The Christian News
5.32K subscribers
3.06K photos
27 videos
720 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
#ልዩ የበዓል ፕሮግራም መካከል የወደድኩትን ልጋብዛችሁ!!!
#ረቡኒ
#እጅግ #ተወዳጅ #የበዓል #ፕሮግራም

ገና ገና ሳይነጋ #ጀምበር ሳትወጣ
ጨለማዉ አይሎ አዲስ ቀን ሊወጣ
ልቤ አላርፍ ብሎ ከሰላሙ እርቆ
ሲዋልል አድሮ ሲቆዝም ሰንብቶ
በ3ኛዉ እለት በማለዳዉ ጀምበር
በሰንበት እለት ያዉ በአይሁድ ምድር ...

#share #ShareThisPost
#likeforfollow

https://youtu.be/hbOX2euBF4w
#በዚህ #ሳምንት #አስደናቂ የቤተሰብ #ፕሮግራም ይከናወናል።
#ኢየሱስ #ኢትዮጵያ #ድንቅ #ወንጌል #አዲስ #አዲስአበባ

ለመጀመሪያ ጊዜ በ2011ዓ.ም "ቅድሚያ ለቤተሰብ" በሚል ርዕስ በተዘጋጀዉ መሰናዶ እና ከ270 በላይ ጥንዶች በተሳተፉበት መድረክ (በድሮዉ አዳራሽ) የመካፈል ዕድል ገጠመኝ በወቅቱ ቅድሚያ ለቤተሰብ መኖር ወሳኝ መሆኑን ተጠቅሶ ቤተክርስቲያን ጤናማ ማህበረሰብ ለመገንባት እንዲህ አይነት ፕሮግራም እንደምታዘጋጅ የቤተክርስቲያኒቱ መሪ ፓስተር ሚኪ ተናግረዉ ነበር።

ቀጥሎ ደግሞ "ፍቅር ለዘወትር አይወድቅም" በሚል በ2014ዓ.ም በተካሔደው እና 300 ጥንዶች በተገኙበት ተወዳጅ ፕሮግራም የመገኘት እድል ነበረኝ።

በወቅቱ መጋቢ ቴዎድሮስ አዲስ ይህ መረሃ ግብር የተዘጋጀው በጋብቻቸው ፍጹም ለሆኑ ሰዎች አይደለም ቤት ሁሌም እየተሰራ ነው የሚሄደው "ይህ ፕሮግራምም የሰዎች ቤት የሚሰራበት ነው" ሲሉ የፕሮግራሙን አላማ ጠቅሰዉ ነበር።

እነሆ አሁን ደግሞ 13ኛ ልዩ የባለ ትዳሮች ቀን ደረሰ ባሳለፍነዉ ዓመት በመረሃ ግብሩ ላይ ቃል ኪዳንን የማደስ መሰናዶ ተከናዉኖ የዓመቱ ምርጥ እናት ከሆኑ እናት የሕይወት ምስክርነት ተሰምቶ ባለትዳሮች በጋራ የማዕድ ጊዜ እንዲያሳልፉ ተደርጓል።

በምስክርነት እጅግ ብዙዎች ተነክተዉ የብዙ ሰዎች የማንቂያ ደዉል ሆኖ ነበር።

በየአመቱ በተቀባ የእግዚአብሔር ቃል አገልግሎት ቤተክርስቲያን አዘጋጅነት በሚሰናዳዉ ይህ ደማቅ ስነስርአት እነሆ #ደረሰ ደረሰ

የዘንድሮው ደግሞ ከሌሎቹ ጊዜያት እጅግ ደማቅ እንደሚሆን አምናለሁ።

ቀን :- አርብ ሚያዚያ 27-2015ዓ.ም
ሰዓት :- ከቀኑ 8:00 ሰዓት
ቦታ :- ቦሌ የተቀባ የእግዚአብሔር ቃል አገልግሎት ቤተክርስቲያን

#ጋብቻ #መልካም #ነዉ
#መልካም
#የዘር_ሐሳቦች #ድንቅ #ፕሮግራም እየመጣልን ነዉ።

በቤተክርስቲያን አመራር፣ በመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ፣ በጸጋ ስጦታና ልምምዶች በወቅታዊ ጉዳዮች በየሳምንቱ በዘር ሐሳቦች የዩቲዩብ #ቻናል ላይ እየተዘጋጀ የሚቀርብ ፕሮግራም

ፕሮግራሞቻችን ለመከታተል የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ።

https://youtu.be/c2QPHkiU-4E
#ነገ #በአዲስ #አበባ #እስታዲየም
#ኑ አዲስ አመትን አብረን እንቀበል።
ከማለዳዉ 12:00 ጀምሮ

መስከረም 1 በአዲስ አበባ እስታዲየም የአምልኮ ፕሮግራም ይካሄዳል።

በኢትዮጵያ ወንጌላውያውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት የ2016ዓ.ም #አዲስ #ዓመት ምክንያት በማድረግ በ "አዲስ አበባ እስታዲየም" ልዩ የበዓል #ፕሮግራም ይካሔዳል።

የጳጉሜ ወር በሙሉ ለሃገራችን ሰላም እና ለምድራችን እረፍት እንዲሆን ጸሎት ሲደረግ እንደ ነበር ይታወሳል።

#ነገ በመስከረም 1/2016ዓ.ም በአዲስ አመት የጾም ጸሎቱ ማጠቃለያ እና የጋራ የአምልኮ እና የምስጋና መረሃ ግብር በአዲስ አበባ እስታዲየም የሚደረግ ሲሆን በመረሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው አብረን አዲስ ዓመትን እንቀበል።
የአዲስ አመትን አስመልክቶ #ልዩ ፕሮግራም በአዲስ አበባ እስታዲየም እየተካሄደ ነው።

በኢትዮጵያ ወንጌላውያውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት የ2016ዓ.ም #አዲስ #ዓመት ምክንያት በማድረግ በ "አዲስ አበባ እስታዲየም" እየተካሄደ በሚገኘው ልዩ የበዓል #ፕሮግራም ላይ ክብርት ቀዳማዊ እመቤት ዝናሽ ታያቸው ፤ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ክብርት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ፤ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ሰላም እና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሃላፊን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው የአብያተክርስቲያናት መሪዎች እና ምዕመናን በተገኙበት በድምቀት እየተከናወነ ይገኛል።

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ክብርት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እና የኢትዮጵያ ወንጌላውያውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት ፕሬዝደንት መጋቢ ጻዲቁ አብዶ የእንኳን አደረሳሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ተጨማሪ ዝርዝር ይዘን እንመለሳለን...

Photo 📷 Hossana Photo & Video Production
#በድል #ተጠናቋል
#እግዚአብሔር #ይመስገን 🙏🙏🙏

#በኢትዮጵያ ወንጌላውያውያን አብያተ ክርስቲያናት #ሕብረት የ2016ዓ.ም #አዲስ #ዓመት ምክንያት በማድረግ በ "አዲስ አበባ እስታዲየም" ሲካሄድ የቆየው #ልዩ የበዓል #ፕሮግራም በድል ተጠናቋል።

በድጋሜ #እንኳን #አደረሳችሁ

#መልካም #አዲስ#አመት እንዲሆንላችሁ እንመኛለን።

Photo 📷 Hossana Photo & Video Production #እናመሰግናለን