The Christian News
5.15K subscribers
3.04K photos
25 videos
714 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
በድሬደዋ መካነ #ኢየሱስ #ቤተክርስቲያን እና በከተማ ከንቲባ ጽ/ቤቱ መካከል ተፈጥሮ የነበረው ችግር በውይይት መፈታቱ ተገለጸ።

ባለፈው ሳምንት በድሬደዋ መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን እና በከተማ ከንቲባ ጽ/ቤቱ መካከል ተፈጥሮ የነበረው ችግር በውይይት መፈታቱን ቤተክርስቲያኗ አስታውቃለች፡፡

“ቤተክርስቲያኗ ትፍረስ” በሚል ላወጣው ደብዳቤም የከንቲባ ጸ/ቤቱ ቤተክርስቲያኗን ይቅርታ መጠየቁን እና ኹሉም ነገር በንግግር እንደሚፈታ መናገሩን ገልጻለች፡፡

በተደረገው ንግግርም ቤተክርስቲኗ የያዘችውን ይዞታ ማልማት ከቻለች በቦታው እንድትቀጥል ካልሆነ ግን የከንቲባ ጸ/ቤቱ ተለዋጭ ቦታ ላይ የምትክ ቤት ሰርቶ እንደሚሰጥ ቃል መግባቱን የቤተክርስቲያኗ ሰብሳቢ በለሳቸው አምባሮ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ራዲዮ ጣቢያ መናገራቸውን ጠቅሶ (አዲስ ማለዳ) በዛሬዉ እለት አስነብቧል።

ከቦታው ተነስቶ ወደ ተለዋጭ ቦታ መሄዱም ቢሆን ከቤተክርስቲያኗ መሪዎች ጋር በመነጋገር ብቻ እንደሆነ መተማመን ላይ መድረሳቸውን ገልጸዋል፡፡

ቀደም ሲል የተላከው ደብዳቤም ቤተክርስቲያነኗ ዙሪያ ላይ ላሉ ተቋማት የተዘጋጀ መሆኑን ከንቲባው መናገራቸውን የገለጹት የቤተክርስቲኗ ሰብሳቢ፤ ይቅርታ መጠየቃቸውንም አነስተዋል፡፡

ስለሆነም ከተቀመጡት ኹለት አማራጮች መካከል ቤተክርስቲያኗ የፈለገችውን መምረጥ እንደምትችል የከንቲባ ጸ/ቤቱ ገልጿል፡፡

በሚቀጥለው ሰኞ ከድሬደዋ ከንቲባ ጋር ለመነጋገር ዋናው ሲኖዶስ ከአዲስ አበባ ወደ ድሬደዋ እንደሚያመራ የተገለጸ ሲሆን፤ ከሚደረገው ሰፊ ውይይት በኋላ ቤተክርስቲያኗ የሚበጃትን ትምርጣለች ብለዋል፡፡

በመጨረሻም የከተማ ከንቲባ ጽ/ቤቱ ጥፋቱን አምኖ ይቅርታ መጠየቅ በመቻሉ ቤተክርስቲያኗ በጣም እንደምታመሰግን የቤተክርስቲያኗ ሰብሳቢ በላቸው አምባሮ አስታውቀዋል፡፡
#መልካም #እለተ ሰንበት ይሁንልን 🙏🙏🙏

ቴክኒካሊ ብልጥ ሆነን የማናልፍበት ዘመን መጥቷል።

ዘመኑን ለማለፍ መንፈሳዊ መሆን የግድ ነዉ። እሱም ከኢየሱስ ጋር #ብቻ መሆን #ነዉ የሚያዋጣዉ።

በመፅሐፍ #ቅዱስ #ብዙ ታሪክ የሰሩ ሰዎችን ብንመለከት #እንኳን አለም እነሱን አይታ ተሸናፊዎችነዉ ያለቻቸዉ። ማንም አይፈልጋቸዉም ነበር።

በዘመናቸዉ #ሁሉ #ኢየሱስ ሲሉ ነበር ካለፉ በኋላ ግን ሁሉም ሰዉ ስለ ኢየሱስ ከ2ሺህ ዘመናት በላይ ይናገራል።

ኢየሱስ ካልክ የዚህ ድንቅ መፅሐፍ አካል ትሆናለህ። መፅሐፍ ቅዱስ የአንድ ታሪክ መፅሐፍ ነዉ። እነዚህ ሁሉ ሰዎች ስለ አንድ ታሪክ ሲናገሩ ነዉ የታሪክ አካል የሆኑት።

#ነብይ ጥሌ
#እስካሁን ከመንግስት ምንም #ፍትህ አላገኘንም

ይህንን ያለችዉ #የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ በዛሬዉ እለት #ጊዳሚ መካነ #ኢየሱስ ምዕመናን ላይ የደረሰዉን ግፍ አስመልክታ በሰጠችዉ ጋዜጣዊ መግለጫ ነዉ።

ቤተክርስቲያኒቱ በሰጠችዉ መግለጫ በወለጋ ጊዳሚ መካነ ኢየሱስ #ቤተክርስቲያን ተወስደው ከተገደሉ 9 #ሰዎች መካከል #5ቱ_ከአንድ_ቤተሰብ መሆናቸው ተገልፆል።

ቤተሰቦቻቸውን #እና ወዳጅ ዘመዶቻቸውን ላጡ ወገኖች ቤተ ክርስቲያኗ መጽናናትን የተመኘች ሲሆን ቤተ ክርስቲያኗ ፍትህን ከመንግስት ለማግኘት ስትጠባበቅ የቆየች ቢሆንም፣ ለአሁኑን ጥቃትም ይሁን ከዚህ በፊት ለተፈጸሙ ጥቃቶች ከመንግስት ዘንድ ምንም አይነት የፍትህ ምላሽ ሳታገኝ ቀርታለች ብሏል።

በጥቃቱ ህይወታቸውን ያጡ ወገኖች ስም ዝርዝር

1. ተሊላ ለሜሳ ታሲሳ
2. ቶሊና ለሜሳ ታሲሳ
3. ታምራት ለሜሳ ታሲሳ
4. ቀበና ቡልቻ ጉተማ
5. ጌታቸው ቤከታ ታይሳ
6. ሂካ አያና ያደሳ
7. ጅረኛ ድንገታ ቴሶ
8. ሰለሞን ድንገታ ቴሶ
9. ሲራጅ ደኑ

መግለጫዉ አክሎ አሁንም መንግስት ዘላቂ #ሰላም እንዲያስከበር፣ ፍትህ እንዲሰፍንና ዜጎች በነጻነት ወጥተው መግባት፣ የአምልኮ ነጻነታቸውን እንዲያስጠብቅ እንደ ከዚህ ቀደሙ ጥሪዋን ታቀርባለች ብሏል መግለጫው።

የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤ/ክ መካነ ኢየሱስ ፕሬዝዳንት ቄስ ዶ/ር ዮናስ ይገዙ በጉዳዩ ላይ የሰጡት መግለጫ ከዚህ በታች ተያይዟል።
ለካሪቢያን ደሴት ቅርብ ከሆነችው Puerto Rico ተወለደ።

Daddy Yankee. ራፐር፡ ገጣሚና እውቅ የሙዚቃ ሰው ነው። በሰፈራችን ጭምር በራዲዮና ስፒከር ተከፍቶ የምናገኘው 'Despacito' ሙዚቃ የእሱ ነው።

በዩቲዩብ ታሪክ 8.31 Billion ተመልካች በማግኘት ቀዳሚውን ሰንጠረዥ ይዟል። ይህን ያህል እጅግ የገነነ ስምና ዝና ቢኖረውም ሕይወቱ ረፍት አጥታለችና አንድ ውሳኔ ይወስን ዘንድ ግድ አለው።

ይህንንም በመጨረሻው የሙዚቃ ኮንሰርቱ ላይ ዓለም በቃኝ ሕይወቴን ለኢየሱስ ሰጥቻለሁ ሲል አሳወቀ። እንዲህ በማለትም ቀጠለ፦ "የምትከተሉኝ ሰዎች ሆይ እኔን ተውኝና እውነት፡ መንገድ፡ ሕይወት የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን ተከተሉ..." አዎ የምድር ዝናና ገንዘብ ከቶም ቢሆን የዘላለም ሕይወት ሊያስገኙልን አይችሉም።

ቅዱስ ኦገስቲን እንዳለው፦ "ኦ አምላክ ሆይ! አንተ የፈጠርካት ልባችን ባንተ ረፍቷን እስክታገኝ ድረስ ስትቅበዘበዝ ትኖራለች።"

ኢየሱስ ረፍትና ሰላም ነው። 'ኑ' ወደ ሕይወት ምንጭ <<ኢየሱስ>>

#ኢየሱስ_የዘላለም_ርስትና_ማረፊያ_ነው
#አስቸኳይ...

ሞትን ለማምለጥ የሚደረግ የሞኞች እሩጫ 🏃‍♂️🏃‍♀️🏃‍♂️🏃‍♂️

ከሰሞኑ #አንድ ዘገባ አነብብኩኝ ዝገባው #ቃል በቃል "የፌስቡክ መስራቹ ማርክ ዙከርበርግ ራሳቸውን ከዓለም ፍጻሜ ለመጠበቅ በሚል መጠለያ እየገነቡ መሆኑ ተገለጸ" ይላል #እንደ ርዕሱ ቢሆን ሁላችንም ፈገግ ብለን ብናልፈው መልካም #ነበር #ግን አይሆንም።

#ሁሉም #ሰው እንደሚሞት እንዲሁም የአለም ፍጻሜ እንዳለ እርግጠኛ ነው። ግን የሚመጣውን ጥፋትም #ይሁን የሚጠብቀውን የዘላለም #ሞት #እንዴት ማምለጥ እንዳለበት የተረዳ አይመስለኝም።

ለዚህም ይመስለኛል ባለጸጋው በአንድ ደሴት #ውስጥ ባለ #መሬት ውስጥ በ100 ሚሊዮን ዶላር መጠለያ በመገንባት #ላይ መሆናቸው የተሰማው።

አንዳንዴ ግን አጠቃቀሙን ካላወቅነው ሃብታም መሆን ከባድ ይመስለኛል።

ከ120 ቢሊዮን ዶላር በላይ የተጣራ ሀብት እንዳላቸው የሚነገረው ቱጃሩ የፌስቡክ መስራች ዙከርበርግ የደሴቲቱን ስፍራ በ170 ሚሊዮን ዶላር ከዓመታት በፊት የገዙት ሲሆን አሁን #ደግሞ #በዚህ ስፍራ ላይ ቅንጡ የክፉ #ጊዜ መኖሪያ #ቤት እየገነቡ ነው፡፡

#ይህ ስፍራ ለኑሮ አስፈላጊ የሚባሉ ምግቦችን ማምረት፣ የኤሌክትሪክ ሀይል፣ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ማድረጊያ ሜዳ፣ ውሃ ዋና #እና ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ አገልግሎቶችን #ሙሉ ለሙሉ ከዚሁ ስፍራ ማግኘት በሚያስችል መልኩ በመገንባት ላይ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

#ክፉ ጊዜ ግን መቼ #ነው? ይህ ክፉ ጊዜ ሲመጣ እንዴት በደሴቶች ተሸሽገን ማለፍ እንችል ይሁን?

#መጽሐፍ #ቅዱስ የጌታ ምጽዓት እና የአለም ፍጻሜ በቀረበ ጊዜ በመጨረሻው ዘመን ጦርነት እና የጦር ወሬ ፤ የተፈጥሮ አደጋ መብዛት እንዳለ ይነግረናል በራዕይ መጽሀፍ ደግሞ ደሴቶችም #ሁሉ ሸሹ ተራራዎችም አልተገኙም ይላል።

ታዲያ ቱጃሩ ወዳጃችን ደሴትም ፈልፍሎ ለክፉ #ቀን የሚሆን ማምለጫ የሚያዘጋጀው ከማን ለመሸሽ ነው?

#ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ #እውነት እውነት እላችኋለሁ ባለጠጋ #ወደ #እግዚአብሔር መንግስት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢገባ ይቀላል ያለው ቃል ግልጽ ይመስላል።

ስለ ስሙ ያላቸውን ሁሉ ትተው የተከተሉት ግን የዘላለምን ሕይወት ይወርሳሉናል።

ለማንኛውም ወዳጄ ማርክን እና ሌሎች ባለጠጎች ከክፉ ቀን ማንም ሸሽቶ አያመልጥም እና መሸሸጊያ ዋሻ ወደ ሆነዉ ኢየሱስ ተሰብስበኝ በተሰጠን ጊዜ ተጠቅመን መጽሀፍ "እነሆ በደመና ይመጣል አይንም ሁሉ ያየዋል" እንደሚል ያንን ለማየት እንናፍቅ "ማራናታ" #አሜን መልዕክታችን ነው።
#ወደ #ጌታ #ሄደ
ወንድዬ ዓሊ

ገጣሚ፣ ደራሲ፣ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ እና የግለታሪኮች ጸሐፊ፣ የድንቅ መዝሙራት ደራሲና ዘማሪ፣ የብዙዎች የሙያ አባት፣ … ወንድዬ ዓሊ በስተመጨረሻ ለሞት እጅ ሰጠ።

በክርስቶስ #ኢየሱስ አምኖ በመዳኑ መዳረሻውን ስለሚያውቅ ከባድ ህመም ቢያደቀውም በጽናት እና ያለ ሀዘን ነፍሱን ሰጠ።

የዘለአለም #ሕይወት ወራሽ ያደረገው የሞተለት #ጌታ ኢየሱስ በወንድዬ ሕይወት አልፎ ለቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን፣ ለአገራችን ስነጽሑፍ ወዳጆች እና ለመላው የወንጌል አማኝ ስለሠራው #ሁሉ ስሙ ብሩክ ይሁን።

The Christian News - የክርስቲያን ዜና ለመላው ወዳጆቹ #እግዚአብሔር መፅናናትን እንዲሰጥ ይመኛል።
#ኢየሱስ ላውድልህ ሃገሩን
#ዘማሪ ይድኔ

ኢየሱስ ላውድልህ ሃገሩን የዘማሪ ይድነቃቸው ተካ የዝማሬ ድግስ #ቅዳሜ መጋቢት 7 ከቀኑ 7 ሰዓት #ጀምሮ በሚሊኒየም #አዳራሽ ይካሄዳል።

ይሄንኑ ድግስ በተመለከተ ዘማሪው ከአጋር አካላት #ጋር ለሚዲያዎች #ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

መግለጫውን ዘማሪ ይድነቃቸው ተካ፡ የሙዚቃ አቀናባሪ ዳዊት ለሚ፡ የድግሱ ብቸኛ አጋር ኤል ሃዳር ኢንጂነሪንግ፡ የጸጥታ አካል ዘጸዓት ሴኩሪቲ እና አስተባባሪዎች መግለጫውን በጋራ ሰጥተዋል።

በሮች ከ4 ሰዓት ጀምሮ ክፍት ይሆናሉ። የተባለ ሲሆን ዘማሪ ይድነቃቸው፡ ከኢየሱስ አልበም እና ቸኮለብኝ አልበኖች ዝማሬዎችን ያቀርባል።

#ነብይ ጥላሁን ጸጋዬ #በእግዚአብሔር ቃል የሚያገለግል ሲሆን ምንም አይነት የመግቢያ ክፍያ እንደሌለዉም ተጠቅሷል።

ከዳዊት ለሚ ባንድ ጋር ለ3 ወራት ዝግጅት ሲደረግ መቆየቱን የጠቀሰዉ ዘማሪ ይድኔ ድግሱ ከአዲስ አበባ ውጪ ባሉ ከተሞችም ይካሄድ ተብሏል።

ኢየሱስ #2 አልበም ከ5 ወራት ፊት ነበር የተለቀቀው። ቸኮለብኝ #1 አልበም 2003 መለቀቁ ይታወሳል።

The Christian News - የክርስቲያን ዜና በመግለጫዉ ላይ ተገኝተን ዝርዝሩን አሰናዳንላችሁ።

#ሙሉ ጋዜጣዊ መግለጫዉን ከደቂቃዎች በኋላ በቪዲዬ ይዘን የምንመለስ ይሆናል።
#እግዚአብሔር #ይመስገን 🙏🙏🙏

በድል ተጠናቋል...

#ኢየሱስ ላውድልህ ሃገሩን በሚል በዘማሪ ይድነቃቸው ተካ የተዘጋጀ የመዝሙር ኮንሰርት #ዛሬ ከቀኑ 7 ሰዓት #ጀምሮ በሚሊኒየም #አዳራሽ ተካሂዷል።

ተወዳጁ #ዘማሪ ይድነቃቸዉ ተካ ከዳዊት ለሚ ባንድ ጋር በመሆን በ2003ዓ.ም የተለቀቀዉን ቁጥር አንድ #ቸኮለብኝ እና ከ5 ወራት በፊት የተለቀቀውን #ኢየሱስ አልበም አቅርቧል።

ነብይ ጥላሁን ጸጋዬ #በእግዚአብሔር ቃል በማካፈል አገልግሏል።

ዘማሪ ይድነቃቸው የአገልግሎት እና የህይወት ወጣ ዉረዱን በተመለከተ አጭር ዘጋቢ የቀረበ ሲሆን የመዝሙር ኮንሰርቱ በድል ተጠናቋል።
43ኛ ሲኖዶስ ተመሰረተ

#የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ #ኢየሱስ 43ኛ ሲኖዶስ የሆነው የጆርጎ ብርብር ሲኖዶስ ምስረታ በትናትናው ዕለት መጋቢት 16, 2016 ዓ.ም በታላቅ ክብረ በዓል እና ቁጥራቸው በሺዎች በሚቆጠሩ ምዕመናን በከተማ ጎዳኖች ላይ በተንፀባረቀ #ደስታ በደበሶ ከተማ፣ ምዕራብ ወለጋ ተካሄደ።
#የኢየሱስ ወታደር ነኝ ... #ወደ አምላኩ ሄደ 😭
ከ40ዓመት በላይ በጌታ ቤት ቆይቷል...

#ሄደ #ወደ አምላኩ ሄደ ...
ኢየሱስን ብሎ አለምን የካደ ሄደ ..😭

ከ1945 - 2016 ...

ሙሉቀን በ1960ና 70ዎቹ ብዙዎች በኢትዮጵያ ወርቃማ በሚባለው የሙዚቃ ዘመን፣ ቁንጮ ከነበሩት መካከል ነዉ ይሉታል። ኋላ ላይም ወደ ጌታ #ኢየሱስ መጥቷል።

ሙሉቀን በ1945 ዓ.ም በጎጃም ክፍለ ሃገር ተወለደ። በልዩ ተሰጦው ምክንያት በ12 አመቱ ሙዚቃን የጀመረው ሙሉቀን፣ በለጋ እድሜው ነበረ በመሸታ ቤቶች ውስጥ “እናቴ ስትወልደኝ መች አማከረችኝ” በሚለው ሙዚቃ የጀመረው።

ሙሉቀን የዘፈኑ አለም በቃኝ ብሎ ወደ ጌታ ከመጣበት 1970ዎቹ ማገባደጃ አካባቢ ጀምሮ በዝማሬ ማገልገሉን ቀጥሏል። በየጊዜው የቀድሞ የዘፈን ወዳጆቹ የእንዝፈን ግብዣ ቢቀርብለትም፣ አሻፈረኝ ብሎ ቀጥሎበታል።

ህመሙ በጠናበት ጊዜም እነ ታማኝ በየነ ልህክምና ወጪ የዘፈን ድግስ እናዘጋጅ ሲሉትም በኔ ስም አይዘፈንም ብሎ በቅድስና የኖረ ጀግና ክርስቲያን ነው።

ሙሉቀን ወደ ክርስቲያኖች ካደረሳቸው መዝሙሮች መካከል “ስለ ውለታህ”፣ አድራሻ ቢስ ሆኜ በዓለም ውስጥ ስጨነቅ”፣ “ሃሌሉያ”፣ “አቤኔዜር” እና ሌሎችንም መዝሙሮችን ከሃሌሉያ አልበሙ አስመቶናል።

በአንድ ወቅት ጋዜጠኛ መታሰቢያ በEBS Tv ላይ "ከኢትዮጵያ ከወጣህ 38 ዓመት ሆኖሃል አትናፍቅህም?" የሚል ጥያቄ ብትሰነዝርለትም ሙሉቀን መለሠ ግን አትናፍቀኝም! ... ኢየሱስን ማየት ነው የናፈቀኝ ማለቱ የቅርብ ዓመች ትዝታ ነዉ።

#ዘማሪ #ሙሉ #ቀን ኑሮውን በአሜሪካን ሃገር ዋሽንግተን ዲሲ ከባለቤቱ ጋር አድርጎ በኖረበት በ71 ዓመቱ ወደ ሚወደውና ወዳገለገለው #ጌታ ሄዷል።

በነገራችን #ላይ ሙሉቀን መለሰ በዓለም የሙዚቃ ስራ ዉስጥ ለ14ዓመት ብቻ ከ13 ዓመቱ እስከ 27ዓመቱ ብቻ ነዉ የቆየው ዘፈን አቁሞ ወደ ጌታ ከመጣ ደግሞ 43 አመታትን አስቆጥሯል።

ከበርካታ ዝማሬዎቹ መካከል
አለም ተስፋ ቁረጭ አልተገናኘንም
አምላክ ከእኔ ጋር ነው አታሸንፊኝም

እንዲሁም
ከኢየሱስ ጋራ ሲሄዱ
ከጌታ ጋራ ሲሄዱ
እንዴት ያምራል ጎዳናዉ
እንዴት ያምራል መንገዱ

በብዙዎች ዘንድ የሚታወቀዉ
የኢየሱስ ወታደር ነኝ
የኢየሱስ ወታደር ነኝ
እዋጋለሁኝ አልሽነፍም
ለጠላት እጅን አልስጥም

የሚሉት ተጠቃሽ ናቸዉ ...

ለሙሉቀን መለሰ ቤተሰብና ወዳጅ ዘመዶች The Christian News - የክርስቲያን ዜና በድጋሜ መጽናናትን ይመኛል።
#ኢየሱስ #ጌታ ነዉ።

ፈረንሳይ ፓሪስ ላይ በ800 ሜትር የሴቶች ፍጻሜ ለሀገሯ ኢትዮጵያ የብር ሜዳሊያ ያስገኘችው ፅጌ ዱጉማ ከውድድሩ በኃላ " JESUS IS LORD ! " የሚል ጽሁፍ አሳይታለች።

ፅጌ ስሟ ተጽፎ ደረቷ ላይ ከተለጠፈበት ወረቀት የጀርባ ክፍል ላይ ነው ይህን መልዕክት ፅፋ ገብታ ያስተላለፈችው።

የዘንድሮ የፓሪስ ኦሎምፒክ የመክፈቻ ስነስርዓት በክርስቲያኖች ዘንድ ቁጣ ቀስቅሶ እንደነበር ይታወሳል።

tikvah