#ዘጠኝ #ክርስቲያኖች #የሞት #ፍርድ ሊወሰንባቸው ይችላል።
በሃገረ ሊቢያ 9 ሚሽነሪዎች የታሰሩ ሲሆን ስድስት ሊቢያውያን ሁለት የጉባኤዎች እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን አሜሪካዊያን ሚሲዮናውያን እና አንድ ፓኪስታናዊ በሊቢያ የውስጥ ደኅንነት ኤጀንሲ ተይዘው ታስረዋል።
እስረኞቹ ክርስትናን በመስበክ ተከሰው ሊገደሉ እንደሚችሉ የካቶሊክ ዜና አገልግሎት አስነብቧል።
ባለፈው ሳምንት የሊቢያ የውስጥ ደህንነት ኤጀንሲ ክርስትናን በመስበክ የተከሰሱትን የሊቢያ እና የውጭ ዜጎችን ለመያዝ በትሪፖሊ ከተማ ዘመቻ ከፍቷል ያለ ሲሆን የጸጥታ ኤጀንሲው በቁጥጥር ስር የዋሉት ሰዎች ቁጥራቸው ምን ያህል እንደሆነ አልገለጸም እና ስማቸውን ከመግለጽ የተቆጠበ ሲሆን የመጀመሪያ ፊደላቸውን ብቻ ገልጿል።
ኤጀንሲው የተያዙትን ሰዎች ፊታቸውን ሸፈኖ ክሱን ሲናዘዙ የሚያሳይ ቪዲዮ አውጥቷል። ሁለቱ አሜሪካውያን በትሪፖሊ በዛውያት አል ዳህማኒ ክፍለ ከተማ በሚገኘው ጌትዌይ ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤት እንግሊዝኛ በማስተማር ላይ ይሠሩ ነበር።
አሜሪካውያኑም ትምህርት ቤቱን በሚስጥር የክርስትና ሃይማኖት መስበኪያ ማዕከል አድርገውታል በሚል ተከሰዋል።
በሊቢያ ያለው የክርስቲያኖች ቁጥር 35,400 (ሰላሳ አምስት ሺህ አራት መቶ) ሲሆን ይህም (ከህዝቡ 0.5%) እንደሆነ የኦፕን ዶርስ መረጃ ያሳያል።
ለክርስትና የማይመቹ ሀገራትን በተመለከተ አመታዊ ሪፖርት የሚሰጠው ኦፕን ዶርስ ሪፖርት መሰረት ሊቢያ ለክርስትና ከማይመቹ 50 ሀገራት መካከል እጅግ አስቸጋሪ በመባል በ5ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።

ከፍተኛው የጀርመን #ፍርድ #ቤት ፅንስ ማስወረድ በሚቻልባቸው ክሊኒኮች አካባቢ #ጸሎት እንዳይደረግ መከልከሉን አገደ።
አንድ ከፍተኛ የጀርመን ፍርድ ቤት ፅንስ ማስወረድ በሚካሄድባቸው ክሊኒኮች አካባቢ ሰላማዊ የጸሎት ስብሰባዎችን መከልከል ሕገ መንግሥታዊ የመሰብሰብ መብትን ይጥሳል ሲል ብይን ሰጥቷል።
በጀርመን እስከ 2019 ድረስ #ውርጃ የሚፈጸምባቸው ክሊኒኮች #አከባቢ ሰዎች እየሄዱ ጽሎት ያደርጉ የነበረ ቢሆንም የክሊኒክ ባለቤቶች ባቀረቡት #ቅሬታ ውርጃ የሚፈጸምባቸው አከባቢዎች ድምጽ አውጥቶም ይሁን በዝምታ ጸሎት ተከልክሎ መቆየቱን ዘገባው አስታውሷል።
ምንም እንኳን አንዳንዶች የፍርድ ቤቱ ውሳኔ መንግስት በፅንስ ማስወረድ ክሊኒኮች አካባቢ የሚደረገውን የጸሎት ማስጠንቀቂያ ለመከልከል ካለው ፍላጎት ጋር በእጅጉ ይቃረናል። ቢሉም 40 Days for Life እንቅቃሴ በበኩሉ ስኬታማ ሲሉ ገልጸውታል።

#አዲስ #ዜና
የካናዳ ፍርድ #ቤት አብያተ ክርስቲያናት ላይ የኮቪድ ወቅት እግድን ይግባኝ ውድቅ አደረገ።
#ፍርድ ቤቱ የካናዳ #ሁለት ግዛቶች #ውስጥ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት የኮቪድ 19 ወረርሺኝ በበረታበት ወቅት በአካል መሰብሰብን አግዶ በነበረበት ወቅት በመሰብሰባቸው ምክንያት ነው ጉዳዩን አልመለከተውም ያለው።
በወቅቱ አብያተ ክርስቲያናቱ በካናዳ #መንግስት የተወሰነውን በአካል ተገናኝቶ የማምለክ እገዳን ተላልፈው ሲሰበሰቡ ነበር ተብሏል።
ዘ ቸርች ኦፍ ጋድስ የተሰኘችው ቤተ ክርስቲያኗ ይሄንንም በመተላልፏ 240ሺህ ዶላር ቅጣት በግዛቷ ፍርድ ቤት ተጥሎባታል።
በኦንታሪዮ የምትገኘው የቸርች ኦፍ ጋድ መሪዎች በበኩላቸው ይሄ የፍርድ ቤት ውሳኔ የእምነት ነጻነትን የሚጋፋ ነው ብለውታል።
በሃገሪቱ የፍትህና ነጻነት ታሪክም አሳዛኝ #ቀን ነው ብለውታል።
ሬስቶራንቶችና ስፖርት ቤቶች፣ መክፈት በተፈቀደበት #ጊዜ #ቤተክርስቲያን እንዲዘጋና አቤቱታን አላስተናግድም ማለታቸው የእምነትን ነጻነት የሚጋፋ ነው ብለውታል።
እኛ ሰውን ሰምተን ሳይሆን #እግዚአብሔርን ነው የምንታዘዘው በማለት በወቅቱ በሮቻቸውን ሳይዘጉ የአምልኮ መርሃ ግብሮቻቸውን ሲያካሂዱ እንደነበረ ገልጸዋል።