የውክልና #ውጊያ‼️መጋቢ ፃዲቁ አብዶ
#ድንቅ #መልዕክት
ጦርነቱ የውክልና ጦርነት ነው የእውነተኛ አምላክና የአማልእክት ጦርነት ...
መነሻ ቃል 1ሳሙ 17
👉 ቁጥር 4 በዚህ ስፍራ #ስለ ጎሊያድ ማንነት ይዘረዝራል ስለ ቁመቱ የጌት #ሰው መሆኑን ጀግንነቱን ትጥቁን ይናገራል::
👉 እስራኤልና ፍልስጤም ሁሌም ይዋጋሉ:: #በአንድ ወቅት #ግን ጎሊያድ ያልተለመደና #እስራኤል ያልተዘጋጁበት የጦር ስልት ይዞ ቀረበ!! #እኔ የፍልስጤማውያንን ወገን ወክዬ አለሁ እናንተም የሚወክላቹ ጀግና ሰው ካላቹ አምጡና እንዋጋ ካሸነፈኝ ህዝቤ #እንደ ተሸነፈ ይቆጠር የሚል::
✝️ ቁጥ 8 " እናንተ የሳኦል ባሪያዎች" ሲል ከእስራኤል ወገን የሆኑትን ወታደሮች ሞራል በሚያወርድ ንግግር ተናገራቸው ከመሪያቸው እንዲሸሹ:: የሰዎቹን #ልብ ለመምታት። #ዛሬም አንዳንድ #ሰዎች #እግዚአብሔር ከሰጣቹ መሪዎች ለመለየት ሲፈልጉ #እንዲህ አይነት ፕሮፓጋንዳ ይዘራሉ ።
✝️ ሰውዬው ከልጅነቱ ጦርነት የለመደ ተክለ ሰውነቱና ትጥቁ አስፈሪ ነበርና ለአርባ ቀንና ሌሊት ጠዋትና ማታ በተናገራቸው ቁጥር ሳዖልም እስራኤልም እጅግ ይደነግጡ ነበር::
👉ይሄኔ በንጉሡ በሳዖል በኩል ጎሊያድን የሚገድል እንዲህ ይደረግለታል የሚል አዋጅ ቢወጣም አንድም ሰው ግን አልተገኘም ነበር::
ጦርነቱ የውክልና ጦርነት ነው የእውነተኛ አምላክና የአማልእክት ጦርነት ነው:: #ስለዚህ ጎሊያድ ዳዊትን በአማልክቶቹ ስም ነው የረገመው #ነገር ግን ይሄንን እውነተኛ #አምላክ የሚወክል ጀግና ሰው አልተገኘም
👉ቀጥሎ ባሉት ቁጥሮች የእሴይ ስምንተኛና የመጨረሻ ስለሆነው ልጅ ስለ ዳዊት ማስተዋወቅ ይጀምራል::
✝️ እግዚአብሔር በስውር ያዘጋጀው ማንም የማያውቀው ከእግዚአብሔር ጋር ግን የሚተዋወቅ ቤተሰቡ የረሳው ጌታ ድል ያለማመደው:: ዳዊትን ወንድሙ እብሪተኛ አለው ቢያሳድገውም ቀዳሚው ቢሆንም አልተረዳውምና::
✝️ ዳዊት ስለ ጎሊያድ ጥያቄን ሲጠይቃቸው ንጉሱ ሳዖልን ጨምሮ ከራሳቸው በላይ ስለ ጎሊያድ አስፈሪነት እንደሰው አወሩት አትችለውም አሉት የአምላክን ጣልቃ ገብነት እረስተዋል::
✝️ ጎሊያድ ላቀረበው እስራኤል ግን ለማያውቀው አዲስ የጦር ስልት የሚገጥም ጀግና በታጣበት ጊዜ እግዚአብሔር በድብቅ ያዘጋጀውን ሰው አመጣ:: ዳዊትም ይህ ያልተገረዘ ማን ነው? አለ‼️
#ይህም ንግግሩ ለሳዖል ደረሰ ሳዖልም ዳዊትን አስጠራው የራሱን ልብስ አለበሰው ። #ይህ የሚያሳየን #ዳዊት በሚያመጣው ድል ተቀባይነትንና ስምን ለራሱ ለመውሰድ በመፈለግ ነበር ። አንዳንድ ሰዎች አሉ በሰው ድካም ድሉን የነሱ አድርገው የሚወስዱ ። ዳዊት ግን በዚህ መንገድ አልለመድኩም አለ::
እግዚአብሔር ባለማመደው ስልት ገባ በአምላኩ በእግዚአብሔር ስም ሊዋጋው #ወደ ጦር ሜዳው ገባ ገደለው በራሱ ሰይፍ አንገቱን ቆረጠው ።
👉👉 መልእክቴ ይህ ነው ‼️
✝️ ዛሬም በህይወት ጉዞአችን ውስጥ ያልለመድነው ፣ ያላወቅነው፣ ያልጠበቅነው ፣ ያልተዘጋጀንበት #እኛ በፍጹም የማንችለው #ፈተና ቢገጥመንም ነገር ግን #ጌታ ከእኛ ጋር አለና ጌታ ባለማመደን መንገድ #ድል ይሰጠናል ያድነናል ይታደገንማል::
✝️ ካፈጠጠብኝ በአለም ካለው
እጅግ ይበልጣል በእኔ ያለው
የፍጥረት ገዢ ተቆጣጣሪው
ጌታ ኢየሱስ ከእኔ ጋራ ነው‼️
#መጋቢ ጻድቁ አብዶ

በርግጥ ወንጌላውያን #በዚህ ደረጃ ፍትሕ ተጓድሎባቸዋል ?
#ይህንን #ጥያቄ #ለምን በተደጋጋሚ ማንሳት አስፈለገ ?
ሁላችሁም መልሱን አዘጋጁ #እኛ #ግን የራሳችንን ሃሳብ እንሰነዝራለን።
በትላንትናዉ ዕለት #የኢትዮጵያ #ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካዉንስል በወንጌላዊያን አማኞች እና አብያተክርስቲናት ላይ እየደረሰ ስላለዉ ፍትህ መጓደል ለሚዲያዎች ጋዜጣዊ #መግለጫ ሰጥቷል።
በካውንስሉ ጠቅላይ ጽሐፊ አማካኝነት በተሰጠዉ መግለጫ #ላይ በዋናነት ከ 6 በላይ .. የሆኑ (የደረሱ የፍትሕ መጓደል) የሚያሳዩ ነጥቦች ተጠቅሰዋል።
1. በደርግ #ዘመን የተወረሱ የቤተክርስቲያን ይዞታዎች በኢሕአዴግ ዘመን በከፊል ቢመለሱም እስካሁን ያልተመለሱ የኦሎምፒያ መሰረተ #ክርስቶስ ፣ የአዲስ ከተማ ገነት፣ የኢትዮጵያ ወንንጌላዊት #ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ብረት የሆነው የጉድ ሼፐርድ ማዕከል ፣ቄራ አካባቢ ያለው የብርሃነ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን አዳራሽ፣እና ሌሎች እስካሁን ያልተመለሱ ይዞታዎች ሲሆኑ እነዚህ ይዞታዎች የቤተክርስቲያን ንብረት በመሆናቸዉ እንዲመለሱ ተጠይቋል።
2 የድሬዳዋ መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን #በአንድ ወር #ጊዜ ዉስጥ ይዞታዋን ለቃ እንድትነሳ የከተማዉ አስተዳደር የወሰንኑ ቢሆንም የከተማዉ አስተዳደር እና የቤተክርስቲያኒቱ መሪዎች እንዲሁም የካውንስሉ አመራሮች ሰፊ ዉይይት አድርገዉ የከተማዉ አስተዳደር ጉዳዩን እየመከረበት ይገኛል። የከተማዉ አስተዳደር የደረሰበትን ደረጃ በአጭር ጊዜ ግልፅ እንዲያደርግ ተጠይቋል።
3 የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር የሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን ይዞታ ነጥቆ የራሱ ጽህፈት #ቤት አድርጎት ይገኛል። እንዲሁም የቃለ #ህይወት ቤተክርስቲያን ይዞታ የሆነዉን የኩሪፍቱ የጸሎት ማዕከል በተመለከተም በማእከሉ #ምንም አይነት የልማት #ስራ ቤተ ክርስቲያን እንዳታከናወን በማገድ የቤተክርስቲያኑን ይዞታ ለመንጠቅ እንቅስቃሴ ላይ እንደሚገኝኝ ተገልጾ የቢሾፍቱ #ከተማ አስተዳደር ከዚህ ህገወጥ ድርጊቱ እንዲቆጠብ እና የወሰደዉን የቤተክርስቲያን ንብረት እንዲመልስ ተጠይቋል።
4. በአዲስ አበባ ዙሪያ ባለችው የሸገር ከተማም የፈረሱ የወንጌላዊያን የእምነት ተቋማት ይዞታቸዉ እንዲመለስ እንዲሁም በከተማዋ ለ23 አብያተክርስቲያናት ከካቢኔ #ቦታ ተወስኖላቸዉ ቦታቸዉን መረከብ ላልቻሉ በአፋጣኝ ካቢኔ የወሰነዉ ዉሳኔ ተግባራዊ እንዲሆን ተጠይቋል።
5 የመቃብር ስፍራን ጥሶ በመግባት እየተደረገ የሚገኘዉ አግባብ ያልሆነ ተግባር በአስቸኳይ እንዲቆም
6 በምዕራብ ኢትዮጵያ በቄለም ወለጋ ዞን በጊዳሜ ወረዳ ዘጠኝ ምእመናንን የአምልኮ ስነስርአት እየፈፀሙ ካሉበት ሌሊት ላይ ተወስደዉ መረሸናችው #እጅግ #አሳዛኝ እንደሆነና ለነዚህ ንፁሃን ፍትህ እንዲሰጥ ተጠይቋል።
በአጠቃላይ #ይህ #ሁሉ እየሆነ ያለዉ የታችኛዉ የመንግስት አካል የመንግስትን ስልጣን በመጠቀም ጥቂት ግለሰቦች የግል አጀንዳ ይዘዉ የሚፈፅሙት ተግባር ነዉ።
የፌደራል መንግስት ጣልቃ በመግባት ፍትህ ሊያሰፍን ይገባል ሲል የኢትዮዽያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት #ካዉንስል በመግለጫዉ አስታዉቋል።
#ታዲያ ይህ ሁሉ የፍትህ ጥያቄ አለ #ማለት መጀመሪያላይ ለጠየኩት ጥያቄ ትክክለኛ ምላሽ በርግጥም ወንጌላውያን በግልፅ በአደባባይ #ፍትሕ ተነፍገዋል የሚል ነዉ።
ይሄንን ጥያቄ በዚህ ሰዓት ለምን ማንሳት አስፈለገ ከተባለ ደግሞ ከዚህ በፊት ለበርካታ አመታት ምላሽ ያላገኙ እና ፍትህ ያልተሰጣቸው ጥያቄዎች ባለበት ዛሬም ሌላ በደል እየደረሰ ስለሆነ ማንሳት አስፈላጊ ነዉ።
The Christian News - የክርስቲያን ዜና የወንጌላውያን ድምፅ በመሆን ለበርካታ ጊዜያት ሲያገለግል ቆይቷል። አሁንም ገና ለቤተክርስቲያን ፍትህ ካልተሰጠ በስተቀር ጥያቄያችንን ማስተጋባታችን ይቀጥላል።
ፍትሕ ለወንጌላዉያን ቤተክርስቲያን