The Christian News
5.37K subscribers
3.08K photos
29 videos
730 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
#ይቅርታ 🙏🙏🙏
#ዜና #ማስተካከያ

በድሬዳዋ ከተማ የምትገኘዉ የኢትዮዽያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ከከተማዉ አስተዳደር ካቢኔ ለአምልኮ የምትገለገልበትን አዳራሽ በአንድ ወር ዉስጥ እንድትለቅ እና ቤተክርስቲያኒቱ ፈርሳ ቦታዉ ለሌላ አገልግሎት ይዉላል መባሉ ይታወቃል።

#ሆኖም_በተለያየ_ማህበራዊ_ሚድያዎች The Christian News - የክርስቲያን ዜና ጨምሮ “የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የድሬዳዋ መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን እንደማትፈርስ ቃል ገብቷል” የሚል መረጃ አሰራጭተናል።

ነገር ግን #ይህ_መረጃ_የተሳሳተ መሆኑን የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነየሱስ ማዕከላዊ ሲኖዶስ #ፕሬዚዳንት_ቄስ_ፈለቀ ጥበበ ገልጸው ቤተክርስቲያኒቱ ከድሬዳዋ አስተዳደር ካቢኔ ጋር እየተነጋገረች እንደምትገኝ ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ተናግረዋል።

#የክርስቲያን ዜና በጉዳዩ ዙሪያ ከቤተክርስቲያኒቱ በቂ መረጃ እየተለቀቀ ባለመሆኑ ጉዳዩ የሁላችንም ነዉ በማለት ድምፃቸዉን ለቤተክርስቲያን ሲያሰሙ የነበሩ የክርስቲያን የማሕበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪ የቤተክርስቲያን ልጆችን መረጃ ስናጋራ የቆየን ሲሆን በዚህም ባሰራጨነዉ ያልተሟላ እና የተሳሳተ ዘገባ #ይቅርታ እንጠይቃለን 🙏🙏🙏
#እይታ
#Opinion

የሰሞኑን #አንድ #ሁለት ዜናዎች ልንገራችሁ።

የቄስ ጉዲና ቱምሳ ባለቤት ጸሃይ ቶሎሳ ግለ #ታሪክ ተመርቋል። መጽሃፉ “በእቶን እሳት ውስጥ” የሚል ነው። የነዚህ ብርቱ እናት ታሪክ እና ምስክርነት ለአንድ አንድ ሰዎች የእምነት መልህቅ ሊሆን ይችላል፣ ቢባል ማጋነን አይሆንም።

ሌላው #ዜና ደግሞ በፌደራል መንግስትና #መንግስት ሸኔ በሚለው እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ብሎ በሚጠራው ቡድን መካከል የተደረገው የሰላም ድርድር አሁንም ሳይሳካ ቀርቷል።

ይሄንን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደህንነት ጉዳዮች አማካሪ ሬድዋን ሁሴን አረጋግጠዋል። ከዚህ የሰላም ድርድር #መልካም ውጤት ይገኛል በሚል፣ ክርስቲያኑ ምነኛ ጓጉቶ እንደነበረ ማሰብ አይከብድም።

በተመሳሳይ ክፍለ ዘመን #ውስጥ ፣ በተመሳሳይ ርዕሳቸው፣ ረግጦ በሚገዛ መንግስት፣ የወንጌልን ነጻ አውጪነት አውጀው፣ የተገደሉ የዘመናት ክስተቶች ላውራችሁ።

#ቄስ_ዴትሪች_ቦንሆፈር በ1906 በጀርመን ብሬስሎው በተባለ ስፍራ የተወለዱ #ሰው ናቸው። እኚህ ሰው ስነ መለኮት አጥኚ ወይም ቲዎሎጂያን፣ ኮንፌሲንግ በተባለች ሉተራዊ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ቄስ #እና ጸረ ናዚ ሰው ነበሩ።

የአዶልፍ ሂትለር ተቃዋሚ መሆን የዋዛ ነገር አይምሰላችሁ። ከናዚው አዶልፍ ሂትለር የአስተዳደር እቅዶች መካከል “ኢውታናዢያ” የሚባል ፕሮግራም ነበረ ይባላል። በዚህ ፕሮግራማቸው ሰው ከሚሰቃይ ቀድሞ መሸኘት የሚል ነው።

#ትንሽ የታመመ የመዳን ተስፋ ሳይሆን፣ ከህመሙ ማረፊያ መግደል ያሰበ “በጣም ቅን ሰው ናቸው” ነበረ። ይሁዲዎች #ላይ ያደረገውን ጭካኔ፣ አለም ያወቀው ነው። ቦንሆፈር ይሄንን ስርዓት ነበረ በአደባባይ ቆሞ የተቃወመው። ያው በእሳት ፊት ቆሞ ነበረና እሳቱ በላው። በተወለደ በ39ኛ አመቱ የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌልን ሰብኮ ተሰቅሎ ተገደለ።

#ቄስ_ጉዲና_ቱምሳ በ1929 በኢትዮጵያ ወለጋ ቦጂ ከተማ የተወለዱ ሰው ናቸው። ተስፋ አደርጋለው ስለ ቄስ ጉዲና የማያውቅ ወንጌላዊ ክርስቲያን፣ ኢትዮጵያ ውስጥ አለ ማለት ይከብዳል። ግን ዝም ብዬ ታሪኩን ልንገራችሁ።

እኚህ ቄስ የስነ መለኮት አጥኚ #ወይም ቲዎሎጂያን፣ #የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ በተባለች ሉተራዊ ቤ/ክ ውስጥ ቄስ እና በሃያሉ ደርግ መንግስት ፊት የቆሙ ሰው ነበሩ። የደርግ ተቃዋሚ መሆንም የዋዛ ነገር አይደለም።

ኮለኔል መንግስቱ ማለት፣ በርሳቸው ዘመን በለጋ እድሜው አፈር የገባ ወጣት፣ በቀይ ሽብር ስም ያለቀው ተቀናቃኝ ፖለቲከኛና ለገዛ አጋሮቻቸው ያልተመለሱ ባለ ደም እጅ ሰው ነበሩ። ያ ኮለኔል መንግስቱና አገዛዙም ነበር ሆኗል።

እግዜር ደጉ፣ የማያሳልፈው የለም። ቄሱ ጉዲና በዚህ ለአፍሪካ እንኳን አይመለስም በተባለ ወታደር ፊት ቆመው “ወንጌል ነጻ ያወጣል” ብለው ሰብከዋል። እሳቸውም እሳት ፊት ቆመዋልና እሳት በላቸው። በተወለዱ በ50 አመታቸው የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ሰብከው በደርግ ወታደሮች ተገደሉ።

የነዚህ ሁለት በእሳት ፊት የቆሙ ቀሳውስት ህይወት፣ በሄሮድስ ፊት ቆሞ እውነት ተናግሮ አንገቱ የተቀላውን መጥምቁ ዮሃንስን ህይወት ይመስላል። የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት፣ በአስፈሪው የሮማ መንግስት ፊት፣ በአይሁድ ካህናት ፊት፣ በፈሪሳዊያንና ግሪካዊያን ፊት “እናንተ የእፉኝት ልጆች እያሉ”፣ መኖር ሳያሳሳቸው፣ መሞት ሳያስፈራቸው ወንጌልን የሰበኩ ጀግኖች ናቸው።

ቄስ ቦንሆፈርና ቄስ ጉዲናም በአፈ ሙዝ እንጂ በአፉ በማያወራ መንግስት ፊት ቆመው፣ መኖር ሳያጓጓቸው፣ ሞት ሳያስፈራቸው ወንጌልን ሳይቀንሱና ሳይጨምሩበት የሰበኩ የቤተ ክርስቲያን ቅሬታዎች፣ የክርስቶስ ልጆች ናቸው።

ዛሬስ መምህሩ፣ ጳጳሱ፣ ቄሱ፣ ፓስተሩ፣ ነብዩ፣ ሐዋርያው፣ ሼፐርዱ፣ ዳዲው የቱ ጋር ቆመሃል? ጌታ ኢየሱስ በጎቼን ጠብቅ ያለው ስመኦን ጴጥሮስ፣ ከአለም 20በመቶ ህዝብን በሚገዛው ግዙፉ የሮማ መንግስት ተዘቅዝቆ ተሰቀለ።

አንተስ በጎቼን ጠብቅ የተባልከው እረኛ ሆይ ፣ ለበጎቹ ስትል፣ እንደ ስመኦን ጴጥሮስ ተዘቅዝቀህ ለመሰቀል፣ እንደ ቦንሆፈር በናዚ ለመሰቀል፣ እንደ ጉዲና በደርግ ወታደር የአሞራ ሲሳይ ለመሆን #ተዘጋጅተሃል?

ክርስቲያን ሆኖ መኖር እራሱ ዋጋ በሚያስከፍልበት በዚህች ምድር ላይ ለወንጌል ዋጋ ለመክፈል የተዘጋጀህ ነህ ወይስ፣ ለአገልግሎትና ለእረፍት በV8 እና FORD F150 የምትምነሸነሽ #ሆነሃል? አለም ህይወት የሆነውን ክርስቶስን ለመስቀል ካልራራች፣ አንተ እውነተኛውን የርሱን ህይወት የምትሰብከውን የምትምርህ #ይመስልሃልን?

ዙሪያ ገባህን አይተህ ወንጌል የሚሰበክ ከጠፋ፣ ከተኩላ የምትጠብቀው በግ ከሌለ፣ ምናልባት ወንጌሉ የሚያስፈልገው፣ እረኝነቱ የሚያስፈልገው፣ ላንተው እራስህ እንዳይሆን የቆምክበትን አስተውል?
#አሳዛኝ #ዜና
#9 #ክርስቲያኖች ተገደሉ።

በቄለም ወለጋ ጊዳሚ መካነ ኢየሱስ ቤ/ክ ጸሎት ላይ የነበሩ ሰዎች ከቤተ ክርስቲያን ተወስደው ተገደሉ

በምዕራብ ኦሮሚያ ቄለም ወለጋ ዞን፣ ጊዳሚ ከተማ ነው ጸሎት ላይ የነበሩት ሰዎች የተገደሉት።

አስተያየታቸውን ለቢቢሲ የሰጡት የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤ/ክ መካነ ኢየሱሱ ቲዎሎጂና ሚሽን መምሪያ ቄስ ዶ/ር ለሊሳ “የአዳር ጸሎት ላይ የነበሩ 9 የቤተ ክርስቲያኗ አባላት፣ በታጣቂዎች ተወስደው ተገድለዋል” ብለዋል።

በቤጊ-ጊዳሚ ሲኖዶስ በጊዳሚ ሰባካ፣ የሃሞ ቶኩማ ማህበረ ምዕመናን የምትገኘው ይህቺ ቤ/ክ አባላት የዛሬ ሳምንት ህዳር 14 ለሊት 8 ሰዓት ነው ከቤተ ክርስቲያኗ የተወሰዱት።

የቤተክርስያኗ ሽማግሌዎች፣ የወጣቶች ኮሚቴ አባላት እንዲሁም ሌሎች አገልጋዮች ናቸው ተወስደው የገደሉት።

ጥቃት አድራሾቹ ማን እንደሆኑ እስካሁን የታወቀ ነገር ግን የለም ስትል ቤተ ክርስቲያኗ አስታውቃለች።

ቢቢሲ ባደረገው ማጣራት መሰረት የተወሰዱት 9 ሰዎች ከሌሎች መካከል ተመርጠው መሆኑን ከቤተ ክርስቲያኗ አባላት አረጋግጧል። ለቅዳሜ ቀን የአምልኮ ፕሮግራም ዝግጅት የአዳር ጸሎት ይካፈሉ የነበሩ ሰዎች 12 ናቸው።

ከ12ቱ ሰዎች መካከል 2 ሴቶችና አንድ እድሜያቸው የገፋ አዛውንት ሳይወሰዱ ቀርተዋል ነው የተባለው።

ተወስደው የተገደሉት ሰዎች ምንም አይነት የፖለቲካዊ ተሳትፎ የላቸውም ነው የተባለው። ቄስ ዶ/ር ለሊሳ “ዘመዶቻቸውን በሞት ላጡ ወገኖች መጽናናትን ተመኝተው፣ መንግስት ለቤተ ክርስቲያን አባላት ፍትህ እንዲሰጥ” ሲል ጠይቀዋል።

በተመሳሳይ የዛሬ አመት እሁድ ቀን ጥቅምት 27 2014 በምስራቅ ወለጋ መካነ ኢየሱስ ቤ/ክ አምልኮ ላይ የነበሩ 15 ምዕመናን ጥቃት ተፈጽሞባቸው መሞታቸው ይታወሳል።

ጥቅምት 2015 ደርሶ በነበረው ግድያ ጥቃት አድራሾቹ ከሌላ አካባቢ የመጡ ናቸው ተብሎ መዘገቡ ይታወሳል ሲል BBC News Amharic አስነብቧል።
#አሳዛኝ #ዜና

12ኛ አመቱን በያዘው የሶርያ እርስ በእርስ ጦርነት ምክኒያት የክርስቲያኖች #ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እያሽቆለቆለ #ነው ተባለ።

በተለይ በበሰሜናዊ ሶርያ የምትገኘው አሌፖ #ከተማ በርካታ ክርስቲያኖች ይገኙባታል የነበረች ከተማ ነች።

ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ 250ሺህ የነበረው የክርስቲያኖች ቁጥር፣ አስደንጋጭ በሆነ ሁኔታ #ወደ 50ሺህ ወርዷል።

በከተማዋ ያሉ ክርስቲያኖች አሌፖ በጦርነቱ ፍርስርሷ ከመውጧቷ በተጨማሪ፣ በአይ ኤስ አይ ኤስ፣ የኩርድ ታጣቂዎች፣ አማጺ ሃይሉና የሶርያ #መንግስት መካከል በሚደረግ ጦርነት የመጀመሪያዎቹ ገፈት ቀማሾች መካከል ናቸው።

ከ200ሺህ #በላይ ክርስቲያኖች ከአሌፖ #ብቻ መሰደዳቸው፣ በሃገሪቱ ጥቂት የሆኑ ክርስቲያኖችን ቁጥርን አደጋ #ላይ ጥሎታል ሲል #አለም አቀፉ #ክርስቲያን ኮንሰርን አስነብቧል።

አሌፖ ከጦርነቱ በፊት በሰሜናዊ ሶርያ የንግድ ማዕከል የነበረችና ጥንታዊ ከተማ ስትሆን፣ ከጦርነቱ ማግስት ተከስቶ በነበረው ርዕደ #መሬት ሳቢያም ሁኔታዋ ከድጡ ወደ ማጡ ሆኗል።

በ2023 የኦፕን ዶርስ ዝርዝር መሰረት ሶርያ 12ኛ ለክርስቲያኖች የማትመች ሃገር ናት።
#አስደሳች #ዜና

የወንጌላውያን #ሚድያ ባለሙያዎች ማህበር ተመሰረተ።

በቢሾፍቱ ሊሳክ ሪዞርት በተካሄደ ምስረታ ጉባኤ #ላይ ከተለያዩ የሚድያ ተቋማት የተውጣጡ የሚድያ ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

በመረሀ ግብሩ ምስረታ ወቅት ማህበሩን ለመመስረት የተካሄደባቸውን የስራ ሪፖርቶች ለተሳታፊዎቹ ያቀረበ ሲሆን በመሀበሩ መተዳደሪያ ደንብ ማርቀቅ ዙሪያ ውይይት ተካሂዶ የማሻሻያ ሀሳቦች ቀርበው መተዳደሪያ ደንቡ ጸድቋል።

በእለቱም የማህበሩን ፕሬዝዳንት እና ምክትል ፕሬዝዳንት እንዲሁም የቦርድ አባላት የተመረጡ ሲሆን በዚህም መሰረት የማህበሩ ፕሬዝዳንት በመሆን ወንድም ዘሪሁን ግርማ ምክትል ፕሬዝዳንት ወንድም መሳይ አለማየሁ የተመረጡ ሲሆን ዘጠኝ የማህበሩ የቦርድ አባላትም ተመርጠዋል።

በእለቱም የጸሎትና #የእግዚአብሄር ቃል በመካፈል ፕሮግራምም ተካሄዷል።

The Christian News - የክርስቲያን ዜና በማሕበሩ ምስረታ ሒደት ዉስጥ በበጎ ፍቃደኝነት ከፍተኛ ስራ ለሰሩ አባላት ምስጋናውን እያቀረበ።

በዛሬዉ እለት ማሕበሩን በቀጣይ ለመምራት ሃላፊነት ለተቀበሉ መሪዎች #መልካም የስራ ዘመን እንዲሆን እንመኛለን።
#NewsUpdate

#ማሳሰቢያ

ከትላንት በስቲያ በቀድሞው አጎና ሲኒማ ህንጻ ላይ በደረሰው የእሳት አደጋ የተለያዩ ተቋማት ንብረቶች መዉደማቸዉ ይታወሳል።

#ይህንን #ዜና በማስመልከት The Christian News - የክርስቲያን ዜና የሕይወት ምንጭ ኢየሱስ ዓለም አቀፍ ቤ/ክ በሚል መጠርያ የምትጠራዉ ቤተክርስቲያን በአደጋዉ ጉዳት እንደደረሰባት የአዲስ አበባ የእሳት እና ድንገተኛ አደጋ ኮሚሽን መረጃን ዋቢ በማድረግ የተዘገቡ ከተለያዩ የግል ሚዲያ ያገኘነዉን #መረጃ ማሰራጨታችን ይታወሳል።

ሆኖም የቤተክርስቲያን መሪዎች በአጎና ሲኒማ ህንጻ በሚገኘው አዳራሽ አምልኮ ካቆሙ #አንድ አመት ያለፋቸዉን መሆኑን ጠቅሰዉ መረጃዉ የተሳሳተ እንደሆነ ገልፀዋል።

በዘገባዉ በቴሌቪዥን ስቲዲዮዉ ለድምጽ መከላከያ ተብሎ በህንጻዉ ግድግዳ ላይ የተገነባዉ እስፖንጅና በቤተክርስቲያኑ ውስጥ የነበረው በርካታ የፕላስቲክ ወንበሮች ለቃጠሎዉ መስፋፋት አስተዋጾኦ እንዳደረጉ የተቋሙ ኮሙኒኬሽን አቶ ንጋቱ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን መናገራቸው ተካቷል።

የቤተክርስቲያኒቱ መሪዎች በበኩላቸው ወንበሮቹ የራሱ የህንፃው ባለቤቶች የመሰብሰቢያ አዳራሽ ንብረት እንደሆነ ተናግረዋል።

አደጋዉን በተመለከተ በዘገባዉ ጎልቶ የወጣዉ የሌላ ተቋማት ጉዳት ስለነበር በዚህ ዉስጥ ቤተክርስቲያን ጉዳት ደርሶባት ከነበር እንደ ክርስቲያን ሃላፊነታችንን ለመወጣት በሚል ዘገባዉን አሰራጭተናል።

በተሰራጨዉ የተሳሳተ ዘገባ #The #christian #news ይቅርታ እየጠየቅን ዘገባዉን ከገፃችን ማንሳታችንን እናሳዉቃለን።
#አስደሳች #ዜና ለወንጌል አማኞች #በሙሉ

#በመስቀል #አደባባይ የንስሐ፣ የምልጃና የምስጋና ፕሮግራም መዘጋጀቱ ተገለጸ።

በዛሬው እለት #የኢትዮጵያ #ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል መሪዎች በአዲስ አበባ በመስቀል አደባባይ የንስሐ፣ የምልጃና የምስጋና ፕሮግራም መዘጋጀቱን ለሚዲያዎች መግለጫ ሰጥተዋል።

በተሰበረ #ልብ፣ በንስሐ መቅረብ የመጀመሪያ ተግባራችን መሆን እንዳለበት የጠቀሱት መሪዎቹ “#ወደ ደጆቹ በመገዛት ወደ አደባባዮቹም በምስጋና ግቡ፣ አመስግኑት፣ ስሙንም ባርኩ” (መዝ 100)፤4 በሚለው ቃለ #እግዚአብሔር መሠረት መጋቢት 8 ቀን 2016 ዓ/ም ከቀኑ 7፡00 ጀምሮ #በአዲስ አበባ #መስቀል አደባባይ የንስሐ፣ የምልጃና የምስጋና በዓል ለማካሄድ አስፈላጊው ዝግጅት #ሁሉ ተጠናቋል ብለዋል።

አሁንም የእርስ በርስ መጠፋፋቱ አልቆመም ያሉት መሪዎቹ መደማመጥና መከባበር በመካከላችን እንዲኖርና ለይቅርታና ለፍቅር ልባችን የቀና እንዲሆንና ፀጋውንም እንዲያበዛልን #እግዚአብሔርን የምንማጸንበት #ጊዜ ይኖራል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በፕሮግራሙ የሚካፈለው የሕዝብ #ብዛት እጅግ ብዙ ስለሆነ ስብሰባው የሚካሄደው በመስቀል አደባባይ ነው፡፡

በመሆኑም መላው የወንጌል አማኝ በነቂስ ወጥቶ #በእግዚአብሔር ፊት የንስሐ፣ የምልጃና የምስጋና ፕሮግራሙ ተካፋይ እንዲሆን ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

The Christian News - የክርስቲያን ዜና በስፍራው ተገኝተን ዝርዝሩን አሰናዳንላችሁ።

#photo Christian tube - ክርስቲያን ቲዩብ

ዝርዝር መረጃ ምሽት ላይ በቪዲዮ ይዘንላችሁ የምንመለስ ይሆናል።
https://www.youtube.com/channel/UCeHRJCDJ0wUDaBfAFmuMa7A?sub_confirmation=1
#ዜና_ዕረፍት !

ወንጌላዊ ተክሉ ከበደ ወዳገለገሉት ጌታ እቅፍ ተሰብስቧል።

ወንጌላዊ ተኩሉ ለረጅም ዓመታት በመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በገጠር በከተማ በትጋት ያገለገሉ ብርቱ የወንጌል አገልጋይ ነበሩ።

የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ዋናው ቢሮ ሠራተኞች እና አገልግሎት የተሰማቸዉን ሐዘን ገልፀዉ ለወዳጅ ቤተሰቦቻቸው መጽናናት እንዲሆን ተመኝተዋል።
#አስደሳች #ዜና

በአሁኑ ወቅት #ብቻ በኢንዶኔዥያ ከ35 በሚበልጡ ቋንቋዎች መጽሃፍ #ቅዱስ ትርጉም እየተካሄደ ይገኛል።

ኢንዶኔዥያን ለየት የሚያደርጋት ነገር፣ በአለማችን #ላይ ብዙ የእስልምና #እምነት ተከታዮች ያሉባት ሃገር መሆኗ ነው። ዋይክሊፍ አሶሴሽን የትርጉም ስራዎቹን የሚያከናውነው፣፣ በአካባቢው ከሚገኙ አብያተ ክርስቲያናትና #አዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ነው።

#አዲሱ የትርጉም ቴክኖሎጂ፣ በየአካባቢው የሚገኙ ክርስቲያኖች የትርጉም ስራውን ከፊት ሆነው ይመሩ ዘንድ ይረዳል ነው የተባለው። ይሄም መጽሃፍ ቅዱስ ባለቤትነታቸውን ይበልጥ ያረጋግጥላቸዋል። ግምገማ፣ ስልጠና፣ ህትመትና ስርጭቱንም ቢሆን እራሳቸው የየአካባቢው #ሰዎች እንዲሳተፉበት ይረዳቸዋል ነው የተባለው።

በአሁኑ ወቅት ብቻ ከዋይክሊፍ ተጨማሪ ሌሎች የመጽሃፍ ቅዱስ ትርጉም ድርጅቶች #አንድ ላይ በመሆን ከ60 በማያንሱ የኢንዶኔዥያ ሃገር ቋንቋዎች እየተተረጎሙ ይገኛሉ።

በኢንዶኔዥያ ብቻ ለሚሰራው የመጽሃፍ ቅዱስ ስራ፣ ከ400 እስከ 500 ሺህ ዶላር በጀት ተይዞለታል። #ይሄ ወጪ ከበጎ ፈቃደኞች የተሰበሰበ ሲሆን ሌሎችም በጸሎት የዚህ #ታላቅ ስራ አካል ይሁኑ ሲል ዋይክሊፍ ጥሪ አቅርቧል።

ኢንዶኔዥያ ውስጥ ከ700 በላይ ቋንቋዎች ይገኛሉ። ይሄም ሃገሪቱን በአለም ላይ ካሉ ቋንቋዎች 10 በመቶ በሃገሪቱ ብቻ መኖሩን ያሳያል።
#ወደ ሚወደዉ ጌታ ሄዷል። #ዜና 😭😭

ዘማሪ ሙሉቀን መለሰ ከዚህ አለም በሞት ተለይቶ ወደሚወደው ጌታ ሄዷል።

የሄደው ወደጌታ ቢሆንም የሚወዱት ሲለይ ያሳዝናልና The Christian News - የክርስቲያን ዜና ለወዳጅ ዘመዶቹ ፣ ለቤተሰቦቹ መፅናናትን እንመኛለን.... 🙏🙏🙏
#አስደሳች #ዜና ካህን #የክርስቲያን ባዛር ሊደረግ ነው።

በመልህቅ ፕሮዳክሽን እና ኢቨንት አዘጋጅነት "ካህን" የተሰኘ እና ጀማሪ እና መካከለኛ የንግድ ስራ ላይ የተሰማሩ #ክርስቲያን ነጋዴዎች የሚሳተፉበት የክርስቲያን ባዛር ሊካሄድ ነው።

ሚያዝያ 12/2016ዓ.ም ቅዳሜ በሚደረገው ፕሮግራም ላይ የአብያተ ክርስቲያናት መሪዎች፤ ታዋቂ የኪነ ጥበብ ሰዎች ፤ ወጣት እና አንጋፋ ዘማሪዎች በክብር እንግድነት ተገኝተው በድምቀት እንደሚከፍቱት አዘጋጆቹ አሳውቀዋል።

በመረሃ ግብሩ የክርስቲያን ባዛር የአምልኮ #ጊዜ የተለያዩ ጨዋታዎች የሚዲያ ሽፋን እንዲሁም ለክርስቲያን ቲክቶከሮች ማበረታቻ የሚሰጥበት ጊዜ እንደሚኖር ታውቋል።

#ቦታ ብሔራዊ ትያትርን ተሻግሮ በከተማና ልማት አዳራሽ ከማለዳው 2:30 ጀምሮ እስከ ምሽት 2:00ሰዓት ይከወናል።

ሁላችሁም ተጋብዛችኋል። ይጎብኙ ፤ ይሸምቱ ፤ አብረውን ያምልኩ።
#ጅማ ክርስቲያን

በጅማ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖ ካምፓስ የቀድሞ የ#ክርስቲያን ተማሪዎች ሕብረት (ኪቶ ፋሚሉ) አባል የነበሩ ተማሪዎች መልካም ግንኙነት ሊያስቀጥል የሚችል ክርስቲያን ኔትወርኪንግ ኢቨንት ተካሄደ።

#ይህ ለሁለተኛ #ጊዜ የተዘጋጀው ፕሮግራም በዋናነት ከዩኒቨርስቲ ተመርቀው ወጥተው በተለያዩ የግል የስራ ዘርፎች የተሰማሩ ተማሪዎችን ግንኙነት ማስቀጠል #እና የተሰማሩበትን የቢዝነስ ዘርፍ አስተዋውቀው #መልካም ግንኙነት እንዲፈጠር ታስቦ የተዘጋጀ እንደሆነ የፕሮግራሙ አስተባባሪ ወንድም አቤኔዜር ማቴዎስ ለክርስቲያን ዜና ተናግሯል።

አቤኒዘር አክሎ ተማሪዎች ከዩኒቨርሲቲ ከተመረቁ በኋላ አብዛኛውን ጊዜ ግንኙነቱ ሲቀጥል አይታይም ይህን ክፍተት ለመቀነስ ያሰበ መልካም ግንኙነት እንደሆነ ተናግሯል።

ይህ ሕብረት በቀጣይ ከጅማ ዩኒቨርሲቲ ውጪ የሚገኙ ሕብረትን ለማሳደግ እንደሚሰሩ ወጣት አቤኔዜር አክሎ ለክርስቲያን ዜና ተናግሯል።

ክርስቲያን #ዜና ያናገራቸው በፕሮግራሙ #ላይ የሚሰሩትን የተለያዩ ስራዎችን ይዘው የቀረቡ የቀድሞ ተማሪዎች ይህ የህብረት ፕሮግራም ከሌሎች ጋር የመተዋወቅን እና የቢዝነስ ስራ በጋራ ለማሳደግ ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ነግረውናል።

The Christian News - የክርስቲያን ዜና በስፍራው ተገኝተን ዘገባውን አዘጋጀን ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ በክርስቲያን ዜና የዮቲዩብ ቻናል ይዘን እንመለሳለን።
#ዜና
«ዲልቢ ገለታ የሱሲፍ" የተሰኘ የመዝሙር ድግስ በሚሊኒየም #አዳራሽ ሊካሄድ ነዉ።

ኤልሀዳር ኢንጂነሪንግ ከዘማሪ ጳውሎስ ተገኝ ጋር በመተባበር «ዲልቢ ገለታ የሱሲፍ» የተሰኘውን የመዝሙር ድግስ በሚኒሊየም አዳራሽ ሰኔ 2/2016 ዓ.ም ቀን ከ7፡00 ጀምሮ ማዘጋጀቱን #ዛሬ ግንቦት 27/2016 ዓ.ም በስካይ ላይት ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል ።

#ዘማሪ ጳውሎስ ተገኝ ሶስት አልበሞችን እና የተለያዩ ዝማሬዎችን ከተለያዩ ዘማሪዎች ጋር በመስራት ለኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ያበረከተ ሲሆን «ሙጫ ካዮ» ከተሰኘ የህፃናት ህብረት ጋር በመሆን ሁለት ቪሲዲዎችን በመስራት ለአማኞች አድርሷል።

በእለቱ ስለታማ ነገሮች ምግብ እና መጠጥ ይዞ መግባት እንደማይቻል የተገለፀ ሲሆን በሚሊኒየም አዳራሽ መጠጥ እና ምግብ በሽያጭ እንደተዘጋጀ ተነግሯል።

በዚህ ፕሮግራም ለመሳተፍ የመግቢያ ዋጋው በነፃ ስለሆነ መጨናነቅ እንዳይፈጠር ከጠዋቱ 4 ሰአት ጀምሮ እንዲገኙ ጥሪ አስተላልፈዋል።

ፎቶ 📸 @ጥላሁን ደሳለኝ

#ወንጌል #ለዓለም #ሁሉ
#ዜና
#ማብቃት_ለክርስቶስ_አገልግሎት_ተማሪዎች_ምረቃ

ማብቃት ለክርስቶስ አገልግሎት የመጽሃፍ ቅዱስ ት/ቤት በማስተርስና ዲፕሎማ ሲያስተምራቸው የቆዩ ተማሪዎቹን በደማቅ ሁኔታ አስመረቀ።

ት/ቤቱ ያለፉትን 3 ዓመታት ከሃገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተወጣጡ ተማሪዎቹን ቦሌ በሚገኘው ዩ ጎ ሲቲ ቸርች ነው ያስመረቀው። ማብቃት ለክርስቶስ ትምህርቶቹን የሚሰጠው አሜሪካን ሃገር ከሚገኘው ካይሮስ ዩኒቨርሲቲ (Sioux Falls Seminary) ጋር በመተባበር ነው።

የAdams Thermal Foundation እና ማብቃት ለክርስቶስ አገልግሎት አፍሪካ ዳይሬክተር ዶ/ር ሳሙኤል ጌታቸው ለተመራቂዎች የእንኳን ደስ አላቹ መልዕክት አጋርተዋል።

ማብቃት ለክርስቶስ የመጽሃፍ ቅዱስ ት/ቤት፣ ተማሪዎችን በመጽሃፍ ቅዱስ እውቀት በማስታጠቅ ለወንጌል አገልግሎት ለማብቃት ይሰራል። አገልግሎቱ በተጨማሪም “10/40 መስኮት” በሚባለው የአለማችን ክፍል የወንጌል ተልዕኮ ሰራተኞችን በማስታጠቅ ይሰራል።
#አሳዛኝ #ዜና

በአክሱም የምትገኘዉ የቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ተዘረፈች። የቀረዉን ንብረትም አዉድመዉታል።

ከሰሞኑ 3 ቅዱሳን በአክሱም መታሰራቸዉ ይታወሳል።
#ዜና
#ወንጌል በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ለማድረስ እንሰራለን።

በዓለም ላይ ካሉት 70 ሚሊዮን መስማት የተሳናቸው ሰዎች ኢየሱስን የሚከተሉ 2 በመቶው ብቻ ሲሆኑ፣ መቀመጫውን አሜሪካ ያደረገው የ DOOR ኢንተርናሽናል ሚኒስቴር ወንጌልን መስማት ለተሳናቸው ሰዎች ለማዳረስ የሚረዳውን አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ቴክኖሎጂን ለመጠቀም መዘጋጀቱን ክርስቲያን ዴይሊ ኢንተርናሽናል አስነበበ።

DOOR ኢንተርናሽናል ሚኒስቴር ሚቺጋን ውስጥ የሚገኝ የክርስቲያን ድርጅት ሲሆን አገልግሎቱ መጽሐፍ ቅዱስን መተርጎም፣ አብያተ ክርስቲያናትን መትከል እና መሪዎችን ወንጌል ወዳልደረሰባቸው አከባቢዎች የሚልክ ሚኒስትሪ ነው።

DOOR ኢንተርናሽናል ብዙ መስማት የተሳናቸው ሰዎችን በወንጌል ለመድረስ AI የምልክት ቋንቋ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞችን የጥበብ ሥራ ለመሥራት ይቻል እንደሆነ ለማየት ሙከራዎችን እያደረገ መሆኑን እና ይህም እንዲሳካ መስማት ከተሳናቸው ሰዎች እየሰራ እንደሆነ ገልጿል።
#ዜና

የመገናኛ ብዙሃን ባለሥልጣን 4 የሃይማኖት የቴሌቭዥን ጣቢያዎችን አስጠነቀቀ

ህጋዊ ፈቃድ ሳይኖራቸው ስርጭት ላይ የሚገኙ የሃይማኖት ቴሌቪዥን ጣቢያዎችን ይመለከታል።

በመገናኛ ብዙኃን አዋጅ 1238/2013 አንቀፅ 30 መሰረት ማንኛውም ሰው ከባለሥልጣኑ የብሮድካስት ፈቃድ ሳያገኝ የብሮድካስት አገልግሎት ማሰራጫ መንገዶችን ተጠቅሞ በብሮድካስት አገልግሎት ስራ ላይ መሰማራት የተከለከለ መሆኑ ተደንግጓል፡፡

በዚሁ መሰረት በአሁኑ ወቅት 43 የሃይማኖት ቴሌቪዥን ጣቢያዎች በመገናኛ ብዙኃን አዋጅ 1238/2013 አንቀጽ 40 ንዑስ አንቀጽ 3/ለ መሰረት የሚጠበቅባቸውን ቅድመ ሁኔታ በማሟላት ከባለሥልጣኑ የሃይማኖት ቴሌቪዥን ፈቃድ አውጥተው በእንቅስቃሴ ላይ ይገኛሉ፡፡

#ይሁን እንጂ ...
1. ኦሲኤን (OCN Tv)
2. ሐሪማ ቴሌቪዥን (Harima Tv)
3. ፕረዘንስ ቴሌቪዥን ( Presence Tv ) እና
4. ጀሰስ ወንደርፉል ቴሌቪዥን (Jesus Wonderful Tv )

የተሰኙ የሃይማኖት ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ከባለሥልጣኑ ህጋዊ ፈቃድ ሳያወጡ በስርጭት ላይ መሆናቸውን ባደረግነው የክትትል ስራ ማረጋገጥ ችለናል፡፡

በመሆኑም ከላይ ስማችሁ የተጠቀሰ የሃይማኖት ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ከዛሬ ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎችን በማሟላት ፈቃድ እንድታወጡ እያሳሰብን ይህን በማታደርጉት ላይ ህጋዊ እርምጃ የምንወስድ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን
#ዜና እረፍት

የ#ኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት ህጋዊ ዕውቅና ባገኘበት ዘመንና ከዚያ መለስ ባሉት ዓመታት ኅብረቱን በተባባሪ ዋና ጸሐፊነት የመሩት አቶ ሙላቱ ታዬ ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው በዛሬው ዕለት ወደ አምላካቸው ዕቅፍ ተሰብስበዋል።

አቶ ሙላቱ ታዬ፣ በኅብረቱ የምሥረታ ዓመታት ተቋሙ ተጠናክሮ እንዲወጣ በብዙ የተጉ፣ በአባል ቤተ እምነቶች ዘንድም ተወዳጅና የተከበሩ ነበሩ።

የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት፣ በወንድማችን፣ በሥራ ባልደረባችንና በአባታችን እረፍት የተሰማውን ጥልቅ ኀዘን እየገለጸ፣ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጆቻቸውና ለመላው ወንጌላውያን አማኞች መጽናናትን ይመኛል። ሲል ሕብረቱ በላከልን መረጃ ገልጿል።

The Christian News - የክርስቲያን ዜና በአቶ ሙላቱ ሕልፈተ ሕይወት የተሰማንን ሀዘን እየገለፅን ለቤተሰቦቻቸው እና ለወዳጆቻቸው መፅናናትን እንመኛል።