The Christian News
5.37K subscribers
3.08K photos
29 videos
730 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
#ሰዉ ሃይማኖታዊ ስርዓት #ዉስጥ ሆኖ #በእግዚአብሔር #መንግስት ዉስጥ ላይሆን ይችላል? 🤔

ዶ/ር ማሙሻ ፈንታ
#አዲስ #ዜና

የካናዳ ፍርድ #ቤት አብያተ ክርስቲያናት ላይ የኮቪድ ወቅት እግድን ይግባኝ ውድቅ አደረገ።

#ፍርድ ቤቱ የካናዳ #ሁለት ግዛቶች #ውስጥ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት የኮቪድ 19 ወረርሺኝ በበረታበት ወቅት በአካል መሰብሰብን አግዶ በነበረበት ወቅት በመሰብሰባቸው ምክንያት ነው ጉዳዩን አልመለከተውም ያለው።

በወቅቱ አብያተ ክርስቲያናቱ በካናዳ #መንግስት የተወሰነውን በአካል ተገናኝቶ የማምለክ እገዳን ተላልፈው ሲሰበሰቡ ነበር ተብሏል።

ዘ ቸርች ኦፍ ጋድስ የተሰኘችው ቤተ ክርስቲያኗ ይሄንንም በመተላልፏ 240ሺህ ዶላር ቅጣት በግዛቷ ፍርድ ቤት ተጥሎባታል።

በኦንታሪዮ የምትገኘው የቸርች ኦፍ ጋድ መሪዎች በበኩላቸው ይሄ የፍርድ ቤት ውሳኔ የእምነት ነጻነትን የሚጋፋ ነው ብለውታል።
በሃገሪቱ የፍትህና ነጻነት ታሪክም አሳዛኝ #ቀን ነው ብለውታል።

ሬስቶራንቶችና ስፖርት ቤቶች፣ መክፈት በተፈቀደበት #ጊዜ #ቤተክርስቲያን እንዲዘጋና አቤቱታን አላስተናግድም ማለታቸው የእምነትን ነጻነት የሚጋፋ ነው ብለውታል።

እኛ ሰውን ሰምተን ሳይሆን #እግዚአብሔርን ነው የምንታዘዘው በማለት በወቅቱ በሮቻቸውን ሳይዘጉ የአምልኮ መርሃ ግብሮቻቸውን ሲያካሂዱ እንደነበረ ገልጸዋል።
#ፍትህ ግን ምንድነው? 🤔 የትስ #ነው ያለው? 🤔
#እኛ ጥያቄያችን #አንድ እና ግልጽ  ነው።

#የቤተክርስቲያናችን_ንብረት_ይመለስልን!!! 🙏🙏🙏

37 ዓመታት በእንባ እና በጸሎት የጸሎት ቤቷን ለማስመለስ ፍትሕን ፍለጋ የተነከራተተችው #ቤተክርስቲያን ዛሬም ፍትህን ፍለጋ ላይ ነች።

የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ከ1950ዎቹ #መጀመሪያ ጀምሮ በተለይ ትምህርትን ከማስፋፋት አንጻር #ለሀገር እና #ለሕዝብ ጥቅም ላበረከተችው አስተዋጽዖ በወቅቱ የነበረው የመንግስት ስረዓት ከምስጋና ይልቅ ት/ቤቶቻችንና ጸሎት ቤቶቻችንን መውረስ ቀሏቸዋል።

በደርግ #መንግስት በግፍ የተወረሰው የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የኦሎምፒያው ጸሎት ቤታችን በአዲስ አበባ የመጀመሪያው የመሰረተ ክርስቶስ የማምለኪያ ስፍራ ነው።

#ይህ የመሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ንብረት #ማለት የሙሉ #ወንጌል ምዕመን እና የሙሉ ወንጌል ቤ/ክ ንብረት ማለት ነው። የመካነ ኢየሱስ ማለት ደግሞ የቃለ ሕይወት ነው። የቃለ ሕይወት ማለት የሕይወት ብረሃን የሕይወት ብረሃን ማለት የገነት የገነት ማለት የጉባኤ እግዚአብሔር ... በአጠቃላይ የወንጌል አማኞች #በሙሉ ነው።

ይህ ከ66 ዓመት በላይ የተሻገረው የጸሎት ስፍራ ንብረት ብቻ አይደለም ይልቁንም ለወንጌል የተሰደዱ ፤ ለወንጌል ዋጋ የከፈሉ የወንጌላውያን አማኞች #ታሪክ እና ቅርስም ጭምር ነው።

በ1943ዓ.ም የተመሰረተችው የመሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ከቀደምት የወንጌል አማኞች ቤተዕምነት መካከል አንዷ ብቻ ሳትሆን እውነተኛው የክርስቶስ ወንጌል ለአዲሱ #ትውልድ  እንዲሸጋገር ከ70 ዓመት በላይ #በኢትዮጵያ በሚመችም በማይመችም ሁኔታ #ውስጥ ስትሰራ ቆይታለች።

#ዛሬ ላይ መዲናችን #አዲስ አበባ ከሌሎች #አለም ላይ ከሚገኙ ከተሞች መካከል ለመወዳደር ሌት ተቀን እየተጋች ትገኛለች። በዚህ ውስጥ ታዲያ በከፊሉ አዳዲስ ሲገነባ በከፊሉ ለተቸገሩት ሲደረስ በሌላ አቅጣጫ ግን እንሳኩን ያልተመለሱ #ብዙ ጥያቄዎች እንዳሉ የአደባባይ ሚስጥር ነው።

ታዲያ በመዲናችን #ዛሬም ፍትህን ከሚጠይቁ ተቋማት መካከል አንጋፋዋ የመሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አንዷ ነች።

ስለዚህ ህጋዊ የሆነው የቤተክርስቲያን ታሪክ ፤ ቅርስ እና ንብረታችን የሆነው የጸሎት ቤቶቻችን ይመለሱልን የማያቋርጥ ጥያቄያችን ነው!!!

ይህ #መልዕክት የሚደረሳችሁ ምዕመናን እና ኢትዮጵያውያን በሙሉ የቤተክርስቲያናችን ንብረት እስኪመለስ ድረስ ሁላችንም #SharePost በማድረግ ለሁሉም እናድርስ!!!

The Christian News - የክርስቲያን ዜና በዚህ ዙሪያ ተጨማሪ ዘገባዎችን በተለያየ ጊዜ ይዘን የምንመለስ ይሆናል።

#share #share #share #share
#እይታ
#Opinion

የሰሞኑን #አንድ #ሁለት ዜናዎች ልንገራችሁ።

የቄስ ጉዲና ቱምሳ ባለቤት ጸሃይ ቶሎሳ ግለ #ታሪክ ተመርቋል። መጽሃፉ “በእቶን እሳት ውስጥ” የሚል ነው። የነዚህ ብርቱ እናት ታሪክ እና ምስክርነት ለአንድ አንድ ሰዎች የእምነት መልህቅ ሊሆን ይችላል፣ ቢባል ማጋነን አይሆንም።

ሌላው #ዜና ደግሞ በፌደራል መንግስትና #መንግስት ሸኔ በሚለው እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ብሎ በሚጠራው ቡድን መካከል የተደረገው የሰላም ድርድር አሁንም ሳይሳካ ቀርቷል።

ይሄንን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደህንነት ጉዳዮች አማካሪ ሬድዋን ሁሴን አረጋግጠዋል። ከዚህ የሰላም ድርድር #መልካም ውጤት ይገኛል በሚል፣ ክርስቲያኑ ምነኛ ጓጉቶ እንደነበረ ማሰብ አይከብድም።

በተመሳሳይ ክፍለ ዘመን #ውስጥ ፣ በተመሳሳይ ርዕሳቸው፣ ረግጦ በሚገዛ መንግስት፣ የወንጌልን ነጻ አውጪነት አውጀው፣ የተገደሉ የዘመናት ክስተቶች ላውራችሁ።

#ቄስ_ዴትሪች_ቦንሆፈር በ1906 በጀርመን ብሬስሎው በተባለ ስፍራ የተወለዱ #ሰው ናቸው። እኚህ ሰው ስነ መለኮት አጥኚ ወይም ቲዎሎጂያን፣ ኮንፌሲንግ በተባለች ሉተራዊ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ቄስ #እና ጸረ ናዚ ሰው ነበሩ።

የአዶልፍ ሂትለር ተቃዋሚ መሆን የዋዛ ነገር አይምሰላችሁ። ከናዚው አዶልፍ ሂትለር የአስተዳደር እቅዶች መካከል “ኢውታናዢያ” የሚባል ፕሮግራም ነበረ ይባላል። በዚህ ፕሮግራማቸው ሰው ከሚሰቃይ ቀድሞ መሸኘት የሚል ነው።

#ትንሽ የታመመ የመዳን ተስፋ ሳይሆን፣ ከህመሙ ማረፊያ መግደል ያሰበ “በጣም ቅን ሰው ናቸው” ነበረ። ይሁዲዎች #ላይ ያደረገውን ጭካኔ፣ አለም ያወቀው ነው። ቦንሆፈር ይሄንን ስርዓት ነበረ በአደባባይ ቆሞ የተቃወመው። ያው በእሳት ፊት ቆሞ ነበረና እሳቱ በላው። በተወለደ በ39ኛ አመቱ የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌልን ሰብኮ ተሰቅሎ ተገደለ።

#ቄስ_ጉዲና_ቱምሳ በ1929 በኢትዮጵያ ወለጋ ቦጂ ከተማ የተወለዱ ሰው ናቸው። ተስፋ አደርጋለው ስለ ቄስ ጉዲና የማያውቅ ወንጌላዊ ክርስቲያን፣ ኢትዮጵያ ውስጥ አለ ማለት ይከብዳል። ግን ዝም ብዬ ታሪኩን ልንገራችሁ።

እኚህ ቄስ የስነ መለኮት አጥኚ #ወይም ቲዎሎጂያን፣ #የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ በተባለች ሉተራዊ ቤ/ክ ውስጥ ቄስ እና በሃያሉ ደርግ መንግስት ፊት የቆሙ ሰው ነበሩ። የደርግ ተቃዋሚ መሆንም የዋዛ ነገር አይደለም።

ኮለኔል መንግስቱ ማለት፣ በርሳቸው ዘመን በለጋ እድሜው አፈር የገባ ወጣት፣ በቀይ ሽብር ስም ያለቀው ተቀናቃኝ ፖለቲከኛና ለገዛ አጋሮቻቸው ያልተመለሱ ባለ ደም እጅ ሰው ነበሩ። ያ ኮለኔል መንግስቱና አገዛዙም ነበር ሆኗል።

እግዜር ደጉ፣ የማያሳልፈው የለም። ቄሱ ጉዲና በዚህ ለአፍሪካ እንኳን አይመለስም በተባለ ወታደር ፊት ቆመው “ወንጌል ነጻ ያወጣል” ብለው ሰብከዋል። እሳቸውም እሳት ፊት ቆመዋልና እሳት በላቸው። በተወለዱ በ50 አመታቸው የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ሰብከው በደርግ ወታደሮች ተገደሉ።

የነዚህ ሁለት በእሳት ፊት የቆሙ ቀሳውስት ህይወት፣ በሄሮድስ ፊት ቆሞ እውነት ተናግሮ አንገቱ የተቀላውን መጥምቁ ዮሃንስን ህይወት ይመስላል። የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት፣ በአስፈሪው የሮማ መንግስት ፊት፣ በአይሁድ ካህናት ፊት፣ በፈሪሳዊያንና ግሪካዊያን ፊት “እናንተ የእፉኝት ልጆች እያሉ”፣ መኖር ሳያሳሳቸው፣ መሞት ሳያስፈራቸው ወንጌልን የሰበኩ ጀግኖች ናቸው።

ቄስ ቦንሆፈርና ቄስ ጉዲናም በአፈ ሙዝ እንጂ በአፉ በማያወራ መንግስት ፊት ቆመው፣ መኖር ሳያጓጓቸው፣ ሞት ሳያስፈራቸው ወንጌልን ሳይቀንሱና ሳይጨምሩበት የሰበኩ የቤተ ክርስቲያን ቅሬታዎች፣ የክርስቶስ ልጆች ናቸው።

ዛሬስ መምህሩ፣ ጳጳሱ፣ ቄሱ፣ ፓስተሩ፣ ነብዩ፣ ሐዋርያው፣ ሼፐርዱ፣ ዳዲው የቱ ጋር ቆመሃል? ጌታ ኢየሱስ በጎቼን ጠብቅ ያለው ስመኦን ጴጥሮስ፣ ከአለም 20በመቶ ህዝብን በሚገዛው ግዙፉ የሮማ መንግስት ተዘቅዝቆ ተሰቀለ።

አንተስ በጎቼን ጠብቅ የተባልከው እረኛ ሆይ ፣ ለበጎቹ ስትል፣ እንደ ስመኦን ጴጥሮስ ተዘቅዝቀህ ለመሰቀል፣ እንደ ቦንሆፈር በናዚ ለመሰቀል፣ እንደ ጉዲና በደርግ ወታደር የአሞራ ሲሳይ ለመሆን #ተዘጋጅተሃል?

ክርስቲያን ሆኖ መኖር እራሱ ዋጋ በሚያስከፍልበት በዚህች ምድር ላይ ለወንጌል ዋጋ ለመክፈል የተዘጋጀህ ነህ ወይስ፣ ለአገልግሎትና ለእረፍት በV8 እና FORD F150 የምትምነሸነሽ #ሆነሃል? አለም ህይወት የሆነውን ክርስቶስን ለመስቀል ካልራራች፣ አንተ እውነተኛውን የርሱን ህይወት የምትሰብከውን የምትምርህ #ይመስልሃልን?

ዙሪያ ገባህን አይተህ ወንጌል የሚሰበክ ከጠፋ፣ ከተኩላ የምትጠብቀው በግ ከሌለ፣ ምናልባት ወንጌሉ የሚያስፈልገው፣ እረኝነቱ የሚያስፈልገው፣ ላንተው እራስህ እንዳይሆን የቆምክበትን አስተውል?
#ሰው ሸሽቶ #ቤተክርስቲያን ሲገባ #እንዴት ይገደላል? አገዳደሉ አሳቃቂ ነው። ቄስ ዶ/ር ዮናስ ይገዙ

የመካነ ኢየሱስ ፕሬዝደንት በዚህ ወረ በመካነኢየሱስ ምዕመናን ላይ የተፈጸመውን ግድያ አስመልክተው በሰጡት ማብራሪያ #መጽሐፍ #ቅዱስ ግምባራቸው #ላይ ነበር የተገደሉት ምዕመናን ከአንድ #ቀን በኋላ ነው የተገኙት ብለዋል።

ፕሬዝደንቱ አክለው #እንደ ቤተክርስቲያን መረጃው እስኪጣራ ነው ይፋ ያላደረግነው ያሉ ሲሆን በቤተክርስቲያን አካሄድ የቻልነውን ያህል ሄደናል ያሉ ሲሆን #መንግስት የሕዝብ የድህንነት #ጉዳይ በእጁ ነውና አሁንም #ተስፋ የምናደርገው መንግስት ገዳዮችን ለፍርድ እንደሚያቀርብ እናምናለን ሲሉም ተናግረዋል።

#ይህ ጥቃት በማን ነው የተፈጸመው ?

ከአደጋው የተረፉት ትክክለኛው ገዳዮች #ምን እንዳደረጉ እነማን እንደሆኑ ያውቃሉ። #ነገር #ግን ለደህንነታቸው ስለሚሰጉ ለመናገር ፍላጎት የላቸውም። መንግስት ግን ተከታትሎ ለፍርድ እንዲያቀርብልን እንጠይቃለን።
#አሳዛኝ #ዜና

12ኛ አመቱን በያዘው የሶርያ እርስ በእርስ ጦርነት ምክኒያት የክርስቲያኖች #ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እያሽቆለቆለ #ነው ተባለ።

በተለይ በበሰሜናዊ ሶርያ የምትገኘው አሌፖ #ከተማ በርካታ ክርስቲያኖች ይገኙባታል የነበረች ከተማ ነች።

ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ 250ሺህ የነበረው የክርስቲያኖች ቁጥር፣ አስደንጋጭ በሆነ ሁኔታ #ወደ 50ሺህ ወርዷል።

በከተማዋ ያሉ ክርስቲያኖች አሌፖ በጦርነቱ ፍርስርሷ ከመውጧቷ በተጨማሪ፣ በአይ ኤስ አይ ኤስ፣ የኩርድ ታጣቂዎች፣ አማጺ ሃይሉና የሶርያ #መንግስት መካከል በሚደረግ ጦርነት የመጀመሪያዎቹ ገፈት ቀማሾች መካከል ናቸው።

ከ200ሺህ #በላይ ክርስቲያኖች ከአሌፖ #ብቻ መሰደዳቸው፣ በሃገሪቱ ጥቂት የሆኑ ክርስቲያኖችን ቁጥርን አደጋ #ላይ ጥሎታል ሲል #አለም አቀፉ #ክርስቲያን ኮንሰርን አስነብቧል።

አሌፖ ከጦርነቱ በፊት በሰሜናዊ ሶርያ የንግድ ማዕከል የነበረችና ጥንታዊ ከተማ ስትሆን፣ ከጦርነቱ ማግስት ተከስቶ በነበረው ርዕደ #መሬት ሳቢያም ሁኔታዋ ከድጡ ወደ ማጡ ሆኗል።

በ2023 የኦፕን ዶርስ ዝርዝር መሰረት ሶርያ 12ኛ ለክርስቲያኖች የማትመች ሃገር ናት።
በአረብ ሃገሯ #ኢራን እስከ 1 #ሚሊዮን የሚጠጉ #ሰዎች #ወደ ክርስትና መጥተዋል ተባለ።

ከ88 ሚሊዮን ህዝቧ 96 በመቶ በላይ የሚሆነው እስልምና ተከታይ በሆነበትና፣ የሃገሪቷ #መንግስት በግልጽ እስላማዊ በሆነባት ኢራን ይሄንን ያክል ቁጥር #ክርስቲያን መገኘቱ ተዓምር ነው ተብሏል።

ሪፖርቱን ይዞት የወጣው The Voice of the Martyrs የተባለው በክርስቲያኖች ላይ የሚደርስን ስደት የሚከታተል ተቋም ነው። ተቋሙ በሪፖርቱ ከ1970 የኢራን አብዮት ወዲህ በሃገሪቱ ክርስቲያኖች ስደት የበረታ መሆኑን ጠቅሷል።

ምንም እንኳን ስደቱ ቢበዛም በተቃራኒውም የክርስቲያኖች ቁጥር መጨመርን አሳይቷል። ቤተ ክርስቲያን በድብቅ ወይም underground ሆና መስፋፋቷን ቀጥላለች።

ሌላዋ የመካከለኛው ምስራቅ #አረብ ሃገር በሆነችው የመን፣ ጆሽዋ ሚኒስትሪ ሪፖርት እንዳደረገው በአለም አቀፍ ደረጃ ካለው ይልቅ በየመን ወደ #ጌታ የሚመጡ ሰዎች ቁጥር ብልጭን አሳይቷል።

በ2024 ሪፖርት መሰረት ኢራን ለክርስቲያኖች አስቸጋሪ ከሆኑ 50 ሀገራት መካከል እጅግ አስቸጋሪ በሚል በ9ኛ ስፍራ የምትገኝ ሲሆን የመን በበኩሏ በ5ኛ ስፍራ ተቀምጣለች።