The Christian News
5.32K subscribers
3.06K photos
27 videos
720 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
#እንኳን #ደስ #አሎት 🙏🙏

#በኢትዮጵያ #ቤተክርስቲያን ወንጌልን በቃልና በኑሮ ምሳሌ በመሆን ያገለገሉት #የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት ፕሬዝደንት መጋቢ ጻድቁ አብዶ እዉቅና ተሰጣቸው።

መሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን 92ኛው ጠቅላላ የመሪዎች ጉባኤ በቢሾፍቱ ከተማ በቤተክርስቲያኗ ኮሌጅ ቅጥር ግቢ እየተካሄደ ይገኛል።

በዚህም ጉባኤ በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ወንጌልን በቃልና በኑሮ ምሳሌ በመሆን ያገለገሉ ቀደምት አባቶች #የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት ፕሬዝደንት መጋቢ ጻድቁ አብዶን ጨምሮ የመሠረተ ክርስቶስና የሌሎች ቤተዕምነት አገልጋዮች ዕውቅና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

በጉባኤው ላይ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች ካዎንስል ጠቅላይ ጸሐፊ ቄስ ደረጄ ጀምበሩን ጨምሮ የተለያዩ የቤተዕምነት መሪዎች ተገኝተዋል።

በጉባኤ ላይ በተለይ መልኩ አስከ ዛሬ እውነተኛውን የእግዚአብሔርን ቃል እውነት በመስበካቸው በመልካም ምሣሌነታቸው ከተመሰከረላቸው መካከል ለአሁኑ 10 ከሌሎች ቤተዕምነቶች 11 ደግሞ ከመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በአጠቃላይ 21 አገልጋዮች በጉባኤ ፊት እውቅና ተበርክቶላቸዋል።

ይህ የእውቅና መርሃግብር ወደፊት በስፋት እንደሚቀጥል የቤተክርስቲያኒቱ ፕሬዚዳንት መጋቢ ደሣለኝ አበበ ገልፀዋል።
#እንኳን #ደስ #አሎት
#አንገፋው_ዘማሪ_መጋቢ_ሸዋዬ_ዳምጤ በሮም #የኢትዮጵያ_ወንጌላዊት_ቤተክርስቲያን_ዋና_መጋቢ ሆነው #ተሾሙ

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል ጠቅላይ ጸሃፊ ቄስ ደረጀ ጀምበሩ የክብር እንግዳ ሆነው ተገኝተዋል።

ኦክቶበር 1/ 2023 ከ4 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት ድረስ በነበረው የአንገፋው የዘማሪ መጋቢ ሸዋዬ ዳምጤ የዋና መጋቢ ሹመት መርሃ ግብር ላይ የተለያዩ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ሲገኙ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል ጠቅላይ ጸሃፊ የሆኑት ቄስ ደረጀ ጀምበሩ የክብር እንግዳ ሆነው በመገኘት የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት አቅርበዋል።

በመቀጠልም ለሚቀጥሉት ዘመናት በሮም የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን ዋና መጋቢ ሆነው ለሚያገለግሉት ለዘማሪ መጋቢ ሸዋዬ ዳምጤ በቤተክርስቲያኗ መሪዎች የሹመት ስርዓትና ጸሎት ተደርገሏቸውል።

ዘማሪ መጋቢ ሸዋዬ ዳምጤ በቀሪው ዘመናቸው በተሰጣቸው ሀላፊነት በታማኝነትና በትጋት የእግዚአብሔርን ፍቃድ ለማገልገል የጌታ ጸጋ እንደሚረዳቸው ገልጸዋል።

ዘማሪ መጋቢ ሸዋዬ ዳምጤ በኢትዮጵያ ወንጌላውያን የዝማሬ ታሪክ ውስጥ ስማቸው በጉልህ ከሚጠቀሱት ቀዳሚ እና ለእግዚአብሔር ህዝብ የሚባርኩ ዝማሬዎችን እንዳቀረቡ ይታወቃል።
#እይታ
#Opinion

የሰሞኑን #አንድ #ሁለት ዜናዎች ልንገራችሁ።

የቄስ ጉዲና ቱምሳ ባለቤት ጸሃይ ቶሎሳ ግለ #ታሪክ ተመርቋል። መጽሃፉ “በእቶን እሳት ውስጥ” የሚል ነው። የነዚህ ብርቱ እናት ታሪክ እና ምስክርነት ለአንድ አንድ ሰዎች የእምነት መልህቅ ሊሆን ይችላል፣ ቢባል ማጋነን አይሆንም።

ሌላው #ዜና ደግሞ በፌደራል መንግስትና #መንግስት ሸኔ በሚለው እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ብሎ በሚጠራው ቡድን መካከል የተደረገው የሰላም ድርድር አሁንም ሳይሳካ ቀርቷል።

ይሄንን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደህንነት ጉዳዮች አማካሪ ሬድዋን ሁሴን አረጋግጠዋል። ከዚህ የሰላም ድርድር #መልካም ውጤት ይገኛል በሚል፣ ክርስቲያኑ ምነኛ ጓጉቶ እንደነበረ ማሰብ አይከብድም።

በተመሳሳይ ክፍለ ዘመን #ውስጥ ፣ በተመሳሳይ ርዕሳቸው፣ ረግጦ በሚገዛ መንግስት፣ የወንጌልን ነጻ አውጪነት አውጀው፣ የተገደሉ የዘመናት ክስተቶች ላውራችሁ።

#ቄስ_ዴትሪች_ቦንሆፈር በ1906 በጀርመን ብሬስሎው በተባለ ስፍራ የተወለዱ #ሰው ናቸው። እኚህ ሰው ስነ መለኮት አጥኚ ወይም ቲዎሎጂያን፣ ኮንፌሲንግ በተባለች ሉተራዊ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ቄስ #እና ጸረ ናዚ ሰው ነበሩ።

የአዶልፍ ሂትለር ተቃዋሚ መሆን የዋዛ ነገር አይምሰላችሁ። ከናዚው አዶልፍ ሂትለር የአስተዳደር እቅዶች መካከል “ኢውታናዢያ” የሚባል ፕሮግራም ነበረ ይባላል። በዚህ ፕሮግራማቸው ሰው ከሚሰቃይ ቀድሞ መሸኘት የሚል ነው።

#ትንሽ የታመመ የመዳን ተስፋ ሳይሆን፣ ከህመሙ ማረፊያ መግደል ያሰበ “በጣም ቅን ሰው ናቸው” ነበረ። ይሁዲዎች #ላይ ያደረገውን ጭካኔ፣ አለም ያወቀው ነው። ቦንሆፈር ይሄንን ስርዓት ነበረ በአደባባይ ቆሞ የተቃወመው። ያው በእሳት ፊት ቆሞ ነበረና እሳቱ በላው። በተወለደ በ39ኛ አመቱ የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌልን ሰብኮ ተሰቅሎ ተገደለ።

#ቄስ_ጉዲና_ቱምሳ በ1929 በኢትዮጵያ ወለጋ ቦጂ ከተማ የተወለዱ ሰው ናቸው። ተስፋ አደርጋለው ስለ ቄስ ጉዲና የማያውቅ ወንጌላዊ ክርስቲያን፣ ኢትዮጵያ ውስጥ አለ ማለት ይከብዳል። ግን ዝም ብዬ ታሪኩን ልንገራችሁ።

እኚህ ቄስ የስነ መለኮት አጥኚ #ወይም ቲዎሎጂያን፣ #የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ በተባለች ሉተራዊ ቤ/ክ ውስጥ ቄስ እና በሃያሉ ደርግ መንግስት ፊት የቆሙ ሰው ነበሩ። የደርግ ተቃዋሚ መሆንም የዋዛ ነገር አይደለም።

ኮለኔል መንግስቱ ማለት፣ በርሳቸው ዘመን በለጋ እድሜው አፈር የገባ ወጣት፣ በቀይ ሽብር ስም ያለቀው ተቀናቃኝ ፖለቲከኛና ለገዛ አጋሮቻቸው ያልተመለሱ ባለ ደም እጅ ሰው ነበሩ። ያ ኮለኔል መንግስቱና አገዛዙም ነበር ሆኗል።

እግዜር ደጉ፣ የማያሳልፈው የለም። ቄሱ ጉዲና በዚህ ለአፍሪካ እንኳን አይመለስም በተባለ ወታደር ፊት ቆመው “ወንጌል ነጻ ያወጣል” ብለው ሰብከዋል። እሳቸውም እሳት ፊት ቆመዋልና እሳት በላቸው። በተወለዱ በ50 አመታቸው የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ሰብከው በደርግ ወታደሮች ተገደሉ።

የነዚህ ሁለት በእሳት ፊት የቆሙ ቀሳውስት ህይወት፣ በሄሮድስ ፊት ቆሞ እውነት ተናግሮ አንገቱ የተቀላውን መጥምቁ ዮሃንስን ህይወት ይመስላል። የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት፣ በአስፈሪው የሮማ መንግስት ፊት፣ በአይሁድ ካህናት ፊት፣ በፈሪሳዊያንና ግሪካዊያን ፊት “እናንተ የእፉኝት ልጆች እያሉ”፣ መኖር ሳያሳሳቸው፣ መሞት ሳያስፈራቸው ወንጌልን የሰበኩ ጀግኖች ናቸው።

ቄስ ቦንሆፈርና ቄስ ጉዲናም በአፈ ሙዝ እንጂ በአፉ በማያወራ መንግስት ፊት ቆመው፣ መኖር ሳያጓጓቸው፣ ሞት ሳያስፈራቸው ወንጌልን ሳይቀንሱና ሳይጨምሩበት የሰበኩ የቤተ ክርስቲያን ቅሬታዎች፣ የክርስቶስ ልጆች ናቸው።

ዛሬስ መምህሩ፣ ጳጳሱ፣ ቄሱ፣ ፓስተሩ፣ ነብዩ፣ ሐዋርያው፣ ሼፐርዱ፣ ዳዲው የቱ ጋር ቆመሃል? ጌታ ኢየሱስ በጎቼን ጠብቅ ያለው ስመኦን ጴጥሮስ፣ ከአለም 20በመቶ ህዝብን በሚገዛው ግዙፉ የሮማ መንግስት ተዘቅዝቆ ተሰቀለ።

አንተስ በጎቼን ጠብቅ የተባልከው እረኛ ሆይ ፣ ለበጎቹ ስትል፣ እንደ ስመኦን ጴጥሮስ ተዘቅዝቀህ ለመሰቀል፣ እንደ ቦንሆፈር በናዚ ለመሰቀል፣ እንደ ጉዲና በደርግ ወታደር የአሞራ ሲሳይ ለመሆን #ተዘጋጅተሃል?

ክርስቲያን ሆኖ መኖር እራሱ ዋጋ በሚያስከፍልበት በዚህች ምድር ላይ ለወንጌል ዋጋ ለመክፈል የተዘጋጀህ ነህ ወይስ፣ ለአገልግሎትና ለእረፍት በV8 እና FORD F150 የምትምነሸነሽ #ሆነሃል? አለም ህይወት የሆነውን ክርስቶስን ለመስቀል ካልራራች፣ አንተ እውነተኛውን የርሱን ህይወት የምትሰብከውን የምትምርህ #ይመስልሃልን?

ዙሪያ ገባህን አይተህ ወንጌል የሚሰበክ ከጠፋ፣ ከተኩላ የምትጠብቀው በግ ከሌለ፣ ምናልባት ወንጌሉ የሚያስፈልገው፣ እረኝነቱ የሚያስፈልገው፣ ላንተው እራስህ እንዳይሆን የቆምክበትን አስተውል?
#የኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናት ምክር #ቤት ሊቋቋም ነው ተባለ።

የኢትዮጵያ #ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን፣ የኢትዮጵያ #ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን እና የኢትዮጵያ #ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ናቸው በኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤትን ለማቋቋም የተስማሙት።

ምክር ቤቱን ለማቋቋም ያስፈለገው፣ በሃገሪቱ አስፈላጊ የሆነውን አስቸኳይ ሰብዓዊ ድጋፍ፣ #ሰላም እና ማህበራዊ መስተጋብርን ለማጠናከር መሆኑ ተገልጿል።

#በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት #ወደ 20 ሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎች በግጭትና ተፈጥሮአዊ ችግሮች ሳቢያ አስቸኳይ ሰብዓዊ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል።

በአብያተ ክርስቲያናቱ መሪዎች መካከል ከህዳር 17-20 ድረስ ሰፊ ውይይት ሲካሄድ ቆይቷል ነው የተባለው።

ከስምምነቱ የተገኘ ቃለ ጉባኤ እንደሚያሳየው፣ ህብረቱ የተነጠሉ ተቋማት ቡድን ብቻ እንዲሆን የታሰበ አይደለም ይላል። ነገር #ግን ደግሞ ማንም አካል ያለ መመዘኛ መጥቶ የሚገባበትም አይሆንም ሲል ያስቀምጣል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ወክለው አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) ፣ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስን ወክለው ቄስ ዮናስ ዮናስ ይገዙ (ዶ/ር)፣ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያንን ወክለው ካርዲናል ብርሃነ ኢየሱስ ሱራፌል ተፈራርመዋል።

ህብረቱን #ወደፊት ለማስኬድ ይረዳ ዘንድ ግብረ ሃይልም ተቋቁሟል።

“እውን የሆነው የኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት፣ ለረጅም አመታት በውይይት ላይ የነበረ ነው፣ ለዚህ ስትሰሩ የነበራችሁ መሪዎች፣ ምስጋና ይገባቸዋል” ሲሉ ቄስ ዶ/ር ዮናስ ይገዙ ምስጋናቸውን ችረዋል።

አክለው #አሁን በክርስቶስ የምናምን ሁላችን በአንድ #ጥላ ስር ሆነን የህዝባችንን የሰላም፣ ፍትህ እና እርቅ ጥሪ በጋራ መልስ የምንሰጥበት አጋጣሚ ነው ብለዋል።
#እስካሁን ከመንግስት ምንም #ፍትህ አላገኘንም

ይህንን ያለችዉ #የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ በዛሬዉ እለት #ጊዳሚ መካነ #ኢየሱስ ምዕመናን ላይ የደረሰዉን ግፍ አስመልክታ በሰጠችዉ ጋዜጣዊ መግለጫ ነዉ።

ቤተክርስቲያኒቱ በሰጠችዉ መግለጫ በወለጋ ጊዳሚ መካነ ኢየሱስ #ቤተክርስቲያን ተወስደው ከተገደሉ 9 #ሰዎች መካከል #5ቱ_ከአንድ_ቤተሰብ መሆናቸው ተገልፆል።

ቤተሰቦቻቸውን #እና ወዳጅ ዘመዶቻቸውን ላጡ ወገኖች ቤተ ክርስቲያኗ መጽናናትን የተመኘች ሲሆን ቤተ ክርስቲያኗ ፍትህን ከመንግስት ለማግኘት ስትጠባበቅ የቆየች ቢሆንም፣ ለአሁኑን ጥቃትም ይሁን ከዚህ በፊት ለተፈጸሙ ጥቃቶች ከመንግስት ዘንድ ምንም አይነት የፍትህ ምላሽ ሳታገኝ ቀርታለች ብሏል።

በጥቃቱ ህይወታቸውን ያጡ ወገኖች ስም ዝርዝር

1. ተሊላ ለሜሳ ታሲሳ
2. ቶሊና ለሜሳ ታሲሳ
3. ታምራት ለሜሳ ታሲሳ
4. ቀበና ቡልቻ ጉተማ
5. ጌታቸው ቤከታ ታይሳ
6. ሂካ አያና ያደሳ
7. ጅረኛ ድንገታ ቴሶ
8. ሰለሞን ድንገታ ቴሶ
9. ሲራጅ ደኑ

መግለጫዉ አክሎ አሁንም መንግስት ዘላቂ #ሰላም እንዲያስከበር፣ ፍትህ እንዲሰፍንና ዜጎች በነጻነት ወጥተው መግባት፣ የአምልኮ ነጻነታቸውን እንዲያስጠብቅ እንደ ከዚህ ቀደሙ ጥሪዋን ታቀርባለች ብሏል መግለጫው።

የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤ/ክ መካነ ኢየሱስ ፕሬዝዳንት ቄስ ዶ/ር ዮናስ ይገዙ በጉዳዩ ላይ የሰጡት መግለጫ ከዚህ በታች ተያይዟል።
በርግጥ ወንጌላውያን #በዚህ ደረጃ ፍትሕ ተጓድሎባቸዋል ?

#ይህንን #ጥያቄ #ለምን በተደጋጋሚ ማንሳት አስፈለገ ?

ሁላችሁም መልሱን አዘጋጁ #እኛ #ግን የራሳችንን ሃሳብ እንሰነዝራለን።

በትላንትናዉ ዕለት #የኢትዮጵያ #ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካዉንስል በወንጌላዊያን አማኞች እና አብያተክርስቲናት ላይ እየደረሰ ስላለዉ ፍትህ መጓደል ለሚዲያዎች ጋዜጣዊ #መግለጫ ሰጥቷል።

በካውንስሉ ጠቅላይ ጽሐፊ አማካኝነት በተሰጠዉ መግለጫ #ላይ በዋናነት ከ 6 በላይ .. የሆኑ (የደረሱ የፍትሕ መጓደል) የሚያሳዩ ነጥቦች ተጠቅሰዋል።

1. በደርግ #ዘመን የተወረሱ የቤተክርስቲያን ይዞታዎች በኢሕአዴግ ዘመን በከፊል ቢመለሱም እስካሁን ያልተመለሱ የኦሎምፒያ መሰረተ #ክርስቶስ ፣ የአዲስ ከተማ ገነት፣ የኢትዮጵያ ወንንጌላዊት #ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ብረት የሆነው የጉድ ሼፐርድ ማዕከል ፣ቄራ አካባቢ ያለው የብርሃነ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን አዳራሽ፣እና ሌሎች እስካሁን ያልተመለሱ ይዞታዎች ሲሆኑ እነዚህ ይዞታዎች የቤተክርስቲያን ንብረት በመሆናቸዉ እንዲመለሱ ተጠይቋል።

2 የድሬዳዋ መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን #በአንድ ወር #ጊዜ ዉስጥ ይዞታዋን ለቃ እንድትነሳ የከተማዉ አስተዳደር የወሰንኑ ቢሆንም የከተማዉ አስተዳደር እና የቤተክርስቲያኒቱ መሪዎች እንዲሁም የካውንስሉ አመራሮች ሰፊ ዉይይት አድርገዉ የከተማዉ አስተዳደር ጉዳዩን እየመከረበት ይገኛል። የከተማዉ አስተዳደር የደረሰበትን ደረጃ በአጭር ጊዜ ግልፅ እንዲያደርግ ተጠይቋል።

3 የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር የሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን ይዞታ ነጥቆ የራሱ ጽህፈት #ቤት አድርጎት ይገኛል። እንዲሁም የቃለ #ህይወት ቤተክርስቲያን ይዞታ የሆነዉን የኩሪፍቱ የጸሎት ማዕከል በተመለከተም በማእከሉ #ምንም አይነት የልማት #ስራ ቤተ ክርስቲያን እንዳታከናወን በማገድ የቤተክርስቲያኑን ይዞታ ለመንጠቅ እንቅስቃሴ ላይ እንደሚገኝኝ ተገልጾ የቢሾፍቱ #ከተማ አስተዳደር ከዚህ ህገወጥ ድርጊቱ እንዲቆጠብ እና የወሰደዉን የቤተክርስቲያን ንብረት እንዲመልስ ተጠይቋል።

4. በአዲስ አበባ ዙሪያ ባለችው የሸገር ከተማም የፈረሱ የወንጌላዊያን የእምነት ተቋማት ይዞታቸዉ እንዲመለስ እንዲሁም በከተማዋ ለ23 አብያተክርስቲያናት ከካቢኔ #ቦታ ተወስኖላቸዉ ቦታቸዉን መረከብ ላልቻሉ በአፋጣኝ ካቢኔ የወሰነዉ ዉሳኔ ተግባራዊ እንዲሆን ተጠይቋል።

5 የመቃብር ስፍራን ጥሶ በመግባት እየተደረገ የሚገኘዉ አግባብ ያልሆነ ተግባር በአስቸኳይ እንዲቆም

6 በምዕራብ ኢትዮጵያ በቄለም ወለጋ ዞን በጊዳሜ ወረዳ ዘጠኝ ምእመናንን የአምልኮ ስነስርአት እየፈፀሙ ካሉበት ሌሊት ላይ ተወስደዉ መረሸናችው #እጅግ #አሳዛኝ እንደሆነና ለነዚህ ንፁሃን ፍትህ እንዲሰጥ ተጠይቋል።

በአጠቃላይ #ይህ #ሁሉ እየሆነ ያለዉ የታችኛዉ የመንግስት አካል የመንግስትን ስልጣን በመጠቀም ጥቂት ግለሰቦች የግል አጀንዳ ይዘዉ የሚፈፅሙት ተግባር ነዉ።

የፌደራል መንግስት ጣልቃ በመግባት ፍትህ ሊያሰፍን ይገባል ሲል የኢትዮዽያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት #ካዉንስል በመግለጫዉ አስታዉቋል።

#ታዲያ ይህ ሁሉ የፍትህ ጥያቄ አለ #ማለት መጀመሪያላይ ለጠየኩት ጥያቄ ትክክለኛ ምላሽ በርግጥም ወንጌላውያን በግልፅ በአደባባይ #ፍትሕ ተነፍገዋል የሚል ነዉ።

ይሄንን ጥያቄ በዚህ ሰዓት ለምን ማንሳት አስፈለገ ከተባለ ደግሞ ከዚህ በፊት ለበርካታ አመታት ምላሽ ያላገኙ እና ፍትህ ያልተሰጣቸው ጥያቄዎች ባለበት ዛሬም ሌላ በደል እየደረሰ ስለሆነ ማንሳት አስፈላጊ ነዉ።

The Christian News - የክርስቲያን ዜና የወንጌላውያን ድምፅ በመሆን ለበርካታ ጊዜያት ሲያገለግል ቆይቷል። አሁንም ገና ለቤተክርስቲያን ፍትህ ካልተሰጠ በስተቀር ጥያቄያችንን ማስተጋባታችን ይቀጥላል።

ፍትሕ ለወንጌላዉያን ቤተክርስቲያን
#ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በየትኛዉም መልክ የተመሳሳይ #ጾታ ጋብቻን አትፈቅድም።

#የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት #ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ጉባኤ ጠቅላይ ጽ/ቤት ከሰሞኑ ርዕሳነ ሊቀ ጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስ ለተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎች የፈቀዱት ቡራኬ ላይ ማብራሪያ ሰጠ።

ከሰሞኑ የሮማዉ ሊቀ ጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስ ቤተክርስቲያኗ ለተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎች ቡራኬ እንዲሰጡ ፈቃድ መስጠታቸዉን የተለያዩ #መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

ይህንኑ ተከትሎም የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ጉባኤ #ጠቅላይ ጽ/ቤት በጉዳዩ #ላይ #መግለጫ አዉጥቷል። ጠቅላይ ጽ/ቤቱ ከካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ስርዓተ አምልኮ ጋር የሚጻረር ወይንም ዉዥንብርን ሊፈጥር የሚችል ስርዓተ አምልኮን ያወግዛል ብሏል።

ሆኖም የጳጳሱ መልዕክት በተቃራኒው ተወስዷል የሚል ሃሳብ ያለዉን መግለጫ ያወጣ ሲሆን ለተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎች ጋብቻን #ግን ጳጳሱ ፈቃድ አልሰጡም ብሏል።

አክሎም የመፅሐፍ ቅዱስ ጥቅስን በማስቀመጥ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በየትኛዉም መልክ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻን አትፈቅድም ፤ አታጸድቅምም ማለቱን ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ከመግለጫው ተመልክቷል።

ቤተክርስቲያኒቱ ሀጢያትን አትባርክም ታወግዛለች #እንጂ ያለዉ መግለጫዉ የተመሳሳይ ጾታ #ጋብቻ የኢትዮጵያ ባህል #እና እሴትን የሚጥስ በመሆኑ ተቀባይነት እንደማይኖረዉም በመግለጫው አስታዉቋል።

በበረከት ሞገስ
#ዳጉ_ጆርናል
#አስደሳች #ዜና ለወንጌል አማኞች #በሙሉ

#በመስቀል #አደባባይ የንስሐ፣ የምልጃና የምስጋና ፕሮግራም መዘጋጀቱ ተገለጸ።

በዛሬው እለት #የኢትዮጵያ #ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል መሪዎች በአዲስ አበባ በመስቀል አደባባይ የንስሐ፣ የምልጃና የምስጋና ፕሮግራም መዘጋጀቱን ለሚዲያዎች መግለጫ ሰጥተዋል።

በተሰበረ #ልብ፣ በንስሐ መቅረብ የመጀመሪያ ተግባራችን መሆን እንዳለበት የጠቀሱት መሪዎቹ “#ወደ ደጆቹ በመገዛት ወደ አደባባዮቹም በምስጋና ግቡ፣ አመስግኑት፣ ስሙንም ባርኩ” (መዝ 100)፤4 በሚለው ቃለ #እግዚአብሔር መሠረት መጋቢት 8 ቀን 2016 ዓ/ም ከቀኑ 7፡00 ጀምሮ #በአዲስ አበባ #መስቀል አደባባይ የንስሐ፣ የምልጃና የምስጋና በዓል ለማካሄድ አስፈላጊው ዝግጅት #ሁሉ ተጠናቋል ብለዋል።

አሁንም የእርስ በርስ መጠፋፋቱ አልቆመም ያሉት መሪዎቹ መደማመጥና መከባበር በመካከላችን እንዲኖርና ለይቅርታና ለፍቅር ልባችን የቀና እንዲሆንና ፀጋውንም እንዲያበዛልን #እግዚአብሔርን የምንማጸንበት #ጊዜ ይኖራል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በፕሮግራሙ የሚካፈለው የሕዝብ #ብዛት እጅግ ብዙ ስለሆነ ስብሰባው የሚካሄደው በመስቀል አደባባይ ነው፡፡

በመሆኑም መላው የወንጌል አማኝ በነቂስ ወጥቶ #በእግዚአብሔር ፊት የንስሐ፣ የምልጃና የምስጋና ፕሮግራሙ ተካፋይ እንዲሆን ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

The Christian News - የክርስቲያን ዜና በስፍራው ተገኝተን ዝርዝሩን አሰናዳንላችሁ።

#photo Christian tube - ክርስቲያን ቲዩብ

ዝርዝር መረጃ ምሽት ላይ በቪዲዮ ይዘንላችሁ የምንመለስ ይሆናል።
https://www.youtube.com/channel/UCeHRJCDJ0wUDaBfAFmuMa7A?sub_confirmation=1
43ኛ ሲኖዶስ ተመሰረተ

#የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ #ኢየሱስ 43ኛ ሲኖዶስ የሆነው የጆርጎ ብርብር ሲኖዶስ ምስረታ በትናትናው ዕለት መጋቢት 16, 2016 ዓ.ም በታላቅ ክብረ በዓል እና ቁጥራቸው በሺዎች በሚቆጠሩ ምዕመናን በከተማ ጎዳኖች ላይ በተንፀባረቀ #ደስታ በደበሶ ከተማ፣ ምዕራብ ወለጋ ተካሄደ።
#ዛሬ ይጠናቀቃል

“መጽሀፍ ቅዱሳዊ እሴቶችን በሕዝባችን #ሕይወት እናስርጽ!” በሚል መሪ ቃል ሲካሄድ የቆየዉ የቅዱሳት መጻሕፍት ዐውደ ርዕይ ዛሬ ይጠናቀቃል።

በአሁኑ ሰዓት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፣ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን እና የወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት መሪዎች በተገኙበት በመካሄድ #ላይ ይገኛል።

#የኢትዮጵያ መጽሐፍ #ቅዱስ ማሕበር አዘጋጅነት የመጽሀፍ ቅዱስ ሳምንት በዓል #እና የቅዱሳት መጻሕፍት ዐውደ ርዕይ ከሰኞ የጀመረ ሲሆን በዛሬዉ እለት የሚጠናቀቅ ይሆናል።

ክርስቲያኑን #ስለ መጽሃፍ ቅዱስ ንባብ ማነቃቃት፣ በመጽሃፍ ቅዱስ ትርጉም ላይ የሚሰሩ አብያተ ክርስቲያናትን በተዛማጅ ስራዎች ላይ ማስተባበር፣ የወንጌል ስብከትን ማበረታት፣ ለአሁኑ ትውልድ የመጽሃፍ ቅዱስን አደራና ሃላፊነት ማስተላለፍ እና መጽሃፍ ቅዱስን ከአደጋዎች መጠበቅ በሳምንቱ ዉስጥ ሲሰራ የነበረ #ስራ ነዉ።

በሳምንቱ ዉስጥ ትውልዱን ስለ ቅዱሳት መጻህፍት እንዲያውቅ የማድረግ ስራ ፣ የህትመት ውጤቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለህዝብ ማድረስ እና ማህበሩን ከህዝብ ጋር ማስተዋወቅ በአውደ ርዕይው ሲከናወን ቆይቷል።

የኢትዮጵያ መፅሐፍ ቅዱስ ማሕበር ሁሉንም ሁሉንም አብያተ ክርስቲያናት እና ምዕመናንን ባለፋት 98 ዓመታት አገልግሏል።

ፎቶ 📷 Hossana production Hossana
የትንሳዔ በዓልን የድሬዳዋ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት በድሬዳዋ ዓለም ዓቀፍ ስታዲየም በተለያየ የአምልኮ ስርዓት አከበሩ።

በዛሬው የትንሳዔ በአል በድሬዳዋ ዓለም ዓቀፍ ስታዲየም ሲከበር የድሬዳዋ አስተዳደር #ከንቲባ ክቡር ከዲር ጁሀርን ጨምሮ የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች፣ በርካታ የወንጌላዉያን ዕምነት ተከታዮችና የሀይማኖት አባቶች ተገኝተዋል።

በድሬዳዋ ዓለም አቀፍ ስታዲየም የድሬዳዋ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት በተዘጋጀው የትንሳኤ በዓል አከባበር ላይ የክብር እንግዳ የነበሩት የአስተዳደሩ ከንቲባ ክቡር ከድር ጁሀር በዓሉን ስናከብር ትላንት የነበሩ ዛሬ ያልነበሩ ወገኖቻችን ቤተ ዘመዶችን ከጎናቸው በመቆምና የተቸገሩትን ደግሞ በመደገፍ መሆን እንዳለበት አስገንዝበው ለመላው ክርስትና ዕምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በፕሮግራሙ #ላይ የድሬዳዋ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ዋና ሰብሳቢ መጋቢ ሚኪያስ ታዬ የዛሬው የትንሳዔ በዓል አከባበር ዝግጅት መሳካት የድሬዳዋ አስተዳደር ላደገላቸዉ ትብብር ላቅ ያለ ምስጋናቸውን አቀርበዋል።

የድሬዳዋ ሀይማኖት ተቋማት ጉባዔ ምክትል ሰብሳቢ ሊቀ ብርሀናት ቀለመ ወርቅ ቢምረው በዛሬው የትንሳኤ በዓል ዲያቢሎስ የታሠረበት፣ ሀጢያት የተሻረበት እንዲሁም ብዙዎች ነጻ የወጡበት በመሆኑ ልዩ ያደርገዋል ብለዋል።

የዛሬው #የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ህብረት የትንሣኤ በዓል ዝግጅት ለስኬት እንዲበቃ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላትም የዕውቅና ምስክር ወረቀት ተበርክቷል።

ጁሌት ተድላ ለድሬ ቲቪ እንደዘገበዉ
ካሜራ:- ምንተስኖት ደረጀ

https://youtu.be/tOWD7qwfcDo
የመጋቢ ቢኒያም ሽታዬ እና ነቢይ ኢዮብ ጭሮ ጨምሮ የ4 ግለሰቦች #ቤተክርስቲያን ፈቃድ ተሰረዘ።

#የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል በስህተት ትምህርትና ልምምዶች ዙሪያ የ3ተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔን ጋዜጣዊ መግለጫ ለሚዲያዎች ሰጥቷል።

የካውንስሉን ምክር ተቀበለው፤ ሕዝብን ከሚያሳስት ተግባራቸው ለመመለስ ፈቃደኛ ሆነው ባለመገኘታቸው፤ ስማቸው ከዚህ በታች የተዘረዘሩት አብያተ ክርስቲያናትና ሚኒስትሪዎች ሠርተፍኬት እንዲሰረዝ ተወስኗል ሲል ዛሬ ባወጣው መግለጫ ጠቅሷል።

በዚህ መሰረት

1. ነቢይ ኢዮብ ጭሮ (ጆይ ጭሮ) (ጋድስ ላይት ግሎሪ ኢንተርናሽናል ሚኒስትሪ)
2. መጋቢ ካሳ ኪራጋ (ገዥዋ ዓለም አቀፍ የክርስቶስ ቤተክርስቲያን)
3. መጋቢ መዝገቡ ሚስጥሩ (የሰማይቱ ጽዮን ማኅበርተኞች የክርስቶስ ቤተክርስቲያን)
4. መጋቢ ቢኒያም ሽታዬ (የእግዚአብሔር መንግስት እውነት ዓለም አቀፍ ሚኒስትሪ) ሙሉ በሙሉ ፈቃዳቸው ተሰርዟል።

በመሆኑም የሚመለከታችሁ የመንግስት አካላት ከላይ ስማቸው የተቀመጡ አካላት ከዚህ ቀደም ከነበረባቸው ስህተቶች እንዲታረሙ በዝርዝር ቢመከሩም ፈጽሞ ሊመለሱ ያልቻሉ መሆናቸው ታውቆ ካውንስሉ ለሚወስደው ማንኛውም አስተዳደራዊ እርምጃ አስፈላጊውን ድግፍ እንዲያደርግ ተጠይቋል።

በቀጣይ በተቋማቱ እና በግለሰቦቹ ስም የተከፈቱ የባንክ ሂሳቦችና ሌሎች ተዛማጅ ጉዳዮች ሁሉ ላይ የሚወስደውን አስተዳደራዊ እርምጃ አስመልከቶ ወደ ተግባር በመቀየር ረገድ ድጋፍ ተጠይቋል።

ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ በቪዲዮ ይዘን የምንመለስ ይሆናል።
#ብዙ ዋጋ የተከፈለበት #በኢትዮጵያ ትልቁ የመፅሐፍ #ቅዱስ መዝገበ ቃላት ተመረቀ።

በዘላለም #መንግስቱ ተጽፎ ከ1,300 ገጾች በላይ ተዋቅሮ ከ4,800 በላይ ቃላት ያካተተው ይህ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት የአብያተ ክርስቲያናት መሪዎች ፤ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና የጸሀፊው ወዳጆች በተገኙበት በCETC) ኢትዮጵያን ቴዎሌጂካል ኮሌጅ በድምቀት ተመርቆ ለአንባብያን ተሰራጭቷል።

በመድረኩ መጽሀፉን #ሙሉ በሙሉ ጽፎ ለማጠናቀቅ 23 ዓመታት እደፈጀ እና በዚህ ስራ #ውስጥ ከፍተኛ አስተዋጽዖ ላበረከቱ አካላት ምስጋናውን አቅርቧል።

ዘላለም መንግስቱ በንግግሩ ይህ መፅሐፍ ማለት እንደ "ማንኪያ" ነው። ዋናው ምግቡ ግን "መፅሐፍ ቅዱስ" ነው። ያለ ሲሆን መጽሐፍ ቅዱስን የበለጠ ለመረዳት የሚያግዝ መጽሐፍ እንደሆነ ተናግሯል።

አክሎም ምንም እንኳን እጨርሰዋለሁ ብዬ ባልጀምረውም ለብዙዎች የሚያግዝ በመሆኑ በእግዚአብሄር እርዳታ ተጠናቋል። ይህ መጽሐፍ በብዙ ውጣ ውረድ ውስጥ የተጻፈ እንደመሆኑ መጠን ይህ መጽሀፍ መጽሀፍ ብቻ ሳይሆን አደራም ጭምር ነው ሲል ተናግሯል።

በመድረኩ ንግግር ያደረጉ መሪዎች እረጅም አመታትን በትዕግት በመጻፍ ይህንን መጽሀፍ በዚህ ወቅት ለኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን በማበርከቱ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። በዚህ ዘመን ያለን አገልጋዮች ይህንን መጽሀፍ ባንጠቀምበት ፤ እና ባንሰራበት ለእኛ እዳ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ዘላለም መንግስቱ ከዚህ ቀደም መንፈስ ቅዱስ እና ካሪዝማዊ ቀውሶች ፤ እንዘምር ወይስ እንዝፈን ፤ ክርስቲያናዊ ኢትዮጵኝነት ፤ የሐሰተኞች እሳተ ጎመራ ፤ ትንቢተ ዕምባቆም ፤ የይሁዳ መልዕክትን ጨምሮ ወደ 20 የሚደርሱ መጽሀፍትን ለኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን አበርክቷል።

#የኢትዮጵያ ቃለ #ሕይወት #ቤተክርስቲያን #ዋና ጸሐፊ ዶ/ር ስምዖን ሙላት #እና የአብያተክርስቲያናት መሪዎች በጽሎት መጽሀፉን መርቀው ለንባብ እንዲበቃ በይፋ መርቀውታል።

The Christian News - የክርስቲያን ዜና በስፍራው ተገኝተን ሙሉ ዘገባውን አሰናዳንላችሁ። በቻናላችን ስም ለወንድም Zelalem Mengistu የተሰማንን እጅግ ትልቅ ደስታ እየገለጽን ሁላችሁም ትጠቀሙበት ዘንድ እናበረታታለን።
ምን እየተፈጠረ እንደሆነ ... ትክክለኛ #መረጃ ለመስማት ቤተክርስቲያ #ለሚዲያ አካላት ጥሪ አቅርባለች።

#የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ኩሪፍቱ ማዕከል ላይ የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር እየወሰደ ላለዉ ኢ-ሕገ መንግስታዊ እርምጃ በተመለከተ ይፋ ለማድረግ ለሚዲያዎች በሙሉ ጥሩ ቀርቧል።

የቤተክርስቲያንን ንብረት በተመለከተ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካዉንስል ጉዳዩን በማብራራት መንግስት እየተወሰደ ያለዉ እርምጃ ተቀባይነት የሌለዉ እንደሆነ መግለጫ መስጠቱ ይታወሳል።

በነገዉ እለት ደግሞ በኢትዮጵያ አንጋፋዋ እና የብዙዎች እናት የሆነችዉ የቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ለሚዲያዎች መግለጫ የምትሰጥ ይሆናል።
#የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ፕሬዝደንት ቄስ ዶ/ር ዮናስ ይገዙ በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር በተከሰተው የእሳት አደጋ ማዘናቸውን ገለፁ፡፡

ፕሬዚዳንት ቄስ ዶ/ር ዮናስ ለድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ ከድር ጁሀር በፅሁፍ ባስተላለፉት መልዕክት ሰኔ 25 ቀን በድሬዳዋ 'አሸዋ ገበያ' በተፈጠረው ድንገተኛ የእሳት አደጋ ከልብ ማዘናቸውን ገልፀው ከአስተዳደሩ ጎን እንደሚቆሙ አስታውቀዋል።

በቅርቡ ከሌሎች የሀይማኖቱ አባቶች ጋር በመሆን የእሳት አደጋው በደረሰበት ስፍራ በአካል ተገኝተው፥ ተጎጂዎችን እንደሚያፅናኑ እና ከአስተዳደሩ ጎን በመሆን አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርጉም የኢትዮጰያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ፕሬዝደንት ቄስ ዶ/ር ዮናስ ይገዙ ጨምረው ገልፀዋል።

መረጃዉ የድሬደዋ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ነዉ።
#የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት #ኅብረት "በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በድንገተኛ የመሬት ናዳ ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች የተሰማውን ጥልቅ ኀዘን ገልጿል።

ሕብረቱ የመጽናናት አምላክ ለቤተሰቦቻቸውና ለአካባቢው ነዋሪዎች ብርታቱን ይሰጥ ዘንድ ይመኛል።

አቅም በፈቀደ መጠን በጸሎትም ሆነ በሚችለው መንገድ ከጎናችሁ እንደሚቆምም አሳዉቋል።
#የኢትዮጵያ ቃለ ህይወት ቤተክርስቲያን በጎፋ ዞን በመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ወገኖች የ10.2ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገች።

የኢትዮጵያ ቃለ ህይወት ቤተክርስቲያን ዋና ጽ/ቤት በጎፋ ዞን፣ ገዜ ጎፋ ወረዳ በመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ወገኖች የ10 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል።

የኢትዮጵያ ቃለ ህይወት ቤተክርስትያን ዋና ጽሐፊ ዶ/ር ስምኦን ሙላቱ፥ ቤተ ክርስትያኒቱ በአደጋው ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች እንደምትፀልይ ተናግረው፤ በቀጣይም ተጨማሪ ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብተዋል።

የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ዳግማዊ አየለ በበኩላቸው፥ ጉዳት የደረባቸው ወገኖች ከተጠለሉባቸው ጊዜያዊ መጠለያዎች መካከል በአካባቢው የሚገኘው የቃለ ህይወት ቤተክርስቲያን አጥቢያ አንዱ መሆኑን ጠቅሰው፤ ስለተደረገው ድጋፍ አመስግነዋል።

በጎፋ ዞን በመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ወገኖች እየተደረገ ያለው ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠሉንም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመልክቷል።
#የኢትዮጵያ ወንጌላዊት መካነ #ኢየሱስ #ቤተክርስቲያን የማዕከላዊ #ደቡብ #ኢትዮጵያ ሲኖዶስ የልማት ኮሚሽን ፤ ኖሮዌ #ቤተክርስቲያን ተራዕዶ እና UN #women በጋር የሚተገብሩት Creating safe #city #and safe #public #space #project ጾታን መስረት ያደረገን ጥቃት ለመከላከል የሚስችል የግንዛቤ ማሳጨበጫ ፕሮግራም በሀዋሳ #ከተማ አካሄድ፡፡

በፕሮግራሙ #ላይ ከካቶሊክ ፤ ከወንጌል አማኞች #እና ከግሮት ኮሚሽን የተወጣጡ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል።

ጾታዊ ጥቃት/በሴቶችና ልጃገረዶች የሚደርሰውን ጥቃት የሚፅየፍ ትወልድ መፍጠር የሚል አላማ የነበረው ፕሮግራም እንደሆነ ተገልጿል።

በፕሮግራሙ ከአቶቴ #እስከ ታቦር መካነ #ኢየሱስ ቤ/ክ ድረስ የእግር ጉዞ የተደረገ ሲሆን በጉዞ ወቅት ተሳታፊዎች የተለያዩ የጹሁፍና የድምፅ መልዕክቶችን በማሰማት በሴቶችንና ልጃገረዶች #ላይ የሚደርሰውን ጥቃት አውግዘዋል፡፡

በተጨማሪም በግሬት ኮሚሽንና በሪፍራል መካነየሱስ ወንድ ወጣቶች #መካከል የእግር ኩዋስ #ውድድር የተካሄድ ሲሆን የውድድሩ አላማ ወንዶች ጾታዊ ጥቃትን ለመከላከል ያላቸውን ቁርጠኝነት ለማሳየት ነው።

ይህም ጥቃት የሚያደርስ ወንድ #ብቻ ሳይሆን የሚቃውም መሆኑን በማሳየት ተሳትፎቸውን ለመጨመር ነው፡፡
በአዲሱ #አመት ከክፋት እርቀን #ወደ መልካምነት እንድንመለስ አሳስባለሁ። ፓስተር ጻዲቁ አብዶ

የ2017 #አዲስ አመት አስመልክቶ #የኢትዮጵያ የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት ፕሬዝደንት መጋቢ ጻዲቁ አንዶ ባስተላለፉት መልዕክት እያንዳንዱ ወቅት የራሱን በረከት ይዞ ይመጣል። ወቅቶች የሚፈራረቁት ለሰዎች የሚሰጡት ካለው በረከት አንጻር ነው ብለዋል።

በአዲሱ #አመት ከክፋት እርቀን #ወደ መልካምነት እንድንመለስ አሳስባለሁ። ያሉት ፓስተር ጻዲቁ ተገቢ ባልሆነ ድርጊቶቻችን ያመጣናቸው ነገሮች በማራቅ ከመቼውም ጊዜ በላይ ለሃገራችን ሰላም ለሕዝባችን መቀባበል እና ይቅር መባባል እንድንሰራ አሳስበዋል።