#አሁን_ኢትዮጵያ_ታላቅ_ሚስዮናውያንን_ላኪ_ሀገር_የምትሆንበት_ጊዜ_መጥቷል።
#ፓስተር_ጌቱ_አያሌው
ሁላችንም እንደምናውቀው ለበርካታ አስርት አመታቶች የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ወንጌልን ወደ ሀገራችን ባመጡ የውጪ ሚስዮናውያን ስራ በብዙ ተባርካለች እንዲሁም የወንጌላውያን ቤተክርስቲያናችን ከማስጀመር አኳያ ብዙ እርዳታ አግኝታለች።
እግዚአብሄር ቤተክርስቲያኒቱ በብዙ ፈተናዎች ውስጥ እንድታልፍ ቢፈቅድም ይህን ተከትሎ አስደናቂ እድገት መጥቷል። በአሁኑ ወቅት በሀገራችን ውስጥ በወንጌላውያን ማህበረሰብ ውስጥ ከ 20 ሚሊዮን በላይ አማኞች እነሚገኙ የሚነገር ሲሆን ፤ ይህም ሀገራችንን ትልቅ የወንጌላውያን አማኞች ቁጥር ካላቸው ሀገራቾች ዝርዝር ተርታ እንድትመደብ አድርጓታል።
በዚህም ወደ ተቀሩት ወንጌል ያልደረሰባቸው የአለማችን ሰዎች አለም-አቀፍ ድንበር ተሻጋሪ ሚስዮናውያንን ለመላክ ያልተነካ አቅም ያልት ሀገር ያደርጋታል።
ሚስዮናውያንን የምንቀበልበት የነበረበትን ወቅት በደስታ አሳልፈነዋል። ነገር ግን በአሁን ወቅት ይህ አቅጣጫ ተቅይሮ ኢትዮጵያ የሚሽን ተልዕኮዋንና ግዴታዋን የምትወጣበት ሚስዮናውያንን የምትልክበት ጊዜ አሁን መጥቷል። መላው አለምም ይጠብቃታል።
#ከሰሞኑ_በአንድ_ትልቅ_ምድረክ_ላይ_ካስተላለፉት_መልዕክት_ተቀንጭቦ_የተወሰደ።

እንደ #ኢየሱስ 40 ቀን እጾማለው ያለው #ፓስተር ሞተ
እንደ #ኢየሱስ ክርስቶስ 40 ቀናት ለመጾም የሞከረው ሞዛምቢካዊ #ፓስተር ሕይወቱ አለፈ።
ፍራንሲስ ባራጃህ የተባለው ፓስተር ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ለ40 ቀናት በመጾም ያደረገውን ምሳሌ ለመድገም ባደረገው ሙከራ ነው ለሕልፈት የተዳረገው።
ፓስተሩ በሞዛምቢክ ማዕከላዊ ግዛት ማኒሺያ ውስጥ የምትገኘው ሳንታ ትሪንዳድ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መሥራች ሲሆን ከጾሙ ጋር በተያያዘ ሕይወቱ ማለፉ ረቡዕ ዕለት ተረጋግጧል።
ፓስተር ፍራንሲስ ባራጃህ በጾሙ ምክንያት ክፉኛ በተዳከመበት ጊዜ ወደ ሆስፒታል የተወሰደ ቢሆንም ሕይወቱን ለማትረፍ ሳይቻል መቅረቱ ተዘግቧል።
ፓስተሩ ጾሙን ለ40 ቀናት ለማድረግ አቅዶ የነበረ ቢሆንም፣ ከ25 ቀናት ጾም በኋላ ግን በከፍተኛ ሁኔታ ክብደቱ ቀንሶ ለመቆምም ሆነ ለመራመድ ከማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሶ ነበር።
ይህም ሆኖ ግለሰቡ በጾሙ የቀጠለ ሲሆን፣ ከቀናት በኋላ ግን በዘመዶቹ እና በቤተክርስቲያኗ አባላት ውትወታ ወደ ሆስፒታል ተወስዷል።
ነገር ግን በጾሙ ምክንያት ክፉኛ በመጎዳቱ የተነሳ ሐኪሞች ጤናውን ለመመለስ ያደረጉት ሙከራ ሳይሳካ ለህልፈት ተዳርጓል።
ፓስተር ፍራንሲስ ባራጃህ ጾሙን ከጀመረ በኋላ በታየበት ከፍተኛ አካላዊ ለውጥ የተነሳ የቤተክርስቲያኗ አባላት እና በዙሪያው ያሉ ሰዎች ሕልፈቱ ብዙም አላስደነቃቸውም።
ፍራንሲስ ባራጃህ በጾሙ ወቅት ከፍተኛ የክብደት መቀነስ እና የሰውነት አቋሙም ተቀይሮ እንደነበር ተነግሯል።
BBC News Amharic

#አዲስ
#ፓስተር_ጻዲቁ ምንድነው_ያሉት?
#አቋም የተያዘባቸው 6 ነጥቦችስ ምን ምን ናቸው?
በኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረትና በግሬት ኮሚሽን ሚኒስትሪ ኢትዮጵያ አዘጋጅነት እየተካሄደ ባለው ጉባኤ ላይ ከሶሰት ሺህ በላይ መሪዎች እየተሳተፉ ይገኛል።
#የሕብረቱ ፕሬዝደንት ፓስተር ጻዲቁ አብዱ ዛሬ በነበረው የመክፈቻ መሰናዶ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት በዋናነት 6 ነጥቦች ላይ ትኩረት እንዲደረግ እና #አቋም እንዲያዝ አጽንዖት እንዲሰጠው አሳስበዋል።
እነዚህ ስድስት ነጥቦች ምን ምን ናቸው?
1. እንደ ወንጌላውያን #ጥላቻን እና ቂም በቀልን ለግጭት የሚዳርጉ ድርጊቶችን እና ሰዎችን ከየትኛውም ወገን ይሁን ለጥላቻ የሚቀሰቅሱ #ለቂም በቀል የሚያነሳሱ ግጭቶች በተለያየ ምክንያት በሰዎች መካከል እንዲነሱ የሚያደርጉ ሰዎችን #እምቢ ማለት እና ልንቃወም ይገባል።
2. በእኛ ወንጌላውያን ስም እይተጠሩ እና #ወንጌላውያን ናቸው ተብሎ እየታሰቡ ነገር ግን ከወንጌላውያን አስተምሮ በእጅጉ የራቁ #የሃሰት #ትምህርት የሚያስተምሩትን ኢ-መጽሐፍ ቅዱሳዊ ልምምድ ያላቸውን ፤ እጅግ የተበላሸ የሞራል #ሕይወት የሚኖሩትን ሰዎች የማንቀበል መሆኑን በይፋ የምንናገርበት እና የምናሳውቅበት ጊዜ ነው።
3. የኢትዮጵያን ሕዝብ #በብሔር እና #በሃይማኖት ለማጋጨት የሚደረገው ሙከራ መቃወም ይገባናል። እምነታቸውም ይሁን ብሔራቸው ከኛ ለተለዩ ሰዎች "ባልንጀራሕን እንደ ራስህ ውደድ" በሚለው መርህ እንዲሁም "ሰዎች እንዲያደርጉላቸሁ የምትወዱትን እናንተም ለሌሎች እንዲሁ አድርጉላቸው። በሚለው ወርቃማ ሕግ እየተመራን ለሰዎች ሁሉ መልካምን እናድርግ። ጥላቻን በፍቅር እናሸንፍ። ለክፉ #መልካም በመመለስ የሚረግሙንን በመመረቅ የጌታችንን ምሳሌ እንከተል።
4. በእምነታችን እና በማንነታችን ምክንያት የሚደረግብንን ማንኛውም #መድሎ እና #ጫና #መቃወም አለብን። ወንጌላውያን ዛሬም በተለያዩ ቦታዎች በተለይም የወንጌላውያን አማኞች ቁጥር በሚያንስባቸው አከባቢዎች እጅግ የከፋ መድሎ እንደሚደረግብን እናውቃለን። ሀገራችን የሁላችንም ሀገር ስለሆነች እንደ ዜጋ ለሃገራችን ሰላም እና ልማት መስራት ይጠበቅብናል። የሌሎች #እምነት ያለ አግባብ #ሲደፈር ዝም አለማለት የራሳችንንም #በሕግ አግባብ ማስጠበቅ ይገባናል።
5. በሰሜኑ የሃገራችን ክፍል የነበረው የእርስ በዕርስ #ጦርነት በሰላማዊ መንገድ ስለተቋጨ እና #ሕዝቡ እፎይታ ስላገኘ አከባቢውም ከጦርነት ስላረፈ ታላቅ ደስታ ተሰምቶናል። ይህ ሰላም ጸንቶ እንዲቆይ እንዲሁም ግጭት ባለባቸው ሌሎች የሃገራችን ክፍሎች ሰላም እንዲሰፍን እኛ ወንጌላውያን እጅግ አብልጠን ልንጸልይ እና ለሰላም የራሳችንን ድርሻ ልንወጣ ይገባል።
6. (አጽንዖት የሚፈልግ #ጉዳይ) #ግብረ_ሰዶም ሰበዓዊም ዲሞክርራሲያዊም መብት አይደለም። #ግብረ_ሰዶም_ሐጢያት_ነው። ግብረ ሰዶም ምንም ከፍቅር ጋር ግንኙነት የለውም። በግብረ ሰዶም ችግር ስለወደቀ ሰው አዝናለሁ። ከዚህ አስከፊ ከሆነ ሐጢያት እንዲወጣ እጸልይለታለሁ። ነገር ግን ሃጢያቱን ልምምዱን የእግዚአብሔር ቃል እጅግ የሚያወግዘው የከፋ #ሐጢያት ስለሆነ #እቃወማለሁ።
ዛሬ በሰበዓዊ ስም የዲሞክራሲ መብት ነው ተብሎ ግብረሶዶማዊነትን በተለያየ መንገድ #በአፍሪካ በተለይም ከ97% በላይ ሃይማኖተኛ በሆንን ሀገር ላይ በተለያየ መንገድ ለመጫን አዕምኖዕችን ለዚህ ዝግጁ የሚደረገውን ግፊት በሙሉ እኛ እንደ #ወንጌላውያን አንቀበል። እንቃወመዋለን።
ግብረ ሰዶም በመጽሐፍ ቅዱስ እጅግ የከፋ ሐጢያት እና የሐጢያት ምሳሌ ነው። ሰዶም እና ጎመራ ተቃጥለው የጠፉት በዚህ ሃጢያት ምክንያት ነው።
እግዚአብሔር ሰዎችን በመልኩ ወንድ እና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው። ጾታዬን ለማወቅ እንድሜዬ 18 መድረስ የለበትም። ስወለድ እና እግዚአብሔር ሲፈጥረኝ ማን እንደሆንኩኝ አውቃለሁ።
ጾታችሁን የምታውቁት ስታድጉ ነው የሚለው አደገኛ አስተምሮ ስለሆነ ዝም ብለን አናልፍም። ግብረ ሰዶም ሰበዓዊነት ሳይሆን ሰበዓዊነትን ወደ አውሬነት የሚለውጥ ስበዓዊነትን የሚያሳንስ ሴጣናዊ የሚያደርግ ሐጢያት ነው።
በየትኛውም #ሐጢያት ላይ ግልጽ #አቋም መውሰድ እንዳለብን ሁሉ በተለይ በግብረሰዶም ላይ አፋችንን ዘግተን የምንቀመጥበት አይደለም። ስለዚህ ለሰዎቹ እናዝናለን ከዚህ ጉድጓድ እና አዝቅት ውስጥ እንዲወጡ በፍቅር እንጸልይላቸዋልን ፤ እናለቅሳለን። ነገር ግን ሐጢያቱ ሐጢያት ነው።
መጋቢ ጻዲቁ አብዶ
የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት ፕሬዝደንት

#አሳዛኝ #ዜና
#አዲስ
በኤርትራ ከ10 ዓመት እስር በኋላ ሕይወታቸው ያለፈው #ፓስተር ቀብራቸው እንዳይፈጸም ተከለከለ።
ከዓመታት እስር በኋላ ሕይወታቸው ያለፈ #ወንጌላዊ የቀብር ሥነ-ስርዓታቸው እንዳይከናወን መከልከሉ ተነገረ።
በአሥመራ ሕይወታቸው ያለፈው የወንጌላውያን #አማኞች ፓስተር እንዳይቀበሩ ክልከላውን ያደረጉት የኤርትራ ባለስልጣናት መሆናቸውን ለቤተሰቡ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ለቢቢሲ ትግርኛ ገልጸዋል።
ከ10 ዓመታት እስር በኋላ ከቀናት በፊት ሕይወታቸው ያለፈው ፓስተር ተስፋይ ሥዩም እስከ ዛሬ ረቡዕ ሚያዚያ 11/2015 ዓ.ም. ድረስ ግብዓተ መሬታቸውን ሳይፈጸም አስክሬናቸው በሆስፒታል እንደሚገኝ ለደኅንነታቸው ሲባል ስማቸውን የምንጠቅሳቸው ምንጮች ተናግረዋል።
ቢቢሲ ከምንጮቹ እንዳረጋገጠው ፓስተር ተስፋይ ሥዩም ከ11 ቀናት በፊት ከዚህ ዓለም በሞት ቢለዩም የቤተሰብ አባላት ቀብራቸውን ለመፈፀም የሚያስችል ፈቃድ ከሚመለከታቸው የመንግሥት ኃላፊዎች ማግኘት አልቻሉም።
በኢትዮጵያ የመሰረት ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አገልጋይ የሆኑት ፓስተር ሚካኤል ለቢቢሲ እንደተናገሩት፣ ፓስተር ተስፋይ በኤርትራ ከቤተክርስቲያኑ መስራቾች አንዱ እንደሆኑ እና በእምነታቸው የተነሳ ከ10 ዓመታት በላይ በእስር መቆየታቸውን ይናገራሉ።
በሁኔታው የተጨነቁት የሟች ቤተሰቦች “የደህንነት ከፍተኛ ባለስልጣናትን” ጨምሮ የተለያዩ ኃላፊዎችን ቢያነጋግሩም መፍትሄ አለማግኘታቸውንም ፓስተር #ሚካኤል ተናግረዋል።
በዚህ ጉዳይ ላይ የኤርትራ #መንግሥት ቃል አቀባይ አቶ የማነ ገብረመስቀልን ምላሽ እንዲሰጡ ያደረግነው ተደጋጋሚ ሙከራ ለጊዜው አልተሳካም። (BBC)
ፓስተር ተስፋይ አስር ዓመት በእስር ቤት ከቆዩ በኋላ በጠና በመታመማቸው የተነሳ ከሁለት ወራት በፊት ከእስር መፈታታቸውን ቤተሰቦቻቸው ይናገራሉ።
ፓስተር ተስፋዬ ከእስር ከተፈቱ በኋላ በሆስፒታል ህክምና ሲከታተሉ ቆየተው ሚያዝያ 1 2015 ዓ.ም ሕይወታቸው አልፏል።
ነገር ግን በሚከተሉት እምነት ምክንያት የቀብር ስነ ስርዓታቸው በትውልድ ቦታቸው አሥመራ በሃዝዝ መካነ መቃብር ለማድረግ ፍቃድ ማግኘት እንዳልቻሉ ፓስተር ሚካኤል አስረድተዋል።
በ60ዎቹ ዕድሜ ውስጥ የሚገኙት ፓስተር #ተስፋዬ ባለትዳርና የአንድ ልጅ አባት ነበሩ።
በኤርትራ ውስጥ በመንግሥት እውቅና የተሰጣቸው ሃይማኖቶች ኦርቶዶክስ ተዋህዶ፣ ካቶሊክ፣ ወንጌላዊ ሉተራን እና ሱኒ እስልምና ብቻ ሲሆኑ የሌላ እምነት ተከታዮች እውቅና አይሰጣቸውም።
የሌላ የእምነት ተከታዮች በእምነታቸው ምክንያት ለእስር ለስደትና እንደሚዳረጉ ይነገራል።
በዚህ ዓመት መጋቢት ወር ላይ በከረን ከተማ በድብቅ በጋራ ለማምለክ ወደ 30 የሚጠጉ #ወንጌላውያን አማኞች ከተሰባሰቡ በኋላ መታሰራቸው ተዘግቦ ነበር።
በወቅቱ ከታሰሩት መካከል ለአቅመ አዳም ያልደረሱ ተማሪዎች እንደሚገኙበት ተገልጿል።
ኤርትራ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት አባል ብትሆንም የሰብአዊ መብቶችን እና የእምነት ነፃነትን በመጣስ ትከሰሳለች።
በኤርትራ ጉዳይ የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ልዩ ራፖርተር ሞሃመድ አብዱልሰላም ባቢከር ከወራት በፊት ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ባቀረቡት ሪፖርት በኤርትራ ያለው የሰብአዊ መብት ሁኔታ እየከፋ መምጣቱን ገልጸው ነበር።
የኤርትራ ባለስልጣናት የመብት ጥሰት ውንጀላውን “ፖለቲካዊ ዓላማ ያለው ነው” ሲሉ የሚተቹ ሲሀን እውቅና ከተሰጣቸው ሃይማኖቶች ውጪ ያሉ እምነቶች የምዕራባውያን አጀንዳ ማስፈጸሚያ ናቸው ይላሉ።

ከ #ፓስተር ሄኖክ ሲንገሌ ጋር የተደረገ አዝናኝ ቆይታ #የአሁን ጊዚ አገልጋዮች ጠንካራ ናቸው #መስሚያቸውን ጥጥ አድርገው ነው የሚያገለግሉት
https://youtu.be/zo9rx-MkSiQ
https://youtu.be/zo9rx-MkSiQ
YouTube
ከ #ፓስተር ሄኖክ ሲንገሌ ጋር የተደረገ አዝናኝ ቆይታ #የአሁን ጊዚ አገልጋዮች ጠንካራ ናቸው #መስሚያቸውን ጥጥ አድርገው ነው የሚያገለግሉት
ከ #ፓስተር ሄኖክ ሲንገሌ ጋር የተደረገ አዝናኝ ቆይታ #የአሁን ጊዚ አገልጋዮች ጠንካራ ናቸው #መስሚያቸውን ጥጥ አድርገው ነው የሚያገለግሉት ወዳችሁ እና ፈቅዳችሁ ስለምትመለከቱን ከልብ እናመሰግናለን!!! Like, Share ማድረጎን አይርሱ!!#በ...
#አዲስ #ዜና
የሐዋሳ ሞቲቴ ፉራ ሆስፒታል ከህይወት #ብርሃን #ቤተክርስቲያን #ጋር በመተባበር በኮምፓሽን #ኢንተርናሽናል ድርጅት በኑሮ ደረጃቸው ዝቅተኛ የሆኑ ህጻናት #ሙሉ የጤና ምርመራ ተደረገላቸው።
ለህጻናቱ ሙሉ ምርመራ በነጻ ያደረገው የሞቲቴ ፉራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ነው።
የሞቲቴ ፉራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ጤና ቡድን (Family Health Team) ከሆስፒታሉ MCC ኮሚቴ ጋር በመተባበር ነው ለEP 706 ህጻናት ልማት ኘሮጀክት አጠቃላይ የጤና ምርመራ ህክምና ያደረገው።
#ፓስተር ጌቱ አያሌው የሐዋሳ ህይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን መጋቢ በከተማችን ካሉ የደሀ ደሀ ህጻናት መካከል የትምህርት፣ የጤና፣ የቀለብና ሌሎችም ድጋፍ የሚደረግላቸው ህጻናት መኖራቸውን ገልጸዋል።
በህጻናት ላይ መንግስት፣ ሁሉም የሃይማኖት ተቋማት፣ ባለሀብቶች፣ እና ሌሎችም በመተባበር ከሰራን ከፍተኛ የሰው ሀይል በማፍራት እናተርፋለን ሀገርም ትባረካለች ብለዋል።
የሞቲቴ ፉራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ስራአስኪያጅ አቶ ይርዳቸው አናቶ በህይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን እና ኮምፓሽን ከሚረዱ ህጻናት ውስጥ ዛሬ ለ3 መቶ 26 ህጻናት መሉ የጤና ምርመራ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
ቀደም ሲል በሆስፒታሉ ይህንን መሰል ተግባር ቤት ለቤት የጤና ህክምና በሚሰጡ ባለሙያዎች እየተተገበረ ስለመሆኑ ያስረዱት አቶ ይርዳቸው ምርመራው የህጻናቱን እድገት ክትትል የሚያደርግ #ነው ብለዋል።
በጤና ማዕከል ሄደው መታከም ለማይችሉ ህጻናት ነጻ ምርመራ መደረጉን የገለጹት አቶ ይርዳቸው ሆስፒታሉ ሙሉ ቁሳቁስ ይዞ በህይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን ግቢ በመገኘት የበጎ ፍቃድ ስራውን እያከናወነ መሆኑን ጠቁመዋል።
ዶ/ር ሳምራዊት ተፈራ በሞቲቴ ፉራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የህጻናት ህክምና ስፔሻሊስት ናቸው።
ለእነዚህ ህጻናት የጤና ምርመራ እንዲደረግ በቀረበ ጥሪ መሰረት ተግባራዊ እያደረጉ ስለመሆኑ ተናግረዋል።
በዚህም የህጻናቱ እድገት፣ የአመጋገብ ሁኔታ፣ኤችአይቪ፣ የመሳሰሉት ምርመራ እየተደረገላቸው መሆኑንም አክለዋል።

#መሪዎች #ድሬደዋ ገብተዋል።
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነየሱስ ማዕከላዊ ሲኖዶስ ፕሬዝዳንት ቄስ ፈለቀ ጥበበና እና የኢትጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል ፅ/ቤት ሃላፊ #ፓስተር_ጌቱ_ለማ ፣ ሌሎችም አመራሮች የድሬዳዋ አስተዳደር ካቢኔ በድሬዳዋ መካነ የሱስ ማህበረ ምዕመናን ይዞታ ላይ ያስተላለፈውን ውሳኔ አስመልክቶ ከከተማይቱ ክቡር ከንቲባ አቶ ከዲር ጁሐር ጋር ለመወያየት በተያዘው ቀጠሮ መሰረት ጥቅምት 25/2016 ዓ/ም ወደ #ድሬዳዋ_ገብተዋል።
አመራሩ ድሬዳዋ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ እንደደረሱ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ክቡር አቶ አርቢቡህ ፣ የፍትህ ጸጥታና ህግ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ አብዱሰላም የከንቲባ ጽ/ቤት ሐላፊ ክቡር አቶ ገበየሁ የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት አመራር ክቡር አቶ ደረጀ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ብሩክ ፣ የድሬዳዋ ሐይማኖት ተቋማት መሪዎች የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ካውንስል አመራሮች እና ሌሎችም የመንግስት አመራሮች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
በመድረኩ ላይ የኃይማኖት ተቋማት ሰብሳቢ የሆኑት ሼህ ኢብራሂም ለሁሉም እኩል ወደሆነችው የአብሮነት የፍቅር እና የመቻቻል ከተማ ወደሆነችው ድሬዳዋ እንኳን መጣችሁ በማለት ከሩቅ በጆሮ የሚሰማው እና በቅርበት በአይን የሚታየው የተለየ መሆኑን በማውሳት በቆይታችሁ መልካም ጊዜ እንደምታሳልፉ ተስፋ አደርግለሁ ብለዋል።
የመካነ አየሱስ ቤተክርስቲያን ከፍተኛ አመራሮችም አመስግነዋል።
ጥቅምት 26 ረፋዱ ላይ የውይይት ጊዜ እንደሚኖር ለማወቅ ተችሏል።

አሜሪካዊው #ፓስተር ለጋዛ #ክርስቲያኖች #ገንዘብ በማሰባሰብ #ላይ ይገኛሉ ተባለ።
ዊሊያም ዴቭሊን የተባለው #ይህ ፓስተር ከ2010 ጀመሮ #ወደ ጋዛ ከ30 ጊዜ በላይ ለሚሽን #ስራ ተመላልሰዋል። በእነዚህ ጉዞአቸውም በጋዛ የሚገኙትን የመጨረሻዎቹን 3 አብያተ ክርስቲያናት ሲያገለግሉ ነው የቆዩት።
በጋዛ ከሚገኙ 2.2 ሚሊዮን ዜጎች መካከል ወደ 1ሺህ የሚጠጉ ብቻ ናቸው ክርስቲያኖች።
በጋዛ በአንዲት የግሪክ ኦሮቶዶክስ #ቤተክርስቲያን ከ500 በላይ ክርስቲያን #እና ሙስሊሞች ተጠልለው የነበረ ቢሆንም በእስራኤል የአየር ጥቃት ቤተ ክርስቲያኗም ፈራርሳ የተጠለሉትም ተሰደዋል።
ሪዲም የተሰኘ የባልቴቶች እና ወላጅ አልባ ሚኒስትሪ በጋዛ የሚያካሂዱት እኚህ ፓስተር ካለፈው የፈረንጆቹ ዲሴምበር #ወር ጀመረው #ወደ 50ሺህ ዶላር መሰብሰብ መቻላቸውን ለክርስቲያን ፖስት ገልጸዋል።
#ምንም #እንኳን ገንዘቡ የተሰበሰበ ቢሆንም ወደ ጋዛ ለመላክ መጀመሪያ ወደ ዌስት ባንክ ከዚያ በጋዛ ላሉ ክርስቲያኖች እንደሚደርስ ነው የተናገሩት።
በጦርነቱ በጋዛ #ብቻ እስካሁን ከ22 ሺህ በላይ ሰዎች ሲገደሉ ወደ 58 ሺህ የሚጠጉ ደግሞ ቆስለዋል። በአንጻሩ በእስራኤል 1200 ሰዎች ህይወት አልፏል። አሁን ለጋዛ ዜጎች የሚያስፍልገው ጸሎት እና ጸሎት ብቻ ነው ብለዋል።
ፓስተር ዊሊያም ዴቭሊን በግብጽ፣ ጋዛ፣ ፓኪስታን፣ አፍጋኒስታን እና ጆርዳን የሚገኙ አናሳ ቁጥር ያላቸውን ክርስቲያኖች የሚያገለግል ሚኒስትሪ ይመራሉ።
ክርስቲያን መሪዎች ወደ ጋዛ ምድር ሄደው ለምን አይረዱም በሚል ጥያቄያቸውም ይታወቃሉ። ለአሁኑ ግጭትም ቢሆን የእስራኤልን ጦር እንዲሁም የሃማስ ጦር ይወቅሳሉ። በቬትናም ጦርነት ተዋጊ ነበርኩ የሚሉት እኚህ #ሰው በጦርነት ዋናዎቹ ተጎጂዎች ንጹሃን ናቸው ብለዋል።

#እንኳን #ደስ #አልዎት
#ፓስተር ደሳለኝ #አበበ ደግም ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ።
የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን 93ኛው ጠቅላላ የመሪዎች ጉባኤ በመሠረተ ክርስቶስ ሴሚናሪ ግቢ ውስጥ እየተካሄደ ይገኛል።
በዚሁ መሠረት ፓስተር ደሣለኝ አበበ ለሁተኛው የአገልግሎት ዘመን 98.8% ድምፅ በማግኘት የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ፕሬዚዳንት ሆነው እንዲያገለግሉ ተመርጧል።
The Christian News - የክርስቲያን ዜና እንኳን ደስ አለዎት በማለት ደስታችንን እየገለፅን #መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንሎት ይመኛል።