The Christian News
5.38K subscribers
3.07K photos
27 videos
724 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
#ጥፋት_በጥፋት_አይመለስም

በጎንደር በወንድሞቻችን ላይ የደረሰው በሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊወገዝ የሚገባ ፀያፍ ተግባር ነው በዚህ ተግባር የተሰማሩትን በህግ ተጠያቂ ማድረግ እና ውጤቱን ለህዝቡ መግለጽ ያስፈልጋል።

የተጎዱ እና ያዘኑትን ወገኖችን ማጽናናት ሀዘናቸውን መጋራት ልባቸው የተሰበረውን መጠገን መካስ ይገባል። ከዚያ ወጭ ግጭቱን ወደ ሌላ አካባቢ ለማዳረስ የሚደረገው በህዝባች ዘንድ የቆዬውን የመከባበር የአብሮነት እሴት ለመናድ ሀገርቷን አጣብቅኝ ውስጥ ለማስገባት እንዲሁም ሃይማኖታዊ መልክ ለማስያዝ የሚደረገው እንቅስቃሴ ከበለጠ ጥፋትና ውድመት በስተቀር የሚያስገኝ ውጤት የለውም።

በዚህ እኩይ ተግባር የተሰማሩ ግለሰቦችም ይሁን ቡድኖች እጃቸውን እንዲሰበስቡ ሀይ ሊባሉ ይገባል አሁን በወራቤ እና በደባርቅ እንዲሁም በሌሎች አከባቢዎች በሃይማኖት ተቋማት ላይ እየደረሰ ያለውን ጥፋት ቀድሞ ሕይወት ሳይጠፋ ውድመት ሳያደርስ በፊት የአከባቢው ማህበረሰብ እና መንግስት በጋራ ትኩረት በመስጠት ማስቆም ያስፈልጋል።

#መጋቢ_ታምራት_አበጋዝ
#የአዲስ_አበባ_ከተማ_የሀይማኖት_ተቋማት_ጉባኤ_ዋና_ጽሐፊ

ፎቶ @ፋይል