The Christian News
5.38K subscribers
3.07K photos
27 videos
724 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
New Album this July‼️

ስለማንነታችን፥እኛ እራሳችን፣በዙሪያችን ያሉ ሰዎች፣አካባቢያችን፣ዓለማችን፣እንዲሁም ሰይጣን የሚሉት ብዙ የተሳሳተ መረጃ ቢኖርም እግዚያብሔር ወይም የእግዚያብሔር ቃል ግን ትክክለኛውን ያሳየናል፣ይነግረናል ስለዚህ በዚህ ሁልጊዜ ነፍሳችን ሀሴት ታድርግ እግዚያብሔር እንደሚያያን ብቻ እራሳችችንን እንመልከት።

#በዚህ #ክረምት #አዲስ #አልበም #ቁጥር2
#በዚህ #ሳምንት #አስደናቂ የቤተሰብ #ፕሮግራም ይከናወናል።
#ኢየሱስ #ኢትዮጵያ #ድንቅ #ወንጌል #አዲስ #አዲስአበባ

ለመጀመሪያ ጊዜ በ2011ዓ.ም "ቅድሚያ ለቤተሰብ" በሚል ርዕስ በተዘጋጀዉ መሰናዶ እና ከ270 በላይ ጥንዶች በተሳተፉበት መድረክ (በድሮዉ አዳራሽ) የመካፈል ዕድል ገጠመኝ በወቅቱ ቅድሚያ ለቤተሰብ መኖር ወሳኝ መሆኑን ተጠቅሶ ቤተክርስቲያን ጤናማ ማህበረሰብ ለመገንባት እንዲህ አይነት ፕሮግራም እንደምታዘጋጅ የቤተክርስቲያኒቱ መሪ ፓስተር ሚኪ ተናግረዉ ነበር።

ቀጥሎ ደግሞ "ፍቅር ለዘወትር አይወድቅም" በሚል በ2014ዓ.ም በተካሔደው እና 300 ጥንዶች በተገኙበት ተወዳጅ ፕሮግራም የመገኘት እድል ነበረኝ።

በወቅቱ መጋቢ ቴዎድሮስ አዲስ ይህ መረሃ ግብር የተዘጋጀው በጋብቻቸው ፍጹም ለሆኑ ሰዎች አይደለም ቤት ሁሌም እየተሰራ ነው የሚሄደው "ይህ ፕሮግራምም የሰዎች ቤት የሚሰራበት ነው" ሲሉ የፕሮግራሙን አላማ ጠቅሰዉ ነበር።

እነሆ አሁን ደግሞ 13ኛ ልዩ የባለ ትዳሮች ቀን ደረሰ ባሳለፍነዉ ዓመት በመረሃ ግብሩ ላይ ቃል ኪዳንን የማደስ መሰናዶ ተከናዉኖ የዓመቱ ምርጥ እናት ከሆኑ እናት የሕይወት ምስክርነት ተሰምቶ ባለትዳሮች በጋራ የማዕድ ጊዜ እንዲያሳልፉ ተደርጓል።

በምስክርነት እጅግ ብዙዎች ተነክተዉ የብዙ ሰዎች የማንቂያ ደዉል ሆኖ ነበር።

በየአመቱ በተቀባ የእግዚአብሔር ቃል አገልግሎት ቤተክርስቲያን አዘጋጅነት በሚሰናዳዉ ይህ ደማቅ ስነስርአት እነሆ #ደረሰ ደረሰ

የዘንድሮው ደግሞ ከሌሎቹ ጊዜያት እጅግ ደማቅ እንደሚሆን አምናለሁ።

ቀን :- አርብ ሚያዚያ 27-2015ዓ.ም
ሰዓት :- ከቀኑ 8:00 ሰዓት
ቦታ :- ቦሌ የተቀባ የእግዚአብሔር ቃል አገልግሎት ቤተክርስቲያን

#ጋብቻ #መልካም #ነዉ
#መልካም
#የዛሬ #ዓመት #በዚህ #ሰዓት
#እግዚአብሔር #ዉሳኔዉን #ወስኗል

የዛሬ ዓመት በዚህ ሰዓት በሀገረ አሜሪካ ፅንስ የማቋረጥ መብት ተሽሮ የብዙ ክርስቲያኖች ደስታ እጥፍ ነበር።

ጉዳዩን አስመልክቶ ሁለቱ የቀድሞ እና የአሁኑ የአሜሪካ ፕሬዝደንቶች በወቅቱ ምን አሉ?

#ፕሬዝዳንት_ጆ_ባይደን ውሳኔውን “ቀይ ስህተት” ያሉት ሲሆን የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ “የሴቶችን ጤና አደጋ ላይ የሚጥል ነው” ሲሉ ተችተዋል።

“ውሳኔው የአክራሪ አስተሳሰብ ውጤት ነው። በጣም አሳዛኝና የተሳሳተ ውሳኔ ነው” ብለዋል። ፅንስ ማቋረጥ ወደሚፈቀድባቸው ግዛቶች ተጉዘው ፅንስ የሚያቋርጡ ሴቶች ክልከላ እንዳይጣልባቸው እንደሚሠሩ ፕሬዝዳንቱ ተናግረዉ ነበር።

ጉዳዪን በተመለከተ ጥያቄ የቀረበላቸው የቀድሞ የአሜሪካ #ፕሬዝደት_ዶናልድ_ትራምፕ በበኩላቸው “እግዚአብሄር ውሳኔውን ወስኗል” ብለዋል።

የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለአምስት አስርት አመታት የዘለቀውን እልባት ያገኘ ህግን ከሻረ በኋላ ፅንስ የማቋረጥ ብሄራዊ መብትን ለማቆም “አምላክ ውሳኔ ወስኗል” ብለዋል።

ዶናልድ ትራምፕ ለፎክስ ኒውስ ከ6-3 በሆነ ድምጽ በድምጽ ብልጫ ካገኘ በኋላ እያንዳንዱ ግዛቶች ፅንስን በማስወረድ ላይ የራሳቸውን ህጎች እንዲያደርጉ መፍቀድ አለባቸው ብለዋል።

#ይህ #ከሆነ #ድፍን #አንድ #አመት ሞላዉ።
#አሜሪካ #ዛሬም #ምንም #እንኳን #In #God #We #trust ቢሉም ...
#ሶስት #አገልጋዬች የእስር ትዕዛዝ ወጥቶባቸዋል።

የአቃቂ ቃሊቲ በሰቃ መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን መጋቢት 25 ቀን 2014 ዓ.ም የአምልኮ ስነ-ስረዓት እየፈፀመች በነበረችበት ወቅት በድንገት የተደራጁ ሐይሎች ቤተክርስቲያኒቱ ላይ ጉዳት እንዳደረሱ ይታወሳል።

በጊዜዉ በአምልኮ #ላይ የነበሩ ምእመናን ድብደባ ተፈፅሞባቸዋል እንዲሁም የቤተክርስቲያኒቱ መገልገያ መሳሪያዎች፥ ሳዉንድ ሲስተም፣ ኪቦርድ፣ ወንበር እና የቢሮ መገልገያ እቃዎችን በመጫን እንዲሁም በምዕመኑ የተቋቋመ ምዕመናኑ የሚገለገልበት የእድር እቃዎችን በቀን በቤተክርስቲያኒቱ ላይ ዝርፊያ መፈፀሙ እና ቤተክርስቲያኒቱን አዳራሽ ማፈራረሳቸዉ በጊዜዉ መዘገቡ ይታወሳል።

ሆኖም ቤተክርስቲያኒቱ ጉዳዩን #ወደ #ህግ ወስዳ #በዚህ ተግባር ላይ የተሳተፋትን በመጠቆም እና ከቤተክርስቲያኒቱ የተዘረፋትን ንብረቶች በማን አለብኝነት እስካሁን የሚጠቀሙ ግለሰቦች መኖራቸዉን ለህግ አካላት ግልፅ ብታደርግም ላቀረበችዉ የፍትህ ጥያቄ ከህግ አካል ምንም አይነት ምላሽ አላገኘችም።

በተጨማሪም የአዲስ አበባ ካቢኔ ለሁሉም የሐይማኖት ተቋማት ቦታ ሲሰጥ ቤተክርስቲያኒቱ ከዋናዉ የኢትዮዽያ መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ፅ/ቤት ዉሳኔ መሰረት የተወሰነላትን ቦታ የተረከበች ሲሆን የተወሰነላትን ቦታ ለክፍለ ከተማ መሃንዲስ አሳይታ ባዶ መሬት መሆኑ ተረጋግጦ ካርታ ተረክባለች።

ነገር ግን በተረከበችዉ ቦታ ላይ ጊዜያዊ የአምልኮ አዳራሽ ለመገንባት በእንቅስቃሴ ላይ እያለች ከወረዳዉ ደንብ ፅ/ቤ ቤተክርስቲያኒቱ ምንም አይነት ግንባታ ማድረግ እንደማትችል እና ይህን የግንባታ ስራ በሚያስተባብሩ ሶስት አገልጋዮች ላይ የእስር ትእዛዝ እንደወጣባቸዉ የአቃቂ ቃሊቲ በሰቃ መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን አስታዉቃለች።
በርግጥ ወንጌላውያን #በዚህ ደረጃ ፍትሕ ተጓድሎባቸዋል ?

#ይህንን #ጥያቄ #ለምን በተደጋጋሚ ማንሳት አስፈለገ ?

ሁላችሁም መልሱን አዘጋጁ #እኛ #ግን የራሳችንን ሃሳብ እንሰነዝራለን።

በትላንትናዉ ዕለት #የኢትዮጵያ #ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካዉንስል በወንጌላዊያን አማኞች እና አብያተክርስቲናት ላይ እየደረሰ ስላለዉ ፍትህ መጓደል ለሚዲያዎች ጋዜጣዊ #መግለጫ ሰጥቷል።

በካውንስሉ ጠቅላይ ጽሐፊ አማካኝነት በተሰጠዉ መግለጫ #ላይ በዋናነት ከ 6 በላይ .. የሆኑ (የደረሱ የፍትሕ መጓደል) የሚያሳዩ ነጥቦች ተጠቅሰዋል።

1. በደርግ #ዘመን የተወረሱ የቤተክርስቲያን ይዞታዎች በኢሕአዴግ ዘመን በከፊል ቢመለሱም እስካሁን ያልተመለሱ የኦሎምፒያ መሰረተ #ክርስቶስ ፣ የአዲስ ከተማ ገነት፣ የኢትዮጵያ ወንንጌላዊት #ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ብረት የሆነው የጉድ ሼፐርድ ማዕከል ፣ቄራ አካባቢ ያለው የብርሃነ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን አዳራሽ፣እና ሌሎች እስካሁን ያልተመለሱ ይዞታዎች ሲሆኑ እነዚህ ይዞታዎች የቤተክርስቲያን ንብረት በመሆናቸዉ እንዲመለሱ ተጠይቋል።

2 የድሬዳዋ መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን #በአንድ ወር #ጊዜ ዉስጥ ይዞታዋን ለቃ እንድትነሳ የከተማዉ አስተዳደር የወሰንኑ ቢሆንም የከተማዉ አስተዳደር እና የቤተክርስቲያኒቱ መሪዎች እንዲሁም የካውንስሉ አመራሮች ሰፊ ዉይይት አድርገዉ የከተማዉ አስተዳደር ጉዳዩን እየመከረበት ይገኛል። የከተማዉ አስተዳደር የደረሰበትን ደረጃ በአጭር ጊዜ ግልፅ እንዲያደርግ ተጠይቋል።

3 የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር የሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን ይዞታ ነጥቆ የራሱ ጽህፈት #ቤት አድርጎት ይገኛል። እንዲሁም የቃለ #ህይወት ቤተክርስቲያን ይዞታ የሆነዉን የኩሪፍቱ የጸሎት ማዕከል በተመለከተም በማእከሉ #ምንም አይነት የልማት #ስራ ቤተ ክርስቲያን እንዳታከናወን በማገድ የቤተክርስቲያኑን ይዞታ ለመንጠቅ እንቅስቃሴ ላይ እንደሚገኝኝ ተገልጾ የቢሾፍቱ #ከተማ አስተዳደር ከዚህ ህገወጥ ድርጊቱ እንዲቆጠብ እና የወሰደዉን የቤተክርስቲያን ንብረት እንዲመልስ ተጠይቋል።

4. በአዲስ አበባ ዙሪያ ባለችው የሸገር ከተማም የፈረሱ የወንጌላዊያን የእምነት ተቋማት ይዞታቸዉ እንዲመለስ እንዲሁም በከተማዋ ለ23 አብያተክርስቲያናት ከካቢኔ #ቦታ ተወስኖላቸዉ ቦታቸዉን መረከብ ላልቻሉ በአፋጣኝ ካቢኔ የወሰነዉ ዉሳኔ ተግባራዊ እንዲሆን ተጠይቋል።

5 የመቃብር ስፍራን ጥሶ በመግባት እየተደረገ የሚገኘዉ አግባብ ያልሆነ ተግባር በአስቸኳይ እንዲቆም

6 በምዕራብ ኢትዮጵያ በቄለም ወለጋ ዞን በጊዳሜ ወረዳ ዘጠኝ ምእመናንን የአምልኮ ስነስርአት እየፈፀሙ ካሉበት ሌሊት ላይ ተወስደዉ መረሸናችው #እጅግ #አሳዛኝ እንደሆነና ለነዚህ ንፁሃን ፍትህ እንዲሰጥ ተጠይቋል።

በአጠቃላይ #ይህ #ሁሉ እየሆነ ያለዉ የታችኛዉ የመንግስት አካል የመንግስትን ስልጣን በመጠቀም ጥቂት ግለሰቦች የግል አጀንዳ ይዘዉ የሚፈፅሙት ተግባር ነዉ።

የፌደራል መንግስት ጣልቃ በመግባት ፍትህ ሊያሰፍን ይገባል ሲል የኢትዮዽያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት #ካዉንስል በመግለጫዉ አስታዉቋል።

#ታዲያ ይህ ሁሉ የፍትህ ጥያቄ አለ #ማለት መጀመሪያላይ ለጠየኩት ጥያቄ ትክክለኛ ምላሽ በርግጥም ወንጌላውያን በግልፅ በአደባባይ #ፍትሕ ተነፍገዋል የሚል ነዉ።

ይሄንን ጥያቄ በዚህ ሰዓት ለምን ማንሳት አስፈለገ ከተባለ ደግሞ ከዚህ በፊት ለበርካታ አመታት ምላሽ ያላገኙ እና ፍትህ ያልተሰጣቸው ጥያቄዎች ባለበት ዛሬም ሌላ በደል እየደረሰ ስለሆነ ማንሳት አስፈላጊ ነዉ።

The Christian News - የክርስቲያን ዜና የወንጌላውያን ድምፅ በመሆን ለበርካታ ጊዜያት ሲያገለግል ቆይቷል። አሁንም ገና ለቤተክርስቲያን ፍትህ ካልተሰጠ በስተቀር ጥያቄያችንን ማስተጋባታችን ይቀጥላል።

ፍትሕ ለወንጌላዉያን ቤተክርስቲያን
#አስቸኳይ...

ሞትን ለማምለጥ የሚደረግ የሞኞች እሩጫ 🏃‍♂️🏃‍♀️🏃‍♂️🏃‍♂️

ከሰሞኑ #አንድ ዘገባ አነብብኩኝ ዝገባው #ቃል በቃል "የፌስቡክ መስራቹ ማርክ ዙከርበርግ ራሳቸውን ከዓለም ፍጻሜ ለመጠበቅ በሚል መጠለያ እየገነቡ መሆኑ ተገለጸ" ይላል #እንደ ርዕሱ ቢሆን ሁላችንም ፈገግ ብለን ብናልፈው መልካም #ነበር #ግን አይሆንም።

#ሁሉም #ሰው እንደሚሞት እንዲሁም የአለም ፍጻሜ እንዳለ እርግጠኛ ነው። ግን የሚመጣውን ጥፋትም #ይሁን የሚጠብቀውን የዘላለም #ሞት #እንዴት ማምለጥ እንዳለበት የተረዳ አይመስለኝም።

ለዚህም ይመስለኛል ባለጸጋው በአንድ ደሴት #ውስጥ ባለ #መሬት ውስጥ በ100 ሚሊዮን ዶላር መጠለያ በመገንባት #ላይ መሆናቸው የተሰማው።

አንዳንዴ ግን አጠቃቀሙን ካላወቅነው ሃብታም መሆን ከባድ ይመስለኛል።

ከ120 ቢሊዮን ዶላር በላይ የተጣራ ሀብት እንዳላቸው የሚነገረው ቱጃሩ የፌስቡክ መስራች ዙከርበርግ የደሴቲቱን ስፍራ በ170 ሚሊዮን ዶላር ከዓመታት በፊት የገዙት ሲሆን አሁን #ደግሞ #በዚህ ስፍራ ላይ ቅንጡ የክፉ #ጊዜ መኖሪያ #ቤት እየገነቡ ነው፡፡

#ይህ ስፍራ ለኑሮ አስፈላጊ የሚባሉ ምግቦችን ማምረት፣ የኤሌክትሪክ ሀይል፣ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ማድረጊያ ሜዳ፣ ውሃ ዋና #እና ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ አገልግሎቶችን #ሙሉ ለሙሉ ከዚሁ ስፍራ ማግኘት በሚያስችል መልኩ በመገንባት ላይ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

#ክፉ ጊዜ ግን መቼ #ነው? ይህ ክፉ ጊዜ ሲመጣ እንዴት በደሴቶች ተሸሽገን ማለፍ እንችል ይሁን?

#መጽሐፍ #ቅዱስ የጌታ ምጽዓት እና የአለም ፍጻሜ በቀረበ ጊዜ በመጨረሻው ዘመን ጦርነት እና የጦር ወሬ ፤ የተፈጥሮ አደጋ መብዛት እንዳለ ይነግረናል በራዕይ መጽሀፍ ደግሞ ደሴቶችም #ሁሉ ሸሹ ተራራዎችም አልተገኙም ይላል።

ታዲያ ቱጃሩ ወዳጃችን ደሴትም ፈልፍሎ ለክፉ #ቀን የሚሆን ማምለጫ የሚያዘጋጀው ከማን ለመሸሽ ነው?

#ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ #እውነት እውነት እላችኋለሁ ባለጠጋ #ወደ #እግዚአብሔር መንግስት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢገባ ይቀላል ያለው ቃል ግልጽ ይመስላል።

ስለ ስሙ ያላቸውን ሁሉ ትተው የተከተሉት ግን የዘላለምን ሕይወት ይወርሳሉናል።

ለማንኛውም ወዳጄ ማርክን እና ሌሎች ባለጠጎች ከክፉ ቀን ማንም ሸሽቶ አያመልጥም እና መሸሸጊያ ዋሻ ወደ ሆነዉ ኢየሱስ ተሰብስበኝ በተሰጠን ጊዜ ተጠቅመን መጽሀፍ "እነሆ በደመና ይመጣል አይንም ሁሉ ያየዋል" እንደሚል ያንን ለማየት እንናፍቅ "ማራናታ" #አሜን መልዕክታችን ነው።