The Christian News
5.37K subscribers
3.07K photos
27 videos
724 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
#ወንጌላውያን #ክርስቲያኖች #በያቤሎ ቦረና በሚገኘው #ኮረብታ ላይ እንዲያመልኩ #ያስገደዳቸው ምንድን #ነው?

በቦረና ያቤሎ ከተማ አቅራቢያ በሚገኝ ኮረብታ ስፍራ ላይ የሚሰግዱ ሰዎች ቪዲዮዎች እና ፎቶዎች በማህበራዊ ድረ-ገጾች ሲንሸራሸሩ ታይተዋል። የኮረብታው ስም 'ገርቢ ጎጥ' ይባላል።

በኮረብታው ስፍራ ላይ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሲጸልዩ እና ሲዘምሩ የሚያሳዩ ቪዲዮዎች ለብዙ ጊዜ በማህበራዊ አውታረ መረቦች ላይ ተሰራጭተዋል።

ቪዲዮው ህጻናት፣ ወጣቶች፣ ሴቶች እና አዛውንቶች ሳይቀሩ ለአምልኮ ተራራ ላይ ሲሰበሰቡ ያሳያል። እነዚህ ሰዎች በበጋ ጸሀይ ውስጥ ቆመው ይሰግዳሉ, በክረምት ደግሞ በዝናብ።

የእነዚህ ሰዎች ቪዲዮ በማህበራዊ ሚዲያ መሰራጨት ከጀመረ በኋላም ሰዎች በተለያዩ ምክንያቶች ሲናገሩ ተደምጠዋል።

ሙሉ የቪዲዮውን ዝርዝር ለመመልከት ሊንኩን ይጠቀሙ። https://www.youtube.com/watch?v=PTuislRsHeM
#ታይላንድ #ክርስቲያኖች

በታይላንድ ውስጥ የክርስቲያን ስደተኞች ከፍተኛ እስር እየተካሄደ ነው።

በታይላንድ የሚኖሩ የፓኪስታን ክርስቲያኖች ለዎርዚ ኒውስ እንደገለጹት የፖሊስ ሃይሎች ለአካለ መጠን ያልደረሱ ህጻናትን ጨምሮ በደርዘን የሚቆጠሩ አማኞችን እያሰሩ ነው ብለዋል።

እሁድ እለት በዎርዚ ኒውስ የተገኘ ምስል እንደሚያሳየው ከሆነ ፖሊስ ከውጪ እና በባንኮክ አካባቢ በሚገኙ ስደተኞች ላይ እርምጃ ሲወስድ ያሳያል።

እንደዘገባው ከሆነ በሳምንቱ መጨረሻ ቢያንስ 10 የፓኪስታን ክርስቲያን ቤተሰቦች ወደ እስር ቤት ተወስደዋል።
#በሊቢያ ስድስት የግብፅ #ክርስቲያኖች ታፍነው ተወሰዱ።

ስድስቱ ሰዎች ለስራ ወደ ሊቢያ ዋና ከተማ ትሪፖሊ ተጉዘዋል እንደነበር ምንጮች ተናግረዋል። ነገር ግን ከኤርፖርት ወደ ስራ ቦታቸው ሲጓዙ በህገ ወጥ ኬላ ላይ መቆማቸው ታውቋል። ሊቢያዊው ሾፌራቸው ወዲያው የተፈታ ሲሆን ነገር ግን ክርስቲያኖቹ ወዳልታወቀ ቦታ ተዛውረዋል ሲሉ ጉዳዩን የሚያውቁ ምንጮች ተናግረዋል።

ድርጊቱን በቅርበት የተከታተለው ግብፃዊው ጋዜጠኛ ናደር ሹክሪ፣ ታጋቾቹ በአንድ ምርኮ 15,000 የሊቢያ ዲናር (3,100 ዶላር) ክፍያ እንደሚፈልጉ ሰምቻለው ሲል ጽፏል።

ናድር ሹክሪ ቤተሰቦቻቸው ቤታቸውን ሳይሸጡ እነዚህን ክፍያዎች መክፈል እንደማይችሉ ተናግራለች። የግብፅ ፕሬዝዳንት እና መንግስት ጣልቃ እንዲገቡ አሳስበዋል።

አክሎም በየቀኑ ድብደባ እንደሚደርስባቸው እና በጣም ትንሽ ምግብ እንደሚያገኙም ተናግሯል።
#አሳዛኝ #ዜና

በእምነታቸው #ምክንያት ከ5ሺህ በላይ #ሰዎች ተገድለዋል።

ባሳለፈው አመት በናይጄሪያ 5,068 #ክርስቲያኖች በእምነታቸው ምክንያት መገደላቸው ተገለጸ። ከፈረንጆቹ 2009 ጀምሮ ደግሞ 52,250 ክርስቲያኖች ተገድለዋል ሲል የአለም አቀፉ የሲቪል ነፃነት እና የህግ የበላይነት ማኅበር (ኢንተርሶሳይቲ) አዲስ ሪፖርት አውጥቷል።

በሪፖርቱ መሰረት በ2023 የመጀመሪያዎቹ 100 ቀናት ውስጥ 1,041 ሰዎች መገደላቸውን የጠቀሰ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ፣ የዓለም አቀፍ የሃይማኖት ነፃነት ኮሚሽነር መፋሰስን አስመልክቶ ማስጠንቀቂያውን ሲያሰሙ የቆዩ ቢሆንም፣ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የናይጄሪያን መንግሥት በጉዳዩ ላይ አንዳችም አለመውሰዱ የክርስቲያኖች መጨፍጨፍ ስለ ፈቀደ ከ2009 ጀምሮ 52,250 ክርስቲያኖች በእምነታቸው ምክንያት መገደላቸውን የኢንተር ሶሳይቲ ዘገባ አረጋግጧል።

እንደዘገባው ከሆነ የቤተዕምነት ቦታዎች ፤ የቤተክርስቲያን ንብረት የሆኑ ትምህርት ቤቶች የጉዳት ሰለባ እንደሆኑ ተጠቅሷል።

በየአመቱ ለክርስትና አስቸጋሪ የሆኑ 50 ሀገራትን ዝርዝር በሚያወጣው ኦፕን ዶርስ መረጃ መሰረት ናይጄሪያ እጅግ አስቸጋሪ በመባል 6ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።
#ዘጠኝ #ክርስቲያኖች #የሞት #ፍርድ ሊወሰንባቸው ይችላል።

በሃገረ ሊቢያ 9 ሚሽነሪዎች የታሰሩ ሲሆን ስድስት ሊቢያውያን ሁለት የጉባኤዎች እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን አሜሪካዊያን ሚሲዮናውያን እና አንድ ፓኪስታናዊ በሊቢያ የውስጥ ደኅንነት ኤጀንሲ ተይዘው ታስረዋል።

እስረኞቹ ክርስትናን በመስበክ ተከሰው ሊገደሉ እንደሚችሉ የካቶሊክ ዜና አገልግሎት አስነብቧል።

ባለፈው ሳምንት የሊቢያ የውስጥ ደህንነት ኤጀንሲ ክርስትናን በመስበክ የተከሰሱትን የሊቢያ እና የውጭ ዜጎችን ለመያዝ በትሪፖሊ ከተማ ዘመቻ ከፍቷል ያለ ሲሆን የጸጥታ ኤጀንሲው በቁጥጥር ስር የዋሉት ሰዎች ቁጥራቸው ምን ያህል እንደሆነ አልገለጸም እና ስማቸውን ከመግለጽ የተቆጠበ ሲሆን የመጀመሪያ ፊደላቸውን ብቻ ገልጿል።

ኤጀንሲው የተያዙትን ሰዎች ፊታቸውን ሸፈኖ ክሱን ሲናዘዙ የሚያሳይ ቪዲዮ አውጥቷል። ሁለቱ አሜሪካውያን በትሪፖሊ በዛውያት አል ዳህማኒ ክፍለ ከተማ በሚገኘው ጌትዌይ ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤት እንግሊዝኛ በማስተማር ላይ ይሠሩ ነበር።

አሜሪካውያኑም ትምህርት ቤቱን በሚስጥር የክርስትና ሃይማኖት መስበኪያ ማዕከል አድርገውታል በሚል ተከሰዋል።

በሊቢያ ያለው የክርስቲያኖች ቁጥር 35,400 (ሰላሳ አምስት ሺህ አራት መቶ) ሲሆን ይህም (ከህዝቡ 0.5%) እንደሆነ የኦፕን ዶርስ መረጃ ያሳያል።

ለክርስትና የማይመቹ ሀገራትን በተመለከተ አመታዊ ሪፖርት የሚሰጠው ኦፕን ዶርስ ሪፖርት መሰረት ሊቢያ ለክርስትና ከማይመቹ 50 ሀገራት መካከል እጅግ አስቸጋሪ በመባል በ5ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።
#የሁለት_አመት #ልጅ #የእድሜ ልክ_እስራት_ተፈረደበት
70,000 የሚጠጉ #ክርስቲያኖች በእምነታቸው ምክንያት #ታስረዋል

The Christian News - የክርስቲያን ዜና

የ2ዓመት ሕጻንን ጨምሮ ቤተሰቦቹ የእድሜ ልክ እስራት ተፈረደባቸው።

ይህ የሆነው በሰሜን ኮርያ ነው። ለክርስትና ከማይመቹ እና እጅግ አስቸጋሪ ከሆኑ 50 ሀገራት መካከል በ1ኛ ስፍራ የምትገኘው #ሰሜን ኮርያ #አዲስ #ዜና ተሰምቷል።

በሰሜን ኮሪያ አንድ የሁለት #ዓመት #ልጅ እና መላው ቤተሰቡ ባለሥልጣኖች በልጁ ወላጆች እጅ #መጽሐፍ #ቅዱስ ማግኘታቸውን ተከትሎ የእድሜ ልክ እስራት እንደተፈረደባቸው የዩናይትድ ስቴትስ ግዛት ዲፓርትመንት የዓለም አቀፍ የሃይማኖት ነፃነት ኮሚሽን የ2022 ዓመታዊ ሪፖርቱን ገልጿል።

ሰሜን ኮሪያ “ሰዎችን በሃይማኖታዊ ተግባራቸው ምክንያት መግደሏን፣ ማሰቃየትን፣ ማሰርን እና አካላዊ ማጎሳቆሏን ቀጥላለች። በሰሜን ኮሪያ ወደ 70,000 የሚጠጉ ክርስቲያኖች በእምነታቸው ምክንያት ታስረዋል ሲል ዘገባው አመልክቷል።

"አግኖስቲዝም" እምነትን የምትከተለዉ ሰሜን ኮርያ ካላት ሕዝብ 400 ሺዎቹ ክርስቲያኖች እንደሆኑ ይነገራል።

ከፈረንጆቹ 2022 ዉጪ በተከታታይ አመታት ለክርስቲያኖች አስቸጋሪ በመባል በ1ኛ ደረጃ ተቀምጣ ቆይታለች።
#ስምንት #አብያተክርስቲያናት #ተቃጠሉ

በፓኪስታን 8 አብያተ ክርስቲያናት በጅምላ ፍርድ መቃጠላቸው ተሰማ።

ቤተ ክርስቲያኖቹ የተቃጠሉት #ሁለት ክርስቲያኖች እምነትን ተሳድባችኋል በሚል ክስ ነው። ቤተ ክርስቲያኖቹ ከመቃጠላቸው በፊት #ሙሉ በሙሉ መዘረፋቸው ነው የተሰማው። ከአብያተ ክርስቲያናቱ በተጨማሪ የክርስቲያኖች ቤቶችም ተዘርፈዋል።

#ክርስቲያኖች #ላይ ስለደረሰ ጉዳት #ግን የተባለ ነገር የለም።
በአካባቢው ያሉ ክርስቲያኖችም አመጹን ተከትሎ አካባቢውን ለቀው ተሰደዋል ነው የተባለው። በፑንጃብ ግዛት ጃራንዋላ በተባለች ከተማ ሁለት ክርስቲያኖች ስማቸው ተጠቅሶ በመስጊድ ስፒከር እስልምናን ተሳድበዋል ከተባለ ብኋላ ነው አመጹ የተጋጋለው ተብሏል።

ከፖሊስ ዘንድ የዘገየ ምላሽ መሰጠቱ ደግሞ በሃገሪቱ መንግስት ላይ ትልቅ ወቀሳን አስነስቷል። ፖሊስ ሁኔታዎች ሳይባባሱ መቆጣጠር ይችል ነበረ በሚል ነው የተወቀሰው።

የሃገሪቱ አብያተ ክርስቲያናት መሪዎች መንግስት ፍትህን እንዲያስከብር ጠይቀዋል። ጥሪውንም ተከትሎ 100 የሚያክሉ ሰዎች ታስረዋል። የሃገሪቱ ጸረ #እምነት #ህግ በተደጋጋሚ ወቀሳ ሲደርስበት ቆይቷል። ከ1987 ወዲህ ብቻ ከ2ሺህ በላይ ተከሰውበት፣ 88 ሰዎች በዚሁ ህግ ምክኒያት ህይወታቸው እንዲያልፍ ሆኗል።

በ2020 ብቻ የተመድ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን 69 ሰዎች እምነት ተሳድባችኋል በሚል ምክኒያት በደቦ ፍርድ መገደላቸውን ክርስቲያን ፖስት አስታዉሷል።

በ2023 ሪፖርት መሰረት ፖኪስታን ለክርስትና አስቸጋሪ ከሚባሉ 50 ሀገራት መካከል በ7ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።
#አሳዛኝ #ዜና
#9 #ክርስቲያኖች ተገደሉ።

በቄለም ወለጋ ጊዳሚ መካነ ኢየሱስ ቤ/ክ ጸሎት ላይ የነበሩ ሰዎች ከቤተ ክርስቲያን ተወስደው ተገደሉ

በምዕራብ ኦሮሚያ ቄለም ወለጋ ዞን፣ ጊዳሚ ከተማ ነው ጸሎት ላይ የነበሩት ሰዎች የተገደሉት።

አስተያየታቸውን ለቢቢሲ የሰጡት የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤ/ክ መካነ ኢየሱሱ ቲዎሎጂና ሚሽን መምሪያ ቄስ ዶ/ር ለሊሳ “የአዳር ጸሎት ላይ የነበሩ 9 የቤተ ክርስቲያኗ አባላት፣ በታጣቂዎች ተወስደው ተገድለዋል” ብለዋል።

በቤጊ-ጊዳሚ ሲኖዶስ በጊዳሚ ሰባካ፣ የሃሞ ቶኩማ ማህበረ ምዕመናን የምትገኘው ይህቺ ቤ/ክ አባላት የዛሬ ሳምንት ህዳር 14 ለሊት 8 ሰዓት ነው ከቤተ ክርስቲያኗ የተወሰዱት።

የቤተክርስያኗ ሽማግሌዎች፣ የወጣቶች ኮሚቴ አባላት እንዲሁም ሌሎች አገልጋዮች ናቸው ተወስደው የገደሉት።

ጥቃት አድራሾቹ ማን እንደሆኑ እስካሁን የታወቀ ነገር ግን የለም ስትል ቤተ ክርስቲያኗ አስታውቃለች።

ቢቢሲ ባደረገው ማጣራት መሰረት የተወሰዱት 9 ሰዎች ከሌሎች መካከል ተመርጠው መሆኑን ከቤተ ክርስቲያኗ አባላት አረጋግጧል። ለቅዳሜ ቀን የአምልኮ ፕሮግራም ዝግጅት የአዳር ጸሎት ይካፈሉ የነበሩ ሰዎች 12 ናቸው።

ከ12ቱ ሰዎች መካከል 2 ሴቶችና አንድ እድሜያቸው የገፋ አዛውንት ሳይወሰዱ ቀርተዋል ነው የተባለው።

ተወስደው የተገደሉት ሰዎች ምንም አይነት የፖለቲካዊ ተሳትፎ የላቸውም ነው የተባለው። ቄስ ዶ/ር ለሊሳ “ዘመዶቻቸውን በሞት ላጡ ወገኖች መጽናናትን ተመኝተው፣ መንግስት ለቤተ ክርስቲያን አባላት ፍትህ እንዲሰጥ” ሲል ጠይቀዋል።

በተመሳሳይ የዛሬ አመት እሁድ ቀን ጥቅምት 27 2014 በምስራቅ ወለጋ መካነ ኢየሱስ ቤ/ክ አምልኮ ላይ የነበሩ 15 ምዕመናን ጥቃት ተፈጽሞባቸው መሞታቸው ይታወሳል።

ጥቅምት 2015 ደርሶ በነበረው ግድያ ጥቃት አድራሾቹ ከሌላ አካባቢ የመጡ ናቸው ተብሎ መዘገቡ ይታወሳል ሲል BBC News Amharic አስነብቧል።
አሜሪካዊው #ፓስተር ለጋዛ #ክርስቲያኖች #ገንዘብ በማሰባሰብ #ላይ ይገኛሉ ተባለ።

ዊሊያም ዴቭሊን የተባለው #ይህ ፓስተር ከ2010 ጀመሮ #ወደ ጋዛ ከ30 ጊዜ በላይ ለሚሽን #ስራ ተመላልሰዋል። በእነዚህ ጉዞአቸውም በጋዛ የሚገኙትን የመጨረሻዎቹን 3 አብያተ ክርስቲያናት ሲያገለግሉ ነው የቆዩት።

በጋዛ ከሚገኙ 2.2 ሚሊዮን ዜጎች መካከል ወደ 1ሺህ የሚጠጉ ብቻ ናቸው ክርስቲያኖች

በጋዛ በአንዲት የግሪክ ኦሮቶዶክስ #ቤተክርስቲያን ከ500 በላይ ክርስቲያን #እና ሙስሊሞች ተጠልለው የነበረ ቢሆንም በእስራኤል የአየር ጥቃት ቤተ ክርስቲያኗም ፈራርሳ የተጠለሉትም ተሰደዋል።

ሪዲም የተሰኘ የባልቴቶች እና ወላጅ አልባ ሚኒስትሪ በጋዛ የሚያካሂዱት እኚህ ፓስተር ካለፈው የፈረንጆቹ ዲሴምበር #ወር ጀመረው #ወደ 50ሺህ ዶላር መሰብሰብ መቻላቸውን ለክርስቲያን ፖስት ገልጸዋል።

#ምንም #እንኳን ገንዘቡ የተሰበሰበ ቢሆንም ወደ ጋዛ ለመላክ መጀመሪያ ወደ ዌስት ባንክ ከዚያ በጋዛ ላሉ ክርስቲያኖች እንደሚደርስ ነው የተናገሩት።

በጦርነቱ በጋዛ #ብቻ እስካሁን ከ22 ሺህ በላይ ሰዎች ሲገደሉ ወደ 58 ሺህ የሚጠጉ ደግሞ ቆስለዋል። በአንጻሩ በእስራኤል 1200 ሰዎች ህይወት አልፏል። አሁን ለጋዛ ዜጎች የሚያስፍልገው ጸሎት እና ጸሎት ብቻ ነው ብለዋል።

ፓስተር ዊሊያም ዴቭሊን በግብጽ፣ ጋዛ፣ ፓኪስታን፣ አፍጋኒስታን እና ጆርዳን የሚገኙ አናሳ ቁጥር ያላቸውን ክርስቲያኖች የሚያገለግል ሚኒስትሪ ይመራሉ።

ክርስቲያን መሪዎች ወደ ጋዛ ምድር ሄደው ለምን አይረዱም በሚል ጥያቄያቸውም ይታወቃሉ። ለአሁኑ ግጭትም ቢሆን የእስራኤልን ጦር እንዲሁም የሃማስ ጦር ይወቅሳሉ። በቬትናም ጦርነት ተዋጊ ነበርኩ የሚሉት እኚህ #ሰው በጦርነት ዋናዎቹ ተጎጂዎች ንጹሃን ናቸው ብለዋል።
#ክርስቶስ እንኳን #ወደ ምድር ቢወርድ #አንድ አዳራሽ መስሪያ ቦታ አይሰጣችሁም

#ክርስቲያኖች ላይ ስደት በዝቷል።

በደቡብ ምስራቅ አውሮፓ በምትገኘው ኮሶቮ፣ ክርስቲያኖች #ላይ ስደት በርትቷል ተባለ።

በሃገሪቱ ክርስቲያኖች #ምንም አይነት የመሰብሰብ መብት እንደሌላቸው #እና ፈቃድ ለማግኘትም ሁኔታዎች እንደሚወሳሰቡባቸው ገልጸዋል።

የአርሜ #ቋንቋ ተናጋሪዎች የሚበዙባት ኮሶቮ፣ 93 በመቶ ዜጎቿ የእስልምና እምነት ተከታዮች ናቸው።

ምንም #እንኳን የሃገሪቱ ህገ መንግስት የሃይማኖት ነጻነትን የሚፈቅድ ቢሆንም፣ ክርስቲያኖች ላይ ግን መድሎና አመጽ ይበረታባቸዋል።

#ይህ ስደት በግል ደረጃም፣ የቀብር ስፍራ መከልከል፣ ንብረት የማፍራት መብት አለማግኘትና ሌሎችም በደሎች እየደረሱባቸው እንደሚገኙ ገልጸዋል።

በተለይ #ወንጌላዊያን ክርስቲያኖች፣ የባንክ ሂሳብ መክፈት፣ ንብረት ማፍራት እና ሰራተኞችን ቀጥሮ የመንቀሳቀስ ዴሞክራሲያዊ መብቶች የላቸውም።

በቅርቡ የወጣ #አንድ ህግ ደግሞ የሰርቢያ ኦርቶዶክስ፣ ካቶሊኮችን እና ሌሎችንም ታሪካዊ አብያተ ክርስቲያናትን ኢላማ ያደረገ ነው ይባልለታል።

በሃገሪቱ ያለፉትን 25 ዓመታት ያገለገሉ አንድ ቄስ ሲናገሩ፣ ያለው ስቃይ በግልጽ ስላልሆነ ይበልጥ ከባድ ያደርገዋል ብለዋል።

ለቀብር እንኳን በሙስሊሞች የቀብር ስፍራ፣ በኢማሞች የተመራ ቀብር ስነ ስርዓት እያደርግን ነው የምንገኘው ብለዋል። ምንም ቢሆን #ግን ለሃገራችን የወንጌል ተስፋ አለን ሲሉም እኚሁ ቄስ ይናገራሉ።

በኮሶቮ በ1980ዎቹ ወንጌላዊያን፣ ክርስቶስ እንኳን ወደ ምድር ቢወርድ አንድ አዳራሽ መስሪያ ቦታ አይሰጣችሁም የሚል ተደጋጋሚ ዛቻ ከወቅቱ ኮሚኒስት መንግስት ሲደርስባቸው እንደ ነበረ ዘገባዉ አስታዉሷል።