16 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡ 00 ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ መንገዶቹ ለጊዜው ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ፡፡

ፕሮግራሙ በሚከበርበት ዙሪያ እና በአካባቢው በግራና በቀኝ ለረጅምም ሆነ ለአጭር ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጨምሮ ገልጿል፡፡
#እንኳን ደስ አለን. .

#ክርስቲያን ፖድካስት #በክርስቲያን ቲዩብ በቅርብ ቀን..

ወንጌላዉያን ዘንድ ፈር ቀዳጅ እና ለብዙዎቻችን ምሳሌ የሆነዉ Christian tube - ክርስቲያን ቲዩብ #አሁን ደግሞ በአዲስ አቀራርብ ብዙዎችን ተደራሽ ለማድረግ መጥቷል።

በጌታ የሆንን ክርስቲያኖች ወንጌልን ለብዙዎች የምንደርስበት ፣ የእግዚአብሔርን ቃል የምንወያይበት፣ በወቅታዊ የቤተክርስቲያን ጉዳይ ላይ ሀሳባችንን የምናካፍልበት፣ የህይወት ተሞክሯችንን ለሌሎች የምናጋራበት፣ እግዚአብሔር ያደረገለንን የምንመሰክርበት የክርስቲያኖች መድረክ ክርስቲያን ፖድካስት በክርስቲያን ቲዩብ የዩቲዩብ ቻናል ተጀምሯል።

https://youtube.com/@christiantube4198?si=yUCsLdTyUAFh8VJz

ማንኛውንም በዚህ ፕሮግራም መነገር አለበት የምትሉትን ነገር ልታጋሩን የምትወዱ በስልክ ቁጥር +251777418556 ይደውሉልን

#ወንጌል በተለያየ መንገድ ያልተደረሱትን ለመድረስ ፣ የተደረሱትን ለማጠንከር ይቀጥላል...
152 #ሰዎች ተጠመቁ!!!

#በመሠረተ #ክርስቶስ #ቤተክርስቲያን 152 ሰዎች የውሃ ጥምቀት ወስደው #ወደ ቤተክርስቲያን ተቀላቀሉ ።

ቦሰት አካባቢ 62 ሰዎች እና በመካከለኛው ሥምጥ ሸለቆ ዝዋይ አጥቢያ አማካኝነት ደግሞ 90 ሰዎች በአጠቃላይ 152 ወገኖች በዛሬው ዕለት የውሃ ጥምቀት ወስደው ወደ ቤተክርስቲያን ተቀላቅለዋል ።

በተጨማሪም #ነገ ዕለት በደቡብ አዳማ ክልል ሌሎች 40 ሰዎች የውሃ ጥምቀት እንደሚወስዱ ይጠበቃል።

በአጠቃላይ በመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን "#አጀንዳ28 19" ወይም "#አጀንዳችን_ወንጌል" የሚለውን እንደ መራህ በመከተል በዓመት እያንዳንዱ አጥቢያ በቁጥር 10% እድገት እንዲያሳዩ በተቀመጠው አቅጣጫ አካል መሆኑ ወደፊትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የኮሚኒኬሽን ቢሮ አሳውቋል።

#ወንጌል ካልሰራን #ምንም አልሰራንም።
#ቤተክርስቲያን እዉቅና ሰጠች።

ወንጌላዊ ጋሽ ቦጋለ ለማ ለረጅም አመታት በቀጠና #ሁለት #ሙሉ #ወንጌል ያገለገሉ #እና አጋሽ ቦጋለ ለማ ለረጅም አመታት በቀጠና ሁለት ሙሉወንጌል ያገለገሉ እና አሁን ደግሞ በአዲስ ከተማ ሙሉ ወንጌል አጥቢያ ውስጥ እያገለገሉ ይገኛሉ ይህንንም በማስመልከት ቤተክርስቲያን እውቅና ሰጥታለች።

ቤተክርስቲያን እንደዚህ ላሉ አገልጋዮች እውቅናና ክብር መስጠቷ እጅግ የሚያበረታታ እና ሊቀጥል የሚገባ ተግባር ነው።

Christian ዜማ Tube ገፅ የተወሰደ...
በኦሮሚያ ክልል ኢሉአባቦራ መቱ ከተማ ለሃይማኖታዊ ስብከት አደባባይ ወጥተው የነበሩ የሙሉ ወንጌል ቤተ ክርስቲያን አባላት በአካባቢው የፀጥታ ኃይሎች ድብደባ ተፈጽሞባቸው ጉዳት እንደደረሰ ለቢቢሲ ተናገሩ።

ቢቢሲ ያነጋገራቸው የቤተክርስቲያኒቱ መሪዎች እና በወቅቱ በስፍራው የነበሩ ግለሰቦች እንዳሉት ከሆነ የፀጥታ ኃይሎቹ በፈጸሙት ድብደባ የተጎዱት ሰዎች ከ20 በላይ እንደሚሆኑ ገልጸዋል።

የመቱ ከተማ ከንቲባ አቶ ተሻለ ኤጀርሶ በበኩላቸው የቤተክርስቲያኒቱ አባላት ያካሄዱት የጎዳና ላይ ስብከት ከተገቢው የመንግሥት አካል ፈቃድ እንዳላገኘ ተናግረዋል።

የሙሉ ወንጌል #ቤተክርስቲያን አገልጋይ የሆኑት ፓስተር ብርሃኑ ዘለቀ በበኩላቸው ከመቱ እና አካባቢዋ የመጡ የቤተክርስቲያኒቷ አባላት እሁድ ግንቦት 25/2016 ዓ.ም ለጎዳና ላይ ስብከት በወጡበት በፖሊስ ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል።

“ወደ ከተማዋ ጎዳና የወጣነው ወንጌል ለመስበክ ነው። ከአንድ #ሺህ #ሰው በላይ ይሆናል በወቅቱ የወጣው። መንገድ ሳንዘጋ በጎዳናው ላይ እየተንቀሳቀስን እየሰበክን ነበር። ሕገ መንግሥታዊ መብታችን ነው። የፀጥታ ኃይሎች መጥተው አስቆሙን” ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

የከተማው ከንቲባ በበኩላቸው “በዕለቱ በከተማችን የትኛውም የእምነት ተቋም በከተማዋ ጎዳና ላይ አምልኮ ለማካሄድ በሚል ፈቃድ አልጠየቀም፣ አልወሰደም። በከተማው ጎዳና ላይ ወጥተው የነበሩ ሰዎችን ፖሊስ አስቁሟቸዋል። ፖሊስ ያስቆማቸው ፈቃድ ስለሌላቸው እና የመሰባሰባቸው ምክንያት ባለመታወቁ ነው” ብለዋል።

ፓስተር ብርሃኑ፣ የፀጥታ ኃይል አባላቱ ምዕመናኑን ካስቆሟቸው በኋላ እየዘመሩ የነበሩትን በመኪና ጭነው ወደ ፖሊስ ጣቢያ መውሰዳቸውንም ይናገራሉ።

ዝርዝር መረጃ ያንብቡ https://www.facebook.com/thechristiannews2018

#ወንጌል
#ዜና
«ዲልቢ ገለታ የሱሲፍ" የተሰኘ የመዝሙር ድግስ በሚሊኒየም #አዳራሽ ሊካሄድ ነዉ።

ኤልሀዳር ኢንጂነሪንግ ከዘማሪ ጳውሎስ ተገኝ ጋር በመተባበር «ዲልቢ ገለታ የሱሲፍ» የተሰኘውን የመዝሙር ድግስ በሚኒሊየም አዳራሽ ሰኔ 2/2016 ዓ.ም ቀን ከ7፡00 ጀምሮ ማዘጋጀቱን #ዛሬ ግንቦት 27/2016 ዓ.ም በስካይ ላይት ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል ።

#ዘማሪ ጳውሎስ ተገኝ ሶስት አልበሞችን እና የተለያዩ ዝማሬዎችን ከተለያዩ ዘማሪዎች ጋር በመስራት ለኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ያበረከተ ሲሆን «ሙጫ ካዮ» ከተሰኘ የህፃናት ህብረት ጋር በመሆን ሁለት ቪሲዲዎችን በመስራት ለአማኞች አድርሷል።

በእለቱ ስለታማ ነገሮች ምግብ እና መጠጥ ይዞ መግባት እንደማይቻል የተገለፀ ሲሆን በሚሊኒየም አዳራሽ መጠጥ እና ምግብ በሽያጭ እንደተዘጋጀ ተነግሯል።

በዚህ ፕሮግራም ለመሳተፍ የመግቢያ ዋጋው በነፃ ስለሆነ መጨናነቅ እንዳይፈጠር ከጠዋቱ 4 ሰአት ጀምሮ እንዲገኙ ጥሪ አስተላልፈዋል።

ፎቶ 📸 @ጥላሁን ደሳለኝ

#ወንጌል #ለዓለም #ሁሉ
በመቱ የሙሉ #ወንጌል አማኞች #ላይ ደረሰ የተባለው ድብደባ እንዲጣራ የአብያተ ክርስቲያናት ኅብረቱ ጠየቀ።

#እሁድ ግንቦት 25 በመቱ ከተማ ለወንጌል ስርጭት በወጡ ክርስቲያኖች ላይ በፖሊስ እና ሚሊሻዎች ድብደባ ተፈጽሟል። ጥቃቱ ከተፈጸመባቸው ወገኖች መካከል አስተያቷን ለአሜሪካ ድምጽ ራድዮ የሰጠችው ኤደን ግርማ እንዲህ ብላለች።

ኤደን ግርማ፣ ጥቃት የደረሰባት “የእሁድ አምልኮ ጨርሰን ለወንጌል ስርጭት ሶሪ ዳቦ የሚባልበት አካባቢ ስንደርስ ፖሊሶችና ሚልሻዎች በመኪና መጡ። መሬት ላይ ተቀመጡ ካሉ በኋላ፣ የተወሰኑ ወጣቶች ወደ ፖሊስ ጣብያ ወሰዱን።

አመሻሽ ላይ ከአንዱ አመራር ጋር ፖሊስ ጣብያው አካባቢ መሬት ተቀመጡ ብሎ እያወራን፣ ፖሊሶችና ሚሊሻዎች ድብደባ ጀመሩ። እኔ ጭንቅላቴን ተመቼ ስደማ፣ ሌሎችም በጣም ተጎድተው ወደ ሆስፒታል ለህክምና ተወስደናል።” ስትል ተናግራለች።

#ቄስ ደበላ ያደታ፣ የኢሉባቦር ዞን ወንጌላዊያን አብያተ ክርስትያናት ህብረት ሰብሳቢ በበኩላቸው “እኛ ህገ መንግስቱ በሚሰጠን መብት መሰረት እምነታችንን የማካሄድ መብት አለን። ከመንግስት ጋርም በሚያስፈልጉ ነገሮች ዙርያ በትብብር ስንሰራ ቆይተናል። መንግስት እንደዚህ ያደርጋል የሚል እምነት ባይኖረንም፣ የመንግስት መዋቅር ውስጥ ያሉ ሰዎች ግን ይሄንን እንዳደረሱ በትክክል እናውቃለን። ስለዚህ ሁኔታው በትክክል እንዲታራ እንጠይቃለን።” ብለዋል።

አቶ ተሻለ ኤጄርሶ፣ የመቱ ከተማ ከንቲባ በበኩላቸው “ከሳምንት በፊት ለነበረው ስብከተ ወንጌል ፍቃድ የተሰጠ ቢሆንም፣ እሁድ ግንቦት 18 ሲደረግ ለነበረው የወንጌል ስርጭት የተሰጠ ፍቃድ የለም። አላስፈላጊ ድብደባና ግጭት ከፖሊስ ዘንድ መድረሱን ተመልክተናል። ከጸጥታ አካላት ጋርም ይሄንኑ ጉዳይ በተመለከተ ምርመራ እየተካሄደ ነው።”

VOA Amharic
#ወንጌል ይቀጥላል_ወንጌልን የሚያሳድዱ ይጠፋሉ
#ቢሾፍቱ ቃለ ህይወት ኩሪፍቱ ማዕከል

በኢትዮጵያ ቃለ ህይወት ቤ/ክ ኩሪፍቱ ማዕከል ላይ ኢ-ህገ መንግስታዊ በደል ደርሷል። ድርጊቱን ተከትሎ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያን ካውንስል መግለጫ ሰጥተዋል።

የጽ/ቤቱ ሃላፊ መጋቢ ጌትነት ለማ፡ ማዕከሉ በባለቤትነት ከያዘው መሬት፡ 40ሺህ ካሬ ሜትር የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር፡ በሃይል ለሁለት ግለሰቦች ተሰጥቷል ብለዋል።

ፍርድ ቤት የመሬት ባለቤትነቱን ለቢሾፍቱ ቃለ ህይወት ኩሪፍቱ ማዕከል ቢያረጋግጥም፡ የከተማ አስተዳደሩ የግንባታና ስራ ሂደትን የከተማ አስተዳደሩ፡ እያዘገየ ቆይቷል። ትላንት ሰኞ ሃምሌ 3 ወታደር ይዞ ወደ ቤ/ክ ግቢ ገብቶ ችካል በመትከል ህገ ወጥ ስራ ሰርቷል።

የከተማ አስተዳደሩ መሬቶችን የማልማት ትልቅ ፍላጎት እንዳለው የሚታወቅ ቢሆንም፡ ስፍራው ለልማት ከሆነ፡ ቤ/ክኗ እየሰራች ቆይታለች ብለዋል የካውንስሉ ጽ/ቤት ሃላፊ።

እኛ ወንጌላዊያን አመጸኞች አይደለንም፡ መንግስት ትክክለኛ ፍርድ እንዲሰጥና ውሳኔ እንዲያስተላልፍ፡ እንጠይቃለን። ድርጊቱን የክልል፡ የፌደራል የመንግስት ሃላፊዎች በታችኛው የመንግስት መዋቅር እየተፈጸሙ ያሉ በደሎች መፍትሄ እንዲሰጡ እንጠይቃለን።

🔴 ዛሬ ሃምሌ 4 የቤተ ክርስቲያኗ መሪዎች ወደ ስፍራው፡ በሄዱበት ወቅት የማዋከብ የማሸማቀቅ እና ወደ እስር መውሰድ ኢ-ህገ መንግስታዊ ድርጊቶች ተፈጽመዋል።

ከዚህ ቀደምም በቢሾፍቱ ሙሉ ወንጌል ቤ/ክ እንዳየነው፡ የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር የፍርድ ቤትን ውሳኔ አያከብርም። እነዚህ ድርጊቶች የመንግስት አካላት ከግል ባለሃብቶች ጋር በመሻረክ የሚሰሩት ነው።

መሰል ድርጊቶች በተለይ በቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር በተደጋጋሚ ሲፈጸሙ አይተናል፡ መጠየቃችንንም አናቆምም። ጥያቄው ዛሬ ባይመለስም፡ ለልጆቻችን እናወርሰዋለን። እንደ ከዚህ ቀደሙ ማርክሲስት መንግስት ሁሉ፡ ወንጌልን የሚያሳድዱ ይጠፋሉ፡ ወንጌል ይቀጥላል። ካስፈለገ ሃገራዊ ሰላማዊ ሰልፍ ጠርተን ጥያቄያችን እናቀርባለን።

የቢሾፍቱ ከተማ ካብኔ እና ከንቲባ ከቤተ ክርስቲያን ላይ እጃችሁን አንሱ! ሲሉ መጋቢ ጌትነት ለማ በመግለጫው አንስተዋል።
ክርስቲያኖች ጸልዩ። ካውንስሉ በቀጣይ ሁኔታዎችን እየተከታተለ ያሳውቃል።

ሙሉ መግለጫውን በዩቱብ ቻናላችን ይጠብቁ
#ዜና
#ወንጌል በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ለማድረስ እንሰራለን።

በዓለም ላይ ካሉት 70 ሚሊዮን መስማት የተሳናቸው ሰዎች ኢየሱስን የሚከተሉ 2 በመቶው ብቻ ሲሆኑ፣ መቀመጫውን አሜሪካ ያደረገው የ DOOR ኢንተርናሽናል ሚኒስቴር ወንጌልን መስማት ለተሳናቸው ሰዎች ለማዳረስ የሚረዳውን አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ቴክኖሎጂን ለመጠቀም መዘጋጀቱን ክርስቲያን ዴይሊ ኢንተርናሽናል አስነበበ።

DOOR ኢንተርናሽናል ሚኒስቴር ሚቺጋን ውስጥ የሚገኝ የክርስቲያን ድርጅት ሲሆን አገልግሎቱ መጽሐፍ ቅዱስን መተርጎም፣ አብያተ ክርስቲያናትን መትከል እና መሪዎችን ወንጌል ወዳልደረሰባቸው አከባቢዎች የሚልክ ሚኒስትሪ ነው።

DOOR ኢንተርናሽናል ብዙ መስማት የተሳናቸው ሰዎችን በወንጌል ለመድረስ AI የምልክት ቋንቋ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞችን የጥበብ ሥራ ለመሥራት ይቻል እንደሆነ ለማየት ሙከራዎችን እያደረገ መሆኑን እና ይህም እንዲሳካ መስማት ከተሳናቸው ሰዎች እየሰራ እንደሆነ ገልጿል።
"የመጨረሻው እራት" ማላገጫ በተደረገበት የፓሪስ ኦሎምፒክ የኢየሱስ ክርስቶስ #ወንጌል ዘመቻ ተጀመረ።

ከ3 ሺህ በላይ ሚሽነሪዎች በስራ ላይ ይገኛሉ።

#Ethiopia የኦሎምፒክ መክፈቻው በፈረንሳይ ያሉ ወንጌላዊያን የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል እንዲሰብኩ እንዳነሳሳቸው ተነግሯል።

ለኦሎምፒኩ ብቻ ከ3 ሺህ በላይ ሚሽነሪዎች በስራ ላይ ይገኛሉ።

በፓሪስና አካባቢዋ ያሉ አብያተ ክርስቲያናት ግለሰቦች የወንጌል ማህበርተኞችና ተቋማት በዚህ ዘመቻ ተሳታፊዎች ሆነዋል።

የሃሳቡ አመንጪዎች የአለም አቀፍ ጸሎት መገናኘት (IPC) 5 ሺህ ከሚሆኑ በአለም ዙሪያ ካሉ የጸሎት ቡድኖች ጋር በመሆን ነው።

የወንጌል ዘመቻው ብቻ ሳይሆን የመክፈቻውን ፕሮግራም ተከትሎ ወደ 500 የሚጠጉ ወንጌል ተኮር እንቅስቃሴዎችም እየተካሄዱ ነው።

1 ሚሊዮን ጸሎት ለፓሪስ ከእነዚህ መካከል ተጠቃሽ ነው። በ2020 የቶክዮ ኦሎምፒክም ተመሳሳይ ዘመቻ ተካሂዶ ነበረ።
የወንጌል ዘመቻው የማህበራዊ ስራዎችንም ይጨምራል ነው የተባለው።

ፈረንሳይ ለአለም ወንጌል ለመስበክ እንደዚህ አይነት የወንጌል አጋጣሚ ዳግም አታገኝም ተብሏል።

የስፖርት ፍቅር እና የአገልግሎት ፍቅር ያላቸው ክርስቲያኖ ይሄንን እድል እንዲጠቀሙ ጥሪ ቀርቧል። እንቅስቃሴውም ከኦሎምፒክ በኋላ እንደሚቀጥል ተነግሯል።