The Christian News
5.38K subscribers
3.07K photos
27 videos
724 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
#ልዩ የበዓል ፕሮግራም መካከል የወደድኩትን ልጋብዛችሁ!!!
#ረቡኒ
#እጅግ #ተወዳጅ #የበዓል #ፕሮግራም

ገና ገና ሳይነጋ #ጀምበር ሳትወጣ
ጨለማዉ አይሎ አዲስ ቀን ሊወጣ
ልቤ አላርፍ ብሎ ከሰላሙ እርቆ
ሲዋልል አድሮ ሲቆዝም ሰንብቶ
በ3ኛዉ እለት በማለዳዉ ጀምበር
በሰንበት እለት ያዉ በአይሁድ ምድር ...

#share #ShareThisPost
#likeforfollow

https://youtu.be/hbOX2euBF4w
ቤተክርስቲያን በአካል ከመገኘት ይልቅ የቤተክርስቲያን አገልግሎቶችን በቀጥታ ስርጭት መመልከት ተወዳጅ እንደሆነ አንድ ጥናት አመለከተ።

በአሜሪካ የፕሮቴስታንት ቤተ ክርስቲያን የሚገለገሉ ምዕመናን ላይ የተደረገ አዲስ ጥናት እንደሚያሳየው በአካል ከመገኘት ይልቅ በቀጥታ ስርጭት የሚተላለፉ የቤተ ክርስቲያን አገልግሎቶችን መመልከት በጣም ተወዳጅ አማራጭ እንደሆነ ዘግቧል።

ዘገባው 40% የሚጠጉት ሰዎች ባለፈው ዓመት ውስጥ ከአምስት ጊዜ በላይ በቀጥታ ስርጭት ተመልክተዋል ሲል Relevant መጽሔት ዘግቧል።

የሕዝብ አስተያየት መስጫው የተካሄደው በላይፍዌይ ጥናት በፈረንጆቹ ከሴፕቴምበር 19-29/2022 እንደሆነ የተጠቀሰ ሲሆን 1,002 ሰዎች ተሳትፈውበታል ተብሏል።

ጥናቱ “ባለፈው ዓመት በአካል ቤተክርስቲያን ከመገኘት ይልቅ በቀጥታ ስርጭት በቪዲዮ ምን ያህል ጊዜ ተመልክተሃል?” የሚል ሲሆን ጥናቱ ከ2019 የኮቪድ ወረርሽኝ በኋላ ሰዎች በአካል ሄደው ከመሳተፍ ይልቅ የቀጥታ ስርጭትን ምርጫቸው አድርጓል ያለ ሲሆን በዚህም ሴቶችን እና ወንዶችን ጨምሮ እድሜያቸው ከ18-65 ዓመት የሆኑ ሰዎች አሳትፊያለሁ ብሏል።

ምልከታ :- በቤተክርስቲያን ዉስጥ የሚደረገዉ የቅዱሳን ሕብረት መፅሐፍ ቅዱሳዊ እና በቅዱሳን መካከል ያለዉን ግንኙነት የሚያጠናክር የተወሰነ የደከሙትን ደግሞ እንዲበረቱ የሚያደርግ ነዉ።

ዛሬ ዛሬ የምዕራባውያን ቤተክርስቲያን አዳዲስ ነገሮች እየፈጠሩ ምዕመናን ከቤተክርስቲያን ሕብረት እንዲቀሩ የሚያደርግ ይመስለናል።

ይህ የቀጥታ #ስርጭት የአገልግሎት አይነት አሁን አሁን የኢትዮጵያ #ቤተክርስቲያን ዉስጥ እየተለመደ መጥቷል። ዛሬ ላይ በአካል ያልተገኙትን ተደራሽ ለማድረግ #እጅግ መልካም ቢሆንም #ነገ ምን እንደሚፈጠር መገመት ይከብዳል።
#ሁሉም #ሊያነበው #የሚገባ #አስቸኳይ #መልዕክት
#እንዴት #ድንቅ #አምላክ #ነው #እኛ #የምናመልከው..

ለ5 #ሰከንድ #ኦክሲጅን ከአለም ላይ ቢጠፋ ምን ይፈጠራል?

ግራቪቲ (የመሬት ስበት) ለ5ሰከንድ ከመሬት ላይ ቢጠፋስ ምን የሚፈጠር ይመስላችኋል? እኛ ሰዎች ምንድነው የምንሆነው?

ምናልባት ደግሞ #አሁን ያለውን የመሬት ስበት እጥፍ ቢሆን ምን ይፈጠራል?

ሌላኛው ለሰው ልጆች #ሁሉ ጠቃሚ የሆነችው ጸሃይ ድንገት ብትጠፋ ... ቀጥሎ የምድራችን እና #የሰው #ልጆች እጣ ፈንታ ምንድነው? በነገራችን ላይ ይህን #ሁሉ ለ5 ሰከንድ #ብቻ ነው።

እነዚህን ጥያቄዎች የሞኝ ጥያቄዎች ይመስላሉ?

#እኔም ለመጀመሪያ #ጊዜ ስሰማቸው እንደዛ ነው ያሰብኩት ነገር ግን #እጅግ መሰረታዊ እንደሆነ የተመለከትኩበትን አንድ ነገር ላካፍላችሁ።

ከጥቂት ቀናት በፊት TechTalk With Solomon በተሰኘ ፕሮግራም #EBS #ቴሌቪዥን ላይ ማለት ነው። ሰለሞን እነዚህ ጥያቄዎች እየጠየቀ ነበር።

ከጥያቄዎች በሻገር ምን ሊፈጠር ይችላል የሚለውን ምናባዊ ምልከታ በሳይንስ አስደግፎ በ2 ተከታታይ ክፍሎች ለተመልካች አቅርቦታል። ለማንኛውም እኔ ያንን ፕሮግራም ስሰማው እጅግ እየዘገነነኝ እና እየተሳቀኩኝ ነበር።

በኋላ #ላይ #ግን ቆም ብዬ ሳስበው እንደዚህ አይነት ፕሮግርሞች ሊበረታቱ የሚገቡ እንደሆነ ገባኝ።

ምክንያቱም እሱ የሚዘረዝራቸው በሙሉ ለ5 ሰከንድ ቢፈጠሩ ምድራችን ላይ የሚፈጠሩት እጅግ ዘግናኝ እልቂቶች እና ነገሮችን ለማስቀረት የሚያስችል አንዳችም ቴክኖሎጂ እስካሁን #በሰው #ልጆች አልተፈጠሩም።

ይህንን ሳስብ እኛ የምናመልከት አምላክ እንዴት #ድንቅ እንደሆነ እና ምድርን #በቃሉ አጽንቶ እና እያንዳንዱ እንቅስቃሴ ያለ አንዳች መፋለስ #ሁሉም ነገር ስረዓታቸው ይዘው እንደሚሄዱ ሳሰብ ደነቀኝ።

ምድር ትንሽ ከሚባሉት ፕላኔቶች መካከል አንዷ ነች። ጸሃይ ደግሞ የምድርን 6ሚሊዮን አከባቢ እጥፍ የሆነች ከግዙፎቹ #መካከል ነች። ታዲያ የጸሃይ ብረሃን እንኳን በልካችን ተመጥኖ የሚደርሰን ለማሰብ የሚከብድ ምን አይነት ጥበብ ነው?

የሰው ልጅ ምናልባትም እየተማረ እና ብዙ እውቀቶችን እየሰበሰብ ሲሄድ ይበልጥ ወደ #አምላኩ እንደሚቀርብ አምናለሁ።

ለማንኛውም እኔ ከምጽፍላችሁ ይልቅ ፕሮግራሙን ገብታችሁ እንድትመለከቱት ሊንኩን አስቀምጬላችኋለሁ። https://www.youtube.com/watch?v=cqZU3b8NDB8&t=89s

#እንዴት #ድንቅ #አምላክ #ነው #እኛ #የምናመልከው..
#መጋቢ ጻዲቁ አብዶ እና መጋቢ እና #ዘማሪ ተስፋዬ ጋቢሶ

የዛሬ አመት ልክ በዚህ ሰዓት ቀጠና #ሁለት #ሙሉ #ወንጌልል #ቤተክርስቲያን በነበረው መረሃ ግብር #የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ሕብረት #ፕሬዝደንት መጋቢ ጻዲቁ አብዶ ለኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን በተለይም ምዕመናንን ከስህተት ትምህርት በመጠበቅ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ልዩ ተሸላሚ በማለት ከልጅነት እስካሁን ድረስ ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን ውስጥ በተለያዩ የሃገራችን ክፍሎች እውነተኛውን ትምህርት በማስተማር ለአገልጋዮች በስደት ውስጥ እና በመከራ #ውስጥ ጸንተው በረሃብ በእጦት ሳይሸነፉ ምሳሌ በመሆን ሲያገለግሉ የነበሩ እና የኖሩ በሚል #ልዩ ተሸላሚ አድርጋ እውቅና ሰጥታ ነበር።

በተመሳሳይ #ዘመን ተሻጋሪ ፤ ገሳጭ ፤ መካሪ ፤ አጽናኝ እና #ክርስቶስ ተኮር በሆኑ ሰማይ ተኮር #ህይወት ህይወት በሚሸቱ ዝማሬዎቻቸው የሚታወቁት መጋቢ እና ዘማሪ ተስፋዬ ጋቢሶ እውቅና የዘጠችው ልክ በዚህ በያዝነው ሳምንት ነበር።

በሁሉም አብያተክርስቲያናት ዘንድ #እጅግ ተወዳጅ እንዲሁም ትውልድን እንደ ድልድይ በመሆን በማገናኘት በትሁትነታቸው የሚታወቁት መጋቢ እና ዘማሪ ተስፋዬ ጋቢሶ የሙሉ ወንጌል ብቻ ሳይሆን የአብያተክርስቲያናት ሁሉ እንቁ ሃብት የሆኑ ሰው ናቸው።

#እግዚአብሔር ብሄር የሰጣቸው ዝማሬዎች ዘመን ተሻጋሪ እና ልብን እና ህይወትን አዳሾች ሲሆኑ በተጨማሪ በማስተማር እና በማሰልጠን ይታወቃሉ።

ይህ ከሆነ እነሆ አንድ አመት ሆነው። #እነዚህ #ሁለት መሪዎች ዛሬም ድረስ #ለኢትዮጵያ #ቤተክርስቲያን ስጦታዎቻችን ናቸው። ስለ እነርሱ እግዚአብሔርን ዘውትር እያመሰገንን #ይህ ትውልድ ዛሬም ብዙ ነገሮችን እነዚህን ከመሰሉ መሪዎች እንደሚማር እምነት አለን።

#ቀሪ #ዘመናቸው #የተባረከ #ይሁን
በመዲናችን #አዲስ አበባ እጅግ ብዙ #ወንጌል የተሰራ ብዙዎች በወንጌል የተደረሱ ይመስላችኋል?

የአዲስ አበባ ጎዳናዎች በተለይም #መገናኛ#ሜክሲኮ#ፒያሳ#ጀሞ#አያት እና ሌሎች አከባቢዎችን ስንመለከት ከተማዋ በወንጌል የተጥለቀለቀች ይመስላል።

#ነገር #ግን ይመስላል #ነው #እንጂ እውነታው #እጅግ ከዚህ የራቀ እንደሆነ በቅርብ #ጊዜ በአንድ መድረክ አስደንጋጭ ሪፖርት ወጥቷል።

#ከተማ ተኮር የወንጌል አገልግሎት በሚል በቀጠና #ሙሉ ወንጌል አጥቢያ #ቤተክርስቲያን ጥናታዊ ጽሁፍ ቀርቦ ነበር።

ታዲያ #ይህ ጥናት ሲቀርብ ከ700 በላይ የሆኑ የአብያተ ክርስቲያናት መሪዎች መጋቢዎች #እና አገልግዮች በቦታው ተገኝተው ነበር።

ጥናቱ #ኢትዮጵያ #ውስጥ የሚገኙ ተለቅ ተለቅ ያሉ 11 ከተሞችን የሚዳስስ የነበረ ቢሆንም እኛ ግን ለጊዜዉ የመዲናችንን አዲስ አበባ #ብቻ የተወሰነ እንበል።

ይህም ጥናት አዲስ አበባ ላይ በወንጌል የተደረሰው ሕዝብ 6 በመቶ ብቻ እንደሆነ ያሳያል።

ይህም በወንጌል ካልተደረሱ የአለማችን ከተሞች መካከል አንዷ አዲስ አበባ እንድትሆን አድርጓታል።

#እንደ ጥናቱ ከሆነ የአዲስ አበባ ከተማ እድገት እጅግ ፈጣን እና ከሌሎች የአለም ከተሞች ጋር ተወዳዳሪነት ባለው መልኩ በፈጣን እድገት ውስጥ የምትገኝ ከተማ እንደሆነች ተጠቅሷል ነገር ግን ይህቺን ከተማ መድረስ በሚችል መልኩ አገልጋዮቻችን ግን ለዚህ ዝግጁ እንዳልሆኑ ጠቁመዋል።

ይህንን ለመድረስ እጅግ ቅንጅት የሚፈልግ ቢሆንም በከተማችን የሚገኙ አገልጋዮች ግን ወደዚህ መስመር ለመግባት ገና ብዙ ስራ እንደሚጠይቅ ተጠቁሟል።

ምናልባት ይህንን ለመቅረፍ የቤት ስራ ተወስዶ በየአመቱ ለመሰብሰብ እና ለመነጋገር ቀጠሮ ቢያዝም ውጤቱን ግን ለወደፊት የምናየው ይሆናል።
#ዓለሜ #እጅግ #ድንቅ ዝማሬ ነው ተባረኩበት.. https://youtu.be/cjRsxtMypeU?si=PESIOiHuAXAS0tXp

ዓለሜ #ዘማሪ ናቲ ካሳ aleme #singer Nati Kassa ተተኪ የቤተክርስቲያን #ልጆች እንዳሉን ማሳያ የሆነ ዝማሬ ነው።

#share በማድረግ ለምትወዷቸው አድርሱላቸው።
በርግጥ ወንጌላውያን #በዚህ ደረጃ ፍትሕ ተጓድሎባቸዋል ?

#ይህንን #ጥያቄ #ለምን በተደጋጋሚ ማንሳት አስፈለገ ?

ሁላችሁም መልሱን አዘጋጁ #እኛ #ግን የራሳችንን ሃሳብ እንሰነዝራለን።

በትላንትናዉ ዕለት #የኢትዮጵያ #ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካዉንስል በወንጌላዊያን አማኞች እና አብያተክርስቲናት ላይ እየደረሰ ስላለዉ ፍትህ መጓደል ለሚዲያዎች ጋዜጣዊ #መግለጫ ሰጥቷል።

በካውንስሉ ጠቅላይ ጽሐፊ አማካኝነት በተሰጠዉ መግለጫ #ላይ በዋናነት ከ 6 በላይ .. የሆኑ (የደረሱ የፍትሕ መጓደል) የሚያሳዩ ነጥቦች ተጠቅሰዋል።

1. በደርግ #ዘመን የተወረሱ የቤተክርስቲያን ይዞታዎች በኢሕአዴግ ዘመን በከፊል ቢመለሱም እስካሁን ያልተመለሱ የኦሎምፒያ መሰረተ #ክርስቶስ ፣ የአዲስ ከተማ ገነት፣ የኢትዮጵያ ወንንጌላዊት #ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ብረት የሆነው የጉድ ሼፐርድ ማዕከል ፣ቄራ አካባቢ ያለው የብርሃነ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን አዳራሽ፣እና ሌሎች እስካሁን ያልተመለሱ ይዞታዎች ሲሆኑ እነዚህ ይዞታዎች የቤተክርስቲያን ንብረት በመሆናቸዉ እንዲመለሱ ተጠይቋል።

2 የድሬዳዋ መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን #በአንድ ወር #ጊዜ ዉስጥ ይዞታዋን ለቃ እንድትነሳ የከተማዉ አስተዳደር የወሰንኑ ቢሆንም የከተማዉ አስተዳደር እና የቤተክርስቲያኒቱ መሪዎች እንዲሁም የካውንስሉ አመራሮች ሰፊ ዉይይት አድርገዉ የከተማዉ አስተዳደር ጉዳዩን እየመከረበት ይገኛል። የከተማዉ አስተዳደር የደረሰበትን ደረጃ በአጭር ጊዜ ግልፅ እንዲያደርግ ተጠይቋል።

3 የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር የሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን ይዞታ ነጥቆ የራሱ ጽህፈት #ቤት አድርጎት ይገኛል። እንዲሁም የቃለ #ህይወት ቤተክርስቲያን ይዞታ የሆነዉን የኩሪፍቱ የጸሎት ማዕከል በተመለከተም በማእከሉ #ምንም አይነት የልማት #ስራ ቤተ ክርስቲያን እንዳታከናወን በማገድ የቤተክርስቲያኑን ይዞታ ለመንጠቅ እንቅስቃሴ ላይ እንደሚገኝኝ ተገልጾ የቢሾፍቱ #ከተማ አስተዳደር ከዚህ ህገወጥ ድርጊቱ እንዲቆጠብ እና የወሰደዉን የቤተክርስቲያን ንብረት እንዲመልስ ተጠይቋል።

4. በአዲስ አበባ ዙሪያ ባለችው የሸገር ከተማም የፈረሱ የወንጌላዊያን የእምነት ተቋማት ይዞታቸዉ እንዲመለስ እንዲሁም በከተማዋ ለ23 አብያተክርስቲያናት ከካቢኔ #ቦታ ተወስኖላቸዉ ቦታቸዉን መረከብ ላልቻሉ በአፋጣኝ ካቢኔ የወሰነዉ ዉሳኔ ተግባራዊ እንዲሆን ተጠይቋል።

5 የመቃብር ስፍራን ጥሶ በመግባት እየተደረገ የሚገኘዉ አግባብ ያልሆነ ተግባር በአስቸኳይ እንዲቆም

6 በምዕራብ ኢትዮጵያ በቄለም ወለጋ ዞን በጊዳሜ ወረዳ ዘጠኝ ምእመናንን የአምልኮ ስነስርአት እየፈፀሙ ካሉበት ሌሊት ላይ ተወስደዉ መረሸናችው #እጅግ #አሳዛኝ እንደሆነና ለነዚህ ንፁሃን ፍትህ እንዲሰጥ ተጠይቋል።

በአጠቃላይ #ይህ #ሁሉ እየሆነ ያለዉ የታችኛዉ የመንግስት አካል የመንግስትን ስልጣን በመጠቀም ጥቂት ግለሰቦች የግል አጀንዳ ይዘዉ የሚፈፅሙት ተግባር ነዉ።

የፌደራል መንግስት ጣልቃ በመግባት ፍትህ ሊያሰፍን ይገባል ሲል የኢትዮዽያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት #ካዉንስል በመግለጫዉ አስታዉቋል።

#ታዲያ ይህ ሁሉ የፍትህ ጥያቄ አለ #ማለት መጀመሪያላይ ለጠየኩት ጥያቄ ትክክለኛ ምላሽ በርግጥም ወንጌላውያን በግልፅ በአደባባይ #ፍትሕ ተነፍገዋል የሚል ነዉ።

ይሄንን ጥያቄ በዚህ ሰዓት ለምን ማንሳት አስፈለገ ከተባለ ደግሞ ከዚህ በፊት ለበርካታ አመታት ምላሽ ያላገኙ እና ፍትህ ያልተሰጣቸው ጥያቄዎች ባለበት ዛሬም ሌላ በደል እየደረሰ ስለሆነ ማንሳት አስፈላጊ ነዉ።

The Christian News - የክርስቲያን ዜና የወንጌላውያን ድምፅ በመሆን ለበርካታ ጊዜያት ሲያገለግል ቆይቷል። አሁንም ገና ለቤተክርስቲያን ፍትህ ካልተሰጠ በስተቀር ጥያቄያችንን ማስተጋባታችን ይቀጥላል።

ፍትሕ ለወንጌላዉያን ቤተክርስቲያን
"... ማን ያውራ ? የነበረ ...."
የባሊ አቦው ልጅ
የሐረር መምህራን ማሰልጠኛ ተማሪው

የመጀመሪያ የጰንጠቆስጠ ቤተ ክርስቲያን አጀማመር በኢትዮጵያ ከፍተኛ አስተዋጽዖ ያበረከቱ
የሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን ምስረታ ውስጥ የነበሩ ባህር ተሻግረው ቤተክርስቲያን በመትከል እና የመንፈስ ቅዱስ ሙላት ላይ በትጋት የሰሩ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ከ60 ዓመት በላይ በማገልገል ባለውለታ የሆኑት ፓስተር ዶክተር ዘለቀ አለሙ ወደ አገለገሉት ጌታ ሄደዋል።

በትዳር ከ46 ዓመታት በላይ ተሻግረዋል በምዕራቡ አለም ያላቸው ቆይታ አጠናቀው ወደ ሀገራቸው ሊገዙ እየተሰናዱ እና "ግሬስ" በተሰኘ ሴንተር የሰው ልጆች በሙሉ በክርስቶስ የተደረገልን ምንድነው የሚለውን እንዲረዱ ለመስራት እና ለመስበክ እና ደቀ መዛሙርት ለማፍራት እቅድ እንደነበራቸው በአንድው ወቅት The Christian News - የክርስቲያን ዜና ጋር #የክርስቲያን እንግዳ ሆነው ድንቅ ቆይታ ባደረግንበት ጊዜ አጫውተውን ነበር።

"... ማን ያውራ ? የነበረ ..." እንዲሉ የኢትዮጵያ ጰንጠቆስጤአዊ እንቅስቃሴ አጀማመር መተረክ ከሚችሉት ጥቂት ሰዎች መካከል አንዱ መጋቢ ዘለቀ አለሙ (ዶ/ር) ነው።

"ሕይወቴ እና ጰንጠቆስጤአዊ እንቅስቃሴ አጀማመር በኢትዮጵያ" በሚለው መጽሐፋቸው ላይ ቀድመው አስተያየት ከሰጡ ሰዎች መካከል መጋቢ በቀለ ወልደ ኪዳን አስተያየታቸው ሰጥተዋ ነበር።

በቻናላችን ከ2ዓመት በፊት ያደረግንላቸውን ቃለ መጠይቅ ሊንኩን በመጫን እንድትመለከቱ ግንዣችን ነው።

https://youtu.be/1FHp-jLOZJI?si=Fn1MqoGRvgaFq30H