The Christian News
5.37K subscribers
3.08K photos
29 videos
730 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
ቤተክርስቲያን በአካል ከመገኘት ይልቅ የቤተክርስቲያን አገልግሎቶችን በቀጥታ ስርጭት መመልከት ተወዳጅ እንደሆነ አንድ ጥናት አመለከተ።

በአሜሪካ የፕሮቴስታንት ቤተ ክርስቲያን የሚገለገሉ ምዕመናን ላይ የተደረገ አዲስ ጥናት እንደሚያሳየው በአካል ከመገኘት ይልቅ በቀጥታ ስርጭት የሚተላለፉ የቤተ ክርስቲያን አገልግሎቶችን መመልከት በጣም ተወዳጅ አማራጭ እንደሆነ ዘግቧል።

ዘገባው 40% የሚጠጉት ሰዎች ባለፈው ዓመት ውስጥ ከአምስት ጊዜ በላይ በቀጥታ ስርጭት ተመልክተዋል ሲል Relevant መጽሔት ዘግቧል።

የሕዝብ አስተያየት መስጫው የተካሄደው በላይፍዌይ ጥናት በፈረንጆቹ ከሴፕቴምበር 19-29/2022 እንደሆነ የተጠቀሰ ሲሆን 1,002 ሰዎች ተሳትፈውበታል ተብሏል።

ጥናቱ “ባለፈው ዓመት በአካል ቤተክርስቲያን ከመገኘት ይልቅ በቀጥታ ስርጭት በቪዲዮ ምን ያህል ጊዜ ተመልክተሃል?” የሚል ሲሆን ጥናቱ ከ2019 የኮቪድ ወረርሽኝ በኋላ ሰዎች በአካል ሄደው ከመሳተፍ ይልቅ የቀጥታ ስርጭትን ምርጫቸው አድርጓል ያለ ሲሆን በዚህም ሴቶችን እና ወንዶችን ጨምሮ እድሜያቸው ከ18-65 ዓመት የሆኑ ሰዎች አሳትፊያለሁ ብሏል።

ምልከታ :- በቤተክርስቲያን ዉስጥ የሚደረገዉ የቅዱሳን ሕብረት መፅሐፍ ቅዱሳዊ እና በቅዱሳን መካከል ያለዉን ግንኙነት የሚያጠናክር የተወሰነ የደከሙትን ደግሞ እንዲበረቱ የሚያደርግ ነዉ።

ዛሬ ዛሬ የምዕራባውያን ቤተክርስቲያን አዳዲስ ነገሮች እየፈጠሩ ምዕመናን ከቤተክርስቲያን ሕብረት እንዲቀሩ የሚያደርግ ይመስለናል።

ይህ የቀጥታ #ስርጭት የአገልግሎት አይነት አሁን አሁን የኢትዮጵያ #ቤተክርስቲያን ዉስጥ እየተለመደ መጥቷል። ዛሬ ላይ በአካል ያልተገኙትን ተደራሽ ለማድረግ #እጅግ መልካም ቢሆንም #ነገ ምን እንደሚፈጠር መገመት ይከብዳል።
#ስላማችሁን #ጠብቁ መጋቢ ደሳለኝ አበበ

#Ethiopiaየመሠረተ #ክርስቶስ #ቤተክርስቲያን የወጣቶች አገልግሎት ክፍል ከፖይሜን ሚኒስትሪ #ጋር በመተባበር #ሠላም_ለወጣቶች_ወጣቶች_ለሠላም በሚል መሪ ሀሳብ ከሁሉም የሐገርቷ #ክፍል ከተውጣጡ የአሰልጣኞች ሥልጠና ለ41 #ወጣቶች #በኢትዮጵያ የሠላም ግንባታ ዙሪያ ሥልጠና እና ውይይት በቢሾፍቱ #ከተማ እያካሄዱ ይገኛል።

በመድረኩ የቤተክርስቲያኒቱ ፕሬዝዳንት መጋቢ ደሣለኝ አበበ #ሠላማችሁን ጠብቁ በማለት ወጣቶቹን አበረታተዋል።

#ሠላም_ነጣቂ_እንጂ_ጠባቅ_አጥታላች ያሉት ፕሬዝዳንቱ የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በበኩሏ በኢትዮጵያ እየተከሰተ ካለው የልዩነት ዘመቻ በተቃራኒ በመቆም ሁሉም ከጥላቻ ፣ ከወቃሽነትና ነቃሽነት ተራ ወጥቶ የሠላም ሰባኪ እንዲሆን በአጽንኦት ተናግሯል።

ውይይቱ #ነገ እንደሚጠናቀቅ ተገልጿል።
#ነገ #በአዲስ #አበባ #እስታዲየም
#ኑ አዲስ አመትን አብረን እንቀበል።
ከማለዳዉ 12:00 ጀምሮ

መስከረም 1 በአዲስ አበባ እስታዲየም የአምልኮ ፕሮግራም ይካሄዳል።

በኢትዮጵያ ወንጌላውያውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት የ2016ዓ.ም #አዲስ #ዓመት ምክንያት በማድረግ በ "አዲስ አበባ እስታዲየም" ልዩ የበዓል #ፕሮግራም ይካሔዳል።

የጳጉሜ ወር በሙሉ ለሃገራችን ሰላም እና ለምድራችን እረፍት እንዲሆን ጸሎት ሲደረግ እንደ ነበር ይታወሳል።

#ነገ በመስከረም 1/2016ዓ.ም በአዲስ አመት የጾም ጸሎቱ ማጠቃለያ እና የጋራ የአምልኮ እና የምስጋና መረሃ ግብር በአዲስ አበባ እስታዲየም የሚደረግ ሲሆን በመረሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው አብረን አዲስ ዓመትን እንቀበል።
#መንገድ #ዝግ #ነዉ

#የኢትዮጲያ #ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል በመስቀል አደባባይ የሚያከናውኑት የፀሎት ፕሮግራም ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የተወሰኑ መንገዶችን ለተሸከርካሪ ዝግ እንደሚደረጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ

አሽከርካሪዎች እንደ ተለመደው ለትራፊክ ፖሊሶች ትዕዛዝ ተባባሪ እንዲሆኑ ተጠይቋል፡፡

#ነገ ዕሁድ መጋቢት 8 ቀን 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ በመስቀል አደባባይ ከሰዓት በሗላ ከቀኑ 7፡30 እስከ 12፡00 ሰዓት ድረስ የኢትዮጲያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል የፀሎት መርሐ-ግብር ስለሚያከናውኑ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚደረጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

አሽከርካሪዎች መረጃው አስቀድሞ ኖሯቸው ሌሎች አማራጭ መንገዶችን በመጠቀም ለትራፊክ ፖሊስ አባላት ትዕዛዝ ተባባሪ እንዲሆኑ ፖሊስ ጥሪውን እያስተላለፈ፡-

• ከቅዱስ ኡራኤል አደባባይ #ወደ መስቀል አደባባይ ለሚጓዙ ተሽከርካሪዎች ኡራኤል አደባባይ ላይ

• ከቦሌ ጌቱ ኮሜርሻል አቅጣጫ ወደ መስቀል አደባባይ ኦሎምፒያ አደባባይ በታች እና በላይ እንዲሁም ግራና ቀኝ

.የቀድሞው አራተኛ ክፍለጦር (ጥላሁን አደባባይ ላይ )

• ከለገሀር መብራት ወደ መስቀል አደባባይ ለሚጓዙ ለገሀር መብራት ላይ

• ከሀራምቤ መብራት ወደ መስቀል አደባባይ ሃራምቤ መብራት ላይ

• ከብሔራዊ ቤተ መንግስት ወደ መስቀል አደባባይ ብሔራዊ ቤተ መንግስት አጠገብ ዕሁድ መጋቢት 8/16 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡ 00 ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ መንገዶቹ ለጊዜው ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ፡፡

ፕሮግራሙ በሚከበርበት ዙሪያ እና በአካባቢው በግራና በቀኝ ለረጅምም ሆነ ለአጭር ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጨምሮ ገልጿል፡፡
152 #ሰዎች ተጠመቁ!!!

#በመሠረተ #ክርስቶስ #ቤተክርስቲያን 152 ሰዎች የውሃ ጥምቀት ወስደው #ወደ ቤተክርስቲያን ተቀላቀሉ ።

ቦሰት አካባቢ 62 ሰዎች እና በመካከለኛው ሥምጥ ሸለቆ ዝዋይ አጥቢያ አማካኝነት ደግሞ 90 ሰዎች በአጠቃላይ 152 ወገኖች በዛሬው ዕለት የውሃ ጥምቀት ወስደው ወደ ቤተክርስቲያን ተቀላቅለዋል ።

በተጨማሪም #ነገ ዕለት በደቡብ አዳማ ክልል ሌሎች 40 ሰዎች የውሃ ጥምቀት እንደሚወስዱ ይጠበቃል።

በአጠቃላይ በመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን "#አጀንዳ28 19" ወይም "#አጀንዳችን_ወንጌል" የሚለውን እንደ መራህ በመከተል በዓመት እያንዳንዱ አጥቢያ በቁጥር 10% እድገት እንዲያሳዩ በተቀመጠው አቅጣጫ አካል መሆኑ ወደፊትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የኮሚኒኬሽን ቢሮ አሳውቋል።

#ወንጌል ካልሰራን #ምንም አልሰራንም።
#እንዴት ልንሆን እንችላለን? #ነገ #ምን ይሆናል ?
ጊዜው የማይገቡን ነገሮች የሚነገሩበት ነው።

አለም የምትለው ሌላ ነው እኛ የምንለው ደግሞ #እግዚአብሔር አለልን ነው።

ጠዋትና #ማታ በሚዲያ የምንሰማው #አለም በብዙ ፍረሃት #ውስጥ ያለችበት #ጊዜ ነው።

#እምነት ሁኔታን መካድ አይደለም ከሁኔታ በላይ የሆነውን #አምላክ ከፍ ማድረግ ነው።

ምንዛሬ ከፍ አለ ዝቅ አለ። ኑሮ ተወደደ እረከሰ ስለዘመኑ የሚወራው አብዛኛው አይገባንም።

#እኔ ግን እንዲህ እላችኋለው ለእግዚአብሔር ዘመን ከፍ አይልም ዝቅ አይልም። ኑሮ ስለረከሰ አልኖርንም ኑሮ ስለተወደደ አንጠፋም።

በሰው ካልኩሌሽን አልኖርንም አሁንም አንኖርም። ምንም እንኳን ምድረበዳ ቢሆን #ኢየሱስ አለ።

ዘመኑ አስጨናቂ ነው ? እውነት ነው ግን ኢየሱስ አለ።