The Christian News
5.37K subscribers
3.08K photos
29 videos
730 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
“ካሁን በኋላ #ሴት #ነኝ የሚሉ ወንዶችን አናስተምርም” ኖተርዳም ስነ መለኮት ኮሌጅ

በአሜሪካ የሚገኘው እውቁ የኖተርዳም ስነ መለኮት ኮሌጅ ከዚህ ቀደም ያስተላለፈውን ውሳኔ ቀለበሰ። በአሜሪካ ኢንድያና ግዛት የሚገኘው የቅድስት #ማርያም ኖተርዳም የሴቶች ስነ መለኮት ኮሌጅ #ነው #ወደ ቀድሞው አቋሜ ተመልሻለው ያለው።

የኮሌጁ ፕሬዝዳንት #እና የቦርድ ሰብሳቢ በጋራ በመሆን “ወደ ካቶሊካዊት እሴታችን ተመልሰናል” ሲሉ መግለጫ አውጥተዋል።

ከወር በፊት ሴት ሆነው ተፈጥረው #ወንድ ነኝ ብለው የሚያምኑ ሰዎችን ኮሌጁ እቀበላለው ብሎ ነበረ። ኮሌጁ በውሳኔው ምክኒያት ትችቶች ተዘንዝረውበታል።

የኮሌጁ ቦርድ እና መሪዎች #ምንም #እንኳን በተለዋዋጭ አለም #ውስጥ ብንኖርም፣ የቤተ ክርስቲያንን አቋም ሳንቀያይር እናስቀጥላለን ሲሉ ተደምጠዋል።

ውሳኔው #ግን በኮሌጁ ተማሪዎች እና መምህራን ዘንድ ተቀባይነት አላገኘም። ይሄንን አይነት ምላሽ ከኮሌጃችን ማህበረሰብ ባንጠብቅም፣ ካቶሊካዊ ማንነታችንን ግን አስጠብቀን መሄድ አለብን ሲሉ ባስተላለፉት መልዕክት ገልጸዋል።

ባለፈው #ወር በወሰንነው ውሳኔ በኮሌጃችን ህብረትን የሚያመጣ መስሎን ነበረ፣ #ነገር ግን ልዩነትን ፈጥረናል፣ ለዚህም #ይቅርታ እንጠይቃለን ብለዋል።
አሜሪካዊው #ፓስተር ለጋዛ #ክርስቲያኖች #ገንዘብ በማሰባሰብ #ላይ ይገኛሉ ተባለ።

ዊሊያም ዴቭሊን የተባለው #ይህ ፓስተር ከ2010 ጀመሮ #ወደ ጋዛ ከ30 ጊዜ በላይ ለሚሽን #ስራ ተመላልሰዋል። በእነዚህ ጉዞአቸውም በጋዛ የሚገኙትን የመጨረሻዎቹን 3 አብያተ ክርስቲያናት ሲያገለግሉ ነው የቆዩት።

በጋዛ ከሚገኙ 2.2 ሚሊዮን ዜጎች መካከል ወደ 1ሺህ የሚጠጉ ብቻ ናቸው ክርስቲያኖች።

በጋዛ በአንዲት የግሪክ ኦሮቶዶክስ #ቤተክርስቲያን ከ500 በላይ ክርስቲያን #እና ሙስሊሞች ተጠልለው የነበረ ቢሆንም በእስራኤል የአየር ጥቃት ቤተ ክርስቲያኗም ፈራርሳ የተጠለሉትም ተሰደዋል።

ሪዲም የተሰኘ የባልቴቶች እና ወላጅ አልባ ሚኒስትሪ በጋዛ የሚያካሂዱት እኚህ ፓስተር ካለፈው የፈረንጆቹ ዲሴምበር #ወር ጀመረው #ወደ 50ሺህ ዶላር መሰብሰብ መቻላቸውን ለክርስቲያን ፖስት ገልጸዋል።

#ምንም #እንኳን ገንዘቡ የተሰበሰበ ቢሆንም ወደ ጋዛ ለመላክ መጀመሪያ ወደ ዌስት ባንክ ከዚያ በጋዛ ላሉ ክርስቲያኖች እንደሚደርስ ነው የተናገሩት።

በጦርነቱ በጋዛ #ብቻ እስካሁን ከ22 ሺህ በላይ ሰዎች ሲገደሉ ወደ 58 ሺህ የሚጠጉ ደግሞ ቆስለዋል። በአንጻሩ በእስራኤል 1200 ሰዎች ህይወት አልፏል። አሁን ለጋዛ ዜጎች የሚያስፍልገው ጸሎት እና ጸሎት ብቻ ነው ብለዋል።

ፓስተር ዊሊያም ዴቭሊን በግብጽ፣ ጋዛ፣ ፓኪስታን፣ አፍጋኒስታን እና ጆርዳን የሚገኙ አናሳ ቁጥር ያላቸውን ክርስቲያኖች የሚያገለግል ሚኒስትሪ ይመራሉ።

ክርስቲያን መሪዎች ወደ ጋዛ ምድር ሄደው ለምን አይረዱም በሚል ጥያቄያቸውም ይታወቃሉ። ለአሁኑ ግጭትም ቢሆን የእስራኤልን ጦር እንዲሁም የሃማስ ጦር ይወቅሳሉ። በቬትናም ጦርነት ተዋጊ ነበርኩ የሚሉት እኚህ #ሰው በጦርነት ዋናዎቹ ተጎጂዎች ንጹሃን ናቸው ብለዋል።