#እይታ
#Opinion
ክርስቶስ የኔ ባላት ቤ/ክ ውስጥ ንግድ ሲበዛ፣ እራሱ ተነስቶ በጅራፍ ነጋዴዎችን ከቤቱ አባሯል። ዮሃ 2፡14-16
ክርስቶስ ፍቅር ነው ተብሎ ሲሰበክ፣ ጅራፍ አንስቶ ማይገረፍ ለሚመስለን፣ ለቤቱ ምን ያክል ቀናተኛ አምልካ መሆኑን ብናውቅ ቤቱን መነገጃ አናደርገውም ነበረ።
ማርቲን ሉተር በ16ኛው ክ/ዘመን ቤ/ክ ተሃድሶ ያስፈልጋታል ብሎ በተቃውሞ እንደተነሳ ታሪክ ያስታውሳል። ለዛ እኛም ዛሬ ድረስ ፕሮቴስታንት/ፕሮቴስተር/ ተብለን እንጠራለን።
ያኔ ክርስቶስን ፈሪሳዊያንና ቄሳር እንደተቃወሙት ሁሉ፣ ሉተርንም ተቃውመው ሊገድሉት ዶልተዋል። አንድ ጎበዝ የወንጌል ሰባኪ በትምህርቱ “ክርስቶስን የሰቀለች አለም፣ ለኛ አትራራልንም” እንዳለው፣ በኛም ዘመን እግዚዓብሔር ቤቱን መነገጃ አታድርጉት ብሎ መነሳት ብዙ ዱላ ያስከትላል።
ዛሬም ቤ/ክ ተሃድሶ ያስፈልጋታል። ክርስቶስ በስጋ መካከላችን ቢኖር እነማንን በዱላ ከቤቱ እንደሚያባር አስቡት። ጳውሎስ በህይወት ቢኖር ለኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን 7 ወይም 8 መጽሃፍ የሚወጣቸው ደብዳቤዎች የሚልክ አይመስላችሁም?
ሰሞኑን “ተሃድሶ ሲታወስ፣ ወንጌላዊያንና የህይወት ለውጥ” በሚል ርዕስ አንድ መሰናዶ በካዛንቺስ ኡራኤል መካነ ኢየሱስ ማህበረ ምዕመናን ተዘጋጅቷል።
የፊታችን ቅዳሜ ጥቅምት 17 የቻልን ወደ ስፍራው ሄደን ስለ ቤተ ክርስቲያን ተሃድሶ እንምከር።
ዋናው መልዕክት ሰሞኑን ተሃድሶ ሲታወስ 505ኛ አመት ነው። እኛስ ባለንበት ህብረትና ማህበር ምን ይታደስ ዘንድ ክርስቶስ ይሻል?
በኦቦሌሳ አዶላ

የሰሞኑን #አንድ #ሁለት ዜናዎች ልንገራችሁ።
የቄስ ጉዲና ቱምሳ ባለቤት ጸሃይ ቶሎሳ ግለ #ታሪክ ተመርቋል። መጽሃፉ “በእቶን እሳት ውስጥ” የሚል ነው። የነዚህ ብርቱ እናት ታሪክ እና ምስክርነት ለአንድ አንድ ሰዎች የእምነት መልህቅ ሊሆን ይችላል፣ ቢባል ማጋነን አይሆንም።
ሌላው #ዜና ደግሞ በፌደራል መንግስትና #መንግስት ሸኔ በሚለው እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ብሎ በሚጠራው ቡድን መካከል የተደረገው የሰላም ድርድር አሁንም ሳይሳካ ቀርቷል።
ይሄንን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደህንነት ጉዳዮች አማካሪ ሬድዋን ሁሴን አረጋግጠዋል። ከዚህ የሰላም ድርድር #መልካም ውጤት ይገኛል በሚል፣ ክርስቲያኑ ምነኛ ጓጉቶ እንደነበረ ማሰብ አይከብድም።
በተመሳሳይ ክፍለ ዘመን #ውስጥ ፣ በተመሳሳይ ርዕሳቸው፣ ረግጦ በሚገዛ መንግስት፣ የወንጌልን ነጻ አውጪነት አውጀው፣ የተገደሉ የዘመናት ክስተቶች ላውራችሁ።
#ቄስ_ዴትሪች_ቦንሆፈር በ1906 በጀርመን ብሬስሎው በተባለ ስፍራ የተወለዱ #ሰው ናቸው። እኚህ ሰው ስነ መለኮት አጥኚ ወይም ቲዎሎጂያን፣ ኮንፌሲንግ በተባለች ሉተራዊ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ቄስ #እና ጸረ ናዚ ሰው ነበሩ።
የአዶልፍ ሂትለር ተቃዋሚ መሆን የዋዛ ነገር አይምሰላችሁ። ከናዚው አዶልፍ ሂትለር የአስተዳደር እቅዶች መካከል “ኢውታናዢያ” የሚባል ፕሮግራም ነበረ ይባላል። በዚህ ፕሮግራማቸው ሰው ከሚሰቃይ ቀድሞ መሸኘት የሚል ነው።
#ትንሽ የታመመ የመዳን ተስፋ ሳይሆን፣ ከህመሙ ማረፊያ መግደል ያሰበ “በጣም ቅን ሰው ናቸው” ነበረ። ይሁዲዎች #ላይ ያደረገውን ጭካኔ፣ አለም ያወቀው ነው። ቦንሆፈር ይሄንን ስርዓት ነበረ በአደባባይ ቆሞ የተቃወመው። ያው በእሳት ፊት ቆሞ ነበረና እሳቱ በላው። በተወለደ በ39ኛ አመቱ የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌልን ሰብኮ ተሰቅሎ ተገደለ።
#ቄስ_ጉዲና_ቱምሳ በ1929 በኢትዮጵያ ወለጋ ቦጂ ከተማ የተወለዱ ሰው ናቸው። ተስፋ አደርጋለው ስለ ቄስ ጉዲና የማያውቅ ወንጌላዊ ክርስቲያን፣ ኢትዮጵያ ውስጥ አለ ማለት ይከብዳል። ግን ዝም ብዬ ታሪኩን ልንገራችሁ።
እኚህ ቄስ የስነ መለኮት አጥኚ #ወይም ቲዎሎጂያን፣ #የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ በተባለች ሉተራዊ ቤ/ክ ውስጥ ቄስ እና በሃያሉ ደርግ መንግስት ፊት የቆሙ ሰው ነበሩ። የደርግ ተቃዋሚ መሆንም የዋዛ ነገር አይደለም።
ኮለኔል መንግስቱ ማለት፣ በርሳቸው ዘመን በለጋ እድሜው አፈር የገባ ወጣት፣ በቀይ ሽብር ስም ያለቀው ተቀናቃኝ ፖለቲከኛና ለገዛ አጋሮቻቸው ያልተመለሱ ባለ ደም እጅ ሰው ነበሩ። ያ ኮለኔል መንግስቱና አገዛዙም ነበር ሆኗል።
እግዜር ደጉ፣ የማያሳልፈው የለም። ቄሱ ጉዲና በዚህ ለአፍሪካ እንኳን አይመለስም በተባለ ወታደር ፊት ቆመው “ወንጌል ነጻ ያወጣል” ብለው ሰብከዋል። እሳቸውም እሳት ፊት ቆመዋልና እሳት በላቸው። በተወለዱ በ50 አመታቸው የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ሰብከው በደርግ ወታደሮች ተገደሉ።
የነዚህ ሁለት በእሳት ፊት የቆሙ ቀሳውስት ህይወት፣ በሄሮድስ ፊት ቆሞ እውነት ተናግሮ አንገቱ የተቀላውን መጥምቁ ዮሃንስን ህይወት ይመስላል። የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት፣ በአስፈሪው የሮማ መንግስት ፊት፣ በአይሁድ ካህናት ፊት፣ በፈሪሳዊያንና ግሪካዊያን ፊት “እናንተ የእፉኝት ልጆች እያሉ”፣ መኖር ሳያሳሳቸው፣ መሞት ሳያስፈራቸው ወንጌልን የሰበኩ ጀግኖች ናቸው።
ቄስ ቦንሆፈርና ቄስ ጉዲናም በአፈ ሙዝ እንጂ በአፉ በማያወራ መንግስት ፊት ቆመው፣ መኖር ሳያጓጓቸው፣ ሞት ሳያስፈራቸው ወንጌልን ሳይቀንሱና ሳይጨምሩበት የሰበኩ የቤተ ክርስቲያን ቅሬታዎች፣ የክርስቶስ ልጆች ናቸው።
ዛሬስ መምህሩ፣ ጳጳሱ፣ ቄሱ፣ ፓስተሩ፣ ነብዩ፣ ሐዋርያው፣ ሼፐርዱ፣ ዳዲው የቱ ጋር ቆመሃል? ጌታ ኢየሱስ በጎቼን ጠብቅ ያለው ስመኦን ጴጥሮስ፣ ከአለም 20በመቶ ህዝብን በሚገዛው ግዙፉ የሮማ መንግስት ተዘቅዝቆ ተሰቀለ።
አንተስ በጎቼን ጠብቅ የተባልከው እረኛ ሆይ ፣ ለበጎቹ ስትል፣ እንደ ስመኦን ጴጥሮስ ተዘቅዝቀህ ለመሰቀል፣ እንደ ቦንሆፈር በናዚ ለመሰቀል፣ እንደ ጉዲና በደርግ ወታደር የአሞራ ሲሳይ ለመሆን #ተዘጋጅተሃል?
ክርስቲያን ሆኖ መኖር እራሱ ዋጋ በሚያስከፍልበት በዚህች ምድር ላይ ለወንጌል ዋጋ ለመክፈል የተዘጋጀህ ነህ ወይስ፣ ለአገልግሎትና ለእረፍት በV8 እና FORD F150 የምትምነሸነሽ #ሆነሃል? አለም ህይወት የሆነውን ክርስቶስን ለመስቀል ካልራራች፣ አንተ እውነተኛውን የርሱን ህይወት የምትሰብከውን የምትምርህ #ይመስልሃልን?
ዙሪያ ገባህን አይተህ ወንጌል የሚሰበክ ከጠፋ፣ ከተኩላ የምትጠብቀው በግ ከሌለ፣ ምናልባት ወንጌሉ የሚያስፈልገው፣ እረኝነቱ የሚያስፈልገው፣ ላንተው እራስህ እንዳይሆን የቆምክበትን አስተውል?