The Christian News
5.32K subscribers
3.06K photos
27 videos
720 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
ተሰምተው የማይጠገቡ እና ብዙ ክፉ ቀናትን እየሰማን የተፅናናንባቸው፣ ብዙ ምድረ በዳዎችን እያደመጥን የተሻገርንባቸው ድንቅ አልበሞችን ያበረከተች ተወዳጅ ዘማሪት ነች።

'ካንተ በቀር አምላክ እኔ አላመልክም` የሚል መጠርያ በሰጠችው ሶስተኛ አልበሟ በጌታ ኢየሱስ መሞትና መነሳት የሚያምኑቱን የየትኛውንም የሀይማኖት ክፍል አባላት ልብ በጥልቀት ነክታበታለች።

ከዝማሬዎቿ ጀርባ ያለዉ ድንቅ ሚስጥር እና የአገልግሎት ምስክርነት ይዘንላችሁ መጥተናል ከህይወት ምስክርነቷ እንድትባረኩበት ጋበዝኳችሁ።

https://youtu.be/47XAMaeJdag
#መጋቢ ጻዲቁ አብዶ እና መጋቢ እና #ዘማሪ ተስፋዬ ጋቢሶ

የዛሬ አመት ልክ በዚህ ሰዓት ቀጠና #ሁለት #ሙሉ #ወንጌልል #ቤተክርስቲያን በነበረው መረሃ ግብር #የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ሕብረት #ፕሬዝደንት መጋቢ ጻዲቁ አብዶ ለኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን በተለይም ምዕመናንን ከስህተት ትምህርት በመጠበቅ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ልዩ ተሸላሚ በማለት ከልጅነት እስካሁን ድረስ ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን ውስጥ በተለያዩ የሃገራችን ክፍሎች እውነተኛውን ትምህርት በማስተማር ለአገልጋዮች በስደት ውስጥ እና በመከራ #ውስጥ ጸንተው በረሃብ በእጦት ሳይሸነፉ ምሳሌ በመሆን ሲያገለግሉ የነበሩ እና የኖሩ በሚል #ልዩ ተሸላሚ አድርጋ እውቅና ሰጥታ ነበር።

በተመሳሳይ #ዘመን ተሻጋሪ ፤ ገሳጭ ፤ መካሪ ፤ አጽናኝ እና #ክርስቶስ ተኮር በሆኑ ሰማይ ተኮር #ህይወት ህይወት በሚሸቱ ዝማሬዎቻቸው የሚታወቁት መጋቢ እና ዘማሪ ተስፋዬ ጋቢሶ እውቅና የዘጠችው ልክ በዚህ በያዝነው ሳምንት ነበር።

በሁሉም አብያተክርስቲያናት ዘንድ #እጅግ ተወዳጅ እንዲሁም ትውልድን እንደ ድልድይ በመሆን በማገናኘት በትሁትነታቸው የሚታወቁት መጋቢ እና ዘማሪ ተስፋዬ ጋቢሶ የሙሉ ወንጌል ብቻ ሳይሆን የአብያተክርስቲያናት ሁሉ እንቁ ሃብት የሆኑ ሰው ናቸው።

#እግዚአብሔር ብሄር የሰጣቸው ዝማሬዎች ዘመን ተሻጋሪ እና ልብን እና ህይወትን አዳሾች ሲሆኑ በተጨማሪ በማስተማር እና በማሰልጠን ይታወቃሉ።

ይህ ከሆነ እነሆ አንድ አመት ሆነው። #እነዚህ #ሁለት መሪዎች ዛሬም ድረስ #ለኢትዮጵያ #ቤተክርስቲያን ስጦታዎቻችን ናቸው። ስለ እነርሱ እግዚአብሔርን ዘውትር እያመሰገንን #ይህ ትውልድ ዛሬም ብዙ ነገሮችን እነዚህን ከመሰሉ መሪዎች እንደሚማር እምነት አለን።

#ቀሪ #ዘመናቸው #የተባረከ #ይሁን
#ክብር #ለእግዚአብሔር #ይሁን 🙏🙏

በርካታ #ሰዎች መሰረታዊ የክርስትና #ትምህርት ተምረው የውሃ ጥምቀት መውሰዳቸው ተገለጸ።

በሀዋሳ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲያን ሰኔ 30 እና ሐምሌ 1/2015 ዓ.ም "እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው" (ማቴ 28፡19-20) በሚለው መሪ ቃል መሰረት ጌታ #ኢየሱስ #ክርስቶስን #የግል አዳኛቸው አድርገው የተቀበሉ ሰዎች የውሃ ጥምቀት ወስደዋል፡፡

በነበረው የውሃ ጥምቀት ስነስርዓት ብዙዎች በመንፈስ ቅዱስ ተሞልተው ሀሴት ያደረጉ ሲሆን፣ ከውሃ ጥምቀት በኋላም ጌታ ኢየሱስ ያደረገላቸውን ነገር መስክረዋል፡፡

በሁለቱ ቀናት የውሃ ጥምቀት የወሰዱት ከሀዋሳ ሙሉ ወንጌል አማኞች አጥቢያ ቤተክርስቲያን ወንድ 15፣ ሴት 25 በድምሩ 40፣ ከሀዋሳ ሙሉ ወንጌል ህብረቶች ወንድ 7፣ ሴት 9 በድምሩ 16 ሲሆኑ፣ በአጠቃላይ ወንድ 22፣ ሴት 34 በድምሩ 56 ወንድሞችና አህቶች የውሃ ጥምቀት ወስደዋል።

በተጨማሪም ቀደም ሲል ጌታን ተቀብለው የውሃ ጥምቀት ወስደው ከእግዚአብሔር መንገድ ርቀው የነበሩ፣ አሁን ግን በንስሃ የተመለሱ ወንድ 3፣ ሴት 4 በድምሩ 7 ሰዎች በቤተክርስቲያኒቱ የሚሰጠውን የመሰረታዊ የክርስትና ትምህርት ተምረው የቤተክርስቲያን አባል መሆናቸው ታውቋል።

በእለቱ የውሃ ጥምቀት የወሰዱት ወገኖች ሁሉም የቤተ ክርስቲያኒቱ አባል መሆናቸውም ተገልጿል።

የሀዋሳ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ስነ ፅሁፍና ስነዳ አገልግሎት
#አስቸኳይ...

ሞትን ለማምለጥ የሚደረግ የሞኞች እሩጫ 🏃‍♂️🏃‍♀️🏃‍♂️🏃‍♂️

ከሰሞኑ #አንድ ዘገባ አነብብኩኝ ዝገባው #ቃል በቃል "የፌስቡክ መስራቹ ማርክ ዙከርበርግ ራሳቸውን ከዓለም ፍጻሜ ለመጠበቅ በሚል መጠለያ እየገነቡ መሆኑ ተገለጸ" ይላል #እንደ ርዕሱ ቢሆን ሁላችንም ፈገግ ብለን ብናልፈው መልካም #ነበር #ግን አይሆንም።

#ሁሉም #ሰው እንደሚሞት እንዲሁም የአለም ፍጻሜ እንዳለ እርግጠኛ ነው። ግን የሚመጣውን ጥፋትም #ይሁን የሚጠብቀውን የዘላለም #ሞት #እንዴት ማምለጥ እንዳለበት የተረዳ አይመስለኝም።

ለዚህም ይመስለኛል ባለጸጋው በአንድ ደሴት #ውስጥ ባለ #መሬት ውስጥ በ100 ሚሊዮን ዶላር መጠለያ በመገንባት #ላይ መሆናቸው የተሰማው።

አንዳንዴ ግን አጠቃቀሙን ካላወቅነው ሃብታም መሆን ከባድ ይመስለኛል።

ከ120 ቢሊዮን ዶላር በላይ የተጣራ ሀብት እንዳላቸው የሚነገረው ቱጃሩ የፌስቡክ መስራች ዙከርበርግ የደሴቲቱን ስፍራ በ170 ሚሊዮን ዶላር ከዓመታት በፊት የገዙት ሲሆን አሁን #ደግሞ #በዚህ ስፍራ ላይ ቅንጡ የክፉ #ጊዜ መኖሪያ #ቤት እየገነቡ ነው፡፡

#ይህ ስፍራ ለኑሮ አስፈላጊ የሚባሉ ምግቦችን ማምረት፣ የኤሌክትሪክ ሀይል፣ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ማድረጊያ ሜዳ፣ ውሃ ዋና #እና ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ አገልግሎቶችን #ሙሉ ለሙሉ ከዚሁ ስፍራ ማግኘት በሚያስችል መልኩ በመገንባት ላይ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

#ክፉ ጊዜ ግን መቼ #ነው? ይህ ክፉ ጊዜ ሲመጣ እንዴት በደሴቶች ተሸሽገን ማለፍ እንችል ይሁን?

#መጽሐፍ #ቅዱስ የጌታ ምጽዓት እና የአለም ፍጻሜ በቀረበ ጊዜ በመጨረሻው ዘመን ጦርነት እና የጦር ወሬ ፤ የተፈጥሮ አደጋ መብዛት እንዳለ ይነግረናል በራዕይ መጽሀፍ ደግሞ ደሴቶችም #ሁሉ ሸሹ ተራራዎችም አልተገኙም ይላል።

ታዲያ ቱጃሩ ወዳጃችን ደሴትም ፈልፍሎ ለክፉ #ቀን የሚሆን ማምለጫ የሚያዘጋጀው ከማን ለመሸሽ ነው?

#ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ #እውነት እውነት እላችኋለሁ ባለጠጋ #ወደ #እግዚአብሔር መንግስት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢገባ ይቀላል ያለው ቃል ግልጽ ይመስላል።

ስለ ስሙ ያላቸውን ሁሉ ትተው የተከተሉት ግን የዘላለምን ሕይወት ይወርሳሉናል።

ለማንኛውም ወዳጄ ማርክን እና ሌሎች ባለጠጎች ከክፉ ቀን ማንም ሸሽቶ አያመልጥም እና መሸሸጊያ ዋሻ ወደ ሆነዉ ኢየሱስ ተሰብስበኝ በተሰጠን ጊዜ ተጠቅመን መጽሀፍ "እነሆ በደመና ይመጣል አይንም ሁሉ ያየዋል" እንደሚል ያንን ለማየት እንናፍቅ "ማራናታ" #አሜን መልዕክታችን ነው።
#ዜና

የመገናኛ ብዙሃን ባለሥልጣን 4 የሃይማኖት የቴሌቭዥን ጣቢያዎችን አስጠነቀቀ

ህጋዊ ፈቃድ ሳይኖራቸው ስርጭት ላይ የሚገኙ የሃይማኖት ቴሌቪዥን ጣቢያዎችን ይመለከታል።

በመገናኛ ብዙኃን አዋጅ 1238/2013 አንቀፅ 30 መሰረት ማንኛውም ሰው ከባለሥልጣኑ የብሮድካስት ፈቃድ ሳያገኝ የብሮድካስት አገልግሎት ማሰራጫ መንገዶችን ተጠቅሞ በብሮድካስት አገልግሎት ስራ ላይ መሰማራት የተከለከለ መሆኑ ተደንግጓል፡፡

በዚሁ መሰረት በአሁኑ ወቅት 43 የሃይማኖት ቴሌቪዥን ጣቢያዎች በመገናኛ ብዙኃን አዋጅ 1238/2013 አንቀጽ 40 ንዑስ አንቀጽ 3/ለ መሰረት የሚጠበቅባቸውን ቅድመ ሁኔታ በማሟላት ከባለሥልጣኑ የሃይማኖት ቴሌቪዥን ፈቃድ አውጥተው በእንቅስቃሴ ላይ ይገኛሉ፡፡

#ይሁን እንጂ ...
1. ኦሲኤን (OCN Tv)
2. ሐሪማ ቴሌቪዥን (Harima Tv)
3. ፕረዘንስ ቴሌቪዥን ( Presence Tv ) እና
4. ጀሰስ ወንደርፉል ቴሌቪዥን (Jesus Wonderful Tv )

የተሰኙ የሃይማኖት ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ከባለሥልጣኑ ህጋዊ ፈቃድ ሳያወጡ በስርጭት ላይ መሆናቸውን ባደረግነው የክትትል ስራ ማረጋገጥ ችለናል፡፡

በመሆኑም ከላይ ስማችሁ የተጠቀሰ የሃይማኖት ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ከዛሬ ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎችን በማሟላት ፈቃድ እንድታወጡ እያሳሰብን ይህን በማታደርጉት ላይ ህጋዊ እርምጃ የምንወስድ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን