The Christian News
5.37K subscribers
3.08K photos
29 videos
730 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
#በነፃ Share በማድረግ ሊረዱ ለሚችሉ ሰዎች መረጃ እንስጣቸው፡፡ written by የጌታ ባሪያ ሀብታሙ
.
#ከሰባት አመት በፊት ነው ወደ ጌታ ገና እንደመጣሁ ሳላቋርጥ የምሰማው አንድ መዝሙር ነበር በተለይ በነበረን የተማሪዎች ፀሎት ህብረት መሀል ሲዘመር መቆም አልችልም እግሮች ይደክማሉ ለኢየሱስ ያለኝን ፍቅር ይጨምረው ነበር እንዲህ የሚል ነበር መዝሙሩ
እንደ ባለሃምሳ ቀን እንደ መጀመሪያው
ና ደግመህ በሕይወቴ
ና ደግመህ በሕይወቴ ሙላኝ በመንፈስህ
ልሂድ ወደሰማይ ልሂድ ወደሰማይ (2x)
#የዚህ መዝሙር ባለቤት ወንድም ሰለሞን ይርጋ ይባላልይ የተወደደ ወንድሞችን የሚወድ ለቤተክርስቲያን ወይም ለቅዱሳን ህብረት ትልቅ ፍቅር ያለው ነው።
#የተወደደ ወንድማች ያወጣቸውን ሶስት የመዝሙር አልበሞች በሙሉ ለቤተክርስቲያን የሰጠ ሲሆን በዚህ ለወንጌል አገልግሎት ይሆን የራሱን ጥቅም የራሳ ትሁት ወንድማችን ነው። በአሁን ሰአት በደቡብ አፍሪካ እየኖር ያለ ሲሆን ስለ እሱ በቅርቡ የሚያሳዝን ዜና ሰምተናል በቅርቡ በደም ካንሰር የተጠቃ ሲሆን ለህክምና እርዳታ ገንዘብ እየተሰበሰበለት ይገኛል። https://gofund.me/8e44e549
#ይህንን ወንድማችን ተረባርበን ብናሳክመው ትውልድን በእርሱ ውስጥ እናድናለን። እግዚአብሔር በዚህ ወንድም ነገ ሊሰራው ያለው ትልቅ ነገር እንዳለ በእምነት ተመልክተን ጌታ የነገውን ሰራተኛው ሰለሞንን በዛሬዎች ሰራተኞች ሊያድን ይወዳልና ይህንን ወንድም በመርዳት ከእግዚአብሔር ሀሳብ ጋር እንቁም፡፡ “ስለዚህ ዕድሉ ካለን ለሰው ሁሉ፣ በተለይም #ለእምነት ቤተ ሰቦች መልካም እናድርግ።” ገላቲያ 6፡10
ለወንድማችን ድጋፉን ለማድረግ ይህን ማስፈንጠርያ ይጫኑ https://gofund.me/8e44e549
በDave khc ተፃፈ
በርግጥ ወንጌላውያን #በዚህ ደረጃ ፍትሕ ተጓድሎባቸዋል ?

#ይህንን #ጥያቄ #ለምን በተደጋጋሚ ማንሳት አስፈለገ ?

ሁላችሁም መልሱን አዘጋጁ #እኛ #ግን የራሳችንን ሃሳብ እንሰነዝራለን።

በትላንትናዉ ዕለት #የኢትዮጵያ #ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካዉንስል በወንጌላዊያን አማኞች እና አብያተክርስቲናት ላይ እየደረሰ ስላለዉ ፍትህ መጓደል ለሚዲያዎች ጋዜጣዊ #መግለጫ ሰጥቷል።

በካውንስሉ ጠቅላይ ጽሐፊ አማካኝነት በተሰጠዉ መግለጫ #ላይ በዋናነት ከ 6 በላይ .. የሆኑ (የደረሱ የፍትሕ መጓደል) የሚያሳዩ ነጥቦች ተጠቅሰዋል።

1. በደርግ #ዘመን የተወረሱ የቤተክርስቲያን ይዞታዎች በኢሕአዴግ ዘመን በከፊል ቢመለሱም እስካሁን ያልተመለሱ የኦሎምፒያ መሰረተ #ክርስቶስ ፣ የአዲስ ከተማ ገነት፣ የኢትዮጵያ ወንንጌላዊት #ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ብረት የሆነው የጉድ ሼፐርድ ማዕከል ፣ቄራ አካባቢ ያለው የብርሃነ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን አዳራሽ፣እና ሌሎች እስካሁን ያልተመለሱ ይዞታዎች ሲሆኑ እነዚህ ይዞታዎች የቤተክርስቲያን ንብረት በመሆናቸዉ እንዲመለሱ ተጠይቋል።

2 የድሬዳዋ መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን #በአንድ ወር #ጊዜ ዉስጥ ይዞታዋን ለቃ እንድትነሳ የከተማዉ አስተዳደር የወሰንኑ ቢሆንም የከተማዉ አስተዳደር እና የቤተክርስቲያኒቱ መሪዎች እንዲሁም የካውንስሉ አመራሮች ሰፊ ዉይይት አድርገዉ የከተማዉ አስተዳደር ጉዳዩን እየመከረበት ይገኛል። የከተማዉ አስተዳደር የደረሰበትን ደረጃ በአጭር ጊዜ ግልፅ እንዲያደርግ ተጠይቋል።

3 የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር የሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን ይዞታ ነጥቆ የራሱ ጽህፈት #ቤት አድርጎት ይገኛል። እንዲሁም የቃለ #ህይወት ቤተክርስቲያን ይዞታ የሆነዉን የኩሪፍቱ የጸሎት ማዕከል በተመለከተም በማእከሉ #ምንም አይነት የልማት #ስራ ቤተ ክርስቲያን እንዳታከናወን በማገድ የቤተክርስቲያኑን ይዞታ ለመንጠቅ እንቅስቃሴ ላይ እንደሚገኝኝ ተገልጾ የቢሾፍቱ #ከተማ አስተዳደር ከዚህ ህገወጥ ድርጊቱ እንዲቆጠብ እና የወሰደዉን የቤተክርስቲያን ንብረት እንዲመልስ ተጠይቋል።

4. በአዲስ አበባ ዙሪያ ባለችው የሸገር ከተማም የፈረሱ የወንጌላዊያን የእምነት ተቋማት ይዞታቸዉ እንዲመለስ እንዲሁም በከተማዋ ለ23 አብያተክርስቲያናት ከካቢኔ #ቦታ ተወስኖላቸዉ ቦታቸዉን መረከብ ላልቻሉ በአፋጣኝ ካቢኔ የወሰነዉ ዉሳኔ ተግባራዊ እንዲሆን ተጠይቋል።

5 የመቃብር ስፍራን ጥሶ በመግባት እየተደረገ የሚገኘዉ አግባብ ያልሆነ ተግባር በአስቸኳይ እንዲቆም

6 በምዕራብ ኢትዮጵያ በቄለም ወለጋ ዞን በጊዳሜ ወረዳ ዘጠኝ ምእመናንን የአምልኮ ስነስርአት እየፈፀሙ ካሉበት ሌሊት ላይ ተወስደዉ መረሸናችው #እጅግ #አሳዛኝ እንደሆነና ለነዚህ ንፁሃን ፍትህ እንዲሰጥ ተጠይቋል።

በአጠቃላይ #ይህ #ሁሉ እየሆነ ያለዉ የታችኛዉ የመንግስት አካል የመንግስትን ስልጣን በመጠቀም ጥቂት ግለሰቦች የግል አጀንዳ ይዘዉ የሚፈፅሙት ተግባር ነዉ።

የፌደራል መንግስት ጣልቃ በመግባት ፍትህ ሊያሰፍን ይገባል ሲል የኢትዮዽያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት #ካዉንስል በመግለጫዉ አስታዉቋል።

#ታዲያ ይህ ሁሉ የፍትህ ጥያቄ አለ #ማለት መጀመሪያላይ ለጠየኩት ጥያቄ ትክክለኛ ምላሽ በርግጥም ወንጌላውያን በግልፅ በአደባባይ #ፍትሕ ተነፍገዋል የሚል ነዉ።

ይሄንን ጥያቄ በዚህ ሰዓት ለምን ማንሳት አስፈለገ ከተባለ ደግሞ ከዚህ በፊት ለበርካታ አመታት ምላሽ ያላገኙ እና ፍትህ ያልተሰጣቸው ጥያቄዎች ባለበት ዛሬም ሌላ በደል እየደረሰ ስለሆነ ማንሳት አስፈላጊ ነዉ።

The Christian News - የክርስቲያን ዜና የወንጌላውያን ድምፅ በመሆን ለበርካታ ጊዜያት ሲያገለግል ቆይቷል። አሁንም ገና ለቤተክርስቲያን ፍትህ ካልተሰጠ በስተቀር ጥያቄያችንን ማስተጋባታችን ይቀጥላል።

ፍትሕ ለወንጌላዉያን ቤተክርስቲያን
#NewsUpdate

#ማሳሰቢያ

ከትላንት በስቲያ በቀድሞው አጎና ሲኒማ ህንጻ ላይ በደረሰው የእሳት አደጋ የተለያዩ ተቋማት ንብረቶች መዉደማቸዉ ይታወሳል።

#ይህንን #ዜና በማስመልከት The Christian News - የክርስቲያን ዜና የሕይወት ምንጭ ኢየሱስ ዓለም አቀፍ ቤ/ክ በሚል መጠርያ የምትጠራዉ ቤተክርስቲያን በአደጋዉ ጉዳት እንደደረሰባት የአዲስ አበባ የእሳት እና ድንገተኛ አደጋ ኮሚሽን መረጃን ዋቢ በማድረግ የተዘገቡ ከተለያዩ የግል ሚዲያ ያገኘነዉን #መረጃ ማሰራጨታችን ይታወሳል።

ሆኖም የቤተክርስቲያን መሪዎች በአጎና ሲኒማ ህንጻ በሚገኘው አዳራሽ አምልኮ ካቆሙ #አንድ አመት ያለፋቸዉን መሆኑን ጠቅሰዉ መረጃዉ የተሳሳተ እንደሆነ ገልፀዋል።

በዘገባዉ በቴሌቪዥን ስቲዲዮዉ ለድምጽ መከላከያ ተብሎ በህንጻዉ ግድግዳ ላይ የተገነባዉ እስፖንጅና በቤተክርስቲያኑ ውስጥ የነበረው በርካታ የፕላስቲክ ወንበሮች ለቃጠሎዉ መስፋፋት አስተዋጾኦ እንዳደረጉ የተቋሙ ኮሙኒኬሽን አቶ ንጋቱ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን መናገራቸው ተካቷል።

የቤተክርስቲያኒቱ መሪዎች በበኩላቸው ወንበሮቹ የራሱ የህንፃው ባለቤቶች የመሰብሰቢያ አዳራሽ ንብረት እንደሆነ ተናግረዋል።

አደጋዉን በተመለከተ በዘገባዉ ጎልቶ የወጣዉ የሌላ ተቋማት ጉዳት ስለነበር በዚህ ዉስጥ ቤተክርስቲያን ጉዳት ደርሶባት ከነበር እንደ ክርስቲያን ሃላፊነታችንን ለመወጣት በሚል ዘገባዉን አሰራጭተናል።

በተሰራጨዉ የተሳሳተ ዘገባ #The #christian #news ይቅርታ እየጠየቅን ዘገባዉን ከገፃችን ማንሳታችንን እናሳዉቃለን።