The Christian News
5.37K subscribers
3.08K photos
29 videos
730 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
የስኬታማ #ጋብቻ #ሚስጥር (ቀመር) #ምንድነዉ? 🤔

በአይነቱ #ልዩ የሆነ ለባለትዳሮች #ብቻ የተዘጋጀ #ድንቅ ፕሮግራም

በሳፋየር አዲስ #ሆቴል ከሐምሌ 24-28 ከምሽት 11:00 - 2:00 ሰዓት
ሐምሌ 29 ሙሉ ቀን

👉 በጥንዶች መካከል የሚፈጠሩ ተግዳሮቾችን የሚመክት ጋብቻን #እንዴት መገንባት ይቻላል።

👉 የጋብቻ #መሰረታዊ ተግዳሮት

👉 #ገንዘብ በጋብቻ ዉስጥ ያለዉ ድርሻ #ምን መምሰል አለበት?

👉 #ስራ እና ትዳርን በሚዛናዊነት መምራት

አዘናጅ :- ጎጆዬ የጋብቻ ሪፎርሜሽን ሴንተር ከCBMC ሚኒስትሪ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር

#ይታደሙ
#ትዳሮን_ይስሩ!!

ለመመዝገብ እና ለበለጠ #መረጃ

0911136520
0911642595

ይደዉሉልን!!!

"ከስልጠናው የሚገኘው ትርፍ የቤተሰብ ቅጥር አዳሽ ግብረ-ሰናይ ድርጅት ለሚያግዛቸው ችግረኛ ጥንዶች የሚውል ይሆናል፡፡"
#ሰው ሸሽቶ #ቤተክርስቲያን ሲገባ #እንዴት ይገደላል? አገዳደሉ አሳቃቂ ነው። ቄስ ዶ/ር ዮናስ ይገዙ

የመካነ ኢየሱስ ፕሬዝደንት በዚህ ወረ በመካነኢየሱስ ምዕመናን ላይ የተፈጸመውን ግድያ አስመልክተው በሰጡት ማብራሪያ #መጽሐፍ #ቅዱስ ግምባራቸው #ላይ ነበር የተገደሉት ምዕመናን ከአንድ #ቀን በኋላ ነው የተገኙት ብለዋል።

ፕሬዝደንቱ አክለው #እንደ ቤተክርስቲያን መረጃው እስኪጣራ ነው ይፋ ያላደረግነው ያሉ ሲሆን በቤተክርስቲያን አካሄድ የቻልነውን ያህል ሄደናል ያሉ ሲሆን #መንግስት የሕዝብ የድህንነት #ጉዳይ በእጁ ነውና አሁንም #ተስፋ የምናደርገው መንግስት ገዳዮችን ለፍርድ እንደሚያቀርብ እናምናለን ሲሉም ተናግረዋል።

#ይህ ጥቃት በማን ነው የተፈጸመው ?

ከአደጋው የተረፉት ትክክለኛው ገዳዮች #ምን እንዳደረጉ እነማን እንደሆኑ ያውቃሉ። #ነገር #ግን ለደህንነታቸው ስለሚሰጉ ለመናገር ፍላጎት የላቸውም። መንግስት ግን ተከታትሎ ለፍርድ እንዲያቀርብልን እንጠይቃለን።
#እንዴት ልንሆን እንችላለን? #ነገ #ምን ይሆናል ?
ጊዜው የማይገቡን ነገሮች የሚነገሩበት ነው።

አለም የምትለው ሌላ ነው እኛ የምንለው ደግሞ #እግዚአብሔር አለልን ነው።

ጠዋትና #ማታ በሚዲያ የምንሰማው #አለም በብዙ ፍረሃት #ውስጥ ያለችበት #ጊዜ ነው።

#እምነት ሁኔታን መካድ አይደለም ከሁኔታ በላይ የሆነውን #አምላክ ከፍ ማድረግ ነው።

ምንዛሬ ከፍ አለ ዝቅ አለ። ኑሮ ተወደደ እረከሰ ስለዘመኑ የሚወራው አብዛኛው አይገባንም።

#እኔ ግን እንዲህ እላችኋለው ለእግዚአብሔር ዘመን ከፍ አይልም ዝቅ አይልም። ኑሮ ስለረከሰ አልኖርንም ኑሮ ስለተወደደ አንጠፋም።

በሰው ካልኩሌሽን አልኖርንም አሁንም አንኖርም። ምንም እንኳን ምድረበዳ ቢሆን #ኢየሱስ አለ።

ዘመኑ አስጨናቂ ነው ? እውነት ነው ግን ኢየሱስ አለ።
የኖርኩት ለወንጌል እንደሚመች እንጂ ለኔ እንደሚመች አይደለም።

“በቦቢቾ መጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ቤት የሁለተኛ ዓመት ተማሪ ነበርኩ። እዚያ ትምህርት ቤት እያለሁ ኮንፈራንስ ነበረ። በዚያ ኮንፍራንስ ላይ መንፈስ ቅዱስ በኃይል ወረደ። መንፈስ ቅዱስ ሲወርድ የክርስቶስን የመስቀል ፍቅር በልባችን አፈሰሰ።

ያ ፍቅር በምንም የሚመዘን አይደለም። ለዚያ ፍቅር ለመጀመሪያ ጊዜ አራት ጠገራ ብር ሰጠሁ። መንፈስ ቅዱስ “ክርስቶስ የሞተው ለአራት ጠገራ ብር አይደለም” አለኝ። ተነስቼ እኔን በጣም የምትወደኝ ጊደር አለች ከኔ ጋር የበቆሎ ቂጣ አብራኝ የምትበላ እሷን ሰጠኋት። እንደገናም መንፈስ ቅዱስ መልሶ “ ኢየሱስ የሞተው ለጊደርህ አይደለም” አለኝ።

የመስቀሉ ፍቅር ከፍቅር ሁሉ የሚበልጥ ነውና ምንም የማደርገው አቅቶኛል። በኃላም መንፈስ ቅዱስ “ለእግዚአብሔር አገልግሎት ዕድሜህን ሁሉ ስጥ” አለኝ። ተነስቼ እጄን ዘርግቼ እዚያው ኮንፍራንስ ላይ ራሴን ሰጠሁ። ያ ፍቅር ነው እስከዛሬ ድረስ የያዘኝ።

ከዚያ በኋላ ለወንጌል አገልግሎት ወደ ጌዲኦ ተልኬ ስሄድ ሃያ ብር ሰጡኝ። ገንዘቡ ለእንጀራ የሚበቃ አልነበረምና ሻይና ዳቦ እየበላሁ ከጓደኛዬ መናሾ ጋር አብሬ ሄድኩ። ዲላ ስደርስ ሰባት ብር ነበር የቀረኝ። ከዚያ በኋላ በየወሩ አሥር ብር ነበር ይላክልኝ የነበረው። ለወንጌል እንደሚመች እንጂ የኖርኩት ለኔ እንደሚመች አይደለም። በፍጹም አይደለም።

#ምን በልቼ ልኖር እችላለሁ? ምን ለብሼ መኖር እችላለሁ? ብዬ አላውቅም። በአንድ ልብስ አራት አመት ያለ ቅያሬ ኖሬያለሁ። እሱ አይደለም የኔ ትኩረት የሚድኑ ነፍሳት ነው፥ የምታድግ ቤተ ክርስቲያን ናት። የኔ ዓላማ እሱ ነው።

እንባዬ ለሱ ነው። አሁንም ቢሆን ደሞዝ የለም፥ ጡረታ የለም ግን አገልግሎት አለኝ። ምንም አላጣሁም #እግዚአብሔር እረኛችን ነው።