The Christian News
5.38K subscribers
3.07K photos
27 videos
724 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
ጥቅምት ወር አንድ እሁድ ፓስተር ሶሙ አቫራዲ በደቡባዊ ሕንድ ካርናታካ ግዛት ውስጥ በምትገኘው በሁባሊ ከተማ ወደሚገኝ ቤተ ክርስቲያናቸው ሲገቡ ደነገጡ።

"በቤተ ክርስቲያኗ ውስጥ በርካታ ሰዎች ተሰባስበው የሂንዱ ሐይማኖታዊ መዝሙሮችን እየዘመሩ፣ መፈክሮችንም እያሰሙ እየጮሁ ነበር"

#የክርስቲያኖች ስደት የበዛባት ሀገር #በሐይማኖት መቀየር ምክንያት ጥቃትን የሚፈሩት ክርስቲያኖች #መንግሥት እያደረገብን ያለው ጉዳይ መልካም ነገር አይደለም። ሁሉም ሊሰማው የሚገባ አስገራሚ የክርስቲያኖች ጉዞ https://youtu.be/Y0m7Dj9rrA0
#የክርስቲያኖች_ስደት_ሊጨመር_ይችላል
The Christian News - የክርስቲያን ዜና

በፈረንጆቹ 2023 በአለም ዙሪያ የክርስቲያኖች ስደት ሊጨምር እንደሚችል አንድ ጥናት አመለከተ።

"በቅርብ ዓመታት ውስጥ ስደት እየጨመረ መጥቷል። 2023 ያንን አዝማሚያ የሚቀጥል ይመስላል" ሲሉ አንድ የክርስቲያን አገልግሎት መሪ አስጠንቅቀዋል።

ሪሊዝ ኢንተርናሽናል የስደት ጉዳዮች ተከታታይ ድርጅት በጥናቱ በናይጄሪያ፣ ህንድ፣ ቻይና እና ኢራን ያለው ሁኔታ ከሌሎች ሀገራት አማኞች ያለውን ሁኔታ አጉልቶ ያሳያል ብሏል።

በናይጄሪያ በፉላኒ ታጣቂዎች የተገደሉት የክርስቲያኖች ቁጥር ከ6,000 በላይ ሲሆን ቦኩሃራም ጨምሮ የሚያደርሰው ጥቃት ጉዳቱን ከፍ እንደሚያደርግ አሳስቧል።

በተመሳሳይ በህንድ ክርስትያኖች ላይ በሂንዱ ብሔርተኞች እየተጠቁ ሲሆን ፀረ ለውጥ ሕጎችም በተለያዩ ግዛቶች እየተሰራጩ ሲሆን ይህም ብሄራዊ ህግ ሊተገበር የጊዜ ጉዳይ ነው ወደሚል ስጋት እንደሚያመራ እንደሆነ ተገልጿል።

የሪሌዝ ኢንተርናሽናል አጋር እንዳለው በኢራን በዚህ አመት በተቀሰቀሰ ተቃውሞ ምክንያት “በእርግጥ ተስፋ የቆረጡ የሌላ ዕምነት ተከታዮች ክርስቲያን እየሆኑ ነው” በዚህም ምክንያት ስደት ሊጨምር እንደሚችል ጥርጥር የለውም።
#ሱዳን #ጦርነት
#ቤተክርስቲያን ማቃጠል
#የክርስቲያኖች #ስደት

በሱዳን እየተካሄደ ያለው ጦርነት አብያተ ክርስቲያናትን ማፈራረሱን ቀጥሏል ተባለ።

ባለፈው ሳምንት #ብቻ #ሁለት የወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት በጦርነቱ ምክኒያት ጋይተዋል። በሱዳን ሁለተኛ ጥንታዊ እና ትልቁ #ቤተክርስቲያን በኦምዱርማን ከተማ ከጥቅም ውጪ ሆኗል።

ጥቃቱ በቤተ ክርስቲያኗ ዙሪያ የሚገኝን የክርስቲያኖች ትምህርት ቤት ኢላማ ያደረገ ቢሆንም፣ የፕሪባይቴሪያን  ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን ህንጻም ፈራርሷል። ውስጥ የሚገኙ መጽሃፍ ቅዱስ፣ የመዝሙር ደብተር እና ዶክመንቶች ከጥቅም ውጪ ሆነዋል።

በቤተ ክርስቲያኑ ዙሪያም ወላጅ አልባ ህጻናት ትምህርት ቤት፣ የጥቃቱ ሰለባ ነው። ምንም እንኳን ህንጻው ላይ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰ ቢሆንም፣ ሰው ላይ ግን የደረሰ ጉዳት የለም።

በጦርነቱ ከጥቅም ውጪ ከሆኑ ቤተ ክርስቲያኖች መካከል አንዱ፣ 81 አመታትን መንፈሳዊና ማህበራዊ አገልግሎቶችን ይሰጥ የነበረ ነው። ባለፈው አርብ በደቡባዊ ካርቱም፣ የሚገኝ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የቦምብ ጥቃት ተፈጽሞበት፣ 5 መነኩሴዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል።

በጦርነቱ ዋነኛ የጥቃት ሰለባ የሆኑት አብያተ ክርስቲያናት መሆናቸውም እየተዘገበ ይገኛል። ኦምዱርማንና ካርቱም ብቻ ፈጣን ድጋፍ ሰጪ የተባለው ጦር፣ ሁለት አብያተ ክርስቲያናትን ተቆጣጥሮ የጦር ማዘዣ አድርጓል። በካርቱም የምትገኝን አንዲት ቤ/ክ ንብረት የሆኑ ተሽከርካሪዎችንም ለጦርነት አላማ እያዋለ ይገናል።

ባለፈው ሚያዝያ ወር ጌሪፍ የተባለን የመጽሃፍ #ቅዱስ ትምህርት ቤት ከጥቅም ውጪ በማድረግ የተማሪዎችን ዶርም፣ መማሪያ ክፍሎችና የአምልኮ ስፍራም ጥቃት ተፈጽሞበት ከጥቅም ውጪ ሆኗል ነው የተባለው።

በሱዳን ጦርና ፈጣን ሃይል ሰጪ በሚባለው ጦር መካከል  እየተካሄደ በሚገኘው 2ኛ አመቱን በያዘው ጦርነት፣ እስካሁን 10ሺህ የሚሆኑ ንጹሃን #ህይወት ያለፈ ሲሆን፣ ወደ 5.6 ሚሊዮን የሚጠጉ #ሰዎች #ቤት ንብረታቸውን ጥለው ተሰደዋል ሲል ተ.መ.ድ አስታውቋል።

የሱዳን ጦር መሪ ጀነራል አብደል ፈታህ አልቡርሃንና የፈጣን ድጋፍ ሰጪ ሃይሉ መሪ ሞሃመድ ሃምዳን ደጋሎ በጋራ የሲቪሉን የሽግግር መንግስት ከስልጣን ካወረዱ በኋላ፣ በመካከላቸው የተፈጠረ ልዩነት ሱዳንን ዛሬ ላይ አድርሷታል።

#ምንም #እንኳን ለ30 አመታት ሱዳንን የመሩት ኦማር አልበሽር የስልጣን ዘመን የነበረው የክርስቲያኖች ስደት ይቀንሳል ተብሎ የነበረ ቢሆንም፣ በጦርነቱ ምክኒያት ግን እየተባባሰ ይገኛል ነው የተባለው።

ኦፕን ዶርስ በ2023ቱ ሪፖርት መሰረት፣ ሱዳን በ2021 ከነበረችበት የ13ኛ ደረጃ የክርስቲያኖች ስደት ተባብሶ ወደ 10ኛ ደረጃ ከፍ አድርጓታል።

ክርስቲያኒቲ ቱደይ እንዳስነበበው በሱዳን ከአጠቃላይ 43 ሚሊዮን ህዝቧ መካከል፣ 4.3 በመቶው ወይም ወደ 2 ሚሊዮን የሚሆነው #ሕዝብ #ክርስቲያን ነው።