The Christian News
5.06K subscribers
3.02K photos
23 videos
712 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
የመዘምራን የጋራ የምክክር #ጊዜ ተካሄደ፡፡

#በኢትዮጵያ #ሙሉ ወንጌል አማኞች #ቤተክርስቲያን #በአዲስ #አበባ እና አከባቢው ሶስት ክልሎች ውስጥ ከሚገኙ አጥቢያዎች የተሳተፉበት የጋራ የምክክር ጊዜ ተከናወነ።

በቀጠና ሁለት ሙሉወንጌል ቤተክርስቲያን በተካሔደዉ መረሀ ግብር መዘምራን፣ የሙዚቃ ተጫዋቾች እና የሶሎ ዘማርያን የተገኙ ሲሆን አገልግሎት የበለጠ ፍሬያማ ለማድረግ እንዲሁም በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ካሉ የቀድሞና አሁን በማገልገል ላይ ካሉ የሙሉ #ወንጌል መዘምራን #አባላት ጋር ሕብረትን ለማጠናከርና ያሉንን ጠንካራ እሴቶች ለማስቀጠል ቃል ተገብቷል ፡፡

በፕሮግራሙ የጎተራ ሙሉ ወንጌል አጥቢያ D መዘምራን እና የስድስት ኪሎ ሙሉ ወንጌል አጥቢያ አሳፍ መዘምራን ያገለገሉ ሲሆን ፓስተር ደበበ ለማ ( ጋሽ ደቤ )፣ ፓስተር ሳሙኤል ወንድሙ ከአትላንታ እና ፓስተር ኤርሚያስ ገ/መድህን ልዩ ልዩ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል፡፡
#ነገ #በአዲስ #አበባ #እስታዲየም
#ኑ አዲስ አመትን አብረን እንቀበል።
ከማለዳዉ 12:00 ጀምሮ

መስከረም 1 በአዲስ አበባ እስታዲየም የአምልኮ ፕሮግራም ይካሄዳል።

በኢትዮጵያ ወንጌላውያውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት የ2016ዓ.ም #አዲስ #ዓመት ምክንያት በማድረግ በ "አዲስ አበባ እስታዲየም" ልዩ የበዓል #ፕሮግራም ይካሔዳል።

የጳጉሜ ወር በሙሉ ለሃገራችን ሰላም እና ለምድራችን እረፍት እንዲሆን ጸሎት ሲደረግ እንደ ነበር ይታወሳል።

#ነገ በመስከረም 1/2016ዓ.ም በአዲስ አመት የጾም ጸሎቱ ማጠቃለያ እና የጋራ የአምልኮ እና የምስጋና መረሃ ግብር በአዲስ አበባ እስታዲየም የሚደረግ ሲሆን በመረሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው አብረን አዲስ ዓመትን እንቀበል።