The Christian News
5.37K subscribers
3.08K photos
29 videos
730 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
“የሰማይ #አምላክ ያከናውንልናል እኛም ባሪያዎቹ ተነስተን እንሰራለን" ክብርት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

“እግዚአብሄር ታላቅ ነገር አደረገልን እኛም ደስ አለን” ክብርት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

የአዲስ አበባ #ከተማ ከንቲባ ክብርት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በዛሬዉ እለት በአዲስ አበባ እስታዲየም ተገኝተዉ ያስተላለፉት #መልዕክት #እግዚአብሔር ተግዳሮት በሚመስል መንገድ ውስጥ በርካታ ነገሮችን አሳክቶ ስራችንን ፍሬያማ አድርጎታል።

#ብዙ የምንወድቅባቸው የሚመስሉ መንገዶችን አልፈናል ዳገቶች ፤ ሸለቆዎች ነበሩ ብዙ ሰላም የሌለባቸውን ሀገሮች ታሪክ ስንመለከት እግዚአብሔር ስለ ሰጠን ሰላም እናመሰግነዋለን።

ፍጹም ስላማችን እንዲደፈርስ እርስ በእርሳችን እንዳንቀባበል እንድንበታተን ወንድም ወንድሙን እንዲገድል ፈጽሞ መበታተን እንዲሆን ያልተሰራ ነገር የለም ከውስጥም ከውጪም ብዙ ጫናዎች ነበሩብን #ነገር #ግን ከእግዚአብሔር ጋር ጸንተን ቆመናል።

በእነዚህ የውጣ ውረድ መንገዶች በጸሎታችሁ አብራችሁን ለነበራችሁ በብዙ መንገድ ስትለፉ ስትደክሙ በልማት ፤ በበጎ አድራጎት ፤ በሰላም ስራዎች ያልተለያችሁን ለትውልዱ መልካሙን ዜና በመንገር ተስፋ እንዲኖረው ይልቁንሙ ከሁኔታዎች በላይ #እግዚአብሔር የሚለውን ለሃገራችን ያለውን እንዲመለከት በማድረግ ብዙ ዋጋ የከፈላችሁ እና የሰራችሁ #በሙሉ እናመሰግናችኋለን።

በአዲሱ አመትም በርካታ ውጥኖች አሉን በርትተን እንሰራለን አንሰንፍም ፤ ፈጽሞ ስንፍናን አልተማርንም በመጽሐፍ #ቅዱስ ተጽፎ ያነበብነው አባታችሁ ተግቶ ሲሰራ ነው። እኛም ልጆቹ ተግተን እንሰራለን።

በፍቅር ወንድማማችን በማስታረቅ ፤ በማቀራረብ የሰላሙን #ዜና እየተናገርን የሰላም ስራተኞች በመሆን እየታወቅን ይልቁንም ለምድራችን ብዙ ፍሬ እንዲበዛ እግዚአብሔር ለምድራችን የወደደውን ያለመከልከል መስራት እንዲችል ምቹ ሁኔታን በመፍጠር ብርቱ ሰራተኞች በመሆን ለመልካም ስራ እጅ ለእጅ ተያይዘን ለምድራችን አብረን እንድንተጋ በዚህ አጋጣሚ ጥሪዬን አቀርባለሁ።

እያየነው ያለነው ፍሬ ተስፋ የሚያስቆርጥ ሳይሆን የሚያበረታ ነው አባቶቻችን ልጆቻችን ይሰሩታል ብለው ያሳለፉትን ይህ ትውልድ እግዚአብሔር እረድቶን በራሳችን እውቀት እና ገንዘብ አባይን ገድበናል ብዙም ፍሬ አግኝተናል ይህ ቀላል አይደለም።

አንድ ላይ ሆነን ከሰራን እና ከተደጋገፍን የያዝነው ስራ በጸድቅ ከፈጸምን ይከናወንልናል ነህምያ “የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል እኛም ባሪያዎቹ ተነስተን እንሰራለን" እንዳለው እኛ ተነስተን እንሰራለን የሰማይ አምላክም ያከናውንልናል።

#ዛሬ የጀመርነው አዲሱ አመት ለሁሉም የሃገራችን ክፍል ሞልቶ የሚፈስበት ወንድማማቾች ተጸጽተው የሚተቃቀፉበት ፤ ለምድራቸው ሰላም በጋራ የሚሰሩበት የኢትዮጵያ እሴት ደምቆ የሚታይበት ብዙ ውድቀቷን የሚፈልጉ #ኢትዮጵያን በሰላማዊነቷ በብዙ ለውጥ እና የልማት ስራዎች የሚሰራበት አመት እንደሚሆንልን እናምናለን።

#መልካም #አዲስ #አመት

Photo 📷 Hossana Photo & Video Production
#መልካም #እለተ ሰንበት ይሁንልን 🙏🙏🙏

ቴክኒካሊ ብልጥ ሆነን የማናልፍበት ዘመን መጥቷል።

ዘመኑን ለማለፍ መንፈሳዊ መሆን የግድ ነዉ። እሱም ከኢየሱስ ጋር #ብቻ መሆን #ነዉ የሚያዋጣዉ።

በመፅሐፍ #ቅዱስ #ብዙ ታሪክ የሰሩ ሰዎችን ብንመለከት #እንኳን አለም እነሱን አይታ ተሸናፊዎችነዉ ያለቻቸዉ። ማንም አይፈልጋቸዉም ነበር።

በዘመናቸዉ #ሁሉ #ኢየሱስ ሲሉ ነበር ካለፉ በኋላ ግን ሁሉም ሰዉ ስለ ኢየሱስ ከ2ሺህ ዘመናት በላይ ይናገራል።

ኢየሱስ ካልክ የዚህ ድንቅ መፅሐፍ አካል ትሆናለህ። መፅሐፍ ቅዱስ የአንድ ታሪክ መፅሐፍ ነዉ። እነዚህ ሁሉ ሰዎች ስለ አንድ ታሪክ ሲናገሩ ነዉ የታሪክ አካል የሆኑት።

#ነብይ ጥሌ
#ፍትህ ግን ምንድነው? 🤔 የትስ #ነው ያለው? 🤔
#እኛ ጥያቄያችን #አንድ እና ግልጽ  ነው።

#የቤተክርስቲያናችን_ንብረት_ይመለስልን!!! 🙏🙏🙏

37 ዓመታት በእንባ እና በጸሎት የጸሎት ቤቷን ለማስመለስ ፍትሕን ፍለጋ የተነከራተተችው #ቤተክርስቲያን ዛሬም ፍትህን ፍለጋ ላይ ነች።

የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ከ1950ዎቹ #መጀመሪያ ጀምሮ በተለይ ትምህርትን ከማስፋፋት አንጻር #ለሀገር እና #ለሕዝብ ጥቅም ላበረከተችው አስተዋጽዖ በወቅቱ የነበረው የመንግስት ስረዓት ከምስጋና ይልቅ ት/ቤቶቻችንና ጸሎት ቤቶቻችንን መውረስ ቀሏቸዋል።

በደርግ #መንግስት በግፍ የተወረሰው የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የኦሎምፒያው ጸሎት ቤታችን በአዲስ አበባ የመጀመሪያው የመሰረተ ክርስቶስ የማምለኪያ ስፍራ ነው።

#ይህ የመሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ንብረት #ማለት የሙሉ #ወንጌል ምዕመን እና የሙሉ ወንጌል ቤ/ክ ንብረት ማለት ነው። የመካነ ኢየሱስ ማለት ደግሞ የቃለ ሕይወት ነው። የቃለ ሕይወት ማለት የሕይወት ብረሃን የሕይወት ብረሃን ማለት የገነት የገነት ማለት የጉባኤ እግዚአብሔር ... በአጠቃላይ የወንጌል አማኞች #በሙሉ ነው።

ይህ ከ66 ዓመት በላይ የተሻገረው የጸሎት ስፍራ ንብረት ብቻ አይደለም ይልቁንም ለወንጌል የተሰደዱ ፤ ለወንጌል ዋጋ የከፈሉ የወንጌላውያን አማኞች #ታሪክ እና ቅርስም ጭምር ነው።

በ1943ዓ.ም የተመሰረተችው የመሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ከቀደምት የወንጌል አማኞች ቤተዕምነት መካከል አንዷ ብቻ ሳትሆን እውነተኛው የክርስቶስ ወንጌል ለአዲሱ #ትውልድ  እንዲሸጋገር ከ70 ዓመት በላይ #በኢትዮጵያ በሚመችም በማይመችም ሁኔታ #ውስጥ ስትሰራ ቆይታለች።

#ዛሬ ላይ መዲናችን #አዲስ አበባ ከሌሎች #አለም ላይ ከሚገኙ ከተሞች መካከል ለመወዳደር ሌት ተቀን እየተጋች ትገኛለች። በዚህ ውስጥ ታዲያ በከፊሉ አዳዲስ ሲገነባ በከፊሉ ለተቸገሩት ሲደረስ በሌላ አቅጣጫ ግን እንሳኩን ያልተመለሱ #ብዙ ጥያቄዎች እንዳሉ የአደባባይ ሚስጥር ነው።

ታዲያ በመዲናችን #ዛሬም ፍትህን ከሚጠይቁ ተቋማት መካከል አንጋፋዋ የመሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አንዷ ነች።

ስለዚህ ህጋዊ የሆነው የቤተክርስቲያን ታሪክ ፤ ቅርስ እና ንብረታችን የሆነው የጸሎት ቤቶቻችን ይመለሱልን የማያቋርጥ ጥያቄያችን ነው!!!

ይህ #መልዕክት የሚደረሳችሁ ምዕመናን እና ኢትዮጵያውያን በሙሉ የቤተክርስቲያናችን ንብረት እስኪመለስ ድረስ ሁላችንም #SharePost በማድረግ ለሁሉም እናድርስ!!!

The Christian News - የክርስቲያን ዜና በዚህ ዙሪያ ተጨማሪ ዘገባዎችን በተለያየ ጊዜ ይዘን የምንመለስ ይሆናል።

#share #share #share #share
#ጉዞ #ወደ #ሞት ... 🚶‍♂️🚶‍♀️🚶‍♂️ ☠️

ከሰሞኑ #BBC ወደ ሞት ጉዞ ብሎ #ልብ ኮርኳሪ ቅስም ሰባሪ ሰፋ #ያለ ዘገባዎችን አስነብቦ ነበር።

በዋናነት ዘገባው #ኢትዮጵያውያን ሳዑዲ ለመግባት በአፋር #እና በጅቡቲ በረሃ የሚያደርጉትን እልህ አስጨራሽ እና ተስፋ አስቆራጭ ጉዞ የሚተርክ ነው።

ልብ አንጠልጣይ እና ምስል ከሳች አድርጎ የሚተርከው ዘገባ #ግን ... እውነተኛ የእግር ዳናቸውን ተከትሎ ባህርን ለማቋረጥ በጭላንጭል #ተስፋ ውስጥ የሚገኙ የተስፈኞችን እውነተኛ የተጋድሎ የጉዞ #ታሪክ ይተርካል።

ተጓዡ ጋዜጠኛ ሕይወትን ለመለወጥ በሚደረገዉ ጉዞ "የቀይ ባሕር ስደተኞችን ማሻገር አልያም በሰፊ ሆዱ ውጦ ማስቀረት አይታክተውም" ሲል ቁጥራቸው እልፍ የሆኑ ተስፈኞች ከነ ተስፋቸዉ ሰጥመዉ እንደቀሩ ፅፏል።

#ታዲያ አሁንም ቢሆን በርካቶች ወደ አገራቸው የሚመልሳቸው እንዳጡ በሚናገሩባት ኦቦክ (የጅቡቲ የባሕር ዳርቻ) ሌሎች በርካቶች ደግሞ እልፍ ሲሉ እልፍ ይገኛል በሚል ጂቡቲ ድንበር ሆነው የመንን ይናፍቃሉ።

ከየመን ለመውጣት ቀዳዳ የጠፋባቸውን በርካታ ስደተኛ እንዳሉም ዘጋቢዉ ያነሳል ወደ ኦቦክ ለአዲስ ስደት የሚተመውን ወጣት እየተመለከቱ ለእኛ ግን ከዚህ ሁሉ አገር ቤት ገብቶ የሚሆነውን መጠበቅ ይሻለናል ብለዉ ከብዙ ስቃይ በኋላ የእግር ጉዟቸውን ወደ #ኢትዮጵያ የሚያደርጉም በርካታ ናቸዉ።

#ዛሬ በዚህ ምልከታዬ #ብዙ #ገንዘብ ስለሌላቸዉ አልያም በሕጋሚ #መንገድ ከሀገር መዉጣት ባለመቻላቸዉ የባህር ተጓዦችን አነሳዋቸዉ እንጂ ፖስፖርት አሰናድተዉ የቋጠሩትን ጥሪት ይዘዉ ልባቸዉ ቀዶሞ የሄደ አካላቸዉ ብቻ የቀረ ቤት ይፍጃቸዉ።

#ታዲያ ከዘገባዉ የተረዳሁት ስደትን ምርጫዉ ያላደረገ ትዉልድ ለመቅረፅ #ቤተክርስቲያን አሁንም #ስራ አለባት መልዕክቴ ነዉ።
#ብዙ ዋጋ የተከፈለበት #በኢትዮጵያ ትልቁ የመፅሐፍ #ቅዱስ መዝገበ ቃላት ተመረቀ።

በዘላለም #መንግስቱ ተጽፎ ከ1,300 ገጾች በላይ ተዋቅሮ ከ4,800 በላይ ቃላት ያካተተው ይህ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት የአብያተ ክርስቲያናት መሪዎች ፤ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና የጸሀፊው ወዳጆች በተገኙበት በCETC) ኢትዮጵያን ቴዎሌጂካል ኮሌጅ በድምቀት ተመርቆ ለአንባብያን ተሰራጭቷል።

በመድረኩ መጽሀፉን #ሙሉ በሙሉ ጽፎ ለማጠናቀቅ 23 ዓመታት እደፈጀ እና በዚህ ስራ #ውስጥ ከፍተኛ አስተዋጽዖ ላበረከቱ አካላት ምስጋናውን አቅርቧል።

ዘላለም መንግስቱ በንግግሩ ይህ መፅሐፍ ማለት እንደ "ማንኪያ" ነው። ዋናው ምግቡ ግን "መፅሐፍ ቅዱስ" ነው። ያለ ሲሆን መጽሐፍ ቅዱስን የበለጠ ለመረዳት የሚያግዝ መጽሐፍ እንደሆነ ተናግሯል።

አክሎም ምንም እንኳን እጨርሰዋለሁ ብዬ ባልጀምረውም ለብዙዎች የሚያግዝ በመሆኑ በእግዚአብሄር እርዳታ ተጠናቋል። ይህ መጽሐፍ በብዙ ውጣ ውረድ ውስጥ የተጻፈ እንደመሆኑ መጠን ይህ መጽሀፍ መጽሀፍ ብቻ ሳይሆን አደራም ጭምር ነው ሲል ተናግሯል።

በመድረኩ ንግግር ያደረጉ መሪዎች እረጅም አመታትን በትዕግት በመጻፍ ይህንን መጽሀፍ በዚህ ወቅት ለኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን በማበርከቱ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። በዚህ ዘመን ያለን አገልጋዮች ይህንን መጽሀፍ ባንጠቀምበት ፤ እና ባንሰራበት ለእኛ እዳ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ዘላለም መንግስቱ ከዚህ ቀደም መንፈስ ቅዱስ እና ካሪዝማዊ ቀውሶች ፤ እንዘምር ወይስ እንዝፈን ፤ ክርስቲያናዊ ኢትዮጵኝነት ፤ የሐሰተኞች እሳተ ጎመራ ፤ ትንቢተ ዕምባቆም ፤ የይሁዳ መልዕክትን ጨምሮ ወደ 20 የሚደርሱ መጽሀፍትን ለኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን አበርክቷል።

#የኢትዮጵያ ቃለ #ሕይወት #ቤተክርስቲያን #ዋና ጸሐፊ ዶ/ር ስምዖን ሙላት #እና የአብያተክርስቲያናት መሪዎች በጽሎት መጽሀፉን መርቀው ለንባብ እንዲበቃ በይፋ መርቀውታል።

The Christian News - የክርስቲያን ዜና በስፍራው ተገኝተን ሙሉ ዘገባውን አሰናዳንላችሁ። በቻናላችን ስም ለወንድም Zelalem Mengistu የተሰማንን እጅግ ትልቅ ደስታ እየገለጽን ሁላችሁም ትጠቀሙበት ዘንድ እናበረታታለን።