The Christian News
5.32K subscribers
3.06K photos
27 videos
720 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
#አንድ #አመት #ሆነዉ
#ቤተክርስቲያን እንስራ

#በኢትዮጵያ #አማኑኤል ህብረት በሐመር #ወረዳ ዲመካ አጥቢያ ቤተክርሲቲያን ምሽት ላይ የዛሬ አመት በዚህ ወር በጣለው ከባድ ዝናብ እና ንፋስ የቤተክርስቲያኒቱ አዳራሽ ወደቀች።

ይህ ከተፈጠር አንድ አመት ሆነዉ። በአከባቢው የሚገኙት የቤተክርስቲያኒቱ አባላት 75% አርብቶ አደር የሆኑ ሲሆን በወቅቱ የተጀመረዉ ድጋፍ በመቋረጡ እስካሁን አልተገነባችም።

አከባቢው ገና በወንጌል ያልተደረሰበት ከመሆኑም ባሻገር በአከባቢው ላሉ የወንጌል ጣቢያዎች እናት ቤተክርስቲያን በመሆኗ ፈተናውን አብዝቶብናል።

የዛሬ አመት ጥሪዉ እንደቀረበ የተወሰነ እርብርብ ለማድረግ የተሞከረ ቢሆንም ድጋፉ ተጠናክር ስላልቀጠለ ዛሬም አከባቢው የነበረችዉ እናት ቤተክርስቲያን የአምልኮ አዳራሽ የላትም።

አሁን ደግሞ ክረምት እየደረሰ በመሆኑ ምዕመናን እና መሪዎች ስጋታችዉ ጨምሯል።

ሁላችንም ተረባርበን ቤተክርስቲያንን እንስራ!!!

“በወንጌልም ማኅበረተኛ እሆን ዘንድ ስለ ወንጌል ሁሉን አደርጋለሁ።” 1ኛ ቆሮንቶስ 9፥23

ወንጌል ለሁሉም !!
ሁሉም ለወንጌል !!

#አድራሻ፦ ዲመካ ከሆስቴ በስተጀርባ
#Bank ACCOUNTS CBE-1000340167318
Emmanuel United Church of Ethiopia Dimeka Local Church (Hamer)

Phone Number:-
☎️ +2519111575204
📱+251 912169165
የመዘምራን የጋራ የምክክር #ጊዜ ተካሄደ፡፡

#በኢትዮጵያ #ሙሉ ወንጌል አማኞች #ቤተክርስቲያን #በአዲስ #አበባ እና አከባቢው ሶስት ክልሎች ውስጥ ከሚገኙ አጥቢያዎች የተሳተፉበት የጋራ የምክክር ጊዜ ተከናወነ።

በቀጠና ሁለት ሙሉወንጌል ቤተክርስቲያን በተካሔደዉ መረሀ ግብር መዘምራን፣ የሙዚቃ ተጫዋቾች እና የሶሎ ዘማርያን የተገኙ ሲሆን አገልግሎት የበለጠ ፍሬያማ ለማድረግ እንዲሁም በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ካሉ የቀድሞና አሁን በማገልገል ላይ ካሉ የሙሉ #ወንጌል መዘምራን #አባላት ጋር ሕብረትን ለማጠናከርና ያሉንን ጠንካራ እሴቶች ለማስቀጠል ቃል ተገብቷል ፡፡

በፕሮግራሙ የጎተራ ሙሉ ወንጌል አጥቢያ D መዘምራን እና የስድስት ኪሎ ሙሉ ወንጌል አጥቢያ አሳፍ መዘምራን ያገለገሉ ሲሆን ፓስተር ደበበ ለማ ( ጋሽ ደቤ )፣ ፓስተር ሳሙኤል ወንድሙ ከአትላንታ እና ፓስተር ኤርሚያስ ገ/መድህን ልዩ ልዩ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል፡፡
#ስላማችሁን #ጠብቁ መጋቢ ደሳለኝ አበበ

#Ethiopiaየመሠረተ #ክርስቶስ #ቤተክርስቲያን የወጣቶች አገልግሎት ክፍል ከፖይሜን ሚኒስትሪ #ጋር በመተባበር #ሠላም_ለወጣቶች_ወጣቶች_ለሠላም በሚል መሪ ሀሳብ ከሁሉም የሐገርቷ #ክፍል ከተውጣጡ የአሰልጣኞች ሥልጠና ለ41 #ወጣቶች #በኢትዮጵያ የሠላም ግንባታ ዙሪያ ሥልጠና እና ውይይት በቢሾፍቱ #ከተማ እያካሄዱ ይገኛል።

በመድረኩ የቤተክርስቲያኒቱ ፕሬዝዳንት መጋቢ ደሣለኝ አበበ #ሠላማችሁን ጠብቁ በማለት ወጣቶቹን አበረታተዋል።

#ሠላም_ነጣቂ_እንጂ_ጠባቅ_አጥታላች ያሉት ፕሬዝዳንቱ የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በበኩሏ በኢትዮጵያ እየተከሰተ ካለው የልዩነት ዘመቻ በተቃራኒ በመቆም ሁሉም ከጥላቻ ፣ ከወቃሽነትና ነቃሽነት ተራ ወጥቶ የሠላም ሰባኪ እንዲሆን በአጽንኦት ተናግሯል።

ውይይቱ #ነገ እንደሚጠናቀቅ ተገልጿል።
#በድል #ተጠናቋል
#እግዚአብሔር #ይመስገን 🙏🙏🙏

#በኢትዮጵያ ወንጌላውያውያን አብያተ ክርስቲያናት #ሕብረት የ2016ዓ.ም #አዲስ #ዓመት ምክንያት በማድረግ በ "አዲስ አበባ እስታዲየም" ሲካሄድ የቆየው #ልዩ የበዓል #ፕሮግራም በድል ተጠናቋል።

በድጋሜ #እንኳን #አደረሳችሁ

#መልካም #አዲስ#አመት እንዲሆንላችሁ እንመኛለን።

Photo 📷 Hossana Photo & Video Production #እናመሰግናለን
#እንኳን #ደስ #አሎት 🙏🙏

#በኢትዮጵያ #ቤተክርስቲያን ወንጌልን በቃልና በኑሮ ምሳሌ በመሆን ያገለገሉት #የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት ፕሬዝደንት መጋቢ ጻድቁ አብዶ እዉቅና ተሰጣቸው።

መሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን 92ኛው ጠቅላላ የመሪዎች ጉባኤ በቢሾፍቱ ከተማ በቤተክርስቲያኗ ኮሌጅ ቅጥር ግቢ እየተካሄደ ይገኛል።

በዚህም ጉባኤ በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ወንጌልን በቃልና በኑሮ ምሳሌ በመሆን ያገለገሉ ቀደምት አባቶች #የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት ፕሬዝደንት መጋቢ ጻድቁ አብዶን ጨምሮ የመሠረተ ክርስቶስና የሌሎች ቤተዕምነት አገልጋዮች ዕውቅና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

በጉባኤው ላይ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች ካዎንስል ጠቅላይ ጸሐፊ ቄስ ደረጄ ጀምበሩን ጨምሮ የተለያዩ የቤተዕምነት መሪዎች ተገኝተዋል።

በጉባኤ ላይ በተለይ መልኩ አስከ ዛሬ እውነተኛውን የእግዚአብሔርን ቃል እውነት በመስበካቸው በመልካም ምሣሌነታቸው ከተመሰከረላቸው መካከል ለአሁኑ 10 ከሌሎች ቤተዕምነቶች 11 ደግሞ ከመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በአጠቃላይ 21 አገልጋዮች በጉባኤ ፊት እውቅና ተበርክቶላቸዋል።

ይህ የእውቅና መርሃግብር ወደፊት በስፋት እንደሚቀጥል የቤተክርስቲያኒቱ ፕሬዚዳንት መጋቢ ደሣለኝ አበበ ገልፀዋል።
#ፍትህ ግን ምንድነው? 🤔 የትስ #ነው ያለው? 🤔
#እኛ ጥያቄያችን #አንድ እና ግልጽ  ነው።

#የቤተክርስቲያናችን_ንብረት_ይመለስልን!!! 🙏🙏🙏

37 ዓመታት በእንባ እና በጸሎት የጸሎት ቤቷን ለማስመለስ ፍትሕን ፍለጋ የተነከራተተችው #ቤተክርስቲያን ዛሬም ፍትህን ፍለጋ ላይ ነች።

የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ከ1950ዎቹ #መጀመሪያ ጀምሮ በተለይ ትምህርትን ከማስፋፋት አንጻር #ለሀገር እና #ለሕዝብ ጥቅም ላበረከተችው አስተዋጽዖ በወቅቱ የነበረው የመንግስት ስረዓት ከምስጋና ይልቅ ት/ቤቶቻችንና ጸሎት ቤቶቻችንን መውረስ ቀሏቸዋል።

በደርግ #መንግስት በግፍ የተወረሰው የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የኦሎምፒያው ጸሎት ቤታችን በአዲስ አበባ የመጀመሪያው የመሰረተ ክርስቶስ የማምለኪያ ስፍራ ነው።

#ይህ የመሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ንብረት #ማለት የሙሉ #ወንጌል ምዕመን እና የሙሉ ወንጌል ቤ/ክ ንብረት ማለት ነው። የመካነ ኢየሱስ ማለት ደግሞ የቃለ ሕይወት ነው። የቃለ ሕይወት ማለት የሕይወት ብረሃን የሕይወት ብረሃን ማለት የገነት የገነት ማለት የጉባኤ እግዚአብሔር ... በአጠቃላይ የወንጌል አማኞች #በሙሉ ነው።

ይህ ከ66 ዓመት በላይ የተሻገረው የጸሎት ስፍራ ንብረት ብቻ አይደለም ይልቁንም ለወንጌል የተሰደዱ ፤ ለወንጌል ዋጋ የከፈሉ የወንጌላውያን አማኞች #ታሪክ እና ቅርስም ጭምር ነው።

በ1943ዓ.ም የተመሰረተችው የመሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ከቀደምት የወንጌል አማኞች ቤተዕምነት መካከል አንዷ ብቻ ሳትሆን እውነተኛው የክርስቶስ ወንጌል ለአዲሱ #ትውልድ  እንዲሸጋገር ከ70 ዓመት በላይ #በኢትዮጵያ በሚመችም በማይመችም ሁኔታ #ውስጥ ስትሰራ ቆይታለች።

#ዛሬ ላይ መዲናችን #አዲስ አበባ ከሌሎች #አለም ላይ ከሚገኙ ከተሞች መካከል ለመወዳደር ሌት ተቀን እየተጋች ትገኛለች። በዚህ ውስጥ ታዲያ በከፊሉ አዳዲስ ሲገነባ በከፊሉ ለተቸገሩት ሲደረስ በሌላ አቅጣጫ ግን እንሳኩን ያልተመለሱ #ብዙ ጥያቄዎች እንዳሉ የአደባባይ ሚስጥር ነው።

ታዲያ በመዲናችን #ዛሬም ፍትህን ከሚጠይቁ ተቋማት መካከል አንጋፋዋ የመሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አንዷ ነች።

ስለዚህ ህጋዊ የሆነው የቤተክርስቲያን ታሪክ ፤ ቅርስ እና ንብረታችን የሆነው የጸሎት ቤቶቻችን ይመለሱልን የማያቋርጥ ጥያቄያችን ነው!!!

ይህ #መልዕክት የሚደረሳችሁ ምዕመናን እና ኢትዮጵያውያን በሙሉ የቤተክርስቲያናችን ንብረት እስኪመለስ ድረስ ሁላችንም #SharePost በማድረግ ለሁሉም እናድርስ!!!

The Christian News - የክርስቲያን ዜና በዚህ ዙሪያ ተጨማሪ ዘገባዎችን በተለያየ ጊዜ ይዘን የምንመለስ ይሆናል።

#share #share #share #share
#የኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናት ምክር #ቤት ሊቋቋም ነው ተባለ።

የኢትዮጵያ #ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን፣ የኢትዮጵያ #ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን እና የኢትዮጵያ #ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ናቸው በኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤትን ለማቋቋም የተስማሙት።

ምክር ቤቱን ለማቋቋም ያስፈለገው፣ በሃገሪቱ አስፈላጊ የሆነውን አስቸኳይ ሰብዓዊ ድጋፍ፣ #ሰላም እና ማህበራዊ መስተጋብርን ለማጠናከር መሆኑ ተገልጿል።

#በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት #ወደ 20 ሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎች በግጭትና ተፈጥሮአዊ ችግሮች ሳቢያ አስቸኳይ ሰብዓዊ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል።

በአብያተ ክርስቲያናቱ መሪዎች መካከል ከህዳር 17-20 ድረስ ሰፊ ውይይት ሲካሄድ ቆይቷል ነው የተባለው።

ከስምምነቱ የተገኘ ቃለ ጉባኤ እንደሚያሳየው፣ ህብረቱ የተነጠሉ ተቋማት ቡድን ብቻ እንዲሆን የታሰበ አይደለም ይላል። ነገር #ግን ደግሞ ማንም አካል ያለ መመዘኛ መጥቶ የሚገባበትም አይሆንም ሲል ያስቀምጣል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ወክለው አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) ፣ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስን ወክለው ቄስ ዮናስ ዮናስ ይገዙ (ዶ/ር)፣ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያንን ወክለው ካርዲናል ብርሃነ ኢየሱስ ሱራፌል ተፈራርመዋል።

ህብረቱን #ወደፊት ለማስኬድ ይረዳ ዘንድ ግብረ ሃይልም ተቋቁሟል።

“እውን የሆነው የኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት፣ ለረጅም አመታት በውይይት ላይ የነበረ ነው፣ ለዚህ ስትሰሩ የነበራችሁ መሪዎች፣ ምስጋና ይገባቸዋል” ሲሉ ቄስ ዶ/ር ዮናስ ይገዙ ምስጋናቸውን ችረዋል።

አክለው #አሁን በክርስቶስ የምናምን ሁላችን በአንድ #ጥላ ስር ሆነን የህዝባችንን የሰላም፣ ፍትህ እና እርቅ ጥሪ በጋራ መልስ የምንሰጥበት አጋጣሚ ነው ብለዋል።
የመጽሃፍ ቅዱስ ሳምንት ሊያካሂድ ነው።

#በኢትዮጵያ የመጽሃፍ ቅዱስ ማህበር አዘጋጅነት የሚካሄደዉ የመፅሐፍ ቅዱስ ሳምንት እና የቅዱሳት መጻህፍት አውደ ርዕይ ከመጋቢት 16-21 የሚቆይ ሲሆን በኢትዮጵያ ስካይ ላይት ሆቴል ነው የሚካሄደው።

ማህበሩ በእነዚህ ቀናት ያለፉትን 98 ዓመታት የሰራቸውን ስራዎች ለታዳሚያን እንደሚያቀርብና ራሱን የሚያስተዋውቅበት መድረክ እንደሚሆን ይጠበቃል።

#ዛሬ ስካይላይት ሆቴል የነበረውን ጋዜጣዊ መግለጫ የማህበሩ ቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር ተስፋጽዮን ደለለኝ፣ የማህበሩ ዋና ጸሃፊ አቶ ይልማ ጌታሁን እና መጋቢ አሸብር ከተማ በጋራ ሰጥተዋል።

መጽሃፍ #ቅዱስ ግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ፣ ክርስቲያኑን ስለ መጽሃፍ ቅዱስ ንባብ ማነቃቃት፣ በመጽሃፍ ቅዱስ ትርጉም ላይ የሚሰሩ አብያተ ክርስቲያናትን በተዛማጅ ስራዎች ላይ ማስተባበር፣ የወንጌል ስብከትን ማበረታት፣ ለአሁኑ ትውልድ የመጽሃፍ ቅዱስን አደራና ሃላፊነት ማስተላለፍ እና መጽሃፍ ቅዱስን ከአደጋዎች መጠበቅ በሳምንቱ ከሚኖሩ ክንውኖች መካከል ናቸው።

ሌላው ማህበሩ ከመጋቢት 16-21 ድረስ የቅዱሳት መጻህፍት አውደ ርዕይ ያከናውናል። በእነዚሁ ቀናቶች የውይይት መድረኮች፣ ሴሚናሮች እና ልዩ ዝግጅቶች ይካሄዳሉ።

ትውልዱን ስለ ቅዱሳት መጻህፍት እንዲያውቅ ማድረግ፣ የህትመት ውጤቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለህዝብ ማድረስ እና ማህበሩን ከህዝብ ጋር ማስተዋወቅ በአውደ ርዕይው የሚከናወኑ ዋና ዋና ስራዎች ናቸው።

የኢትዮጵያም ይሁን የአለም አቀፉ መጽሃፍ ቅዱስ ማህበር እስከ ቅርብ ጊዜ የመጽሃፍ ቅዱስ ተደራሽነት ላይ ብቻ ሲሰራ የቆየ ሲሆን፣ አሁን ግን ተጽኖ ፈጣሪነቱም ላይ መስራት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል ብለዋል።
#በኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል የተዘጋጀ የፀሎት መርሃ ግብር በመስቀል አደባባይ እየተካሄደ ነው።

ለሀገር ሰላምና አንድነት እየተካሄደ በሚገኘው የጸሎትና ምስጋና መርሃ ግብር በኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ስር ያሉ የተለያዩ ቤተክርስቲያናት መሪዎች፣ አባቶች፣ ዘማሪያን፣ መጋቢዎች እና ሌሎችም ተገኝተዋል።
#ደረሰ ደረሰ ደረሰ ...

የመጽሃፍ #ቅዱስ ሳምንት

#በኢትዮጵያ የመጽሃፍ ቅዱስ ማህበር አዘጋጅነት የሚካሄደዉ የመፅሐፍ ቅዱስ ሳምንት #እና የቅዱሳት መጻህፍት አውደ ርዕይ ከመጋቢት 16-21 በኢትዮጵያ ስካይ ላይት ሆቴል።

ክርስቲያኑን #ስለ መጽሃፍ ቅዱስ ንባብ ማነቃቃት፣ በመጽሃፍ ቅዱስ ትርጉም ላይ የሚሰሩ አብያተ ክርስቲያናትን በተዛማጅ ስራዎች ላይ ማስተባበር፣ የወንጌል ስብከትን ማበረታት፣ ለአሁኑ ትውልድ የመጽሃፍ ቅዱስን አደራና ሃላፊነት ማስተላለፍ እና መጽሃፍ ቅዱስን ከአደጋዎች መጠበቅ በሳምንቱ ከሚኖሩ ክንውኖች መካከል ናቸው።

ትውልዱን ስለ ቅዱሳት መጻህፍት እንዲያውቅ ማድረግ፣ የህትመት ውጤቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለህዝብ ማድረስ እና ማህበሩን ከህዝብ ጋር ማስተዋወቅ በአውደ ርዕይው የሚከናወኑ ዋና ዋና ስራዎች ናቸው።

#ሁላችሁም ተጋብዛችኋል።

መግቢያ #በነፃ ...
#መቀሌ

#ታላቁ ተልዕኮ ኢትዮጵያ 10 ቢሮውን በትግራይ መቀሌ ከፈተ።

ግሬት ኮሚሽን ከ1972 ዓ.ም. ጀምሮ #በኢትዮጵያ የወንጌል ስራን ሲሰራ ቆይቷል። በአሁኑ ወቅት በአዳማ፣ ባህርዳር፣ ሃረር፣ ሃዋሳ፣ ጅማ፣ ነቀምቴ፣ አርባ ምንጭ፣ ሆሳዕና እና አምቦ የአካባቢ ቢሮዎችን አቋቁሞ በየአካባቢው ከሚገኙ ሚኒስትሪዎችና አብያተ ክርስቲያናት ጋር ወንጌልን እየሰራ ይገኛል።

ግሬት ኮሚሽን #ኢትዮጵያ ሚኒስትሪ፣ የጂሰስ ፊልምን በ74 የሃገር ውስጥ ቋንቋዎች በማስተርጎምና በ10 ሃገራት ውስጥ ኢንዲጂተስ በተሰኘ የቴክኖሎጂ ማህበረሰብን በመፍጠር በኢትዮጵያና ከኢትዮጵያ ውጪም ወንጌልን እየሰራ ይገኛል።

ከጦርነት መልስ የወንጌል ስርጭት ማዕከል በትግራይ የተከፈተውን ይሄንን ቢሮ ያስተባበረው ወንድም #ካሳሁን_ሰዒድ ሲሆን በመድረኩ እውቅና ተሰጥቶታል።

ወንድም ካሳሁን መቀሌ እና መላውን ትግራይ ላለፉት 10 ዓመታት በወንጌል ለመድረስ ሲያገለግል ቆይቷል።

ምንጭ፣ GCMEthiopia

ዜናውን ከወደዱት Like
ማንኛውም አስተያየት እና ጥያቄ ካሎት Comment
በፍጥነት ለወዳጆ ለማካፈል #share ያድረጉ
#ብዙ ዋጋ የተከፈለበት #በኢትዮጵያ ትልቁ የመፅሐፍ #ቅዱስ መዝገበ ቃላት ተመረቀ።

በዘላለም #መንግስቱ ተጽፎ ከ1,300 ገጾች በላይ ተዋቅሮ ከ4,800 በላይ ቃላት ያካተተው ይህ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት የአብያተ ክርስቲያናት መሪዎች ፤ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና የጸሀፊው ወዳጆች በተገኙበት በCETC) ኢትዮጵያን ቴዎሌጂካል ኮሌጅ በድምቀት ተመርቆ ለአንባብያን ተሰራጭቷል።

በመድረኩ መጽሀፉን #ሙሉ በሙሉ ጽፎ ለማጠናቀቅ 23 ዓመታት እደፈጀ እና በዚህ ስራ #ውስጥ ከፍተኛ አስተዋጽዖ ላበረከቱ አካላት ምስጋናውን አቅርቧል።

ዘላለም መንግስቱ በንግግሩ ይህ መፅሐፍ ማለት እንደ "ማንኪያ" ነው። ዋናው ምግቡ ግን "መፅሐፍ ቅዱስ" ነው። ያለ ሲሆን መጽሐፍ ቅዱስን የበለጠ ለመረዳት የሚያግዝ መጽሐፍ እንደሆነ ተናግሯል።

አክሎም ምንም እንኳን እጨርሰዋለሁ ብዬ ባልጀምረውም ለብዙዎች የሚያግዝ በመሆኑ በእግዚአብሄር እርዳታ ተጠናቋል። ይህ መጽሐፍ በብዙ ውጣ ውረድ ውስጥ የተጻፈ እንደመሆኑ መጠን ይህ መጽሀፍ መጽሀፍ ብቻ ሳይሆን አደራም ጭምር ነው ሲል ተናግሯል።

በመድረኩ ንግግር ያደረጉ መሪዎች እረጅም አመታትን በትዕግት በመጻፍ ይህንን መጽሀፍ በዚህ ወቅት ለኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን በማበርከቱ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። በዚህ ዘመን ያለን አገልጋዮች ይህንን መጽሀፍ ባንጠቀምበት ፤ እና ባንሰራበት ለእኛ እዳ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ዘላለም መንግስቱ ከዚህ ቀደም መንፈስ ቅዱስ እና ካሪዝማዊ ቀውሶች ፤ እንዘምር ወይስ እንዝፈን ፤ ክርስቲያናዊ ኢትዮጵኝነት ፤ የሐሰተኞች እሳተ ጎመራ ፤ ትንቢተ ዕምባቆም ፤ የይሁዳ መልዕክትን ጨምሮ ወደ 20 የሚደርሱ መጽሀፍትን ለኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን አበርክቷል።

#የኢትዮጵያ ቃለ #ሕይወት #ቤተክርስቲያን #ዋና ጸሐፊ ዶ/ር ስምዖን ሙላት #እና የአብያተክርስቲያናት መሪዎች በጽሎት መጽሀፉን መርቀው ለንባብ እንዲበቃ በይፋ መርቀውታል።

The Christian News - የክርስቲያን ዜና በስፍራው ተገኝተን ሙሉ ዘገባውን አሰናዳንላችሁ። በቻናላችን ስም ለወንድም Zelalem Mengistu የተሰማንን እጅግ ትልቅ ደስታ እየገለጽን ሁላችሁም ትጠቀሙበት ዘንድ እናበረታታለን።
የቤተክርስቲያን ማዕከል መዉሰድ ሕጋዊነት የሌለዉ እና ተገቢ አይደለም። ቄስ ዶ/ር ቶሎሳ ጉዲና

በኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ኩሪፍቱ ማዕከል ዙሪያ ብዙ የቤተክርስቲያን መሪዎች ዝምታቸዉን ሰብረዉ ለቤተክርስቲያን ድምፅእየሆኑ ነዉ።

በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ተወዳጅ እና አንጋፋ ከሆኑ መሪዎች መካከል ቄስ ዶ/ር ቶሎሳ ጉዲናም በዛሬዉ እለት አስተያየታቸዉን የሰጡ ሲሆን #በኢትዮጵያ #መልካም የሆነ ነገር እየተሰራ ስለሆነ ብዙዎች የራሳቸዉን ቦታ ሁሉ ሰጥተዋል።

#ነገር #ግን ያለ ተገቢ ሁኔታ ከ35 ዓመት በላይ የቤተክርስቲያን ንብረት የሆነዉን የቃለ ሕይወት ቦታ በጎልበት ማጠር እና መዉሰድ ተገቢ አይደለም ሲሉ የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር የወሰደዉን እርምጃ ተገቢ እንዳልሆነ ተናግረዋል።

በሀይል ይህንን የቤተክርስቲያን ንብረት መዉሰድ ተገቢ አይደለም ያሉት ቄስ ቶሎሳ ይህንን ማድረግ #ቤተክርስቲያን ለሀገር ያበረከተችዉን አስተዋፅዖ መካድ ነዉ ብለዋል።

ቄስ ቶሎሳ አክለዉም የቤተክርስቲያን ማዕከል መዉሰድ ሕጋዊነት የሌለዉ እና ተገቢ አይደለም ሲሉ ተናግረዋል።