The Christian News
5.32K subscribers
3.06K photos
27 videos
720 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
#ዘማሪ ይሳኮር #ይቅርታ ጠይቋል። #ቤተክርስቲያን ግን ምንም ምላሽ አልሰጠችም።

ሰሞኑን በሚዲያ በድሬዳዋ ህያው ቃል ቤተክርስቲያን በመቅረቴ ትንሽ ቅራኔ በመፈጠሩ ይቅርታ ስለመጠየቅ እና በአጋጠመኝ የግል ችግር ያልቻልኩ ሲሆን ለማስረዳት እንዳልሞክር ስልኬ በመሰረቁ ምክንያት ነው።

ለይቅርታ በመዘግየቴ በዚህ ምክንያት ያሳዘንኩዋቹ ሰዎች እና ህያው ቃል ቤተክርስቲያን ታላቅ ይቅርታን እጠይቃለሁ ።

የቤተክርስቲያኒቱን መጋቢ ምስክር ይቅርታዬን ስለተቀበልክ ከልብ አመሰግናለሁ። ጌታ ካለ እና ዕድሉን ካገኘን ሌላ ጊዜ በሰፊው መጥቼ ፀጋ እንከፍላለን ።

ምንም እንኳን ዘማሪዉ ምክንያቱን በዚህ መልክ ቢያስቀምጥም ዘማሪ ይሳኮር ፕሮግራም በያዘበት ቀን ከሐምሌ 13 እስከ 16 እግር ኳስ ከሰፈር ልጆች ጋር እየተጫወተ እንደነበር የሚያሳይ መረጃዎች ደርሰዉናል።
#ዘማሪ #በረከት ተስፋዬ #ይቅርታ ጠየቀ።
ንስሀ #ገብቻለሁ

የተወደዳችሁ እህቶቼና ወንድሞቼ ዛሬ ወደ እናንተ የመጣሁት ይቅርታን ስለመጠየቅ ጉዳይ ነዉ።

ባለፈዉ ጊዜ በኮንሰርቴ ጉዳይ ወደናንተ መልእክት አቅርቤ ነበር። እናም ዛሬ የቀጠና ሁለት ሙሉ ወንጌል መሪዎች ጠርተዉኝ ስለ ጉዳዩ ሲነግሩኝ ስተት እንደሰራዉ አወኩኝ።

አዳራሹ ለአምልኮ ኮንሰርት አገልግሎት የተከፈተ መስሎኝ ነበር ነገር ግን በአንዳንድ ምክንያቶች ክፍት አለመሆኑን ሲነግሩኝ እኔ የሰማሁት ነገር የዉሸት መረጃ ነበር። ከዚህም የተነሳ ስሜታዊ ሆኜ በለቀቅኩት ፅሁፍ የቤተ ክርስቲያንን መሪዎች አሳዝኛለዉ።

እንዲሁም ሰዎችን ወደተለየ ሀሳብ በለቀቅኩት ፅሁፍ መርቻለዉ። በእዉነት ዛሬ ከመሪዎች ጋር ሳወራ በደልን እንደፈፀምኩ ተረድቼ ንስሀ ገብቻለዉ መሪዎችም ተንበርክኬ መርቀዉ ፀልየዉ ሸኝተዉኛል።

ጌታ ኢየሱስ ይባርካቸዉ እኔን ታናሹን ጠርተዉ ለማቅናት ለሄዱትን እርምጃ ጌታ ይክፈላቸዉ። እኔ በጣም አዝኜ ስሜቴም ተጎድቶ ነበር እወዳቸዉ ስለነበር። ዛሬ ተፈዉሻለዉ። በተረፈ የሙሉወንጌል መሪዎችንና ቤተ ክርስቲያንን ባርኩልኝ።

ወንድማቹ በረከት ተስፋዬ #ነኝ
በተወዳጁ በአንጋፋው መጋቢ እና #ዘማሪ አገኘው ይደግ የተዘጋጀው " #እግዚአብሔር እያለ" የተሰኘው የዝማሬ ኮንሰርት በደመቀ ሁኔታ ተካሄደ።

በምስራቅ መሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በተካሄደዉ ፕሮግራም ጥሪ የተደረገላቸው የወንጌላውያን አማኞችና አገልጋዮች አንጋፋ ዘማሪዎች መሪዎች ተገኝተዋል።

ዘማሪ አገኘው ይደግ ከቁጥር አንድ ካሴቱ "ሀይለኛ እንደ አንተ የለም" አንስቶ ከሌሎችም የዝማሬ ሰዱቆችሁ የተወጣጡ ዝማሬዎችሁን ከሪትም ኳየር ጋር በመቀናጀት ያቀረበ ሲሆን በዶ/ር ማሙሻ ፈንታ "የሚጮኸው የኢየሱስ ደም" በሚል መሪ ቃል ዕብ12:24 ባለው ክፍል መሰረት የእግዚአብሔርን ቃል መልዕክት ቀርቦአል ።

በዘማሪ መጋቢ ተስፋዬ ጋቢሶ"የሚቋቋምህ ማንም የለም" የሚለውን ዝማሬአቸውን በማቅረብ አገልግለዋል።

በመቀጠል በዘማሪ መጋቢ አገኘው ይደግ የተጻፈው "ስንሰበሰብ" የተሰኘው የመጽሐፍ ምረቃ የተካሄደ ሲሆን በዘማሪ መጋቢ ተስፋዬ ጋቢሶና በቤተክርስቲያን አባቶች በጸሎት ተባርኮ መጽሐፉ ተመርቆ ለእግዚአብሔር ህዝብ ለንባብ ቀርቧል።

በመጨረሻም በዘማሪ መጋቢ አገኘው ይደግ እጣዬ እና ምስጋና ይዤ መጣሁኝ ዝማሬ ቀርቦ መርሐ ግብሩ ተጠናቋል።
#ዓለሜ #እጅግ #ድንቅ ዝማሬ ነው ተባረኩበት.. https://youtu.be/cjRsxtMypeU?si=PESIOiHuAXAS0tXp

ዓለሜ #ዘማሪ ናቲ ካሳ aleme #singer Nati Kassa ተተኪ የቤተክርስቲያን #ልጆች እንዳሉን ማሳያ የሆነ ዝማሬ ነው።

#share በማድረግ ለምትወዷቸው አድርሱላቸው።
#ኢየሱስ ላውድልህ ሃገሩን
#ዘማሪ ይድኔ

ኢየሱስ ላውድልህ ሃገሩን የዘማሪ ይድነቃቸው ተካ የዝማሬ ድግስ #ቅዳሜ መጋቢት 7 ከቀኑ 7 ሰዓት #ጀምሮ በሚሊኒየም #አዳራሽ ይካሄዳል።

ይሄንኑ ድግስ በተመለከተ ዘማሪው ከአጋር አካላት #ጋር ለሚዲያዎች #ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

መግለጫውን ዘማሪ ይድነቃቸው ተካ፡ የሙዚቃ አቀናባሪ ዳዊት ለሚ፡ የድግሱ ብቸኛ አጋር ኤል ሃዳር ኢንጂነሪንግ፡ የጸጥታ አካል ዘጸዓት ሴኩሪቲ እና አስተባባሪዎች መግለጫውን በጋራ ሰጥተዋል።

በሮች ከ4 ሰዓት ጀምሮ ክፍት ይሆናሉ። የተባለ ሲሆን ዘማሪ ይድነቃቸው፡ ከኢየሱስ አልበም እና ቸኮለብኝ አልበኖች ዝማሬዎችን ያቀርባል።

#ነብይ ጥላሁን ጸጋዬ #በእግዚአብሔር ቃል የሚያገለግል ሲሆን ምንም አይነት የመግቢያ ክፍያ እንደሌለዉም ተጠቅሷል።

ከዳዊት ለሚ ባንድ ጋር ለ3 ወራት ዝግጅት ሲደረግ መቆየቱን የጠቀሰዉ ዘማሪ ይድኔ ድግሱ ከአዲስ አበባ ውጪ ባሉ ከተሞችም ይካሄድ ተብሏል።

ኢየሱስ #2 አልበም ከ5 ወራት ፊት ነበር የተለቀቀው። ቸኮለብኝ #1 አልበም 2003 መለቀቁ ይታወሳል።

The Christian News - የክርስቲያን ዜና በመግለጫዉ ላይ ተገኝተን ዝርዝሩን አሰናዳንላችሁ።

#ሙሉ ጋዜጣዊ መግለጫዉን ከደቂቃዎች በኋላ በቪዲዬ ይዘን የምንመለስ ይሆናል።
#እግዚአብሔር #ይመስገን 🙏🙏🙏

በድል ተጠናቋል...

#ኢየሱስ ላውድልህ ሃገሩን በሚል በዘማሪ ይድነቃቸው ተካ የተዘጋጀ የመዝሙር ኮንሰርት #ዛሬ ከቀኑ 7 ሰዓት #ጀምሮ በሚሊኒየም #አዳራሽ ተካሂዷል።

ተወዳጁ #ዘማሪ ይድነቃቸዉ ተካ ከዳዊት ለሚ ባንድ ጋር በመሆን በ2003ዓ.ም የተለቀቀዉን ቁጥር አንድ #ቸኮለብኝ እና ከ5 ወራት በፊት የተለቀቀውን #ኢየሱስ አልበም አቅርቧል።

ነብይ ጥላሁን ጸጋዬ #በእግዚአብሔር ቃል በማካፈል አገልግሏል።

ዘማሪ ይድነቃቸው የአገልግሎት እና የህይወት ወጣ ዉረዱን በተመለከተ አጭር ዘጋቢ የቀረበ ሲሆን የመዝሙር ኮንሰርቱ በድል ተጠናቋል።
#ዘማሪ ቴዎድሮስ ታደሰ (ቴዲ) #ፓስተር ተደርጎ ተሾመ።

ዘማሪ ቴዲ በአሁኑ ሰዓት "አንድ ምዕራፍ" በሚል የዝማሬ ኮንሰርት እያከናወነ ሲሆን በኮንሰርቱ ላይ በመጋቢነት ሲሾም የቀረውን ጊዜ በተሰጠው ጸጋ #እግዚአብሔርን እና የእግዚአብሔን ሕዝብ በታማኝነት እና በቅንነት በተሰጠው ጸጋ ልክ ለማገልገል ቃል ገብቷል።

ቃል የማስገባቱን ስነ-ስረዓት የፌይዝ ባይብል ኢንተርናሽናል ቤተክርስቲያን መሪ የሆኑት ቢሾፕ ዳዊት ሞላልኝ አስፈጽመዋል።
#የኢየሱስ ወታደር ነኝ ... #ወደ አምላኩ ሄደ 😭
ከ40ዓመት በላይ በጌታ ቤት ቆይቷል...

#ሄደ #ወደ አምላኩ ሄደ ...
ኢየሱስን ብሎ አለምን የካደ ሄደ ..😭

ከ1945 - 2016 ...

ሙሉቀን በ1960ና 70ዎቹ ብዙዎች በኢትዮጵያ ወርቃማ በሚባለው የሙዚቃ ዘመን፣ ቁንጮ ከነበሩት መካከል ነዉ ይሉታል። ኋላ ላይም ወደ ጌታ #ኢየሱስ መጥቷል።

ሙሉቀን በ1945 ዓ.ም በጎጃም ክፍለ ሃገር ተወለደ። በልዩ ተሰጦው ምክንያት በ12 አመቱ ሙዚቃን የጀመረው ሙሉቀን፣ በለጋ እድሜው ነበረ በመሸታ ቤቶች ውስጥ “እናቴ ስትወልደኝ መች አማከረችኝ” በሚለው ሙዚቃ የጀመረው።

ሙሉቀን የዘፈኑ አለም በቃኝ ብሎ ወደ ጌታ ከመጣበት 1970ዎቹ ማገባደጃ አካባቢ ጀምሮ በዝማሬ ማገልገሉን ቀጥሏል። በየጊዜው የቀድሞ የዘፈን ወዳጆቹ የእንዝፈን ግብዣ ቢቀርብለትም፣ አሻፈረኝ ብሎ ቀጥሎበታል።

ህመሙ በጠናበት ጊዜም እነ ታማኝ በየነ ልህክምና ወጪ የዘፈን ድግስ እናዘጋጅ ሲሉትም በኔ ስም አይዘፈንም ብሎ በቅድስና የኖረ ጀግና ክርስቲያን ነው።

ሙሉቀን ወደ ክርስቲያኖች ካደረሳቸው መዝሙሮች መካከል “ስለ ውለታህ”፣ አድራሻ ቢስ ሆኜ በዓለም ውስጥ ስጨነቅ”፣ “ሃሌሉያ”፣ “አቤኔዜር” እና ሌሎችንም መዝሙሮችን ከሃሌሉያ አልበሙ አስመቶናል።

በአንድ ወቅት ጋዜጠኛ መታሰቢያ በEBS Tv ላይ "ከኢትዮጵያ ከወጣህ 38 ዓመት ሆኖሃል አትናፍቅህም?" የሚል ጥያቄ ብትሰነዝርለትም ሙሉቀን መለሠ ግን አትናፍቀኝም! ... ኢየሱስን ማየት ነው የናፈቀኝ ማለቱ የቅርብ ዓመች ትዝታ ነዉ።

#ዘማሪ #ሙሉ #ቀን ኑሮውን በአሜሪካን ሃገር ዋሽንግተን ዲሲ ከባለቤቱ ጋር አድርጎ በኖረበት በ71 ዓመቱ ወደ ሚወደውና ወዳገለገለው #ጌታ ሄዷል።

በነገራችን #ላይ ሙሉቀን መለሰ በዓለም የሙዚቃ ስራ ዉስጥ ለ14ዓመት ብቻ ከ13 ዓመቱ እስከ 27ዓመቱ ብቻ ነዉ የቆየው ዘፈን አቁሞ ወደ ጌታ ከመጣ ደግሞ 43 አመታትን አስቆጥሯል።

ከበርካታ ዝማሬዎቹ መካከል
አለም ተስፋ ቁረጭ አልተገናኘንም
አምላክ ከእኔ ጋር ነው አታሸንፊኝም

እንዲሁም
ከኢየሱስ ጋራ ሲሄዱ
ከጌታ ጋራ ሲሄዱ
እንዴት ያምራል ጎዳናዉ
እንዴት ያምራል መንገዱ

በብዙዎች ዘንድ የሚታወቀዉ
የኢየሱስ ወታደር ነኝ
የኢየሱስ ወታደር ነኝ
እዋጋለሁኝ አልሽነፍም
ለጠላት እጅን አልስጥም

የሚሉት ተጠቃሽ ናቸዉ ...

ለሙሉቀን መለሰ ቤተሰብና ወዳጅ ዘመዶች The Christian News - የክርስቲያን ዜና በድጋሜ መጽናናትን ይመኛል።
#ዜና
«ዲልቢ ገለታ የሱሲፍ" የተሰኘ የመዝሙር ድግስ በሚሊኒየም #አዳራሽ ሊካሄድ ነዉ።

ኤልሀዳር ኢንጂነሪንግ ከዘማሪ ጳውሎስ ተገኝ ጋር በመተባበር «ዲልቢ ገለታ የሱሲፍ» የተሰኘውን የመዝሙር ድግስ በሚኒሊየም አዳራሽ ሰኔ 2/2016 ዓ.ም ቀን ከ7፡00 ጀምሮ ማዘጋጀቱን #ዛሬ ግንቦት 27/2016 ዓ.ም በስካይ ላይት ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል ።

#ዘማሪ ጳውሎስ ተገኝ ሶስት አልበሞችን እና የተለያዩ ዝማሬዎችን ከተለያዩ ዘማሪዎች ጋር በመስራት ለኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ያበረከተ ሲሆን «ሙጫ ካዮ» ከተሰኘ የህፃናት ህብረት ጋር በመሆን ሁለት ቪሲዲዎችን በመስራት ለአማኞች አድርሷል።

በእለቱ ስለታማ ነገሮች ምግብ እና መጠጥ ይዞ መግባት እንደማይቻል የተገለፀ ሲሆን በሚሊኒየም አዳራሽ መጠጥ እና ምግብ በሽያጭ እንደተዘጋጀ ተነግሯል።

በዚህ ፕሮግራም ለመሳተፍ የመግቢያ ዋጋው በነፃ ስለሆነ መጨናነቅ እንዳይፈጠር ከጠዋቱ 4 ሰአት ጀምሮ እንዲገኙ ጥሪ አስተላልፈዋል።

ፎቶ 📸 @ጥላሁን ደሳለኝ

#ወንጌል #ለዓለም #ሁሉ