The Christian News
5.37K subscribers
3.08K photos
29 videos
730 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
#መጽሐፍ ምረቃ

"የሚስዮናዊው ማስታወሻ"

የሚስዮናዊው ማስታወሻ የተሰኘ መጽሐፍ በሚስዮናዊ አገልጋይ ፊልሞና ሴባ ተጽፎ በቤዛ ኢንተርናሽናል ቤተ ክርስቲያን እየተመረቀ ይገኛል።

መጽሐፉ ሚስዮናዊው በደቡብ እና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሲሰራ የነበረበትን የሚስዮን ቆይታ ያትታል።
በመጽሐፉ ዙርያ ጸሃፊ ስሜ ታደሰ ማብራርያ ሰጥተዋል።
#የሁለት_አመት #ልጅ #የእድሜ ልክ_እስራት_ተፈረደበት
70,000 የሚጠጉ #ክርስቲያኖች በእምነታቸው ምክንያት #ታስረዋል

The Christian News - የክርስቲያን ዜና

የ2ዓመት ሕጻንን ጨምሮ ቤተሰቦቹ የእድሜ ልክ እስራት ተፈረደባቸው።

ይህ የሆነው በሰሜን ኮርያ ነው። ለክርስትና ከማይመቹ እና እጅግ አስቸጋሪ ከሆኑ 50 ሀገራት መካከል በ1ኛ ስፍራ የምትገኘው #ሰሜን ኮርያ #አዲስ #ዜና ተሰምቷል።

በሰሜን ኮሪያ አንድ የሁለት #ዓመት #ልጅ እና መላው ቤተሰቡ ባለሥልጣኖች በልጁ ወላጆች እጅ #መጽሐፍ #ቅዱስ ማግኘታቸውን ተከትሎ የእድሜ ልክ እስራት እንደተፈረደባቸው የዩናይትድ ስቴትስ ግዛት ዲፓርትመንት የዓለም አቀፍ የሃይማኖት ነፃነት ኮሚሽን የ2022 ዓመታዊ ሪፖርቱን ገልጿል።

ሰሜን ኮሪያ “ሰዎችን በሃይማኖታዊ ተግባራቸው ምክንያት መግደሏን፣ ማሰቃየትን፣ ማሰርን እና አካላዊ ማጎሳቆሏን ቀጥላለች። በሰሜን ኮሪያ ወደ 70,000 የሚጠጉ ክርስቲያኖች በእምነታቸው ምክንያት ታስረዋል ሲል ዘገባው አመልክቷል።

"አግኖስቲዝም" እምነትን የምትከተለዉ ሰሜን ኮርያ ካላት ሕዝብ 400 ሺዎቹ ክርስቲያኖች እንደሆኑ ይነገራል።

ከፈረንጆቹ 2022 ዉጪ በተከታታይ አመታት ለክርስቲያኖች አስቸጋሪ በመባል በ1ኛ ደረጃ ተቀምጣ ቆይታለች።
#ታላቁ #የወንጌል ..
#ሰላም #ውድ #ቤተሰቦቻችን ከሰሞኑ #የኢትዮጵያ ወንጌላዊት #ቤተክርስቲያን መካነ #ኢየሱስ የመጽሐፍ #ቅዱስ ሳምንትን እያከበረች በክብረ በዓሉ የወንጌል አርበኛውን ኦኒስሞስ ነሲብን አስባለች።

ለመሆኑ እኚህ የወንጌል አርበኛ #ማን ናቸው? #ለኢትዮጵያ #ቤተክርስቲያን ያበረከቱት አስተዋጾስ ምን ይመስላል? የሚለውን በጥቂቱ እናስቃኛችሁ።

የክርስትና ስማቸው "ኦነሲሞስ" የሚባል ሲሆን የትውልድ ስማቸው #ግን "ሂካ አዋጅ" የሚባል ሲሆን የተወለዱት በ1856ዓ.ም በቀድሞ የኢሊባቦር #ክፍለ #ሀገር በሁሩም የምትገኝ #ልዩ ስሟ ኦጊ በመባል የምትጠራ መንደር #ነው

ኦነሲሞስ ገና በለጋነቱ በባርነት ከተሸጠ በኋላ ሙዚየንገር የተባለ የፈረንሳይ ቆንጺላ ነሻ አውጥቶት በአከባቢው የነበሩ የስዊድን ሚሲዮኖች እንዲያሳድጓቸው በአደራ እንደ ሰጣቸው በታሪክ ተመዝግቧል።

ኦነሲሞስ ኢርትራ በትምህርት ቤት በነበሩበት ወቅት #የክርስቶስ #ወንጌል ተመስክሮላቸው ጌታን ከተቀበሉ በኋላ ተጠምቀው #ኦነሲሞስ የሚል የክርስትና ስማቸውን ተቀበሉ።

ኦነሲሞስ ልዩ #ስጦታ እና #ክህሎት ያላቸው ስለነበሩ ይህንን አይተው ለትምህርት #ወደ ሲውድን ተላኩ በወቅቱ እድሜያቸው #20 ነበር ስዊድን ትምህርታቸውን አጠናቀው ከተመለሱ በኋላ የኦሮሞ (ኤክስጼዲሽን) የወንጌል ጉዞ ቡድን አባል እና መሪ በመሆን ለ3 #ጊዜ የተሳተፉ ሲሆን ከዚህ #ጉዞ በኋላ #መጽሐፍ #ቅዱስን ወደ #ኦሮምኛ የመተርጎም ስራቸውን እንደ ጀመሩ አረን የተባለ ጸሐፊ ዘግቦታል።

የኦሮምኛ መጽሐፍ #ቅዱስ ተርጓሚ እና የወንጌል አርበኛ የሆኑትን ኦነሲሞስ ነሲብ ታሪክን ከብዙ በጥቂቱ ቤተክርስቲያኒቱ በ2014ዓ.ም የመጸሐፍ ቅዱስ ቀንን በማስመልከት ለሳቸው በተዘጋጀው የመታሰቢያ ፕሮግራም ላይ ከቀረበው #ጽሁፍ በዚህ መልክ ቀንጭበን አቀረብንላችሁ።
#አስደሳች #ዜና #ለኢትዮጵያ #ቤተክርስቲያን

#የአማርኛ #መጽሐፍ #ቅዱስ መዝገበ ቃላት በድል ተጠናቋል።

ይሄንን ዜና እንደሰማው በቅድምያ እግዚአብሄርን አመሰገንኩኝ ምክንያቱም ለቤተክርስቲያን የአሁኑን ጨምሮ ለቀጣዩ ትውልድ የሚሆን በረከት እየመጣ እንደሆነ አምናለሁ።

ዜናው ለ23 ዓመታት ሲለፋበት የነበረው "የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት" በእግዚአብሄር እርዳታ እንደተጠናቀቀ የሚገልጽ ነው።

ምንም እንኳን የሕትመት ስራው በቅርብ ጊዜ የሚከናወን ቢሆንም የአንድ ወጣት እድሜ የሚያክል ተለፍቶበት የተሰራ ስራ እንደመመልከት ግን የሚያስደስት ነገር ያለ አይመስለኝም።

ለማንኛውም መጽሐፉ ገና ስላልታተመ ዝርዝር ጉዳይ የለኝም ነገር ግን ስለጸሃፊው እና ከዚህ ቀደም ስለነበሩት ስራዎች ግን የተወሰነ ልበል።

ጸሐፊው ዘላለም መንግስቱ ይባላል። ብዙዎች በምላቴ #ክርስትና ስራዎቹ ያውቁታል። ላለፉት ከ3 አስርት አመታት በላት #የኢትዮጵያን #ቤተክርስቲያን በበርካታ መልኩ እያገለገለ የሚገኝ ወንድም ነው።

የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ በነበረበት ጊዜ ስለ ጌታ ከሰማ በኋላ ከዲያቆንነት እስከ ወንጌላዊነት ... በበርካታ የአገልሎት ስራዎች በኢትዮጵያ ቃለሕይወት ቤተክርስቲያን አገልግሎ ተገልግሎ ዘልቋል።

ወንድም ዘላለም በ1984 የታተመች እና "አዲስ ሕይወትን የማዳረስ ዘዴ" የሚል ርዕስ ያላት በወንጌል ስርጭት እና በደቀመዝሙርነት ላይ የምታተኩር መጽሐፍ ጀምሮ የነህምያ መጽሐፍ ማጥኛ እና ቀላል ማብራሪያ "መፍረስ እና መታደስ" "መጽሐፍ ቅዱስ እና የአፈታት ስሕተቶች " የሚሉ መጽሀፍትን ለቤተክርስቲያን አበርክቷል።

ብዙዎች "መንፈስ #ቅዱስ እና ካሪዝማዊ ቀውሶች" በሚል 1988 ለሕትመት በበቃውን መጽሐፍ ያውቁታል። ምንም እንኳን ይህ መጽሀፍ የዛሬ 27ዓመት ገደማ ቢጻፍም ዛሬም ድረስ መነጋገሪያ ነው።

"ክርስቲያናዊ ኢትዮጰኝነት" "እንዝፍን ወይስ እንዘምር" "የሃሰተኞች እሳተ ገሞራ" የተሰኙት ደግሞ የቅርብ ጊዜ የወንድም ዘላለም ስጦታዎች ናቸው።

አብዛኛው #ሰው ደግሞ በአንድ ወቅት "ይድረስ ለዘማሪዎች" በሚል በወጣው ሲዲ ዛሬም ድረስ ያስታውሱታል። በነገራችን ላይ ወንድም ዘላለም "ይድረስ ለዘማሪዎች" የሚለውን ሃሳብ ዛሬ ባለንበት ሁኔታ ቢሰራው ምን ሊፈጠር እንደሚችል መገመት እጅግ ይከብደኛል።

በምካቴ ክርስትና ብዙዎችን ከሃሰተኛ ነብያት እና ትምህርቶቻቸው ለመታደግ ለአመታት ሲታገል ቆይቷል።

መኖሪያውን በባህር ማዶ ላስ ቬጋስ ያደረገው ወንድም ዘላለም ዛሬም ድረስ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የነገ እጣ ፈንታ ዘውትር ሲያስጨንቀው እመለከታለሁ።

ከ30 ዓመት በላይ በመጽሀፍ ስራ ውስጥ የቆየው ወንድም ዘላለም ከሰሞኑ ላለፉት 23 ዓመታት ሲደክምበት የነበረውን ስራ መጨረሱን አብስሯል። ይህ ለኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን እጅግ ትልቅ የምስራች ነው።

ምክንያቱም እስከዛሬ በቤተክርስቲያን ይህን የመሰለ መፅመፍ አልነበረም ታዲያ ለመጽሀፍ ቅዱስ ተማሪዎች ብቻ ሳይሆን ለሃገራችን የቋንቋ እድገትም አንድ ሃሳብ እንዳዋጣ አምናለሁ።

ከዚህ ቀደም #የክርስቲያን #ዜና ወንድም ዘላለምን ቃለ መጠይቅ የማድረግ እድል ያገኘን ሲሆን ምናልባት ለወደፊት በድጋሜ እንደምናገኘው ተስፋ እናደርጋለንን።

ለማንኛውም ለዚህ ድንቅ ስራ ግን እግዚያብሄርን እያመሰገንን በትዕግስት ስለጨረሰው ለወንድም ዘላለም አድናቆታችን ይድረሰው። ምንልባት ጥቂት በሚባል ጊዜ ውስጥ የእርማት ስራው ተጠናቆ ለህትመት እንደሚበቃ እና ሁላችንም ጋር እንደሚደርስ እምነታችን ትልቅ ነው።

ለማንኛውም ስለ ሁሉም #እግዚያብሄር ክብሩን ይውሰድ።
ለሙሉ #ጊዜ አገልጋዮች ሲሰጥ የቆየው #መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሥልጠና ተጠናቀቀ።

“Biblical Education By Extension (BEE World)” እና በዳላስ ያለችው የኢትዮጵያ ወንጌላውያን ቤተ ክርስቲያን በአጋርነት ሲያሠለጥኗቸው የነበሩትን ዐሥራ ሰባት የመጀመሪያ ዙር ተማሪዎችን አስመረቁ።

ሥልጠናው የተሰጠው ከተለያዩ ቤተ እምነት ለመጡ የሙሉ ጊዜ አገልጋዮች ሲሆን፣ ሠልጣኞቹ በአገልግሎት ስፍራቸው ሳሉ አገልግሎታቸውን በተሻለ መልኩ ማካሄድ እንዲችሉ የሚያስችሏቸውን መጽሐፍ ቅዱሳዊና ሥነ መለኮታዊ ኮርሶች እንዲያገኙ የሚያስችሏቸው ናቸው ተብሏል።

ሥልጠናው ላለፉት ሦስት ዓመታት በአዳማ #ከተማ ሲሰጥ የቈየ ሲሆን፣ ተማሪዎቹ ወደ አካባቢያቸው በመሄድ በዐሥራ ስድስት ቡድኖች ውስጥ ያሉ 256 ተማርዎችን በማሠልጠን ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

“BEE World” መቀመጫውን በአሜሪካን አገር ያደረገ ለትርፍ ያልተቋቋመ ተቋም ሲሆን፣ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ላሉና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሥልጠና ላላገኙ አገልጋዮች በፓስቶራል ሚኒስትሪ ዲፕሎማ፣ በቲዮሎጂና ቸርች ሊደርሺፕ አሶሺዬት ዲግሪ እንዲሁም በቲዮሎጂ የመጀመሪያ ዲግሪ የሚሰጥ አገልግሎት ነው።

#የኢትዮጵያ #ወንጌላውያን #ቤተክርስቲያን በዳላስ ከBEE World ጋር በአጋርነት ሲሰጡ የቆዩት ሥልጠና፣ በቀጣይነት በደብረ ብርሃን ከተማ የሚሰጥ ሲሆን፣ ከአካባቢው የሚመጡ የሙሉ ጊዜ አገልጋዮች በሠልጠናው ተካፋይ እንደሚሆኑ ለሕንጸት የተደረሰው መረጃ ያስረዳል።

ምንጭ @Hintset Christian Society- ሕንጸት ክርስቲያናዊ ማኅበር
#ሰው ሸሽቶ #ቤተክርስቲያን ሲገባ #እንዴት ይገደላል? አገዳደሉ አሳቃቂ ነው። ቄስ ዶ/ር ዮናስ ይገዙ

የመካነ ኢየሱስ ፕሬዝደንት በዚህ ወረ በመካነኢየሱስ ምዕመናን ላይ የተፈጸመውን ግድያ አስመልክተው በሰጡት ማብራሪያ #መጽሐፍ #ቅዱስ ግምባራቸው #ላይ ነበር የተገደሉት ምዕመናን ከአንድ #ቀን በኋላ ነው የተገኙት ብለዋል።

ፕሬዝደንቱ አክለው #እንደ ቤተክርስቲያን መረጃው እስኪጣራ ነው ይፋ ያላደረግነው ያሉ ሲሆን በቤተክርስቲያን አካሄድ የቻልነውን ያህል ሄደናል ያሉ ሲሆን #መንግስት የሕዝብ የድህንነት #ጉዳይ በእጁ ነውና አሁንም #ተስፋ የምናደርገው መንግስት ገዳዮችን ለፍርድ እንደሚያቀርብ እናምናለን ሲሉም ተናግረዋል።

#ይህ ጥቃት በማን ነው የተፈጸመው ?

ከአደጋው የተረፉት ትክክለኛው ገዳዮች #ምን እንዳደረጉ እነማን እንደሆኑ ያውቃሉ። #ነገር #ግን ለደህንነታቸው ስለሚሰጉ ለመናገር ፍላጎት የላቸውም። መንግስት ግን ተከታትሎ ለፍርድ እንዲያቀርብልን እንጠይቃለን።
#እንኳን #አደረሳችሁ

በታላት ጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የነቀምቴ ማህበረ ምዕመናን 100ኛ ዓመት ክብረ-በዓል ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር በድምቀት ተካሄደ።

ማህበረ ምዕመኑ ከፍተኛ ዝግጅት ሲያደርግበት የቆየው 100ኛው ዓመት የምስረታ #እና የአገልግሎት ቆይታን የሚዘክረው ክቡረ በዓል ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር፣ ማህበረ ምዕመኑ ስድስት ሺህ ሰዎችን እንዲያስተናግድ ባስገነባው አዲሱ የአምላክ አዳራሽ ተካሂዷል።

ከማስጀመሪያ መርሃ-ግብሩ #አንድ #ቀን አስቀድሞ የማህበሩ ምዕመናን በነቀምቄ #ከተማ በነቂስ በመውጣት የከተማ ፅዳት እና የጎዳና #ላይ የወንጌል ስርጭት አድርገዋል።

በዓሉንም ለመካፈል ከመላው #ኢትዮጵያ በርካታ እንግዶች፣ በውጪ ሀገራት የሚኖሩ የማኅበረ ምዕመኑ #ልጆች እና ማህበረ ምዕመኗን ለበርካታ ዓመታት ያገለገሉ ሚሲዮናዊያን ተገኝተዋል።

በዕለቱም በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና የእንግሊዝኛ ቋንቋዎች የተዘጋጀ እና የማህበረ ምዕመኑን የ100 ዓመታት አገልግሎት የዳሰሰ #መጽሐፍ ተመርቋል።

በዓሉም በተለያዩ መርሀ ግብሮች እስከ ታህሳስ 21/2016 ዓ.ም የሚከበር ይሆናል።

The Christian News - የክርስቲያን ዜና በድጋሜ ለማህበረ ምዕመኗ አባላት እና ለመላዉ ክርስቲያኖች እንኳን አደረሳችሁ ብለን #መልካም ምኞታችንን እንገልፃለን።
#አስቸኳይ...

ሞትን ለማምለጥ የሚደረግ የሞኞች እሩጫ 🏃‍♂️🏃‍♀️🏃‍♂️🏃‍♂️

ከሰሞኑ #አንድ ዘገባ አነብብኩኝ ዝገባው #ቃል በቃል "የፌስቡክ መስራቹ ማርክ ዙከርበርግ ራሳቸውን ከዓለም ፍጻሜ ለመጠበቅ በሚል መጠለያ እየገነቡ መሆኑ ተገለጸ" ይላል #እንደ ርዕሱ ቢሆን ሁላችንም ፈገግ ብለን ብናልፈው መልካም #ነበር #ግን አይሆንም።

#ሁሉም #ሰው እንደሚሞት እንዲሁም የአለም ፍጻሜ እንዳለ እርግጠኛ ነው። ግን የሚመጣውን ጥፋትም #ይሁን የሚጠብቀውን የዘላለም #ሞት #እንዴት ማምለጥ እንዳለበት የተረዳ አይመስለኝም።

ለዚህም ይመስለኛል ባለጸጋው በአንድ ደሴት #ውስጥ ባለ #መሬት ውስጥ በ100 ሚሊዮን ዶላር መጠለያ በመገንባት #ላይ መሆናቸው የተሰማው።

አንዳንዴ ግን አጠቃቀሙን ካላወቅነው ሃብታም መሆን ከባድ ይመስለኛል።

ከ120 ቢሊዮን ዶላር በላይ የተጣራ ሀብት እንዳላቸው የሚነገረው ቱጃሩ የፌስቡክ መስራች ዙከርበርግ የደሴቲቱን ስፍራ በ170 ሚሊዮን ዶላር ከዓመታት በፊት የገዙት ሲሆን አሁን #ደግሞ #በዚህ ስፍራ ላይ ቅንጡ የክፉ #ጊዜ መኖሪያ #ቤት እየገነቡ ነው፡፡

#ይህ ስፍራ ለኑሮ አስፈላጊ የሚባሉ ምግቦችን ማምረት፣ የኤሌክትሪክ ሀይል፣ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ማድረጊያ ሜዳ፣ ውሃ ዋና #እና ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ አገልግሎቶችን #ሙሉ ለሙሉ ከዚሁ ስፍራ ማግኘት በሚያስችል መልኩ በመገንባት ላይ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

#ክፉ ጊዜ ግን መቼ #ነው? ይህ ክፉ ጊዜ ሲመጣ እንዴት በደሴቶች ተሸሽገን ማለፍ እንችል ይሁን?

#መጽሐፍ #ቅዱስ የጌታ ምጽዓት እና የአለም ፍጻሜ በቀረበ ጊዜ በመጨረሻው ዘመን ጦርነት እና የጦር ወሬ ፤ የተፈጥሮ አደጋ መብዛት እንዳለ ይነግረናል በራዕይ መጽሀፍ ደግሞ ደሴቶችም #ሁሉ ሸሹ ተራራዎችም አልተገኙም ይላል።

ታዲያ ቱጃሩ ወዳጃችን ደሴትም ፈልፍሎ ለክፉ #ቀን የሚሆን ማምለጫ የሚያዘጋጀው ከማን ለመሸሽ ነው?

#ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ #እውነት እውነት እላችኋለሁ ባለጠጋ #ወደ #እግዚአብሔር መንግስት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢገባ ይቀላል ያለው ቃል ግልጽ ይመስላል።

ስለ ስሙ ያላቸውን ሁሉ ትተው የተከተሉት ግን የዘላለምን ሕይወት ይወርሳሉናል።

ለማንኛውም ወዳጄ ማርክን እና ሌሎች ባለጠጎች ከክፉ ቀን ማንም ሸሽቶ አያመልጥም እና መሸሸጊያ ዋሻ ወደ ሆነዉ ኢየሱስ ተሰብስበኝ በተሰጠን ጊዜ ተጠቅመን መጽሀፍ "እነሆ በደመና ይመጣል አይንም ሁሉ ያየዋል" እንደሚል ያንን ለማየት እንናፍቅ "ማራናታ" #አሜን መልዕክታችን ነው።
#መጽሐፍ #ቅዱስ የማያነብ #ክርስቲያን የተበደለ ነው”

ይህንን ያሉት የኢትዮጵያ የመጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር የቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር ተስፋጽዮን ደለለው ናቸው።

“መጽሀፍ ቅዱሳዊ እሴቶችን በሕዝባችን ሕይወት እናስርጽ!” በሚል መሪ ቃል የቅዱሳት መጻሕፍት ዐውደ ርዕይ ማስጀመሪያ መረሃ ግብር እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የማህበሩ ቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር ተስፋጽዮን ደለለው “መጽሐፍ ቅዱስ ያነበቡት ሁሉ ሕይወታቸው ተለውጧል ስለዚህ አሁን ያለው ትውልድ እንዲነብ ልናበረታታው ይገባል ብለዋል።” ብለዋል።

አክለውም መጽሐፍ ቅዱስን የማያነብ እና የማይገልጥ ክርስቲያን የተበደለ ነው። ማህበሩ ከማሳተም እና ከማሰራጨት ውጪ ብቻውን ምንም ማድረግ አይችልም በመሆኑም ህዝበ ምዕመኑ መጽሐፍ ቅዱስን አጠንክሮ እንዲያነብ ስለሚያስፈልግ ይህንን መድረክ አዘጋጅተናል ብለዋል።

የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር አዘጋጅነት የመጽሀፍ ቅዱስ ሳምንት በዓል እና የቅዱሳት መጻሕፍት ዐውደ ርዕይ መክፈቻ መረሃ ግብር በስካይ ላይት ሆቴል የአብያተ ክርስቲያናት መሪዎች በተገኙበት በመካሄድ ላይ ይገኛል።

መረሃ ግብሩ የቀጠለ ሲሆን The Christian News - የክርስቲያን ዜና በስፍራው የምንገኝ ሲሆን ተጨማሪ ዝርዝር መረጃዎች ይዘን የምንመለስ ይሆናል።