The Christian News
5.32K subscribers
3.06K photos
27 videos
720 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
#ፍትህ_ይወጣል_ከሰማይ

ልክ ያልሆነውን ልክ አይደለም እንላለን። የፈረንሳይ መካነኢየሱስ ቤተክርክቲያንን ለመዝጋት የተደረገው ነገር ልክ አይደለም ግለሰብ ከቤተክርስቲያን የበለጠ ስልጣን የለውም። ፍትህ ለፈረንሳይ መካነኢየሱስ ቤተክርስቲያን። ከመካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ጎን እቆማለሁ።

#መጋቢ_እና_ዘማሪ_እንዳ ወ/ጊዮርጊስ

ብዙዎችን ያሳደገች ለአመታት የኖረች ታላቅ ቤተክርስቲያን በአንድ ግለሰብ የተነሳ ፈፅሞ ልትዘጋ አይገባም። ፍትህ ለፈረንሳይ መካነኢየሱስ ቤተክርስቲያን። ከመካነኢየሱስ ቤተክርስቲያን ጎን ነኝ።

#ሐዋሪያው_ታምራት_ታረቀኝ
#መጋቢ_ዮሐንስ_በሰና
#እረጅም_እድሜ_እንዲሰጣቸው
ከ50 ዓመታት በላይ በአሜሪካ፣ በእስያ፣ በአዉሮፓ እና በአፍሪካ እንዲሁም በልዩነት በኢትዮጲያ ወንጌል ያገለገሉ የወንጌል አርበኛ መጋቢ ዮሐንስ ባሳና ዛሬም በ73 እድምያቸዉ እንደ ወትሮ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ የእግዚአብሔር ቃል ትዉልድን በማስታጠቅ ላይ የሚገኙ ሞደል አገልጋይ ናቸው።
በረከቶቻችን እንደሆኑ እንመሰክራለን! ስለ እሳቸዉ እግዚአብሔር ይመስገን።
የወንጌል አባታችን በጨለማዉ ደርግ ዘመን እንኳ በአደባባይ ወንጌልን የሰበኩ ሰዉን በሃለሉያ የሚያደክሙ ሳይሆኑ ከጌታ የተሰጣቸዉን የቃሉን መገለጥ የሚያዘንቡ የጌታሰዉ ናቸዉና ዕድሜአቸዉ የተባረከ ይሁን፡፡
#አዲስ_አሳዛኝ_መረጃ
#ወደ_አምላካቸዉ_እቅፍ_ተሰበሰቡ
#the_christian_news

#መጋቢ_ዳኜ_አሰፋ_አረፉ

መጋቢ ዳኜ አሰፉ በመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በ1960ዎቹ ሙሉጊዜያቸውን ለወንጌል አገልግሎት ከሰጡ ቀደምት አገልጋዮች አንዱ ነበሩ።

በተለይ በአዲስአበባ ከተማ (ኦሎምፒያ) አገልግሎት ከጀመሩ ከመጀመሪያዎቹ አንዱ እንደነበሩና ለብዙ አገልጋዮች መነሣት ምክንያት እንደነበሩ የታርክ ድርሣናት ያስረዳሉ።

በተጨማሪም የመሠረተ ክርስቶስ መዘምራን( #ቢጫው ኳየር) የተደራጁት በመጋቢ ዳኜ አሰፋ እንደነበር ይነገራል።
መጋቢ ዳኜ በአሜሪካን ሀገር እየኖሩና እያገለገሉ እንደነበረና ወደሚወዱትና ወዳገለገሉት አባታቸው እቅፍ ተሰብስበዋል።

ለቤተሰቦቻቸውና ዘመዶቻቸው መጽናናት እንዲሆን ጸሎታችን ነው።

#መሠረተ_ክርስቶስ_ቤተክርስቲያን!
#ድንቅ_ስራ....
#መጋቢ_እና_ዘማሪ #እምዳለ_ወልደጊዮርጊስ_አስገራሜ_ስራ_ሰርቷል

ፓስተር እንዳለ ወልደጊዮርጊስ በሜሪጆይ ለሆሳዕና የአረጋውያን መርጃ ማእከል የሚመራትን ቤተምህረት ቤተክርስቲያን ምዕመናን በማስተባበር ያሰባሰበውን የ500,000 ብር የገንዘብ ድጋፍ አስረክቧል።

እንዲህ ባሉ ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ መሳተፍ ከቤተክርስቲያን መሪዎች ይጠበቃልና ሌሎቻችንም ከእንዳለ በመማር አቅመደካሞችን እንርዳ።

@ዘካሪያስ
#ጥፋት_በጥፋት_አይመለስም

በጎንደር በወንድሞቻችን ላይ የደረሰው በሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊወገዝ የሚገባ ፀያፍ ተግባር ነው በዚህ ተግባር የተሰማሩትን በህግ ተጠያቂ ማድረግ እና ውጤቱን ለህዝቡ መግለጽ ያስፈልጋል።

የተጎዱ እና ያዘኑትን ወገኖችን ማጽናናት ሀዘናቸውን መጋራት ልባቸው የተሰበረውን መጠገን መካስ ይገባል። ከዚያ ወጭ ግጭቱን ወደ ሌላ አካባቢ ለማዳረስ የሚደረገው በህዝባች ዘንድ የቆዬውን የመከባበር የአብሮነት እሴት ለመናድ ሀገርቷን አጣብቅኝ ውስጥ ለማስገባት እንዲሁም ሃይማኖታዊ መልክ ለማስያዝ የሚደረገው እንቅስቃሴ ከበለጠ ጥፋትና ውድመት በስተቀር የሚያስገኝ ውጤት የለውም።

በዚህ እኩይ ተግባር የተሰማሩ ግለሰቦችም ይሁን ቡድኖች እጃቸውን እንዲሰበስቡ ሀይ ሊባሉ ይገባል አሁን በወራቤ እና በደባርቅ እንዲሁም በሌሎች አከባቢዎች በሃይማኖት ተቋማት ላይ እየደረሰ ያለውን ጥፋት ቀድሞ ሕይወት ሳይጠፋ ውድመት ሳያደርስ በፊት የአከባቢው ማህበረሰብ እና መንግስት በጋራ ትኩረት በመስጠት ማስቆም ያስፈልጋል።

#መጋቢ_ታምራት_አበጋዝ
#የአዲስ_አበባ_ከተማ_የሀይማኖት_ተቋማት_ጉባኤ_ዋና_ጽሐፊ

ፎቶ @ፋይል
#መጋቢ ጻዲቁ አብዶ እና መጋቢ እና #ዘማሪ ተስፋዬ ጋቢሶ

የዛሬ አመት ልክ በዚህ ሰዓት ቀጠና #ሁለት #ሙሉ #ወንጌልል #ቤተክርስቲያን በነበረው መረሃ ግብር #የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ሕብረት #ፕሬዝደንት መጋቢ ጻዲቁ አብዶ ለኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን በተለይም ምዕመናንን ከስህተት ትምህርት በመጠበቅ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ልዩ ተሸላሚ በማለት ከልጅነት እስካሁን ድረስ ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን ውስጥ በተለያዩ የሃገራችን ክፍሎች እውነተኛውን ትምህርት በማስተማር ለአገልጋዮች በስደት ውስጥ እና በመከራ #ውስጥ ጸንተው በረሃብ በእጦት ሳይሸነፉ ምሳሌ በመሆን ሲያገለግሉ የነበሩ እና የኖሩ በሚል #ልዩ ተሸላሚ አድርጋ እውቅና ሰጥታ ነበር።

በተመሳሳይ #ዘመን ተሻጋሪ ፤ ገሳጭ ፤ መካሪ ፤ አጽናኝ እና #ክርስቶስ ተኮር በሆኑ ሰማይ ተኮር #ህይወት ህይወት በሚሸቱ ዝማሬዎቻቸው የሚታወቁት መጋቢ እና ዘማሪ ተስፋዬ ጋቢሶ እውቅና የዘጠችው ልክ በዚህ በያዝነው ሳምንት ነበር።

በሁሉም አብያተክርስቲያናት ዘንድ #እጅግ ተወዳጅ እንዲሁም ትውልድን እንደ ድልድይ በመሆን በማገናኘት በትሁትነታቸው የሚታወቁት መጋቢ እና ዘማሪ ተስፋዬ ጋቢሶ የሙሉ ወንጌል ብቻ ሳይሆን የአብያተክርስቲያናት ሁሉ እንቁ ሃብት የሆኑ ሰው ናቸው።

#እግዚአብሔር ብሄር የሰጣቸው ዝማሬዎች ዘመን ተሻጋሪ እና ልብን እና ህይወትን አዳሾች ሲሆኑ በተጨማሪ በማስተማር እና በማሰልጠን ይታወቃሉ።

ይህ ከሆነ እነሆ አንድ አመት ሆነው። #እነዚህ #ሁለት መሪዎች ዛሬም ድረስ #ለኢትዮጵያ #ቤተክርስቲያን ስጦታዎቻችን ናቸው። ስለ እነርሱ እግዚአብሔርን ዘውትር እያመሰገንን #ይህ ትውልድ ዛሬም ብዙ ነገሮችን እነዚህን ከመሰሉ መሪዎች እንደሚማር እምነት አለን።

#ቀሪ #ዘመናቸው #የተባረከ #ይሁን
የውክልና #ውጊያ‼️መጋቢ ፃዲቁ አብዶ
#ድንቅ #መልዕክት

ጦርነቱ የውክልና ጦርነት ነው የእውነተኛ አምላክና የአማልእክት ጦርነት ...

    መነሻ ቃል 1ሳሙ 17

👉 ቁጥር 4 በዚህ ስፍራ #ስለ ጎሊያድ ማንነት ይዘረዝራል ስለ ቁመቱ የጌት #ሰው መሆኑን ጀግንነቱን ትጥቁን ይናገራል::

👉 እስራኤልና ፍልስጤም ሁሌም ይዋጋሉ:: #በአንድ ወቅት #ግን  ጎሊያድ ያልተለመደና #እስራኤል ያልተዘጋጁበት የጦር ስልት ይዞ ቀረበ!! #እኔ የፍልስጤማውያንን ወገን ወክዬ አለሁ እናንተም የሚወክላቹ ጀግና ሰው ካላቹ አምጡና እንዋጋ ካሸነፈኝ ህዝቤ #እንደ ተሸነፈ ይቆጠር የሚል::

✝️ ቁጥ 8 " እናንተ የሳኦል ባሪያዎች" ሲል ከእስራኤል ወገን የሆኑትን ወታደሮች ሞራል በሚያወርድ ንግግር ተናገራቸው ከመሪያቸው እንዲሸሹ:: የሰዎቹን #ልብ ለመምታት። #ዛሬም  አንዳንድ #ሰዎች #እግዚአብሔር ከሰጣቹ መሪዎች ለመለየት ሲፈልጉ #እንዲህ አይነት ፕሮፓጋንዳ ይዘራሉ ።

✝️ ሰውዬው ከልጅነቱ ጦርነት የለመደ ተክለ ሰውነቱና ትጥቁ አስፈሪ ነበርና ለአርባ ቀንና ሌሊት ጠዋትና ማታ በተናገራቸው ቁጥር ሳዖልም እስራኤልም እጅግ ይደነግጡ ነበር::

👉ይሄኔ በንጉሡ በሳዖል በኩል ጎሊያድን የሚገድል እንዲህ ይደረግለታል የሚል አዋጅ ቢወጣም አንድም ሰው ግን አልተገኘም ነበር::

ጦርነቱ የውክልና ጦርነት ነው የእውነተኛ አምላክና የአማልእክት ጦርነት ነው:: #ስለዚህ ጎሊያድ ዳዊትን በአማልክቶቹ ስም ነው የረገመው #ነገር ግን ይሄንን እውነተኛ #አምላክ የሚወክል ጀግና ሰው አልተገኘም

👉ቀጥሎ ባሉት ቁጥሮች የእሴይ ስምንተኛና የመጨረሻ ስለሆነው ልጅ ስለ ዳዊት ማስተዋወቅ ይጀምራል::

✝️ እግዚአብሔር በስውር ያዘጋጀው ማንም የማያውቀው ከእግዚአብሔር ጋር ግን የሚተዋወቅ ቤተሰቡ የረሳው ጌታ ድል ያለማመደው:: ዳዊትን ወንድሙ እብሪተኛ አለው ቢያሳድገውም ቀዳሚው ቢሆንም አልተረዳውምና::

✝️ ዳዊት ስለ ጎሊያድ ጥያቄን ሲጠይቃቸው ንጉሱ ሳዖልን ጨምሮ ከራሳቸው በላይ ስለ ጎሊያድ አስፈሪነት እንደሰው አወሩት አትችለውም አሉት የአምላክን ጣልቃ ገብነት እረስተዋል::

✝️ ጎሊያድ ላቀረበው እስራኤል ግን ለማያውቀው አዲስ የጦር ስልት የሚገጥም ጀግና በታጣበት ጊዜ እግዚአብሔር በድብቅ ያዘጋጀውን ሰው አመጣ:: ዳዊትም ይህ ያልተገረዘ ማን ነው? አለ‼️

#ይህም ንግግሩ ለሳዖል ደረሰ ሳዖልም ዳዊትን አስጠራው የራሱን ልብስ አለበሰው ። #ይህ የሚያሳየን #ዳዊት በሚያመጣው ድል ተቀባይነትንና ስምን ለራሱ ለመውሰድ በመፈለግ ነበር ። አንዳንድ ሰዎች አሉ በሰው ድካም ድሉን የነሱ አድርገው የሚወስዱ ። ዳዊት ግን በዚህ መንገድ አልለመድኩም አለ::

እግዚአብሔር ባለማመደው ስልት ገባ በአምላኩ በእግዚአብሔር ስም ሊዋጋው #ወደ ጦር ሜዳው ገባ ገደለው በራሱ ሰይፍ አንገቱን ቆረጠው ።

      👉👉 መልእክቴ ይህ ነው ‼️

✝️ ዛሬም በህይወት ጉዞአችን ውስጥ ያልለመድነው ፣ ያላወቅነው፣ ያልጠበቅነው ፣ ያልተዘጋጀንበት #እኛ በፍጹም የማንችለው #ፈተና  ቢገጥመንም ነገር ግን #ጌታ ከእኛ ጋር አለና ጌታ ባለማመደን መንገድ #ድል ይሰጠናል ያድነናል ይታደገንማል::

✝️ ካፈጠጠብኝ  በአለም ካለው
     እጅግ ይበልጣል በእኔ ያለው
     የፍጥረት ገዢ ተቆጣጣሪው
     ጌታ ኢየሱስ ከእኔ ጋራ ነው‼️

#መጋቢ ጻድቁ አብዶ