The Christian News
5.32K subscribers
3.06K photos
27 videos
720 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
#የኢየሱስ ወታደር ነኝ ... #ወደ አምላኩ ሄደ 😭
ከ40ዓመት በላይ በጌታ ቤት ቆይቷል...

#ሄደ #ወደ አምላኩ ሄደ ...
ኢየሱስን ብሎ አለምን የካደ ሄደ ..😭

ከ1945 - 2016 ...

ሙሉቀን በ1960ና 70ዎቹ ብዙዎች በኢትዮጵያ ወርቃማ በሚባለው የሙዚቃ ዘመን፣ ቁንጮ ከነበሩት መካከል ነዉ ይሉታል። ኋላ ላይም ወደ ጌታ #ኢየሱስ መጥቷል።

ሙሉቀን በ1945 ዓ.ም በጎጃም ክፍለ ሃገር ተወለደ። በልዩ ተሰጦው ምክንያት በ12 አመቱ ሙዚቃን የጀመረው ሙሉቀን፣ በለጋ እድሜው ነበረ በመሸታ ቤቶች ውስጥ “እናቴ ስትወልደኝ መች አማከረችኝ” በሚለው ሙዚቃ የጀመረው።

ሙሉቀን የዘፈኑ አለም በቃኝ ብሎ ወደ ጌታ ከመጣበት 1970ዎቹ ማገባደጃ አካባቢ ጀምሮ በዝማሬ ማገልገሉን ቀጥሏል። በየጊዜው የቀድሞ የዘፈን ወዳጆቹ የእንዝፈን ግብዣ ቢቀርብለትም፣ አሻፈረኝ ብሎ ቀጥሎበታል።

ህመሙ በጠናበት ጊዜም እነ ታማኝ በየነ ልህክምና ወጪ የዘፈን ድግስ እናዘጋጅ ሲሉትም በኔ ስም አይዘፈንም ብሎ በቅድስና የኖረ ጀግና ክርስቲያን ነው።

ሙሉቀን ወደ ክርስቲያኖች ካደረሳቸው መዝሙሮች መካከል “ስለ ውለታህ”፣ አድራሻ ቢስ ሆኜ በዓለም ውስጥ ስጨነቅ”፣ “ሃሌሉያ”፣ “አቤኔዜር” እና ሌሎችንም መዝሙሮችን ከሃሌሉያ አልበሙ አስመቶናል።

በአንድ ወቅት ጋዜጠኛ መታሰቢያ በEBS Tv ላይ "ከኢትዮጵያ ከወጣህ 38 ዓመት ሆኖሃል አትናፍቅህም?" የሚል ጥያቄ ብትሰነዝርለትም ሙሉቀን መለሠ ግን አትናፍቀኝም! ... ኢየሱስን ማየት ነው የናፈቀኝ ማለቱ የቅርብ ዓመች ትዝታ ነዉ።

#ዘማሪ #ሙሉ #ቀን ኑሮውን በአሜሪካን ሃገር ዋሽንግተን ዲሲ ከባለቤቱ ጋር አድርጎ በኖረበት በ71 ዓመቱ ወደ ሚወደውና ወዳገለገለው #ጌታ ሄዷል።

በነገራችን #ላይ ሙሉቀን መለሰ በዓለም የሙዚቃ ስራ ዉስጥ ለ14ዓመት ብቻ ከ13 ዓመቱ እስከ 27ዓመቱ ብቻ ነዉ የቆየው ዘፈን አቁሞ ወደ ጌታ ከመጣ ደግሞ 43 አመታትን አስቆጥሯል።

ከበርካታ ዝማሬዎቹ መካከል
አለም ተስፋ ቁረጭ አልተገናኘንም
አምላክ ከእኔ ጋር ነው አታሸንፊኝም

እንዲሁም
ከኢየሱስ ጋራ ሲሄዱ
ከጌታ ጋራ ሲሄዱ
እንዴት ያምራል ጎዳናዉ
እንዴት ያምራል መንገዱ

በብዙዎች ዘንድ የሚታወቀዉ
የኢየሱስ ወታደር ነኝ
የኢየሱስ ወታደር ነኝ
እዋጋለሁኝ አልሽነፍም
ለጠላት እጅን አልስጥም

የሚሉት ተጠቃሽ ናቸዉ ...

ለሙሉቀን መለሰ ቤተሰብና ወዳጅ ዘመዶች The Christian News - የክርስቲያን ዜና በድጋሜ መጽናናትን ይመኛል።