The Christian News
5.38K subscribers
3.07K photos
27 videos
724 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
#አሳዛኝ #ዜና

ሳምሪ ላትመለስ ሄዳለች።

እሷን ለማዳን በጸሎት ፣በገንዘብ ፣ ፌስቡክ ላይ ሼር በማድረግ ፥ስለለሷ ድምጽ በመሆን እሷን ለማዳን ባለን አቅም ብንረባረብላትም ሳምሪን ልናቆያት አልቻልንም።

ፈጣሪ የወደደውን አድርጓልና፥ ለምን እንዲህ ሆነ ማለት አንችልም።

ለመላው ቤተሰቦቿ፣ ዘመድ አዝማድ ፣ የልብ ጓደኞቿ
እንዲሁም ለደጋጎቹ የኢትዮጵያ ህዝብ መጽናናትን ይሁን🙏🙏🙏
#አሳዛኝ #ዜና

በአሜሪካ ዩታ ግዛት ውስጥ የዴቪስ ስኩል ዲስትሪክት ትምህርት አስተዳደር መጽሐፍ ቅዱስን “አመጽ እና ነውር” የያዘ በሚል ከመጀመርያ ደረጃ ትምህርት ቤቶቹ ማገዱ ተሰምቷል።

የትምህርት ቤቶቹ አስተዳደር መጽሐፍ ቅዱስን ያገደው አንድ ቤተሰብ የኪንግ ጀምስ ዕትም ለሕጻናት ተስማሚ ያልሆኑ ክፍሎችን ይዟል ብሎ ቅሬታ ማስገባቱን ተከትሎ ነው።

መጽሐፍ ቅዱሰን ማገድ የመጣው ወግ አጥባቂዎች በግዛቲቱ አከራካሪ የሆኑ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት መብቶች እንዲሁም ዘርና ማንነት ላይ ያተኮሩ ትምህርቶች እንዳይሰጡ ለማገድ የሚያስችል ከፍተኛ ጥረት ካደረጉ በኋላ ነው።

በዩታህ መጽሐፍ ቅዱስን ከትምህርት ቤቶች እንዲታገድ የሚጠይቀው ቅሬታ የገባው በሕዳር ወር አካባቢ ሲሆን፣ ቀድሞውንም መጽሐፍ ቅዱስ በሥርዓተ ትምህርቱ አካል ያልነበረ መሆኑን በመግለጽ ስምንት መጽሐፍ ቅዱሶችን ከትምህርት ቤቶቹ መደርደርያ ላይ መሰብሰባቸውን አስተዳዳሪዎቹ ይፋ አድርገዋል።

ጉዳዩን የተመለከተው ኮሚቴ መጽሐፍ ቅዱስ የትኛው ክፍል ላይ “ነውር የሆኑ፣ ጭካኔና አመጽ የሚያነሳሱ አንቀጾችን የያዘ” እንደሆነ አላብራራም።

በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ግን መጽሐፍ ቅዱስ ይኖራል ተብሏል።

ቦን ጆንሰን በመጀመርያ ደረጃ የሚማር ልጅ ያለው ሲሆን በግዛቲቱ የተወሰደውን እርምጃ እንደሚቃወም ለሲቢኤስ ኒውስ ገልጿል።

“ከመጽሐፍ ቅዱስ የሚቀነስ ክፍል መኖሩን ማሰብ አልችልም። ልክ ምስል እንደማውጣት እኮ አይደለም” ብሏል።

ከዩታ ሌላ መጽሐፍ ቅዱስን ከመደርደሪያቸው ላይ ያስወገዱ ሌሎች የአሜሪካ ግዛቶችም አሉ።

ባለፈው ዓመት የቴክሳስ ግዛት ከቤተ መጻሕፍት መደርደርያዎች የወግ አጥባቂዎችን የተወሰኑ መጻሕፍትን ለማገድ የጀመሩትን ጥረት ለማስቆም በሚል የቀረቡ ቅሩታዎችን ተከትሎ መጽሐፍ ቅዱስን ከመደርደርያዎቹ ላይ ሰብስቧል።
#አሳዛኝ #ዜና

ተማሪዎቹ የወንጌል #መዝሙር እየዘመሩ በነበረበት በድንገት #ተገደሉ

ይህ ከሰሞኑ በኡጋንዳ አንድ አዳሪ #ትምህርት ቤት የተጸፈመ እውነተኛ #ታሪክ ነው።

ኡጋንዳ ውስጥ ባለፈው ሳምንት አርብ በአንድ ትምህርት ቤት ላይ በተፈጸመ ዘግናኝ ጭፍጨፋ በርካታ ሕጻናት መገደላቸው ይታወሳል።

ከሟቾቹ መካከል ብዙዎቹ አዳጊዎች ናቸው።

ጥቃቱ የተፈጸመበት የአዳሪ #ትምህርት ቤት ሲሆን፣ አክራሪዎቹ ጥቃቱን የፈጠሙበት መንገድ ማደሪያ ክፍሎች ላይ ነዳጅ አርከፍክሎ እሳት በመለኮስ እና በገጀራ ሰውነትን በመቆራረጥ ጭምር እንደሆነ ተዘግቧል።

አንዲት ከዚህ ትምህርት ቤት ማዶ ባለ ቤት ነዋሪ የሆነች #ሴት ለቢቢሲ ስዋሂሊ ያየችውን መስክራለች።

“ልጆቹ የወንጌል #መዝሙር እየዘመሩ ነበር፤ ከዚያ ድንገት ኡኡታ ተሰማ” ብላለች።

ፖንዱዌ ሉቢሪሃ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚገኘውም በኡጋንዳ እና በኮንጎ ድንበር አቅራቢያ ነው።

ለቢቢሲ ስዋሂሊ ምስክርነቷን የሰጠችው ሜሪ ማሲካ ከጥቃቱ ጀምሮ እንቅልፍ መተኛት እንዳልቻለች ተናግራለች።

“ተማሪዎቹ ሁልጊዜ ከመተኛታቸው በፊት ይጸልያሉ፤ አርብ ዕለት የሆነው ግን ያልተለመደ ነው፤ ጸሎታቸው በድንገት ተቋረጠ” ትላለች ሜሪ ማሲካ።

ይህ የሆነው ምሽት አራት ሰዓት ላይ ነው።

#ውድ The Christian News - የክርስቲያን ዜና ቤተሰቦች በሙሉ ከዚህ በኋላ የቀረው ዝርዝር ታሪክ እጅግ ዘግናኝ በመሆኑ ዘገባ ውስጥ ልናካትተው አልወደድንም ነገር ግን ሙሉ ውን ማንበብ ለሚፈልግ BBC News Amharic ዌብ ሳይትን መመልከት ይችላል።
#አሳዛኝ #ዜና

በአሜሪካ አንዲት እናት #ክርስቶስ #ወደ ምድር በቶሎ ለፍርድ እንዲመጣ በሚል #ሁለት ልጆቿን ገደለች።

በዩናይትድ ስቴትስ የምትኖር አንዲት እናት በአፖካሊፕቲክ ሃይማኖታዊ እምነቷ መሰረት ሁለት ልጆቿን በመግደል እና የባሏን የቀድሞ ሚስት ለመግደል በማሴር የእድሜ ልክ እስራት ተፈርዶባታል።

ሎሪ ቫሎው የተባለችዉ ይህችዉ #ሴት በግንቦት ወር የ16 ዓመቷን ሴት ልጇን ታይሊ ራያን እና የሰባት ዓመት በማደጎ የወሰደችዉን #ወንድ ልጇን ኢያሱ "ጄጄ" ቫሎውን በመግደል ጥፋተኛ ተብላለች፡፡

የእናታችን ኃጢአት (Sins of Our Mother) በሚል የዚህችዉ ሴት የህይወት #ታሪክ በኔትፍሊክስ እውነተኛ የወንጀል ዘጋቢ #ፊልም የቀረበ ሲሆን የኢየሱስ ክርስቶስን ዳግም ምጽዓት እንዲሆን ልጆቿን መግደሏ ከአምላክ የተሰጠ ራዕይ መሆኑን ትናገራለች፡፡

ዳኛ ስቲቨን ደብሊው ቦይስ በቫሎው የወንጀል ድርጊት ላይ ባሳለፉት የጥፋተኛነት ዉሳኔ በሶስት ተከታታይ የእድሜ ልክ እስራት በይነዋል፡፡ በወላጅ የተፈጸመውን የልጅ ግድያ “በእርግጥ መገመት ከምችለው በላይ አስደንጋጭ ነገር” ሲሉ ዳኛዉ ገልጸዋል።

ቫሎው ልጆቿን ከገደለች በኃላ #እንኳን እንደጠፉ ገልጻ ባታዉቅም በፖሊስ አስክሬናቸዉ ተገኝቷል፡፡

#ዳጉ_ጆርናል
#አሳዛኝ_ዜና_እረፍት 😭

ልብ ይሰብራል 😭

#Ethiopia | ሆሳዕና እጅግ በጣም ጥልቅ ሀዘን ዉስጥ ናት።

ዛሬ ከሆሣዕና ወደ አዲስ አበባ ጉዞ ላይ እያሉ ሶዶ ወረዳ አናቲ ቀበሌ በመኪና አደጋ የሆሣዕና ከተማ እናት ቃለ ህይወት ቤተክርስቲያን መሪ እና አገልጋይ የሆኑ ዮናስ ዱባለ እና አብረውት ከነበሩት ከሁለት ጓደኞቹ ጋር ህይወታቸው አልፏል።

በትራፊክ አደጋ የ4 ሰዎች ህይወት ማለፉና 4ሰዎች ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው የሶዶ ወረዳ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

የሶዶ ወረዳ የትራፊክ አደጋ መከላከልና ፍሰት ቁጥጥር ማስተባበሪያ ኃላፊ ዋና ሳጅን አማረ ታከለ እንዳሉት በዛሬው እለት ከጠዋቱ 12:00 ሰአት ላይ የህዝብ ማመላለሻ FSR የሰሌዳ ቁጥር ደቡብ 13955 የሆነ 49 ሰዎችን ጭኖ ከአዲስ አበባ እየመጣ ከሆስአና ወደ አዲስ አበባ የሚሄድ የሰሌዳ ቁጥሩ B-20669 ላንድ ክሮዘር መኪና ጋር በሶዶ ወረዳ አናቲ ቀበሌ በመጋጨት የ4 ሰዎች ህይወት ማለፉና 4ሰዎች ከባድ ጉዳት እንደደረሰ ገልፀዋል፡፡

ዋና ሳጅን ጨምረው እንዳብራሩት አደጋው የተከሰተበት ሰአት የአየር ንብረቱ ጭጋጋማ በመሆኑ እንዲሁም አደጋ የደረሰበት አካባቢ መንገዱ ብልሽት ያለበት በመሆኑ በየጊዜው አደጋ እንደሚደርስና በተደጋጋሚ በትራፊክ አደጋ የሰዎች ህይወት የሚቀጥፍና ከፍተኛ የንብረት ውድመት የሚያስከትል በመሆኑ አሽከርካሪዎች ከፍጥነት በላይ ባለማሽከርከር ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ማስገንዘባቸውን የዘገበው የሶዶ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው ፡፡

እግዚአብሔር አምላክ ለቤተሰቡ ለቤተክርስቲያን ምዕመን ለወዳጅ ዘመዶቹ በሙሉ መፅናናትን እንመኛለን 🙏🙏 😭😭😭😭
#አሳዛኝ #ዜና
#ቄስ #ወደ #ጌታ #ተሰብስበዋል 🙏🙏🙏

የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረትን ከመጋቢት 1999 ዓ.ም እስከ ኅዳር 2008 ዓ.ም በዋና ጸሐፊነት የመሩት ቄስ ዓለሙ ሼጣ በዛሬው ዕለት ወደ ሚወዱትና ወዳገለገሉት አምላካቸው ዕቅፍ ተሰብስበዋል።

ኅብረቱን በታማኝነትና በጥበብ በመምራት በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅ የነበሩት ወንድማችንና አባታችን ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም ድካም በማረፍ ሞቶ ወደ ተቤዣቸው #ጌታ ክብር ገብተዋል።

የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት፣ በወንድማችን፣ በሥራ ባልደረባችንና በአባታችን እረፍት የተሰማውን ጥልቅ ኀዘን እየገለጸ፣ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጆቻቸውና ለመላው ወንጌላውያን አማኞች መጽናናትን ይመኛል።

The Christian News - የክርስቲያን ዜና ለሁሉም መፅናናትን ይመኛል። 🙏🙏🙏 😭😭😭
#አሳዛኝ #ዜና
#9 #ክርስቲያኖች ተገደሉ።

በቄለም ወለጋ ጊዳሚ መካነ ኢየሱስ ቤ/ክ ጸሎት ላይ የነበሩ ሰዎች ከቤተ ክርስቲያን ተወስደው ተገደሉ

በምዕራብ ኦሮሚያ ቄለም ወለጋ ዞን፣ ጊዳሚ ከተማ ነው ጸሎት ላይ የነበሩት ሰዎች የተገደሉት።

አስተያየታቸውን ለቢቢሲ የሰጡት የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤ/ክ መካነ ኢየሱሱ ቲዎሎጂና ሚሽን መምሪያ ቄስ ዶ/ር ለሊሳ “የአዳር ጸሎት ላይ የነበሩ 9 የቤተ ክርስቲያኗ አባላት፣ በታጣቂዎች ተወስደው ተገድለዋል” ብለዋል።

በቤጊ-ጊዳሚ ሲኖዶስ በጊዳሚ ሰባካ፣ የሃሞ ቶኩማ ማህበረ ምዕመናን የምትገኘው ይህቺ ቤ/ክ አባላት የዛሬ ሳምንት ህዳር 14 ለሊት 8 ሰዓት ነው ከቤተ ክርስቲያኗ የተወሰዱት።

የቤተክርስያኗ ሽማግሌዎች፣ የወጣቶች ኮሚቴ አባላት እንዲሁም ሌሎች አገልጋዮች ናቸው ተወስደው የገደሉት።

ጥቃት አድራሾቹ ማን እንደሆኑ እስካሁን የታወቀ ነገር ግን የለም ስትል ቤተ ክርስቲያኗ አስታውቃለች።

ቢቢሲ ባደረገው ማጣራት መሰረት የተወሰዱት 9 ሰዎች ከሌሎች መካከል ተመርጠው መሆኑን ከቤተ ክርስቲያኗ አባላት አረጋግጧል። ለቅዳሜ ቀን የአምልኮ ፕሮግራም ዝግጅት የአዳር ጸሎት ይካፈሉ የነበሩ ሰዎች 12 ናቸው።

ከ12ቱ ሰዎች መካከል 2 ሴቶችና አንድ እድሜያቸው የገፋ አዛውንት ሳይወሰዱ ቀርተዋል ነው የተባለው።

ተወስደው የተገደሉት ሰዎች ምንም አይነት የፖለቲካዊ ተሳትፎ የላቸውም ነው የተባለው። ቄስ ዶ/ር ለሊሳ “ዘመዶቻቸውን በሞት ላጡ ወገኖች መጽናናትን ተመኝተው፣ መንግስት ለቤተ ክርስቲያን አባላት ፍትህ እንዲሰጥ” ሲል ጠይቀዋል።

በተመሳሳይ የዛሬ አመት እሁድ ቀን ጥቅምት 27 2014 በምስራቅ ወለጋ መካነ ኢየሱስ ቤ/ክ አምልኮ ላይ የነበሩ 15 ምዕመናን ጥቃት ተፈጽሞባቸው መሞታቸው ይታወሳል።

ጥቅምት 2015 ደርሶ በነበረው ግድያ ጥቃት አድራሾቹ ከሌላ አካባቢ የመጡ ናቸው ተብሎ መዘገቡ ይታወሳል ሲል BBC News Amharic አስነብቧል።
በርግጥ ወንጌላውያን #በዚህ ደረጃ ፍትሕ ተጓድሎባቸዋል ?

#ይህንን #ጥያቄ #ለምን በተደጋጋሚ ማንሳት አስፈለገ ?

ሁላችሁም መልሱን አዘጋጁ #እኛ #ግን የራሳችንን ሃሳብ እንሰነዝራለን።

በትላንትናዉ ዕለት #የኢትዮጵያ #ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካዉንስል በወንጌላዊያን አማኞች እና አብያተክርስቲናት ላይ እየደረሰ ስላለዉ ፍትህ መጓደል ለሚዲያዎች ጋዜጣዊ #መግለጫ ሰጥቷል።

በካውንስሉ ጠቅላይ ጽሐፊ አማካኝነት በተሰጠዉ መግለጫ #ላይ በዋናነት ከ 6 በላይ .. የሆኑ (የደረሱ የፍትሕ መጓደል) የሚያሳዩ ነጥቦች ተጠቅሰዋል።

1. በደርግ #ዘመን የተወረሱ የቤተክርስቲያን ይዞታዎች በኢሕአዴግ ዘመን በከፊል ቢመለሱም እስካሁን ያልተመለሱ የኦሎምፒያ መሰረተ #ክርስቶስ ፣ የአዲስ ከተማ ገነት፣ የኢትዮጵያ ወንንጌላዊት #ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ብረት የሆነው የጉድ ሼፐርድ ማዕከል ፣ቄራ አካባቢ ያለው የብርሃነ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን አዳራሽ፣እና ሌሎች እስካሁን ያልተመለሱ ይዞታዎች ሲሆኑ እነዚህ ይዞታዎች የቤተክርስቲያን ንብረት በመሆናቸዉ እንዲመለሱ ተጠይቋል።

2 የድሬዳዋ መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን #በአንድ ወር #ጊዜ ዉስጥ ይዞታዋን ለቃ እንድትነሳ የከተማዉ አስተዳደር የወሰንኑ ቢሆንም የከተማዉ አስተዳደር እና የቤተክርስቲያኒቱ መሪዎች እንዲሁም የካውንስሉ አመራሮች ሰፊ ዉይይት አድርገዉ የከተማዉ አስተዳደር ጉዳዩን እየመከረበት ይገኛል። የከተማዉ አስተዳደር የደረሰበትን ደረጃ በአጭር ጊዜ ግልፅ እንዲያደርግ ተጠይቋል።

3 የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር የሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን ይዞታ ነጥቆ የራሱ ጽህፈት #ቤት አድርጎት ይገኛል። እንዲሁም የቃለ #ህይወት ቤተክርስቲያን ይዞታ የሆነዉን የኩሪፍቱ የጸሎት ማዕከል በተመለከተም በማእከሉ #ምንም አይነት የልማት #ስራ ቤተ ክርስቲያን እንዳታከናወን በማገድ የቤተክርስቲያኑን ይዞታ ለመንጠቅ እንቅስቃሴ ላይ እንደሚገኝኝ ተገልጾ የቢሾፍቱ #ከተማ አስተዳደር ከዚህ ህገወጥ ድርጊቱ እንዲቆጠብ እና የወሰደዉን የቤተክርስቲያን ንብረት እንዲመልስ ተጠይቋል።

4. በአዲስ አበባ ዙሪያ ባለችው የሸገር ከተማም የፈረሱ የወንጌላዊያን የእምነት ተቋማት ይዞታቸዉ እንዲመለስ እንዲሁም በከተማዋ ለ23 አብያተክርስቲያናት ከካቢኔ #ቦታ ተወስኖላቸዉ ቦታቸዉን መረከብ ላልቻሉ በአፋጣኝ ካቢኔ የወሰነዉ ዉሳኔ ተግባራዊ እንዲሆን ተጠይቋል።

5 የመቃብር ስፍራን ጥሶ በመግባት እየተደረገ የሚገኘዉ አግባብ ያልሆነ ተግባር በአስቸኳይ እንዲቆም

6 በምዕራብ ኢትዮጵያ በቄለም ወለጋ ዞን በጊዳሜ ወረዳ ዘጠኝ ምእመናንን የአምልኮ ስነስርአት እየፈፀሙ ካሉበት ሌሊት ላይ ተወስደዉ መረሸናችው #እጅግ #አሳዛኝ እንደሆነና ለነዚህ ንፁሃን ፍትህ እንዲሰጥ ተጠይቋል።

በአጠቃላይ #ይህ #ሁሉ እየሆነ ያለዉ የታችኛዉ የመንግስት አካል የመንግስትን ስልጣን በመጠቀም ጥቂት ግለሰቦች የግል አጀንዳ ይዘዉ የሚፈፅሙት ተግባር ነዉ።

የፌደራል መንግስት ጣልቃ በመግባት ፍትህ ሊያሰፍን ይገባል ሲል የኢትዮዽያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት #ካዉንስል በመግለጫዉ አስታዉቋል።

#ታዲያ ይህ ሁሉ የፍትህ ጥያቄ አለ #ማለት መጀመሪያላይ ለጠየኩት ጥያቄ ትክክለኛ ምላሽ በርግጥም ወንጌላውያን በግልፅ በአደባባይ #ፍትሕ ተነፍገዋል የሚል ነዉ።

ይሄንን ጥያቄ በዚህ ሰዓት ለምን ማንሳት አስፈለገ ከተባለ ደግሞ ከዚህ በፊት ለበርካታ አመታት ምላሽ ያላገኙ እና ፍትህ ያልተሰጣቸው ጥያቄዎች ባለበት ዛሬም ሌላ በደል እየደረሰ ስለሆነ ማንሳት አስፈላጊ ነዉ።

The Christian News - የክርስቲያን ዜና የወንጌላውያን ድምፅ በመሆን ለበርካታ ጊዜያት ሲያገለግል ቆይቷል። አሁንም ገና ለቤተክርስቲያን ፍትህ ካልተሰጠ በስተቀር ጥያቄያችንን ማስተጋባታችን ይቀጥላል።

ፍትሕ ለወንጌላዉያን ቤተክርስቲያን
#አሳዛኝ #ዜና

12ኛ አመቱን በያዘው የሶርያ እርስ በእርስ ጦርነት ምክኒያት የክርስቲያኖች #ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እያሽቆለቆለ #ነው ተባለ።

በተለይ በበሰሜናዊ ሶርያ የምትገኘው አሌፖ #ከተማ በርካታ ክርስቲያኖች ይገኙባታል የነበረች ከተማ ነች።

ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ 250ሺህ የነበረው የክርስቲያኖች ቁጥር፣ አስደንጋጭ በሆነ ሁኔታ #ወደ 50ሺህ ወርዷል።

በከተማዋ ያሉ ክርስቲያኖች አሌፖ በጦርነቱ ፍርስርሷ ከመውጧቷ በተጨማሪ፣ በአይ ኤስ አይ ኤስ፣ የኩርድ ታጣቂዎች፣ አማጺ ሃይሉና የሶርያ #መንግስት መካከል በሚደረግ ጦርነት የመጀመሪያዎቹ ገፈት ቀማሾች መካከል ናቸው።

ከ200ሺህ #በላይ ክርስቲያኖች ከአሌፖ #ብቻ መሰደዳቸው፣ በሃገሪቱ ጥቂት የሆኑ ክርስቲያኖችን ቁጥርን አደጋ #ላይ ጥሎታል ሲል #አለም አቀፉ #ክርስቲያን ኮንሰርን አስነብቧል።

አሌፖ ከጦርነቱ በፊት በሰሜናዊ ሶርያ የንግድ ማዕከል የነበረችና ጥንታዊ ከተማ ስትሆን፣ ከጦርነቱ ማግስት ተከስቶ በነበረው ርዕደ #መሬት ሳቢያም ሁኔታዋ ከድጡ ወደ ማጡ ሆኗል።

በ2023 የኦፕን ዶርስ ዝርዝር መሰረት ሶርያ 12ኛ ለክርስቲያኖች የማትመች ሃገር ናት።
#አሳዛኝ_መረጃ 😭
ዘማሪ ካሌብ ጉዳት ደርሶበታል 😭😭 በአስቸኳይ ሼር ይደረግ
                     ( አቤል ደመላሽ )
ባሳለፍንው ቅዳሜ የአገልጋዮች ህብረት በሚያዘጋጁት የማለዳ ጸሎት እና ስፖርታዊ እንቅስቃሴ መካከል ካሌቦ እንደወትሮው ኳስ ለመጫዎት ከወገኖች ጋር ህብረትም ለማድረግ በማሰብ ተገኝቶ ነበር ። ጥቂት እንደተጫወቱ ካለብ በፍጥነት ሲሮት ወደቀ አወዳደቁ ከባድ ስለነበረ የቀኝ እጁ ክፉኛ ተጎዳ አጥንቱ ተሰበረ ።

ጓደኞቹ ተደናግጠው ሆስፒታል ቢወስዱትም ጉዳቱ  ቀላል አልሆነም ከባድ ሰርጀሪ መሰራት እንዳለበት ተነገረው ።

ነገሩን ለማሳጠር ያክል በካሌብ ዝማሬዎች በእውነት ጠቅሞናል "ሳቄ ነው " "የኔ የኔ " ሌሎችም ይጠቀሳሉ ።

ስለሆነም ቅዱሳን የካሌብ ወላጅ ዘመዶች በቅርብ የሉምና እንደ መልካም ቤተሰብ አለንልህ እንበለው ። በጸሎት እናስበው ከጎኑም እንቁምለት ለሰርጀሪ እና ለተለያዩ ወጪዎች ይሆን ዘንድ የቻልንውን ሁሉ ወደ አካውንቱ እናስገባለት ። 
👉 Commercial bank of ethiopia👉 1000362843441
ፍቅራችሁን ግለጡለት እየደወላችሁ አይዞህ በሉት ።
ስልክ ቁጥሩ +251 911524288 ነው ።
ከተረባረብን እና ካገዝንው አሁን ካለበት ሆስፒታል ይልቅ የተሻለ ህክምና ማግኘት ወደሚችልበት ይሄዳል ።
ሁላችንም ብዙ ሰው ጋር እንዲደርስ #ሼር እናድርገው ።
#አሳዛኝ #ዜና

በአክሱም የምትገኘዉ የቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ተዘረፈች። የቀረዉን ንብረትም አዉድመዉታል።

ከሰሞኑ 3 ቅዱሳን በአክሱም መታሰራቸዉ ይታወሳል።