The Christian News
5.32K subscribers
3.06K photos
27 videos
720 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
#እንኳን #ደስ #አሎት
#አንገፋው_ዘማሪ_መጋቢ_ሸዋዬ_ዳምጤ በሮም #የኢትዮጵያ_ወንጌላዊት_ቤተክርስቲያን_ዋና_መጋቢ ሆነው #ተሾሙ

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል ጠቅላይ ጸሃፊ ቄስ ደረጀ ጀምበሩ የክብር እንግዳ ሆነው ተገኝተዋል።

ኦክቶበር 1/ 2023 ከ4 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት ድረስ በነበረው የአንገፋው የዘማሪ መጋቢ ሸዋዬ ዳምጤ የዋና መጋቢ ሹመት መርሃ ግብር ላይ የተለያዩ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ሲገኙ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል ጠቅላይ ጸሃፊ የሆኑት ቄስ ደረጀ ጀምበሩ የክብር እንግዳ ሆነው በመገኘት የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት አቅርበዋል።

በመቀጠልም ለሚቀጥሉት ዘመናት በሮም የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን ዋና መጋቢ ሆነው ለሚያገለግሉት ለዘማሪ መጋቢ ሸዋዬ ዳምጤ በቤተክርስቲያኗ መሪዎች የሹመት ስርዓትና ጸሎት ተደርገሏቸውል።

ዘማሪ መጋቢ ሸዋዬ ዳምጤ በቀሪው ዘመናቸው በተሰጣቸው ሀላፊነት በታማኝነትና በትጋት የእግዚአብሔርን ፍቃድ ለማገልገል የጌታ ጸጋ እንደሚረዳቸው ገልጸዋል።

ዘማሪ መጋቢ ሸዋዬ ዳምጤ በኢትዮጵያ ወንጌላውያን የዝማሬ ታሪክ ውስጥ ስማቸው በጉልህ ከሚጠቀሱት ቀዳሚ እና ለእግዚአብሔር ህዝብ የሚባርኩ ዝማሬዎችን እንዳቀረቡ ይታወቃል።
#መልካም #እለተ ሰንበት ይሁንልን 🙏🙏🙏

ቴክኒካሊ ብልጥ ሆነን የማናልፍበት ዘመን መጥቷል።

ዘመኑን ለማለፍ መንፈሳዊ መሆን የግድ ነዉ። እሱም ከኢየሱስ ጋር #ብቻ መሆን #ነዉ የሚያዋጣዉ።

በመፅሐፍ #ቅዱስ #ብዙ ታሪክ የሰሩ ሰዎችን ብንመለከት #እንኳን አለም እነሱን አይታ ተሸናፊዎችነዉ ያለቻቸዉ። ማንም አይፈልጋቸዉም ነበር።

በዘመናቸዉ #ሁሉ #ኢየሱስ ሲሉ ነበር ካለፉ በኋላ ግን ሁሉም ሰዉ ስለ ኢየሱስ ከ2ሺህ ዘመናት በላይ ይናገራል።

ኢየሱስ ካልክ የዚህ ድንቅ መፅሐፍ አካል ትሆናለህ። መፅሐፍ ቅዱስ የአንድ ታሪክ መፅሐፍ ነዉ። እነዚህ ሁሉ ሰዎች ስለ አንድ ታሪክ ሲናገሩ ነዉ የታሪክ አካል የሆኑት።

#ነብይ ጥሌ
#ሱዳን #ጦርነት
#ቤተክርስቲያን ማቃጠል
#የክርስቲያኖች #ስደት

በሱዳን እየተካሄደ ያለው ጦርነት አብያተ ክርስቲያናትን ማፈራረሱን ቀጥሏል ተባለ።

ባለፈው ሳምንት #ብቻ #ሁለት የወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት በጦርነቱ ምክኒያት ጋይተዋል። በሱዳን ሁለተኛ ጥንታዊ እና ትልቁ #ቤተክርስቲያን በኦምዱርማን ከተማ ከጥቅም ውጪ ሆኗል።

ጥቃቱ በቤተ ክርስቲያኗ ዙሪያ የሚገኝን የክርስቲያኖች ትምህርት ቤት ኢላማ ያደረገ ቢሆንም፣ የፕሪባይቴሪያን  ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን ህንጻም ፈራርሷል። ውስጥ የሚገኙ መጽሃፍ ቅዱስ፣ የመዝሙር ደብተር እና ዶክመንቶች ከጥቅም ውጪ ሆነዋል።

በቤተ ክርስቲያኑ ዙሪያም ወላጅ አልባ ህጻናት ትምህርት ቤት፣ የጥቃቱ ሰለባ ነው። ምንም እንኳን ህንጻው ላይ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰ ቢሆንም፣ ሰው ላይ ግን የደረሰ ጉዳት የለም።

በጦርነቱ ከጥቅም ውጪ ከሆኑ ቤተ ክርስቲያኖች መካከል አንዱ፣ 81 አመታትን መንፈሳዊና ማህበራዊ አገልግሎቶችን ይሰጥ የነበረ ነው። ባለፈው አርብ በደቡባዊ ካርቱም፣ የሚገኝ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የቦምብ ጥቃት ተፈጽሞበት፣ 5 መነኩሴዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል።

በጦርነቱ ዋነኛ የጥቃት ሰለባ የሆኑት አብያተ ክርስቲያናት መሆናቸውም እየተዘገበ ይገኛል። ኦምዱርማንና ካርቱም ብቻ ፈጣን ድጋፍ ሰጪ የተባለው ጦር፣ ሁለት አብያተ ክርስቲያናትን ተቆጣጥሮ የጦር ማዘዣ አድርጓል። በካርቱም የምትገኝን አንዲት ቤ/ክ ንብረት የሆኑ ተሽከርካሪዎችንም ለጦርነት አላማ እያዋለ ይገናል።

ባለፈው ሚያዝያ ወር ጌሪፍ የተባለን የመጽሃፍ #ቅዱስ ትምህርት ቤት ከጥቅም ውጪ በማድረግ የተማሪዎችን ዶርም፣ መማሪያ ክፍሎችና የአምልኮ ስፍራም ጥቃት ተፈጽሞበት ከጥቅም ውጪ ሆኗል ነው የተባለው።

በሱዳን ጦርና ፈጣን ሃይል ሰጪ በሚባለው ጦር መካከል  እየተካሄደ በሚገኘው 2ኛ አመቱን በያዘው ጦርነት፣ እስካሁን 10ሺህ የሚሆኑ ንጹሃን #ህይወት ያለፈ ሲሆን፣ ወደ 5.6 ሚሊዮን የሚጠጉ #ሰዎች #ቤት ንብረታቸውን ጥለው ተሰደዋል ሲል ተ.መ.ድ አስታውቋል።

የሱዳን ጦር መሪ ጀነራል አብደል ፈታህ አልቡርሃንና የፈጣን ድጋፍ ሰጪ ሃይሉ መሪ ሞሃመድ ሃምዳን ደጋሎ በጋራ የሲቪሉን የሽግግር መንግስት ከስልጣን ካወረዱ በኋላ፣ በመካከላቸው የተፈጠረ ልዩነት ሱዳንን ዛሬ ላይ አድርሷታል።

#ምንም #እንኳን ለ30 አመታት ሱዳንን የመሩት ኦማር አልበሽር የስልጣን ዘመን የነበረው የክርስቲያኖች ስደት ይቀንሳል ተብሎ የነበረ ቢሆንም፣ በጦርነቱ ምክኒያት ግን እየተባባሰ ይገኛል ነው የተባለው።

ኦፕን ዶርስ በ2023ቱ ሪፖርት መሰረት፣ ሱዳን በ2021 ከነበረችበት የ13ኛ ደረጃ የክርስቲያኖች ስደት ተባብሶ ወደ 10ኛ ደረጃ ከፍ አድርጓታል።

ክርስቲያኒቲ ቱደይ እንዳስነበበው በሱዳን ከአጠቃላይ 43 ሚሊዮን ህዝቧ መካከል፣ 4.3 በመቶው ወይም ወደ 2 ሚሊዮን የሚሆነው #ሕዝብ #ክርስቲያን ነው።
#እንኳን #አደረሳችሁ

በታላት ጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የነቀምቴ ማህበረ ምዕመናን 100ኛ ዓመት ክብረ-በዓል ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር በድምቀት ተካሄደ።

ማህበረ ምዕመኑ ከፍተኛ ዝግጅት ሲያደርግበት የቆየው 100ኛው ዓመት የምስረታ #እና የአገልግሎት ቆይታን የሚዘክረው ክቡረ በዓል ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር፣ ማህበረ ምዕመኑ ስድስት ሺህ ሰዎችን እንዲያስተናግድ ባስገነባው አዲሱ የአምላክ አዳራሽ ተካሂዷል።

ከማስጀመሪያ መርሃ-ግብሩ #አንድ #ቀን አስቀድሞ የማህበሩ ምዕመናን በነቀምቄ #ከተማ በነቂስ በመውጣት የከተማ ፅዳት እና የጎዳና #ላይ የወንጌል ስርጭት አድርገዋል።

በዓሉንም ለመካፈል ከመላው #ኢትዮጵያ በርካታ እንግዶች፣ በውጪ ሀገራት የሚኖሩ የማኅበረ ምዕመኑ #ልጆች እና ማህበረ ምዕመኗን ለበርካታ ዓመታት ያገለገሉ ሚሲዮናዊያን ተገኝተዋል።

በዕለቱም በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና የእንግሊዝኛ ቋንቋዎች የተዘጋጀ እና የማህበረ ምዕመኑን የ100 ዓመታት አገልግሎት የዳሰሰ #መጽሐፍ ተመርቋል።

በዓሉም በተለያዩ መርሀ ግብሮች እስከ ታህሳስ 21/2016 ዓ.ም የሚከበር ይሆናል።

The Christian News - የክርስቲያን ዜና በድጋሜ ለማህበረ ምዕመኗ አባላት እና ለመላዉ ክርስቲያኖች እንኳን አደረሳችሁ ብለን #መልካም ምኞታችንን እንገልፃለን።
“ካሁን በኋላ #ሴት #ነኝ የሚሉ ወንዶችን አናስተምርም” ኖተርዳም ስነ መለኮት ኮሌጅ

በአሜሪካ የሚገኘው እውቁ የኖተርዳም ስነ መለኮት ኮሌጅ ከዚህ ቀደም ያስተላለፈውን ውሳኔ ቀለበሰ። በአሜሪካ ኢንድያና ግዛት የሚገኘው የቅድስት #ማርያም ኖተርዳም የሴቶች ስነ መለኮት ኮሌጅ #ነው #ወደ ቀድሞው አቋሜ ተመልሻለው ያለው።

የኮሌጁ ፕሬዝዳንት #እና የቦርድ ሰብሳቢ በጋራ በመሆን “ወደ ካቶሊካዊት እሴታችን ተመልሰናል” ሲሉ መግለጫ አውጥተዋል።

ከወር በፊት ሴት ሆነው ተፈጥረው #ወንድ ነኝ ብለው የሚያምኑ ሰዎችን ኮሌጁ እቀበላለው ብሎ ነበረ። ኮሌጁ በውሳኔው ምክኒያት ትችቶች ተዘንዝረውበታል።

የኮሌጁ ቦርድ እና መሪዎች #ምንም #እንኳን በተለዋዋጭ አለም #ውስጥ ብንኖርም፣ የቤተ ክርስቲያንን አቋም ሳንቀያይር እናስቀጥላለን ሲሉ ተደምጠዋል።

ውሳኔው #ግን በኮሌጁ ተማሪዎች እና መምህራን ዘንድ ተቀባይነት አላገኘም። ይሄንን አይነት ምላሽ ከኮሌጃችን ማህበረሰብ ባንጠብቅም፣ ካቶሊካዊ ማንነታችንን ግን አስጠብቀን መሄድ አለብን ሲሉ ባስተላለፉት መልዕክት ገልጸዋል።

ባለፈው #ወር በወሰንነው ውሳኔ በኮሌጃችን ህብረትን የሚያመጣ መስሎን ነበረ፣ #ነገር ግን ልዩነትን ፈጥረናል፣ ለዚህም #ይቅርታ እንጠይቃለን ብለዋል።
አሜሪካዊው #ፓስተር ለጋዛ #ክርስቲያኖች #ገንዘብ በማሰባሰብ #ላይ ይገኛሉ ተባለ።

ዊሊያም ዴቭሊን የተባለው #ይህ ፓስተር ከ2010 ጀመሮ #ወደ ጋዛ ከ30 ጊዜ በላይ ለሚሽን #ስራ ተመላልሰዋል። በእነዚህ ጉዞአቸውም በጋዛ የሚገኙትን የመጨረሻዎቹን 3 አብያተ ክርስቲያናት ሲያገለግሉ ነው የቆዩት።

በጋዛ ከሚገኙ 2.2 ሚሊዮን ዜጎች መካከል ወደ 1ሺህ የሚጠጉ ብቻ ናቸው ክርስቲያኖች።

በጋዛ በአንዲት የግሪክ ኦሮቶዶክስ #ቤተክርስቲያን ከ500 በላይ ክርስቲያን #እና ሙስሊሞች ተጠልለው የነበረ ቢሆንም በእስራኤል የአየር ጥቃት ቤተ ክርስቲያኗም ፈራርሳ የተጠለሉትም ተሰደዋል።

ሪዲም የተሰኘ የባልቴቶች እና ወላጅ አልባ ሚኒስትሪ በጋዛ የሚያካሂዱት እኚህ ፓስተር ካለፈው የፈረንጆቹ ዲሴምበር #ወር ጀመረው #ወደ 50ሺህ ዶላር መሰብሰብ መቻላቸውን ለክርስቲያን ፖስት ገልጸዋል።

#ምንም #እንኳን ገንዘቡ የተሰበሰበ ቢሆንም ወደ ጋዛ ለመላክ መጀመሪያ ወደ ዌስት ባንክ ከዚያ በጋዛ ላሉ ክርስቲያኖች እንደሚደርስ ነው የተናገሩት።

በጦርነቱ በጋዛ #ብቻ እስካሁን ከ22 ሺህ በላይ ሰዎች ሲገደሉ ወደ 58 ሺህ የሚጠጉ ደግሞ ቆስለዋል። በአንጻሩ በእስራኤል 1200 ሰዎች ህይወት አልፏል። አሁን ለጋዛ ዜጎች የሚያስፍልገው ጸሎት እና ጸሎት ብቻ ነው ብለዋል።

ፓስተር ዊሊያም ዴቭሊን በግብጽ፣ ጋዛ፣ ፓኪስታን፣ አፍጋኒስታን እና ጆርዳን የሚገኙ አናሳ ቁጥር ያላቸውን ክርስቲያኖች የሚያገለግል ሚኒስትሪ ይመራሉ።

ክርስቲያን መሪዎች ወደ ጋዛ ምድር ሄደው ለምን አይረዱም በሚል ጥያቄያቸውም ይታወቃሉ። ለአሁኑ ግጭትም ቢሆን የእስራኤልን ጦር እንዲሁም የሃማስ ጦር ይወቅሳሉ። በቬትናም ጦርነት ተዋጊ ነበርኩ የሚሉት እኚህ #ሰው በጦርነት ዋናዎቹ ተጎጂዎች ንጹሃን ናቸው ብለዋል።
#እንኳን #አደርሳችሁ

The Christian News - የክርስቲያን ዜና
#22 ዓመታትን #በእግዚአብሔር ቸርነት

አገልግሎት የጀመረዉ በሀረር ከተማ ነዉ። በአገልግሎት ጉዞ ዉስጥ ከመደብደብ አንስቶ በርካታ መንገዶችን አልፏል።

በ90ዎቹ በመላዉ #ኢትዮጵያ የተሃድሶ እንቅስቃሴ ተቀስቅሶ በነበረበት ወቅት ከነበሩ ወጣቶች መካከል አንዱ ነዉ።

ዛሬ በአማኑኤል ቤተክርስቲያን ከሚያገለግሉ ወጣት እና አንጋፋ ከሚባሉት መካከል ይጠቀሳል።

ሀረር ፣ ናዝሬት ፣ እና ሜክሲኮ አማኑኤል ቤተክርስቲያን ላለፉት ከ20 ዓመታት በላይ አገልግሏል።

በአሁኑ ሰዓት ደግሞ የአማኑኤል ህብረት ቤተክርስቲያን "ሀልዎት" አጥቢያን ላለፉት አራት ዓመታት እየመራ ይገኛል።

ላለፉት በርካታ አመታት በአገልግሎት ብዙዎች የተባረኩበት ተወዳጁ አገልጋይ ነብይ ዘኔ በዚህ ሳምንት እጅግ ከሚወዳት እና ለአገልግሎቱ አጋር ከሆነችዉ ባለቤቱ ጋር ከተጋቡ 22 ዓመታትን አስቆጥረዋል።

#እንኳን አደረሳችሁ። ቀሪ ዘመናችሁም የተባረከ እንዲሆን መልካም ምኞታችን ነዉ።
#እንኳን ደስ አለን. .

#ክርስቲያን ፖድካስት #በክርስቲያን ቲዩብ በቅርብ ቀን..

ወንጌላዉያን ዘንድ ፈር ቀዳጅ እና ለብዙዎቻችን ምሳሌ የሆነዉ Christian tube - ክርስቲያን ቲዩብ #አሁን ደግሞ በአዲስ አቀራርብ ብዙዎችን ተደራሽ ለማድረግ መጥቷል።

በጌታ የሆንን ክርስቲያኖች ወንጌልን ለብዙዎች የምንደርስበት ፣ የእግዚአብሔርን ቃል የምንወያይበት፣ በወቅታዊ የቤተክርስቲያን ጉዳይ ላይ ሀሳባችንን የምናካፍልበት፣ የህይወት ተሞክሯችንን ለሌሎች የምናጋራበት፣ እግዚአብሔር ያደረገለንን የምንመሰክርበት የክርስቲያኖች መድረክ ክርስቲያን ፖድካስት በክርስቲያን ቲዩብ የዩቲዩብ ቻናል ተጀምሯል።

https://youtube.com/@christiantube4198?si=yUCsLdTyUAFh8VJz

ማንኛውንም በዚህ ፕሮግራም መነገር አለበት የምትሉትን ነገር ልታጋሩን የምትወዱ በስልክ ቁጥር +251777418556 ይደውሉልን

#ወንጌል በተለያየ መንገድ ያልተደረሱትን ለመድረስ ፣ የተደረሱትን ለማጠንከር ይቀጥላል...
"ክቡር #ልጆች " ተመረቀ።

ክቡር ልጆች ትኩረቱን ልጆች ላይ ያደረገ በተለይ ለቤተሰብ ግንባታ መሰረታዊያንን ያካተተ ነው።

መጽሃፉ የልጆችን ስነ ልቦና መገንባትና የስሜት ስብራት ለመጠገን የሚረዱ ቁልፍ መንገዶችን በስፋት የሚዳስስ ነው።

በትላንትናው እለት በኢንተርናሽናል ኢቫንጀሊካል ቸርች በተካሄደው ምረቃ መጋቢ በቀለ ወ/ኪዳን፡ አምባሳደር ሙሉ ሰለሞን፡ ማስተር በላቸው ግርማ (የሳቅ ንጉስ)፡ የእስራኤል አምባሳደር በኢትዮጵያ እና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች ታድመዋል።

የመጽሃፉ ጸሃፊ ብርሃኑ በላቸው፡ በቤቶቻችን ምንም #እንኳን ወንበር ባንለቅላቸውም የከበሩ ልጆች እንዳሉን ስናስብ፡ በስነ ልቦና የጠነከሩ ልጆች እንፈጥራለን ሲል The Christian News - የክርስቲያን ዜና አስተያየቱን ሰጥቷል። ክቡር ልጆችን ለማንበብ ማንም ሰው መውለድ አይጠበቅበትም፡ ቢያንስ ታናናሽ ወንድም ልና እህቶቻችን ክቡር ናቸው ብሏል።

ዛሬ ልጆችን የሚሰማ ሃገር፡ ቤ/ክ፡ ቤተሰብ ከሌለ ነገ ትውልድ አይኖርም። ስለዚህ በዚህ መጽሃፍ ውስጥ ለልጆች ትኩረት መሰጠቱ ልጆችን የሚሰማ መኖሩን ያሳያል ተብሏል።

The Christian News - የክርስቲያን ዜና በስፍራው ተገኝተን ዘገባውን አሰናዳንላችሁ።

የዕለቱን ፕሮግራም የሚገልፅ ተጨማሪ ፎቶዎችኝ ማየት ከፈለጉ የፌስቡክ ገፃችን ላይ ያገኛሉ።
#ክርስቶስ እንኳን #ወደ ምድር ቢወርድ #አንድ አዳራሽ መስሪያ ቦታ አይሰጣችሁም

#ክርስቲያኖች ላይ ስደት በዝቷል።

በደቡብ ምስራቅ አውሮፓ በምትገኘው ኮሶቮ፣ ክርስቲያኖች #ላይ ስደት በርትቷል ተባለ።

በሃገሪቱ ክርስቲያኖች #ምንም አይነት የመሰብሰብ መብት እንደሌላቸው #እና ፈቃድ ለማግኘትም ሁኔታዎች እንደሚወሳሰቡባቸው ገልጸዋል።

የአርሜ #ቋንቋ ተናጋሪዎች የሚበዙባት ኮሶቮ፣ 93 በመቶ ዜጎቿ የእስልምና እምነት ተከታዮች ናቸው።

ምንም #እንኳን የሃገሪቱ ህገ መንግስት የሃይማኖት ነጻነትን የሚፈቅድ ቢሆንም፣ ክርስቲያኖች ላይ ግን መድሎና አመጽ ይበረታባቸዋል።

#ይህ ስደት በግል ደረጃም፣ የቀብር ስፍራ መከልከል፣ ንብረት የማፍራት መብት አለማግኘትና ሌሎችም በደሎች እየደረሱባቸው እንደሚገኙ ገልጸዋል።

በተለይ #ወንጌላዊያን ክርስቲያኖች፣ የባንክ ሂሳብ መክፈት፣ ንብረት ማፍራት እና ሰራተኞችን ቀጥሮ የመንቀሳቀስ ዴሞክራሲያዊ መብቶች የላቸውም።

በቅርቡ የወጣ #አንድ ህግ ደግሞ የሰርቢያ ኦርቶዶክስ፣ ካቶሊኮችን እና ሌሎችንም ታሪካዊ አብያተ ክርስቲያናትን ኢላማ ያደረገ ነው ይባልለታል።

በሃገሪቱ ያለፉትን 25 ዓመታት ያገለገሉ አንድ ቄስ ሲናገሩ፣ ያለው ስቃይ በግልጽ ስላልሆነ ይበልጥ ከባድ ያደርገዋል ብለዋል።

ለቀብር እንኳን በሙስሊሞች የቀብር ስፍራ፣ በኢማሞች የተመራ ቀብር ስነ ስርዓት እያደርግን ነው የምንገኘው ብለዋል። ምንም ቢሆን #ግን ለሃገራችን የወንጌል ተስፋ አለን ሲሉም እኚሁ ቄስ ይናገራሉ።

በኮሶቮ በ1980ዎቹ ወንጌላዊያን፣ ክርስቶስ እንኳን ወደ ምድር ቢወርድ አንድ አዳራሽ መስሪያ ቦታ አይሰጣችሁም የሚል ተደጋጋሚ ዛቻ ከወቅቱ ኮሚኒስት መንግስት ሲደርስባቸው እንደ ነበረ ዘገባዉ አስታዉሷል።
#እንኳን #ደስ አለህ

#ወጣቱ ወንድማገኝ የመላዉ አፍሪካ አብያተክርስቲያናት ጉባኤ የጠቅላላ ኮሚቴ አባል በመሆን ተመርጧል።

የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነየሱስ የልጆች እና ወጣቶች አገልግሎት መምሪያ ዳይሬክተር ወንድማገኝ ኡዴሳ
ናይጄሪያ አቡጃ እየተካሄደ በሚገኘዉ በ12ኛው የመላ አፍሪካ አብያተ ክርስቲያናት ጉባኤ ወጣቶችን በመወከል የጠቅላላ ኮሚቴ አባል በመሆን ተመርጧል::

The Christian News - የክርስቲያን ዜና የተሰማንን ደስታ እየገለፅን #መልካም የአገልግሎት #ጊዜ እንዲሆንልህ እንመኛለን። Wondmagegn Udessa Bidire 🙏🙏🙏
#እንኳን ደስ አላችሁ
🎓🎓🎓🎓🎓

በዲግሪ፡ ማስተርስ እና ፒ ኤች ዲ ፕሮግራሞች በርቀት፡ በማታ፡ ቅዳሜና እሁድ እንዲሁም Online በመረጡት ፕሮግራም ወደርሶ ቀርበናል።

#9720 ይደውሉ፡ አሁኑኑ ይመዝገቡ
ለOnline ትምህርት ፈላጊዎች
              👇👇👇
www.elearning.gelilaseminary.com
መመዝገብና መማር ትችላላችሁ
!
ገሊላ ኢንተርናሽናል ሴሚናርየም
#እንኳን #ደስ #አልዎት

#ፓስተር ደሳለኝ #አበበ ደግም ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ።

የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን 93ኛው ጠቅላላ የመሪዎች ጉባኤ በመሠረተ ክርስቶስ ሴሚናሪ ግቢ ውስጥ እየተካሄደ ይገኛል።

በዚሁ መሠረት ፓስተር ደሣለኝ አበበ ለሁተኛው የአገልግሎት ዘመን 98.8% ድምፅ በማግኘት የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ፕሬዚዳንት ሆነው እንዲያገለግሉ ተመርጧል።

The Christian News - የክርስቲያን ዜና እንኳን ደስ አለዎት በማለት ደስታችንን እየገለፅን #መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንሎት ይመኛል።