The Christian News
5.37K subscribers
3.08K photos
29 videos
730 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
አጀንዳ_28
#ወንጌል_አጀንዳችን_ነዉ!!!
The Christian News - የክርስቲያን ዜና

በመሰረተ-ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የምስራቅ አዲስ አበባ አጥቢያ ከመጋቢት 27/ 2014 ጀምሮ ከተለያየ የሀገሪቱ ክፍሎች ተውጣጥተው ሲሰለጥኑ የነበሩ 35 የወንጌል ሚስዮናውያንን ትላንት ሚያዝያ 2/2014 አስመርቃ አሰማርታለች።

ይህም የአጀንዳ 28/19 ወይም "ወንጌል አጀንዳችን ነው!" የሚለውን የቤተ-ክርስቲያኒቱ ዋነኛ መርህ በተግባር የታየበት በመሆኑ ሌሎች አጥቢያዎች ከዚህ ተሞክሮ እንደሚወስዱ ይጠበቃል።

#ስለ_ወንጌል_ሁሉን_እናደርጋለን!
#በሰላም_ተጠናቋል
The Christian News - የክርስቲያን ዜና

የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን #91ኛው_መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ በሠላም ተጠናቀቀ።

ከነሐሴ 15 /2014ዓም ጀምሮ በቢሾፍቱ ከተማ መሠረተ ክርስቶስ ሴሚናሪዮም ግቢ ውስጥ በየደረጃው የሚገኙ የቤተክርስቲያንቷ የአመራር አካላት በሀገራችን ወቅታዊ ሁኔታ እና በቤተክርስቲያን የህልውና ተግዳሮት ዙሪያ ምክክርና ጸሎት ሲደረግ ቆይቷል።

ከነሐሴ 19 እስከ 21/2014 ዓም ደግሞ #ስለ_ወንጌል_ሁሉን_አደርጋለሁ " በሚል መሪ ቃል መደበኛ የቤተክርስቲያኒቱ ጠቅላላ ጉባኤ ሲካሄድ ቆይቶ ልዩ ልዩ ውሳኔዎችን በማሣለፍ ዛሬ አመሻሹን በአምልኮና ዝማሬ ተጠናቋል።

በዚሁ መሠረት ከመደበኛ እና የተለመዱ ተግባራት በተጨማሪ፣
፩) ዘጠኝ አዳዲስ የክልል አደረጃጀት ጥያቄዎችን መርምሮ አጽድቋል።
፪) ለሚቀጥሉ ሦስት ዓመታት የሚያገለግሉ 11 የአመራር ጉባኤ አባላትን መርጦ ሾሟል።
፫) በመሠረተ ክርስቶስ ሴሚናሪም ግቢ ውስጥ ተገንብቶ በአንድ ጊዜ ከ1000 ሰዎች በላይ የሚይዝና ከ27ሚልዮን ብር በላይ ወጭ የተደረገበት ዘመናዊ አዳራሽ አስመርቋል።

በአጠቃላይ ከኢትዮጵያ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት የቤተ እምነት መሪዎች በተጨማሪ ከአሜሪካ፣ ከካናዳ እና ከጀርመን የቤተክርስቲያኒቱ አጋር ድርጅት ተወካዮች የጉባኤው ታዳሚ እንደነበሩ ከፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ከተገኘው መረጃ መረዳት ተችሏል።

በመጨረሻም በጦርነት ለተጎዱ ወገኖች አብሮነትን ለመግለጽ ያህል የጉባኤው አባላት ገንዘብ በማወጣት ቀለብ አጥተው ለተቸገረ የወንጌል አገልጋዮች እንዲላክላቸው ከመደረጉ በተጨማሪ ስለ ሀገራችን ወቅታዊ ሁኔታ ምልጃና የህብረት ጸሎት በማድረግ ነሐሴ 21/2914 ዓም ጉባኤው በሠላም መጠናቀቁን መጠናቀቁን ለማወቅ ተችሏል።
#ስለ_ፍቅር

ተወዳጁ አርቲስት ጋሽ ስዩም ተፈራ በአንድ ወቅት ጥበብ በቤተክርስቲያን ውስጥ (ልጅ) ነበረች። የሚንከባከባት እና የሚጠብቃት ስታጣ ወደ እንጀራ እናቷ (አለም) ሄደች ብለው ሲናገሩ ሰምቼ ነበር።

አሁን ጥበብ ወደ ቤተክርስቲያን እየተመለሰች ይመስላል። ለማንኛው በከሬጅ አርት ሚኒስትሪ የተዘጋጀ #ስለ_ፍቅር የተሰኘ ልዩ የወንጌል ኢነ ጥበብ ፌስቲቫል ተዘጋጅቷል።

በአዲስ አበባ እና በአቅራቢያዋ ለምትገኙ በሙሉ ታሕሳስ 22/2015ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ጀመሮ በወንጌል አምኞች ምርጦቹ 7000 ቤተክርስቲያን ተጋብዛችኋል።

በእለቱ በጥበብ ስራዎቻቸው የምንወዳቸው ድንቅ የኪነ ጥበብ ባለሞያዎች ታድመው የጥበብ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ። ከሌሎች ቦታዎች ለሚመጡ የጥበብ ፍቅር ላላቸው በሙሉ ልምዳቸውን ያካፍላሉ። ወንጌልን በጥበብ ሲያስተላልፉ ይቆያሉ።

ተወዳጇ አርቲስት ማክዳ ሃይሌ Mackda Haile Maki ላለፉት አመታት በከሬጀ አርት ሚኒስትሪ እጅግ ብዙ ስራዎች ስትሰራ ቆይታለች አሁን ደግሞ በጋራ የምንሰራበትን ድንቅ ዝግጅት አሰናድታልናለች በመታደም እየተዝናናን ቁም ነገር እንድንጨብጥ #እነሆ_ጥሪያችን_ለሁላችሁም ይድረስ።

አድራሻ #ምርጦቹ 7000 ቤተክርስቲያን (ከደንበል ወደ MKC Head Office) ሲጓዙ
"በዉጪ #ሀገር ሆናችሁ የጥላቻን #ንግግር የምትዘሩ ከድርጊታችሁ እንድትቆጠቡ አሳስባለሁ" ፖስተር ፃዲቁ አብዶ

የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት ፕሬዝደንት ፓስተር ጻዲቁ አብዶ ይህንን ያሉት በአዲስ አበባ እስታዲየም እየተካሄደ ባለው የአዲስ አመት #ልዩ ፕሮግራም #ላይ ነው።

ፓሰተር ጻዲቁ በመልዕክታቸው 2016 #ሰላም የምንሆንበት አንዳችን ሌላውን የምናንጽበት ፤ የምንገነባበት ለሌላው ውድቀት የማንሰራበት ፤ ወጥመድ የማንዘረጋበት ፤ ድልድይ የምንገነባበት ድልድይ የምንሰራበት #ዘመን እንዲሆንልን #እግዚአብሔር በሉዓላዊነቱ ይርዳን ብለዋል።

ሰላም ለማንም #ሰው እጅግ አስፈላጊ ነው ያሉት መጋቢ ጻዲቁ ከሰላም ውጪ የሚገኝ ምንም ነገር የለም ቢገኝም አይቆይም ስለዚህ ለሁላችንም ሰላም እንዲሆን እለምናለሁ።

እኛ ክርስቲያኖች እንደ አማኝ ሀገራችን ሰላም እንድትሆን እንጸልያለን ምንም #እንኳን እንድምንፈልገው ባይሆንም እግዚአብሔር በሚያውቀው በዘላለማዊ እውቀቱ #ወደ #መልካም ነገር እንደምናልፍ እናምናለን።

እኛ እንደ ሰው ድርሻ ሰላም የሚቀጥልበትን እና የምንተናነጽበትን እንፈልግ ፤ ጥላቻን ከመዝራት እንቆጠብ ፤ ጥላቻ ከልባችን ይወገድ ፤ የቂም በቀል ፍላጎት ከውስጣችን ይጥፋ።

በውጪ ሀገር ሆነው የጥላቻን አረፋ በማሕበራዊ ሚዲያ የሚደፍቁ ሰዎች #ስለ እግዚአብሔር ብለው ጥላቻቸውን ከመዝራት እንዲቆጠቡ በዚህ አጋጣሚ በዚህ ጉባኤ በይፋ መልዕክት አስተላልፋለሁ ብለዋል።

Photo 📷 Hossana Photo & Video Production
የውክልና #ውጊያ‼️መጋቢ ፃዲቁ አብዶ
#ድንቅ #መልዕክት

ጦርነቱ የውክልና ጦርነት ነው የእውነተኛ አምላክና የአማልእክት ጦርነት ...

    መነሻ ቃል 1ሳሙ 17

👉 ቁጥር 4 በዚህ ስፍራ #ስለ ጎሊያድ ማንነት ይዘረዝራል ስለ ቁመቱ የጌት #ሰው መሆኑን ጀግንነቱን ትጥቁን ይናገራል::

👉 እስራኤልና ፍልስጤም ሁሌም ይዋጋሉ:: #በአንድ ወቅት #ግን  ጎሊያድ ያልተለመደና #እስራኤል ያልተዘጋጁበት የጦር ስልት ይዞ ቀረበ!! #እኔ የፍልስጤማውያንን ወገን ወክዬ አለሁ እናንተም የሚወክላቹ ጀግና ሰው ካላቹ አምጡና እንዋጋ ካሸነፈኝ ህዝቤ #እንደ ተሸነፈ ይቆጠር የሚል::

✝️ ቁጥ 8 " እናንተ የሳኦል ባሪያዎች" ሲል ከእስራኤል ወገን የሆኑትን ወታደሮች ሞራል በሚያወርድ ንግግር ተናገራቸው ከመሪያቸው እንዲሸሹ:: የሰዎቹን #ልብ ለመምታት። #ዛሬም  አንዳንድ #ሰዎች #እግዚአብሔር ከሰጣቹ መሪዎች ለመለየት ሲፈልጉ #እንዲህ አይነት ፕሮፓጋንዳ ይዘራሉ ።

✝️ ሰውዬው ከልጅነቱ ጦርነት የለመደ ተክለ ሰውነቱና ትጥቁ አስፈሪ ነበርና ለአርባ ቀንና ሌሊት ጠዋትና ማታ በተናገራቸው ቁጥር ሳዖልም እስራኤልም እጅግ ይደነግጡ ነበር::

👉ይሄኔ በንጉሡ በሳዖል በኩል ጎሊያድን የሚገድል እንዲህ ይደረግለታል የሚል አዋጅ ቢወጣም አንድም ሰው ግን አልተገኘም ነበር::

ጦርነቱ የውክልና ጦርነት ነው የእውነተኛ አምላክና የአማልእክት ጦርነት ነው:: #ስለዚህ ጎሊያድ ዳዊትን በአማልክቶቹ ስም ነው የረገመው #ነገር ግን ይሄንን እውነተኛ #አምላክ የሚወክል ጀግና ሰው አልተገኘም

👉ቀጥሎ ባሉት ቁጥሮች የእሴይ ስምንተኛና የመጨረሻ ስለሆነው ልጅ ስለ ዳዊት ማስተዋወቅ ይጀምራል::

✝️ እግዚአብሔር በስውር ያዘጋጀው ማንም የማያውቀው ከእግዚአብሔር ጋር ግን የሚተዋወቅ ቤተሰቡ የረሳው ጌታ ድል ያለማመደው:: ዳዊትን ወንድሙ እብሪተኛ አለው ቢያሳድገውም ቀዳሚው ቢሆንም አልተረዳውምና::

✝️ ዳዊት ስለ ጎሊያድ ጥያቄን ሲጠይቃቸው ንጉሱ ሳዖልን ጨምሮ ከራሳቸው በላይ ስለ ጎሊያድ አስፈሪነት እንደሰው አወሩት አትችለውም አሉት የአምላክን ጣልቃ ገብነት እረስተዋል::

✝️ ጎሊያድ ላቀረበው እስራኤል ግን ለማያውቀው አዲስ የጦር ስልት የሚገጥም ጀግና በታጣበት ጊዜ እግዚአብሔር በድብቅ ያዘጋጀውን ሰው አመጣ:: ዳዊትም ይህ ያልተገረዘ ማን ነው? አለ‼️

#ይህም ንግግሩ ለሳዖል ደረሰ ሳዖልም ዳዊትን አስጠራው የራሱን ልብስ አለበሰው ። #ይህ የሚያሳየን #ዳዊት በሚያመጣው ድል ተቀባይነትንና ስምን ለራሱ ለመውሰድ በመፈለግ ነበር ። አንዳንድ ሰዎች አሉ በሰው ድካም ድሉን የነሱ አድርገው የሚወስዱ ። ዳዊት ግን በዚህ መንገድ አልለመድኩም አለ::

እግዚአብሔር ባለማመደው ስልት ገባ በአምላኩ በእግዚአብሔር ስም ሊዋጋው #ወደ ጦር ሜዳው ገባ ገደለው በራሱ ሰይፍ አንገቱን ቆረጠው ።

      👉👉 መልእክቴ ይህ ነው ‼️

✝️ ዛሬም በህይወት ጉዞአችን ውስጥ ያልለመድነው ፣ ያላወቅነው፣ ያልጠበቅነው ፣ ያልተዘጋጀንበት #እኛ በፍጹም የማንችለው #ፈተና  ቢገጥመንም ነገር ግን #ጌታ ከእኛ ጋር አለና ጌታ ባለማመደን መንገድ #ድል ይሰጠናል ያድነናል ይታደገንማል::

✝️ ካፈጠጠብኝ  በአለም ካለው
     እጅግ ይበልጣል በእኔ ያለው
     የፍጥረት ገዢ ተቆጣጣሪው
     ጌታ ኢየሱስ ከእኔ ጋራ ነው‼️

#መጋቢ ጻድቁ አብዶ
#እነሆ ንጉሳችን #በሐዋሳ
#ስለ #ፍቅር የጎዳና ሩጫ

እነሆ ንጉሳችን መንፈሳዊ ድግስ መጋቢት 13 & 14 በሐዋሳ ሊካሄድ መሆኑን መጋቢ በጋሻው ደሳለኝ አሳወቁ።

መጋቢ በጋሻው ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ መንፈሳዊ ድግሱ የክርስቶስ ቤት መዓዛ ቤተክርስቲያን (አሮማ ኦፍ ዘ ሃውስ ኦፍ ክራይስት አለም አቀፍ ቤ/ክ) ባለፈው አመት የተካሄደውን ድግስ በሃዋሳ መድገም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ነው ብለዋል።

መንፈሳዊ ድግሱ በሐዋሳ እና አካባቢዋ ታላቅ የወንጌል ሪቫይቫል ማስጀመሪያ ደውል ድምጽ ማሰሚያ አላማ ማድረጉን ገልጸዋል።

በሐዋሳ መስቀል አደባባይ ንጉሳችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሚገንበት፣ በዝማሬ ማዕበል ንጉሱን ከፍ የምናደርግበት፣ ነብሳት የሚድኑበት፣ የታመሙ የሚፈወሱበት፣ የጠፉ የሚመለሱበት፣ የወደቁ የሚነሱበት፣ መንፈሳዊ ጉባኤ ይሆናል ብለዋል በመግለጫው።

ቅዳሜ መጋቢት 13 በዛው በሃዋሳ "ስለ ፍቅር" የተሰኘ 3 ኪ.ሜ. የጎዳና ላይ ሩጫ እንደሚካሄድም መጋቢ በጋሻው ገልጸዋል።

በመሆኑም በሐዋሳና አካባቢዋ የምትኖሩ ክርስቲያኖች፣ መጋቢት 13 እና 14 በመስቀል አደባባይ ተገናኝተን እግዚአብሔርን እናመስግነው፣ በጎዳና ላይ እስፖርታዊ እንቅስቃሴውም እንድንሳተፍ ሲሉ የአሮማ ቸርች ዋና መጋቢ፣ መጋቢ በጋሻው ደሳለኝ ጥሪ አቅርበዋል።

እነሆ ንጉሳችን ባለፈው አመት መጋቢት 17 በሚሊንየም አዳራሽ በአሮማ ቸርች መጋቢ በጋሻው ደሳለኝ አዘጋጅነት መካሄዱ ይታወሳል።
#ደረሰ ደረሰ ደረሰ ...

የመጽሃፍ #ቅዱስ ሳምንት

#በኢትዮጵያ የመጽሃፍ ቅዱስ ማህበር አዘጋጅነት የሚካሄደዉ የመፅሐፍ ቅዱስ ሳምንት #እና የቅዱሳት መጻህፍት አውደ ርዕይ ከመጋቢት 16-21 በኢትዮጵያ ስካይ ላይት ሆቴል።

ክርስቲያኑን #ስለ መጽሃፍ ቅዱስ ንባብ ማነቃቃት፣ በመጽሃፍ ቅዱስ ትርጉም ላይ የሚሰሩ አብያተ ክርስቲያናትን በተዛማጅ ስራዎች ላይ ማስተባበር፣ የወንጌል ስብከትን ማበረታት፣ ለአሁኑ ትውልድ የመጽሃፍ ቅዱስን አደራና ሃላፊነት ማስተላለፍ እና መጽሃፍ ቅዱስን ከአደጋዎች መጠበቅ በሳምንቱ ከሚኖሩ ክንውኖች መካከል ናቸው።

ትውልዱን ስለ ቅዱሳት መጻህፍት እንዲያውቅ ማድረግ፣ የህትመት ውጤቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለህዝብ ማድረስ እና ማህበሩን ከህዝብ ጋር ማስተዋወቅ በአውደ ርዕይው የሚከናወኑ ዋና ዋና ስራዎች ናቸው።

#ሁላችሁም ተጋብዛችኋል።

መግቢያ #በነፃ ...
#ዛሬ ይጠናቀቃል

“መጽሀፍ ቅዱሳዊ እሴቶችን በሕዝባችን #ሕይወት እናስርጽ!” በሚል መሪ ቃል ሲካሄድ የቆየዉ የቅዱሳት መጻሕፍት ዐውደ ርዕይ ዛሬ ይጠናቀቃል።

በአሁኑ ሰዓት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፣ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን እና የወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት መሪዎች በተገኙበት በመካሄድ #ላይ ይገኛል።

#የኢትዮጵያ መጽሐፍ #ቅዱስ ማሕበር አዘጋጅነት የመጽሀፍ ቅዱስ ሳምንት በዓል #እና የቅዱሳት መጻሕፍት ዐውደ ርዕይ ከሰኞ የጀመረ ሲሆን በዛሬዉ እለት የሚጠናቀቅ ይሆናል።

ክርስቲያኑን #ስለ መጽሃፍ ቅዱስ ንባብ ማነቃቃት፣ በመጽሃፍ ቅዱስ ትርጉም ላይ የሚሰሩ አብያተ ክርስቲያናትን በተዛማጅ ስራዎች ላይ ማስተባበር፣ የወንጌል ስብከትን ማበረታት፣ ለአሁኑ ትውልድ የመጽሃፍ ቅዱስን አደራና ሃላፊነት ማስተላለፍ እና መጽሃፍ ቅዱስን ከአደጋዎች መጠበቅ በሳምንቱ ዉስጥ ሲሰራ የነበረ #ስራ ነዉ።

በሳምንቱ ዉስጥ ትውልዱን ስለ ቅዱሳት መጻህፍት እንዲያውቅ የማድረግ ስራ ፣ የህትመት ውጤቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለህዝብ ማድረስ እና ማህበሩን ከህዝብ ጋር ማስተዋወቅ በአውደ ርዕይው ሲከናወን ቆይቷል።

የኢትዮጵያ መፅሐፍ ቅዱስ ማሕበር ሁሉንም ሁሉንም አብያተ ክርስቲያናት እና ምዕመናንን ባለፋት 98 ዓመታት አገልግሏል።

ፎቶ 📷 Hossana production Hossana