#አዲስ_መረጃ
#ለኢትዮጵያ_የምልጃና_የአምልኮ_ጊዜ_ሊዘጋጅ_ነው
The Christian News - የክርስቲያን ዜና
በዘጽዓት አፖስቶሊክ ሪፎርሜሽን ቤተክርስቲያን አዘጋጅነት “ለኢትዮጵያ የምልጃ እና የአምልኮ ምሽት” በሚል ርዕስ ልዩ የአምልኮ እና ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ ማድረጊያ መሰናዶ በመስቀል አደባባይ ሊከናወን ነው።
ጉዳዩን በተመለከተ የፕሮግራሙ አስተባባሪዎች ከደቂቃዎች በፊት ጋዜጣዊ መግለጫ በማዶ ሆቴል ሰጥተዋል።
መረሃ ግብሩ የወንጌል አማኙ ማህበረሰብ በሃገር ጉዳይ ላይ ጸሎት እንዲያደርግ በማስተባበር እና ለሰላም የበኩሉን የሚወጣበት መድረክ መፍጠር እና በጦርነቱ ለተጎዱ የማህበረሰቦች ክፍሎች በዘላቂነት መልሶ ማቋቋም የሚሆን የሃብት ማሰባሰብ የሚል አላማ ያለው ነው።
ዛሬ በነበረው መግለጫ ቤተክርስቲያን ከዚህ ቀደም በማህበራዊም ይሁን በመንፈሳዊ አገልግሎት የወንጌል አማኞች የማህበረሰብ ክፍል ጨምሮ ሁሉንም ኢትዮጵያውያንን ስታገለግል እና ሃገራዊ ሃላፊነቷን ስትወጣ መቆየቷን ጠቅሰው አሁን ደግሞ ወቅቱን እና ሃጋራዊ ጥሪውን በሚመጥን መልኩ ታላቅ ሃገራዊ መረሃ ግብር ለማቅረብ ዝጅግቱን ማጠናቀቃቸውን ጠቅሰዋል።
በመሆኑን “ጥር አንድን ለኢትዮጵያ” በሚል ሃሳብ የፊታችን ጥር 1 ቀን 2014ዓ.ም በመስቀል አደባባይ ከቀኑ 9:00 እስከ ምሽቱ 2:00ሰዓት የምልጃ እና የአምልኮ መረሃ ግብር ማሰናዳታቸውን የፕሮግራሙ አዘጋጆች ተናግረዋል።
እንደ አዘጋጆቹ ገለጻ ከሆነ በእለቱ ስለ ሃገራችን ወቅታዊ ሁኔታ የጽሎት እና የምልጃ ጊዜ የሚኖር ሲሆን በዝማሬ አምላክን የምናመሰግንበት እና በሰሜኑ የሃገራችን ክፍል ካለው ጦርነት ጋር ተያይዞ ለተፈናቀሉ እና ችግር ውስጥ ለሚገኙ ዜጎቻችን የሃብት ማሰባሰብ መረሃ ግብርም እንደሚኖር ተናግረዋል።
በአዲስ አበባ እና ዙሪያዋ የሚገኙ ከተሞች፤ ከባህር ማዶ የሚመጡ ኢትዮጵያውያን ዲያስፖራዎች ፤ የተለያዩ የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች፤ ከፍተኛ የመንግስት እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት አመራሮች እና የሃገር ሽማግሌዎች የሚገኙበት ፕሮግራም እንደሆነም በመግለጫው ተጠቅሷል።
ሙሉውን መረጃ The Christian News - የክርስቲያን ዜና በስፍራው ተገኝተን አዘጋጀነው።
ተጨማሪ ማብራሪያ በምስል በYoutube ቻናላችን ይዘን የምንመለስ ይሆናል።
https://www.youtube.com/channel/UCeHRJCDJ0wUDaBfAFmuMa7A?sub_confirmation=1

#ታላቁ #የወንጌል ..
#ሰላም #ውድ #ቤተሰቦቻችን ከሰሞኑ #የኢትዮጵያ ወንጌላዊት #ቤተክርስቲያን መካነ #ኢየሱስ የመጽሐፍ #ቅዱስ ሳምንትን እያከበረች በክብረ በዓሉ የወንጌል አርበኛውን ኦኒስሞስ ነሲብን አስባለች።
ለመሆኑ እኚህ የወንጌል አርበኛ #ማን ናቸው? #ለኢትዮጵያ #ቤተክርስቲያን ያበረከቱት አስተዋጾስ ምን ይመስላል? የሚለውን በጥቂቱ እናስቃኛችሁ።
የክርስትና ስማቸው "ኦነሲሞስ" የሚባል ሲሆን የትውልድ ስማቸው #ግን "ሂካ አዋጅ" የሚባል ሲሆን የተወለዱት በ1856ዓ.ም በቀድሞ የኢሊባቦር #ክፍለ #ሀገር በሁሩም የምትገኝ #ልዩ ስሟ ኦጊ በመባል የምትጠራ መንደር #ነው።
ኦነሲሞስ ገና በለጋነቱ በባርነት ከተሸጠ በኋላ ሙዚየንገር የተባለ የፈረንሳይ ቆንጺላ ነሻ አውጥቶት በአከባቢው የነበሩ የስዊድን ሚሲዮኖች እንዲያሳድጓቸው በአደራ እንደ ሰጣቸው በታሪክ ተመዝግቧል።
ኦነሲሞስ ኢርትራ በትምህርት ቤት በነበሩበት ወቅት #የክርስቶስ #ወንጌል ተመስክሮላቸው ጌታን ከተቀበሉ በኋላ ተጠምቀው #ኦነሲሞስ የሚል የክርስትና ስማቸውን ተቀበሉ።
ኦነሲሞስ ልዩ #ስጦታ እና #ክህሎት ያላቸው ስለነበሩ ይህንን አይተው ለትምህርት #ወደ ሲውድን ተላኩ በወቅቱ እድሜያቸው #20 ነበር ስዊድን ትምህርታቸውን አጠናቀው ከተመለሱ በኋላ የኦሮሞ (ኤክስጼዲሽን) የወንጌል ጉዞ ቡድን አባል እና መሪ በመሆን ለ3 #ጊዜ የተሳተፉ ሲሆን ከዚህ #ጉዞ በኋላ #መጽሐፍ #ቅዱስን ወደ #ኦሮምኛ የመተርጎም ስራቸውን እንደ ጀመሩ አረን የተባለ ጸሐፊ ዘግቦታል።
የኦሮምኛ መጽሐፍ #ቅዱስ ተርጓሚ እና የወንጌል አርበኛ የሆኑትን ኦነሲሞስ ነሲብ ታሪክን ከብዙ በጥቂቱ ቤተክርስቲያኒቱ በ2014ዓ.ም የመጸሐፍ ቅዱስ ቀንን በማስመልከት ለሳቸው በተዘጋጀው የመታሰቢያ ፕሮግራም ላይ ከቀረበው #ጽሁፍ በዚህ መልክ ቀንጭበን አቀረብንላችሁ።

#አስደሳች #ዜና #ለኢትዮጵያ #ቤተክርስቲያን
#የአማርኛ #መጽሐፍ #ቅዱስ መዝገበ ቃላት በድል ተጠናቋል።
ይሄንን ዜና እንደሰማው በቅድምያ እግዚአብሄርን አመሰገንኩኝ ምክንያቱም ለቤተክርስቲያን የአሁኑን ጨምሮ ለቀጣዩ ትውልድ የሚሆን በረከት እየመጣ እንደሆነ አምናለሁ።
ዜናው ለ23 ዓመታት ሲለፋበት የነበረው "የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት" በእግዚአብሄር እርዳታ እንደተጠናቀቀ የሚገልጽ ነው።
ምንም እንኳን የሕትመት ስራው በቅርብ ጊዜ የሚከናወን ቢሆንም የአንድ ወጣት እድሜ የሚያክል ተለፍቶበት የተሰራ ስራ እንደመመልከት ግን የሚያስደስት ነገር ያለ አይመስለኝም።
ለማንኛውም መጽሐፉ ገና ስላልታተመ ዝርዝር ጉዳይ የለኝም ነገር ግን ስለጸሃፊው እና ከዚህ ቀደም ስለነበሩት ስራዎች ግን የተወሰነ ልበል።
ጸሐፊው ዘላለም መንግስቱ ይባላል። ብዙዎች በምላቴ #ክርስትና ስራዎቹ ያውቁታል። ላለፉት ከ3 አስርት አመታት በላት #የኢትዮጵያን #ቤተክርስቲያን በበርካታ መልኩ እያገለገለ የሚገኝ ወንድም ነው።
የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ በነበረበት ጊዜ ስለ ጌታ ከሰማ በኋላ ከዲያቆንነት እስከ ወንጌላዊነት ... በበርካታ የአገልሎት ስራዎች በኢትዮጵያ ቃለሕይወት ቤተክርስቲያን አገልግሎ ተገልግሎ ዘልቋል።
ወንድም ዘላለም በ1984 የታተመች እና "አዲስ ሕይወትን የማዳረስ ዘዴ" የሚል ርዕስ ያላት በወንጌል ስርጭት እና በደቀመዝሙርነት ላይ የምታተኩር መጽሐፍ ጀምሮ የነህምያ መጽሐፍ ማጥኛ እና ቀላል ማብራሪያ "መፍረስ እና መታደስ" "መጽሐፍ ቅዱስ እና የአፈታት ስሕተቶች " የሚሉ መጽሀፍትን ለቤተክርስቲያን አበርክቷል።
ብዙዎች "መንፈስ #ቅዱስ እና ካሪዝማዊ ቀውሶች" በሚል 1988 ለሕትመት በበቃውን መጽሐፍ ያውቁታል። ምንም እንኳን ይህ መጽሀፍ የዛሬ 27ዓመት ገደማ ቢጻፍም ዛሬም ድረስ መነጋገሪያ ነው።
"ክርስቲያናዊ ኢትዮጰኝነት" "እንዝፍን ወይስ እንዘምር" "የሃሰተኞች እሳተ ገሞራ" የተሰኙት ደግሞ የቅርብ ጊዜ የወንድም ዘላለም ስጦታዎች ናቸው።
አብዛኛው #ሰው ደግሞ በአንድ ወቅት "ይድረስ ለዘማሪዎች" በሚል በወጣው ሲዲ ዛሬም ድረስ ያስታውሱታል። በነገራችን ላይ ወንድም ዘላለም "ይድረስ ለዘማሪዎች" የሚለውን ሃሳብ ዛሬ ባለንበት ሁኔታ ቢሰራው ምን ሊፈጠር እንደሚችል መገመት እጅግ ይከብደኛል።
በምካቴ ክርስትና ብዙዎችን ከሃሰተኛ ነብያት እና ትምህርቶቻቸው ለመታደግ ለአመታት ሲታገል ቆይቷል።
መኖሪያውን በባህር ማዶ ላስ ቬጋስ ያደረገው ወንድም ዘላለም ዛሬም ድረስ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የነገ እጣ ፈንታ ዘውትር ሲያስጨንቀው እመለከታለሁ።
ከ30 ዓመት በላይ በመጽሀፍ ስራ ውስጥ የቆየው ወንድም ዘላለም ከሰሞኑ ላለፉት 23 ዓመታት ሲደክምበት የነበረውን ስራ መጨረሱን አብስሯል። ይህ ለኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን እጅግ ትልቅ የምስራች ነው።
ምክንያቱም እስከዛሬ በቤተክርስቲያን ይህን የመሰለ መፅመፍ አልነበረም ታዲያ ለመጽሀፍ ቅዱስ ተማሪዎች ብቻ ሳይሆን ለሃገራችን የቋንቋ እድገትም አንድ ሃሳብ እንዳዋጣ አምናለሁ።
ከዚህ ቀደም #የክርስቲያን #ዜና ወንድም ዘላለምን ቃለ መጠይቅ የማድረግ እድል ያገኘን ሲሆን ምናልባት ለወደፊት በድጋሜ እንደምናገኘው ተስፋ እናደርጋለንን።
ለማንኛውም ለዚህ ድንቅ ስራ ግን እግዚያብሄርን እያመሰገንን በትዕግስት ስለጨረሰው ለወንድም ዘላለም አድናቆታችን ይድረሰው። ምንልባት ጥቂት በሚባል ጊዜ ውስጥ የእርማት ስራው ተጠናቆ ለህትመት እንደሚበቃ እና ሁላችንም ጋር እንደሚደርስ እምነታችን ትልቅ ነው።
ለማንኛውም ስለ ሁሉም #እግዚያብሄር ክብሩን ይውሰድ።

#መጋቢ ጻዲቁ አብዶ እና መጋቢ እና #ዘማሪ ተስፋዬ ጋቢሶ
የዛሬ አመት ልክ በዚህ ሰዓት ቀጠና #ሁለት #ሙሉ #ወንጌልል #ቤተክርስቲያን በነበረው መረሃ ግብር #የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ሕብረት #ፕሬዝደንት መጋቢ ጻዲቁ አብዶ ለኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን በተለይም ምዕመናንን ከስህተት ትምህርት በመጠበቅ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ልዩ ተሸላሚ በማለት ከልጅነት እስካሁን ድረስ ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን ውስጥ በተለያዩ የሃገራችን ክፍሎች እውነተኛውን ትምህርት በማስተማር ለአገልጋዮች በስደት ውስጥ እና በመከራ #ውስጥ ጸንተው በረሃብ በእጦት ሳይሸነፉ ምሳሌ በመሆን ሲያገለግሉ የነበሩ እና የኖሩ በሚል #ልዩ ተሸላሚ አድርጋ እውቅና ሰጥታ ነበር።
በተመሳሳይ #ዘመን ተሻጋሪ ፤ ገሳጭ ፤ መካሪ ፤ አጽናኝ እና #ክርስቶስ ተኮር በሆኑ ሰማይ ተኮር #ህይወት ህይወት በሚሸቱ ዝማሬዎቻቸው የሚታወቁት መጋቢ እና ዘማሪ ተስፋዬ ጋቢሶ እውቅና የዘጠችው ልክ በዚህ በያዝነው ሳምንት ነበር።
በሁሉም አብያተክርስቲያናት ዘንድ #እጅግ ተወዳጅ እንዲሁም ትውልድን እንደ ድልድይ በመሆን በማገናኘት በትሁትነታቸው የሚታወቁት መጋቢ እና ዘማሪ ተስፋዬ ጋቢሶ የሙሉ ወንጌል ብቻ ሳይሆን የአብያተክርስቲያናት ሁሉ እንቁ ሃብት የሆኑ ሰው ናቸው።
#እግዚአብሔር ብሄር የሰጣቸው ዝማሬዎች ዘመን ተሻጋሪ እና ልብን እና ህይወትን አዳሾች ሲሆኑ በተጨማሪ በማስተማር እና በማሰልጠን ይታወቃሉ።
ይህ ከሆነ እነሆ አንድ አመት ሆነው። #እነዚህ #ሁለት መሪዎች ዛሬም ድረስ #ለኢትዮጵያ #ቤተክርስቲያን ስጦታዎቻችን ናቸው። ስለ እነርሱ እግዚአብሔርን ዘውትር እያመሰገንን #ይህ ትውልድ ዛሬም ብዙ ነገሮችን እነዚህን ከመሰሉ መሪዎች እንደሚማር እምነት አለን።
#ቀሪ #ዘመናቸው #የተባረከ #ይሁን