The Christian News
5.38K subscribers
3.07K photos
27 videos
724 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
ስፒከር የመታቸው #ግለሰብ
#እግዚአብሔር #ይመስገን #ደህና #ናቸዉ

#በዘማሪ #በረከት #ተስፋዬ የመድረክ አገልግሎት #ወቅት የሙዚቃ ስፒከር ወድቆ አንድ ሰው ላይ ጉዳት ሲያደርስ የሰሞኑን ማህበራዊ #ሚድያ መቀባበያ ሆኗል።

ከሁለት አመት በፊት በቡታጅራ ከተማ ተደርጎ በነበረ መንፈሳዊ ኮንፈራንስ አንድ አባት ላይ ትልቅ እስፒከር ሲወድቅ የሚያሳይ ቪድዮ በማህበራዊ ሲመላለስ ነበረ። በወቅቱ ግለሰቡ ላይ ትልቅ ጉዳት አስከትሎ እንደነበረ ዘማሪው ገልጿል።

ሆኖም ድርጊቱ የተፈጸመው ከሁለት አመት በፊት ሲሆን፣ በወቅቱን ከስፒከሩ ክብደት አንጻር እኚህ ግለሰብ ላይ የጤና እክል አድርሶ እንደነበረ ዘማሪው ገልጿል።

በወቅቱም አስፈላጊው የህክምና ክትትል እንደተደረገም ዘማሪ በረከት ገልጿል። በአሁኑ ወቅት ግለሰቡ በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኝ ገልጿል።

ከዚህም የከፋ የመድረክ አካባቢ ጉዳቶችን በአገልግሎት ዘመን አይቻለው ያለው ዘማሪ በረከት፣ አስተባባሪዎች፣ አገልጋዮች ይሄንን አይታችሁ መድረክ አካባቢ ጥንቃቄ እንድታደርጉ አደራ እላለሁ ብሏል።
#አስደሳች #ዜና

የወንጌላውያን #ሚድያ ባለሙያዎች ማህበር ተመሰረተ።

በቢሾፍቱ ሊሳክ ሪዞርት በተካሄደ ምስረታ ጉባኤ #ላይ ከተለያዩ የሚድያ ተቋማት የተውጣጡ የሚድያ ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

በመረሀ ግብሩ ምስረታ ወቅት ማህበሩን ለመመስረት የተካሄደባቸውን የስራ ሪፖርቶች ለተሳታፊዎቹ ያቀረበ ሲሆን በመሀበሩ መተዳደሪያ ደንብ ማርቀቅ ዙሪያ ውይይት ተካሂዶ የማሻሻያ ሀሳቦች ቀርበው መተዳደሪያ ደንቡ ጸድቋል።

በእለቱም የማህበሩን ፕሬዝዳንት እና ምክትል ፕሬዝዳንት እንዲሁም የቦርድ አባላት የተመረጡ ሲሆን በዚህም መሰረት የማህበሩ ፕሬዝዳንት በመሆን ወንድም ዘሪሁን ግርማ ምክትል ፕሬዝዳንት ወንድም መሳይ አለማየሁ የተመረጡ ሲሆን ዘጠኝ የማህበሩ የቦርድ አባላትም ተመርጠዋል።

በእለቱም የጸሎትና #የእግዚአብሄር ቃል በመካፈል ፕሮግራምም ተካሄዷል።

The Christian News - የክርስቲያን ዜና በማሕበሩ ምስረታ ሒደት ዉስጥ በበጎ ፍቃደኝነት ከፍተኛ ስራ ለሰሩ አባላት ምስጋናውን እያቀረበ።

በዛሬዉ እለት ማሕበሩን በቀጣይ ለመምራት ሃላፊነት ለተቀበሉ መሪዎች #መልካም የስራ ዘመን እንዲሆን እንመኛለን።