The Christian News
5.37K subscribers
3.08K photos
29 videos
730 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
#ፍትህ
#የሀላባዋ_ታዳጊ_ሊዲያ_ጉዳይ
#ኢየሱስ

በቀን 22/06/2015 እንደማንኛውም ጊዜ ሊዲያ ት/ቤት ለመማር ክፍሏ ተገኝታለች።አንዲት ሙስሊም ተማሪ በክፍሏ ትወድቃለች። ወድቃም ኢየሱስ ጌታ ነው ትላለች።

ይኼኔ ነው ተማሪዋን ከነለበሰችው ዩኒፎርም ያለ ፖሊስ እና ፍርድ ቤት መጥሪያ አፋፍሶ ወደ ሀላባ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ይወስዷታል፤''ልጄን'' እያለ ሊጠይቃት የሄደውን አባቷንም ያስሩታል።ከዛ አባቷን ይፈቱታል።

ከተያዘችበት 5 ቀን በኋላ በ5ኛው ቀን 27/06/2015 ፍ/ቤት ያቀርቧታል፣"ድግምት ሙስሊም ተማሪዎች ላይ በመስራት ወንጀል ጠርጥረናታል የ14 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ይሰጠን" በማለታቸው 11 ቀን ተፈቅዶላቸው የ14 ዓመት ታዳጊዋን ከፖሊስ ጣቢያ ወደ ሃላባ ማረሚያ ተቋም ውስዷት እየማቀቀች ትገኛለች።

በምርመራ ወቅት በንቅሳት ድግምት አሰርተሻል በሚል እርቃኗን አስቀርቶ እንደፈተሿት እና ሊነገር የማይችል የመብት እና የስነልቦና ጥቃት እንደደረሰባት ሊዲያ ትናግራለች።

#ወንጌል ወንጀል አይደለም!!!
#ፍትህ_ለሊዲያ

በታዳጊዋ ዙሪያ Christian tube - ክርስቲያን ቲዩብ እና ሌሎች ማሕበራዊ ሚዲያዎች ለምታደርጉት ጥረት ምስጋናችን ከፍ ያለ ነዉ።

#share #ShareThisPost
#አሳዛኝ  #ዜና
#የሃሰተኛ #አስተማሪዎች #ዉጤት

በኬንያ ክርስቶስን ቶሎ ለማግኘት በረሃብ አድማ ላይ የነበሩ አራት  ሰዎች #ሞቱ

በኬንያ የባህር ጠረፍ ኪሊፊ አውራጃ አራት ሰዎች ህይወታቸው አልፈው የተገኙ ሲሆን በርካቶች ደግሞ ክፉኛ መጎዳታቸው የተሰማ ሲሆን የምግብ አድማ በማድረግ የዓለምን ፍጻሜ ሲጠባበቁ እንደነበረ ተጠቁሟል።

#ፖሊስ እንዳስታወቀው ለተከታታይ ቀናት በጫካ ውስጥ ግለሰቦቹ በፃም "ኢየሱስን ለማግኘት እንዲጠበቁ በኃይማኖት አባት" ከተነገራቸው በኋላ ይህው ድርጊት አጋጥሟል።

ፖሊስ ባደረገው የነፍስ አድን ጥረት 11 ሰዎችን በህይወት ማትረፍ ችሏል። በህይወት ከተረፉት መካከል ስድስቱ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን በከፋ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ተጠቁሟል ። ሌሎች የቀሩ ሰዎች በጫካ ውስጥ እንዳሉ መነገሩን ተከትሎ ፖሊስ ዛሬ ጠዋት ተጨማሪ ኃይል በማሰማራት ፍለጋ እንደሚቀጥል ገልጿል።

ፖሊስ በጫካው ውስጥ በቅርብ ቀናት የተቀብሩ ሰዎች አስክሬን ማግኘቱን አስታውቋል። ግለሰቦቹ ፈጥነው ወደ መንግሥተ ሰማያት ለመድረስ በረሃብ እንዲሞቱ ያደረገው የጉድ ኒውስ ኢንተርናሽናል #ቤተክርስቲያን መሪ መሆኑ ተነግሯል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል

#share
#ShareThisPost
#likeforlikes
#ኢትዮጵያ
#ልዩ የበዓል ፕሮግራም መካከል የወደድኩትን ልጋብዛችሁ!!!
#ረቡኒ
#እጅግ #ተወዳጅ #የበዓል #ፕሮግራም

ገና ገና ሳይነጋ #ጀምበር ሳትወጣ
ጨለማዉ አይሎ አዲስ ቀን ሊወጣ
ልቤ አላርፍ ብሎ ከሰላሙ እርቆ
ሲዋልል አድሮ ሲቆዝም ሰንብቶ
በ3ኛዉ እለት በማለዳዉ ጀምበር
በሰንበት እለት ያዉ በአይሁድ ምድር ...

#share #ShareThisPost
#likeforfollow

https://youtu.be/hbOX2euBF4w
#አስደሳች #ዜና

የአቃቂ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤ/ክ የወጣቶች አገልግሎት በአቃቂ ቃሊቲ ያሉ በአብያተክርስቲያናት ስር የሚገኙ ወጣቶችን በማስተባበር ስፓርታዊ ዉድድር ሊያካሂድ ነዉ።

የስፓርታዊ ዉድድሩ አላማ በአካባቢዉ ያሉ ክርስቲያን ወጣቶችን አንድነት ለማጠናከር እና ይህን አንድነት ለወንጌል አገልግሎት ለመጠቀም ታሳቢ ያደረገ ነዉ።

የእስፖርታዉ ዉድድሩ የመክፈቻ ስነስረአት እና እጣ የማዉጣት ጊዜ በአዘጋጇ አቃቃ ሙሉ ወንጌል ቤ/ክ ሚያዚያ 15 ቀን 2015 ዓ/ም ተካሂዷል።

በፕሮግራሙ የዝማሬ የቃል ጊዜ እንዲሁም የአንድነት እና እርስ በእርስ የመተዋወቅ ጊዜ እንደነበር ኢቫንጀሊካል ቲቪ ከስፍራዉ ተገኝቶ ዘግቧል።

#share #ShareThisPost