#አዲስ
#ፓስተር_ጻዲቁ ምንድነው_ያሉት?
#አቋም የተያዘባቸው 6 ነጥቦችስ ምን ምን ናቸው?
በኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረትና በግሬት ኮሚሽን ሚኒስትሪ ኢትዮጵያ አዘጋጅነት እየተካሄደ ባለው ጉባኤ ላይ ከሶሰት ሺህ በላይ መሪዎች እየተሳተፉ ይገኛል።
#የሕብረቱ ፕሬዝደንት ፓስተር ጻዲቁ አብዱ ዛሬ በነበረው የመክፈቻ መሰናዶ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት በዋናነት 6 ነጥቦች ላይ ትኩረት እንዲደረግ እና #አቋም እንዲያዝ አጽንዖት እንዲሰጠው አሳስበዋል።
እነዚህ ስድስት ነጥቦች ምን ምን ናቸው?
1. እንደ ወንጌላውያን #ጥላቻን እና ቂም በቀልን ለግጭት የሚዳርጉ ድርጊቶችን እና ሰዎችን ከየትኛውም ወገን ይሁን ለጥላቻ የሚቀሰቅሱ #ለቂም በቀል የሚያነሳሱ ግጭቶች በተለያየ ምክንያት በሰዎች መካከል እንዲነሱ የሚያደርጉ ሰዎችን #እምቢ ማለት እና ልንቃወም ይገባል።
2. በእኛ ወንጌላውያን ስም እይተጠሩ እና #ወንጌላውያን ናቸው ተብሎ እየታሰቡ ነገር ግን ከወንጌላውያን አስተምሮ በእጅጉ የራቁ #የሃሰት #ትምህርት የሚያስተምሩትን ኢ-መጽሐፍ ቅዱሳዊ ልምምድ ያላቸውን ፤ እጅግ የተበላሸ የሞራል #ሕይወት የሚኖሩትን ሰዎች የማንቀበል መሆኑን በይፋ የምንናገርበት እና የምናሳውቅበት ጊዜ ነው።
3. የኢትዮጵያን ሕዝብ #በብሔር እና #በሃይማኖት ለማጋጨት የሚደረገው ሙከራ መቃወም ይገባናል። እምነታቸውም ይሁን ብሔራቸው ከኛ ለተለዩ ሰዎች "ባልንጀራሕን እንደ ራስህ ውደድ" በሚለው መርህ እንዲሁም "ሰዎች እንዲያደርጉላቸሁ የምትወዱትን እናንተም ለሌሎች እንዲሁ አድርጉላቸው። በሚለው ወርቃማ ሕግ እየተመራን ለሰዎች ሁሉ መልካምን እናድርግ። ጥላቻን በፍቅር እናሸንፍ። ለክፉ #መልካም በመመለስ የሚረግሙንን በመመረቅ የጌታችንን ምሳሌ እንከተል።
4. በእምነታችን እና በማንነታችን ምክንያት የሚደረግብንን ማንኛውም #መድሎ እና #ጫና #መቃወም አለብን። ወንጌላውያን ዛሬም በተለያዩ ቦታዎች በተለይም የወንጌላውያን አማኞች ቁጥር በሚያንስባቸው አከባቢዎች እጅግ የከፋ መድሎ እንደሚደረግብን እናውቃለን። ሀገራችን የሁላችንም ሀገር ስለሆነች እንደ ዜጋ ለሃገራችን ሰላም እና ልማት መስራት ይጠበቅብናል። የሌሎች #እምነት ያለ አግባብ #ሲደፈር ዝም አለማለት የራሳችንንም #በሕግ አግባብ ማስጠበቅ ይገባናል።
5. በሰሜኑ የሃገራችን ክፍል የነበረው የእርስ በዕርስ #ጦርነት በሰላማዊ መንገድ ስለተቋጨ እና #ሕዝቡ እፎይታ ስላገኘ አከባቢውም ከጦርነት ስላረፈ ታላቅ ደስታ ተሰምቶናል። ይህ ሰላም ጸንቶ እንዲቆይ እንዲሁም ግጭት ባለባቸው ሌሎች የሃገራችን ክፍሎች ሰላም እንዲሰፍን እኛ ወንጌላውያን እጅግ አብልጠን ልንጸልይ እና ለሰላም የራሳችንን ድርሻ ልንወጣ ይገባል።
6. (አጽንዖት የሚፈልግ #ጉዳይ) #ግብረ_ሰዶም ሰበዓዊም ዲሞክርራሲያዊም መብት አይደለም። #ግብረ_ሰዶም_ሐጢያት_ነው። ግብረ ሰዶም ምንም ከፍቅር ጋር ግንኙነት የለውም። በግብረ ሰዶም ችግር ስለወደቀ ሰው አዝናለሁ። ከዚህ አስከፊ ከሆነ ሐጢያት እንዲወጣ እጸልይለታለሁ። ነገር ግን ሃጢያቱን ልምምዱን የእግዚአብሔር ቃል እጅግ የሚያወግዘው የከፋ #ሐጢያት ስለሆነ #እቃወማለሁ።
ዛሬ በሰበዓዊ ስም የዲሞክራሲ መብት ነው ተብሎ ግብረሶዶማዊነትን በተለያየ መንገድ #በአፍሪካ በተለይም ከ97% በላይ ሃይማኖተኛ በሆንን ሀገር ላይ በተለያየ መንገድ ለመጫን አዕምኖዕችን ለዚህ ዝግጁ የሚደረገውን ግፊት በሙሉ እኛ እንደ #ወንጌላውያን አንቀበል። እንቃወመዋለን።
ግብረ ሰዶም በመጽሐፍ ቅዱስ እጅግ የከፋ ሐጢያት እና የሐጢያት ምሳሌ ነው። ሰዶም እና ጎመራ ተቃጥለው የጠፉት በዚህ ሃጢያት ምክንያት ነው።
እግዚአብሔር ሰዎችን በመልኩ ወንድ እና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው። ጾታዬን ለማወቅ እንድሜዬ 18 መድረስ የለበትም። ስወለድ እና እግዚአብሔር ሲፈጥረኝ ማን እንደሆንኩኝ አውቃለሁ።
ጾታችሁን የምታውቁት ስታድጉ ነው የሚለው አደገኛ አስተምሮ ስለሆነ ዝም ብለን አናልፍም። ግብረ ሰዶም ሰበዓዊነት ሳይሆን ሰበዓዊነትን ወደ አውሬነት የሚለውጥ ስበዓዊነትን የሚያሳንስ ሴጣናዊ የሚያደርግ ሐጢያት ነው።
በየትኛውም #ሐጢያት ላይ ግልጽ #አቋም መውሰድ እንዳለብን ሁሉ በተለይ በግብረሰዶም ላይ አፋችንን ዘግተን የምንቀመጥበት አይደለም። ስለዚህ ለሰዎቹ እናዝናለን ከዚህ ጉድጓድ እና አዝቅት ውስጥ እንዲወጡ በፍቅር እንጸልይላቸዋልን ፤ እናለቅሳለን። ነገር ግን ሐጢያቱ ሐጢያት ነው።
መጋቢ ጻዲቁ አብዶ
የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት ፕሬዝደንት

#ሱዳን #ጦርነት
በሱዳኑ ጦርነት ቤተክርስቲያን እና ክርስቲያኖች እየተጎዱ ነው።
በሱዳን በተቀሰቀሰው የእርስ በርስ ግጭት አራት አብያተ ክርስቲያናት ወድመዋል ክርስቲያኖችም ተገድለዋል ከፊሎቹም ቆስለዋል።
ባፕቲስት ፕሬስ ይዞት በወጣው ዘገባ ሁለት ሳምንት የሆነው ውጊያ አስካሁን በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈ ሲሆን በሱዳን ካለው አደጋ አንዱ በአብያተ ክርስቲያናት እና በክርስቲያኖች ላይ የሚደርሰው ስደት ነው ሲል ገልጿል።
በጦርነቱ ቁጥራቸው እየጨመረ የመጣ ክርስቲያኖች ተገድለዋል የሚለው ዘገባው በተጨማሪም ጉዳት የደረሰባቸው ክርስቲያኖች በመንግስት ሆስፒታሎች ህክምና ሳያገኙ እየተመለሱ ሲሆን ክርስቲያኖች ለሌሎች ዜጎች እየቀረበ ያለው የምግብ እርዳታ እየተነፈገ መሆኑን ምንጮችን ጠቅሶ ዘገባው አትቷል።
ጦርነቱ ከተቀሰቀሰበት ጊዜ ጀምሮ ቢያንስ አራት አብያተ ክርስቲያናት መውደማቸውን ሪፖርቱ ያከለ ሲሆን የአብያተ ክርስቲያናቱን ስም እና የጉዳታቸውን መጠንም ተንትኗል።
የሃገሪቱን ሕዝብ 4.3 በመቶ ብቻ የሚሸፍኑት እና 2ሚሊዮን ክርስቲያኖች እንደሚኖሩባት የሚነገረው ሱዳን በ2023 ሪፖርት መሰረት ለክርስትና አስቸጋሪ ከሚባሉ 50 ሀገራት መካከል በ10ኛ ስፍራ ተቀምጣለች።

#ቤተክርስቲያን ማቃጠል
#የክርስቲያኖች #ስደት
በሱዳን እየተካሄደ ያለው ጦርነት አብያተ ክርስቲያናትን ማፈራረሱን ቀጥሏል ተባለ።
ባለፈው ሳምንት #ብቻ #ሁለት የወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት በጦርነቱ ምክኒያት ጋይተዋል። በሱዳን ሁለተኛ ጥንታዊ እና ትልቁ #ቤተክርስቲያን በኦምዱርማን ከተማ ከጥቅም ውጪ ሆኗል።
ጥቃቱ በቤተ ክርስቲያኗ ዙሪያ የሚገኝን የክርስቲያኖች ትምህርት ቤት ኢላማ ያደረገ ቢሆንም፣ የፕሪባይቴሪያን ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን ህንጻም ፈራርሷል። ውስጥ የሚገኙ መጽሃፍ ቅዱስ፣ የመዝሙር ደብተር እና ዶክመንቶች ከጥቅም ውጪ ሆነዋል።
በቤተ ክርስቲያኑ ዙሪያም ወላጅ አልባ ህጻናት ትምህርት ቤት፣ የጥቃቱ ሰለባ ነው። ምንም እንኳን ህንጻው ላይ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰ ቢሆንም፣ ሰው ላይ ግን የደረሰ ጉዳት የለም።
በጦርነቱ ከጥቅም ውጪ ከሆኑ ቤተ ክርስቲያኖች መካከል አንዱ፣ 81 አመታትን መንፈሳዊና ማህበራዊ አገልግሎቶችን ይሰጥ የነበረ ነው። ባለፈው አርብ በደቡባዊ ካርቱም፣ የሚገኝ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የቦምብ ጥቃት ተፈጽሞበት፣ 5 መነኩሴዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል።
በጦርነቱ ዋነኛ የጥቃት ሰለባ የሆኑት አብያተ ክርስቲያናት መሆናቸውም እየተዘገበ ይገኛል። ኦምዱርማንና ካርቱም ብቻ ፈጣን ድጋፍ ሰጪ የተባለው ጦር፣ ሁለት አብያተ ክርስቲያናትን ተቆጣጥሮ የጦር ማዘዣ አድርጓል። በካርቱም የምትገኝን አንዲት ቤ/ክ ንብረት የሆኑ ተሽከርካሪዎችንም ለጦርነት አላማ እያዋለ ይገናል።
ባለፈው ሚያዝያ ወር ጌሪፍ የተባለን የመጽሃፍ #ቅዱስ ትምህርት ቤት ከጥቅም ውጪ በማድረግ የተማሪዎችን ዶርም፣ መማሪያ ክፍሎችና የአምልኮ ስፍራም ጥቃት ተፈጽሞበት ከጥቅም ውጪ ሆኗል ነው የተባለው።
በሱዳን ጦርና ፈጣን ሃይል ሰጪ በሚባለው ጦር መካከል እየተካሄደ በሚገኘው 2ኛ አመቱን በያዘው ጦርነት፣ እስካሁን 10ሺህ የሚሆኑ ንጹሃን #ህይወት ያለፈ ሲሆን፣ ወደ 5.6 ሚሊዮን የሚጠጉ #ሰዎች #ቤት ንብረታቸውን ጥለው ተሰደዋል ሲል ተ.መ.ድ አስታውቋል።
የሱዳን ጦር መሪ ጀነራል አብደል ፈታህ አልቡርሃንና የፈጣን ድጋፍ ሰጪ ሃይሉ መሪ ሞሃመድ ሃምዳን ደጋሎ በጋራ የሲቪሉን የሽግግር መንግስት ከስልጣን ካወረዱ በኋላ፣ በመካከላቸው የተፈጠረ ልዩነት ሱዳንን ዛሬ ላይ አድርሷታል።
#ምንም #እንኳን ለ30 አመታት ሱዳንን የመሩት ኦማር አልበሽር የስልጣን ዘመን የነበረው የክርስቲያኖች ስደት ይቀንሳል ተብሎ የነበረ ቢሆንም፣ በጦርነቱ ምክኒያት ግን እየተባባሰ ይገኛል ነው የተባለው።
ኦፕን ዶርስ በ2023ቱ ሪፖርት መሰረት፣ ሱዳን በ2021 ከነበረችበት የ13ኛ ደረጃ የክርስቲያኖች ስደት ተባብሶ ወደ 10ኛ ደረጃ ከፍ አድርጓታል።
ክርስቲያኒቲ ቱደይ እንዳስነበበው በሱዳን ከአጠቃላይ 43 ሚሊዮን ህዝቧ መካከል፣ 4.3 በመቶው ወይም ወደ 2 ሚሊዮን የሚሆነው #ሕዝብ #ክርስቲያን ነው።