The Christian News
5.32K subscribers
3.06K photos
27 videos
720 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
#ወይ_ጉድ_አሜሪካ፡.እግዚአብሔር ሆይ እርዳን! የገጠመኝን ጉድ እነሆ፡...
===(ከ2 ዓመት በፊት በፌስቡክ የተለጠፈ)
#ለአምልኮ ወደ ቤተ ክርስቲያን ለመሄድ ከዶርሜ ወጣሁ፡፡ ገና የግቢው በር ጋ ሲደርስ አንድ ፈረንጅ ከግቢያችን 'Security' ጋር ያወራል፡፡ 'Security'ው ጠራኝና ፈረንጁን እንዲረዳው ነገረኝ፡፡ እኔም ተቀበልኩኝና አነጋገርኩት፡፡ ፈረንጁም፡ ከአሜሪካን (USA) ሀገር እንደመጣ፡ ቤተ ክርስቲያን መሄድ እንደሚፈልግ ነገረኝ፡፡ እኔም መጀመሪያ ሊሄድ ካሰብኩበት ቤ/ክ ሃሳቤን ቀየርኩና ወደ አንድ ታሪካዊት ቤ/ክ ሊወስደው ወሰንኩኝ፡፡ ወደተኮናተረው ታክሲ ገባን፡፡ ሁለት ልጆች፡1 ወንድና 1 ሴት ታክሲው ውስጥ ነበሩ፡፡ ዕድሜያቸው ከ 14-16 አይበልጥም፡፡ የዛሬ 11 ዓመት ከኢትዮጵያ ላሳድጋቸው የወሰድኳቸው ልጆቼ ናቸው፡ ወላጆቻቸውን እንዲያናግሩ ይዤአቸው መጥቼ ነው ብሎ አስተዋወቀኝ፡፡ ጤና ይስጥልኝ ስላቸው፡ Ohhh...no Amharic, just English...አሉኝ፡፡ Ok፡ welcome to your homeland...ብዬ ሰላም አልኳቸው፡፡ ለባለ ታክሲውም የእንኳን ለጌታችን ትንሳኤ በዓል አደረሰህ ሰላምታዬን ካቀረብኩለት በኃላ እየተጫወትን ጉዞ ወደ ቤተ ክርስቲያን፡፡ ከጥቂት ደቂቃዎች በኃላ ደረስን፡ ገባን፡፡ ጸለይን፡ ስለ ጌታችን ትንሳኤ ቃል ሰማን፡ በዝማሬም አምልከን ጨርሰን ወጣን፡፡ እንደወጣን ስለ አሜሪካን ሀገር ክርስትና አንድ አንድ ጥያቄዎችን መጠየቅ ጀመርኩኝ፡፡ እንዴት ነው ክርስትና በአሜሪካ? ከማነበውና ከሚሰማው ሲረዳ እያሽቆለቆለ እንደሆነ ነው፡ ለዚህም ደግሞ የhomosexuality(ተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ), እንዲሁም የአንድ አንድ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ልምምዶች በዋናነት እንደምክንያትነት ይጠቀሳሉ ሲባል አምብቤያለሁ፡ ሰምቼአለሁ፡ እስቲ አንተም አውራኝ ስለዚህ ጉዳይ ብዬ ሳበቃ፡ እያየሁት ፊቱ ጠቆረ፡ ምነው ምን ሆንክ ብዬ ስለው፡ ቀጠለና እንዲህ አለኝ፡ 'እንዴት ነው homosexuality ምክንያት ሊሆን የሚችለው? Homosexual መሆኑ ምኑጋ ነው ጥፋቱ፡...'ወዘተ ብሎ ተናገረ፡፡ በጣም አዘንኩኝ፡ በጣም ደነገጥኩኝ፡፡ አግብተሃል ስለው፡ አዎን፡ የታለች በለቤትህ ስለው፡ 'አሜሪካ አለኝ' (ወንድ ይሁን ሴት ትሁን አልገለጸም):: ልጆችስ አሏችሁ ስለው 'ይኼው የምታያቸው ናቸው' ስለኝ፡ no no...ማለቴ ከናንቴ አብራክ የወጡ ስለው፡ 'አይ የለንም' አለኝ፡፡ ክርስቲያን ነህ ስለው፡ 'ይኼው እያየሄኝ፡ አብረን አምልከን እየወጣን' አለኝ፡፡ Ok አልኩኝ የማጣራት ሥራዬን ከሠራሁ በኃላ፡፡ ከዚያም እንዲህ አልኩት፡ የክርስትና መሰረቱ የእግዚአብሔር ቃል ነው፡ ቃሉ ደግሞ በብሉይም፡ በአዲስም ኪዳን፡ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ ሀጥያትና ርኩሰት እንደሆነ ይናገራል (በ2ቱም ኪዳኖች የተፃፈውን እየጠቀስኩ), ታድያ ቅዱስ ቃሉ እንዲህ ካለ፡ አንተም ደግሞ ክርስቲያን ነኝ ካልክ፡ ቃሉ የሚለው አንተ ከምትለው እንዴት ተጋጨ? ወይስ ሌላ መጽሐፍ ጻፋችሁ ስለው፡ አይ መፅሐፉ እራሱ ነው፡ ያነበብክልኝን ጥቅሶች ሁሉንም አውቃቸዋለሁ፡ የዛ ዘመን አውድ(context) እና የዚህ ዘመን ይለያያል፡፡የጥቅሶቹን Context ስናይ ስለ ተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ አይደለም ብሎ ተከራከረኝ በግልፅ ቋንቋ የተፃፈውን፡፡ ከሁሉም ያሳዘነኝ ያስደነገጠኝና ያናደደኝ፡ የጉድፈቻ ልጆቹ በተኩራራና በቁጣ ስሜት እንዲህ አሉኝ፡ 'የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ ምን ችግር አለው? ሰው የፈለገውን ማግባትና አብሮ መኖር ይችላል፡ እናንተ የሰውን መብት ለምን ትጋፋላችሁ? አንተ የዘረዘርካቸው ጥቅሶች ሁሉ ሀጥያት ስለመሆኑ አይናገሩም፡ አውዳቸው ሌላ ነው፡...'' አሉኝ በማከታተል፡፡ ወዮ ወየው፡...ጉድ ስሙ ይኼው ፡፡(በውጪም በሀገር ውስጥም ያላችሁ ወላጆች፡ ልጆቻችሁን ታውቃላችሁን ፡ ዬት ነው የሚማሩት፡ ዬት ነው የሚውሉት፡ ከማንስ ጋር፡...ምንድነው የሚማሩት፡ በስልካቸውና በኮምፒዩተራቸውስ ምንድነው የያዙት፡...አደራ ተከታተሏቸው፡ ልጅን በሚሄድበት መንገድ መምራት የወላጆች ሀላፊነት ነው: ይኼን ጽሁፍ ቀድሜ በአፋን ኦሮሞ ጽፌ፡ እንዲህ የሚል comment አነበብኩ፡ " homosexual የሆኑ ነጮችም ጥቁሮችም ልጅ መውለድ ስለማይችሉ፡ በስመ ጉድፈቻ ከሀገራችንና ከሌሎች ድሃ ሀገሮች ልጆችን እየሰበሰቡ አሳድገው፡ እነሱንም እንደዚሁ ያረጓቸውና በዚህ ክፉ መርዝ በክለው ይህን እርኩሰት እንዲያባብሱ በጀት መድበውላቸው ይልኩብናል፡,...ጉድ እየሆነ ነው ብሎ ጻፈልኝ)
አሁን ውስጤ ከማዘን አልፎ ተቆጣ፡ የሆነ ሀይል መጣብኝና የእግዚአብሔርን ቃል በድፍረት መናገር ጀመርኩኝ፡ እንዲህም አልኳቸው፡ ገና በመጀመሪያ በዘፍ. 1 ላይ፡ እግዚአብሔር ሰውን ወንድና ሴት አድርጓ፡ አዳምና ሔዋንን ፈጠረ ይላል እንጂ ወንድና ወንድ አድርጓ አዳምና አብርሃምን ወይም ሴትና ሴት አድርጓ ሔዋንና ሣራን ፈጠራቸው አይልም፡፡ ሰውን ብቻ ሳይሆን ሌሎች እንስሳትንም እንደዚሁ አድርጓ ፈጠራቸው፡ ብዙ ተባዙም አላቸዉ፡፡ እግዚአብሔር ደግሞ በሥራው ትክክል ነው፡፡ የእግዚአብሔርን አሠራር የሚቃወም ደግሞ ሴይጣንና መልዕክተኞቹ ናቸው፡፡ የእግዚአብሔር ቃል ርኩሰት ነው የሚለውን እነሱ ኖርማል ነው፡ መብት ነው፡ ፍላጓት ነው...እያሉ ያስፋፋሉ፡፡ ከእግዚአብሔር በተቃራኒው ይሄዳሉ፡፡ ብዙ ካወራሁላቸው በኋላ እንዲህ ብዬ ደመደምኩላቸው፡ ቤተ ክርስቲያን መመላለስ እና ክርስቲያን ሆኖ መኖር የተለያዪ ነገሮች ናቸው፡፡ ክርስትና ክርስቶስን መኖር ነው፡ እርሱን የመከተል ህይወት ነው፡፡ እግዚአብሔር አይለዋወጥም፡ ያኔ ሀጥያት ነው ያለዉን ዛሬ አይቀይረውም፡፡ ነገር ግን፡ እርሱ የፍቅር አምላክ ስለሆነ ማንም እንዲጠፋ፡ ከሴይጣን ጋር በገሃነም እንዲጣልና ለዘለዓለም እንዲሰቃይ አይፈልግም፡፡ የመዳንን መንገድ አዘጋጅቷል፡ መንገዱም አንድና አንድ ብቻ ነው፡
ጌታ ኢየሱስን በማመን፡ በፈሰሰው ደሙ መጽዳት ነው፡ ደሙ ዛሬም ትኩስ ነው፡ ከሀጥያት ሁሉ ያነፃል፡፡ እግዚአብሔር ዛሬ ይኼን እንዲነግራችሁ አገናኘን፡ ከጥፋት ጓዳና ውጡ፡ የርኩሰትን አጀንዳ አታራምዱ፡ መጨረሻችሁ እንዲያምር ክርስቶስን በህይወታችሁ አንግሱት፡ ተከተሉት፡፡ እርሱን በህይወታችሁ ካነገሳችሁና በእውነት ከተከተላችሁ፡ በዘላለማዊው ቤታችን በመንግስተ ሰማያት እንገናኛለን ብዬ ተሰናበተኳቸዉ፡፡

#በመጨረሻም ወንድሜ፡ አንቺም እህቴ፡ ዓለም በክፋት እየባሰች እየሄደች ነው፡፡ ሴይጣን አጭር ጊዜ እንደቀረው አውቆ የጨለማውን ሥራ በመገናኛ ብዙሃን፡ በማህበረሰብ ሚድያ፡ በተለያዪ የቴክኖሎጂ ውጤቶች፡ በአካል ሰዎችንም በመጠቀም የጥፋት አጀንዳውን ሌት-ተቀን እያስፋፋ ይገኛል፡፡ እባክህን ሴይጣንንና መልዕክተኞችን አትስማቸው፡ የሰማይና የምድር ጌታ የሆነውን ኢየሱስን ግን ስማው፡ ከጥፋት ትድናለህ፡ በህይወት ትኖራለህ፡ መንግስተ ሰማያትንም ትወርሳለህ!
#ወንድማዊ ግዴታዬ ነውና ጊዜዬን ሰጥቼ ፃፍኩልህ፡ ውድ ጊዜህን ሰውተህ ስላነበብክልኝ አመሰግናለሁ!
#እኔ በመፃፍ ድርሻዬን ተወጥቼአለሁ፡ ትውልዱን ለመታደግ SHARE ማድረግ ያንተ ፈንታ ነው፡፡
ሌሎች ተመሳሳይ ትምህርቶችን በ t.me/wondmagegnudessa ቴሌግራም ቻናል ማግኘት ትችላለህ፡፡
#ጤና ይስጥልኝ!
#እኔ_ፕሮቴስታንት_ነኝ

ጋዜጠኛ አበበ ግደይ:- ብዙ አትሌቶች ድል ካደረጉ በኋላ በዘፋኞች ተወድሰዋል። ድልህን አስመልክቶ (አበበ ቢቂላ በሮጠበትና ባሸነፈበት ከተማ) ማን ቢዘፍንልህ ትመርጣለህ?

ሰለሞን ባረጋ:- እኔ እንኳን ስለ ዘፈን ብዙ አላውቅም። እኔ ፕሮቴስታንት ነኝ።
ምንም አላንገራገረም። መቀባባትም አልሞከረም።- " እኔ ፕሮቴስታንት ነኝ"።
ጌታ ይባርከው። ጌታ ከፍ ሲያረገው ራሱን ዝቅ አድርጎ ጌታውን ከፍ አደረገ።

✍🏾 Abebe Abdissa
#አዲስ_መረጃ
#እኔ_አይደለሁም #ነብይት_ብርቱካን
The Christian News - የክርስቲያን ዜና

ነብይ ብርቱካን /TMH/ትግራይ ሚዲያ ሃውስ ስሟን ጠቅሶ ያሰራጨው መረጃ ውሸት መሆኑን ተናግራ ይሄንን ድርጊት ከማድርግ እንድትቆጠቡ ስትል መልክቷን አስተላልፋለች።

ከሰሞኑ TMH ፓስተር ብርቱካን የምትባል ሴት ናት በሚል ለኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር አብይ አህመድ ስትጽልይ እና የተለያዩ መልዕክቶችን ስታስተላልፍ የተቀረጸ ድምጽ በማህበራዊ ሚዲያ ማጋራቱ ይታወሳል።

ሆኖም ጉዳዩን በተመለከተ ነብይት ብርቱካን በሰጠችው ሃሳብ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በምንም ሁኔታ የመገናኘት እድል እንዳልነበራት እና ጸለየት ተብሎ የተለቀቀው ድምጽም የሷ እንዳልሆነ ታናግራለች።

ምንም እንኳን በማህበራዊ ሚዲያ በTMH የተሰራጨው መረጃ ጸሎቱን ያደረገችው የእግዚያብሄር ክብር መገለጫ አለም አቀፍ ቤተክርስቲያን ነብይት "ነብይት ብርቱካን ጣሰው" ነች ብሎ ስም ሳይጠራ አልያም እንደ ዶ/ር አብይ ፎቶዋን ያለቀቀ ቢሆንም ጋዜጠኛው ግን ፓስተር ብርቱን በሚል ስም ጠቅሷል።

ይህን ተከትሎም ነብይት ብርቱካን በማህበራዊ ሚዲያ ስሜ ተጠቅሶ የተሰራጨው መረጃ ወይም ድምጽ የኔ አይደለም እንደውም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ተገናኝተው እንደማያውቁ ተናግራለች።

ፈጣን ወቅታዊ ታማኝ ሀገርኛ እና አለማቀፍ የክርስቲያናዊ ዜናዎችን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናሌን በዚህ ሊንክ ይቀላቀሉ።
https://t.me/TCNEW
በኢንስታግራም ቤተሰብ እንሁን
https://www.instagram.com/thechristiannews1/
አዳዲስ ዜናዎች በምስል እና ድምጽ ለማግኘት የዩቲዩብ ቻናላችንን በዚህ ሊንክ ይጎብኙ እና ቤተሰብ ይሁኑ!!!
#እኔ_የኢየሱስ_ክርስቶስ_ምስክር_ነኝ

የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ በዚህ ክረምት በመላው ኢትዮጵያ የወንጌል ስርጭት ልታከናውን ነው።

ቤተክርስቲያኒቱ በምታዘጋጀው የወንጌል ስርጭት ላይ ሁሉም ሰው የቻለውን እንዲያደርግ እና በንቃት እንዲሳተፍ የቤተክርስቲያኒቱ ፕሬዝደንት ቄስ ዮናስ ይገዙ ተናግረዋል።

“ሰዎች ሁሉ ሊድኑ እና እውነቱን ወደ ማወቅ ሊደርሱ በሚወድ በእግዚአብሄር በመድሃኒታችን ፊት መልካም እና ደስ የሚያሰኝ ይህ ነው” በሚል ርዕስ በተዘጋጀው የወንጌል ስርጭት ሁላችንም የመዳንን እና የመልካሙን የምስራች ወንጌል በመመስከር ሰዎችን ወደ እግዚአብሄር መንግስት እንጥራ ሲሉ ጥሪ ያቀረቡት ደግሞ የቤተክርስቲያኒቱ ጠቅላይ ጸሐፊ ቄስ ተሾመ አመኑ ናቸው።

“ኑ ሁላችንም የመዳንን ወንጌል በጋራ እንመስክር”
#አንድ #ሰው በጌታ ያልሆነ ወዳጁ፣ ወደ ቤተ ክርስቲያናቹ ይዘኸኝ ሂድ ብሎ ይጠይቀዋል።

ይሄ ሰው የራሱን ማህበር እዳይወስደው፣ የምስባኩን ድራማ ፈራ! አሰብ አደረገና ይሻላል ብሎ ወዳሰበበት #ወደ ሌላ ህብረት ይዞት ሄደ። እዚያ የነበረው መድረክና ምስባክም ሰውየውን ከሰቀቀን አላዳነውም። ከዚያ ይሄ ወዳጁ ምን አለው፣ እዚህ #ቦታ አይደለም #እኔ፣ አንተስ ምን ታደርጋለህ አለው?

#እንደ #ክርስቲያን #አንድ አማኝ ያልሆነ #ሰው፣ ወደምትሄድበት ቤ/ክ ውሰደኝ ቢለን የት ይዘነው እንሄዳለን?

ፕሮፌሰር አታላይ አለም
የውክልና #ውጊያ‼️መጋቢ ፃዲቁ አብዶ
#ድንቅ #መልዕክት

ጦርነቱ የውክልና ጦርነት ነው የእውነተኛ አምላክና የአማልእክት ጦርነት ...

    መነሻ ቃል 1ሳሙ 17

👉 ቁጥር 4 በዚህ ስፍራ #ስለ ጎሊያድ ማንነት ይዘረዝራል ስለ ቁመቱ የጌት #ሰው መሆኑን ጀግንነቱን ትጥቁን ይናገራል::

👉 እስራኤልና ፍልስጤም ሁሌም ይዋጋሉ:: #በአንድ ወቅት #ግን  ጎሊያድ ያልተለመደና #እስራኤል ያልተዘጋጁበት የጦር ስልት ይዞ ቀረበ!! #እኔ የፍልስጤማውያንን ወገን ወክዬ አለሁ እናንተም የሚወክላቹ ጀግና ሰው ካላቹ አምጡና እንዋጋ ካሸነፈኝ ህዝቤ #እንደ ተሸነፈ ይቆጠር የሚል::

✝️ ቁጥ 8 " እናንተ የሳኦል ባሪያዎች" ሲል ከእስራኤል ወገን የሆኑትን ወታደሮች ሞራል በሚያወርድ ንግግር ተናገራቸው ከመሪያቸው እንዲሸሹ:: የሰዎቹን #ልብ ለመምታት። #ዛሬም  አንዳንድ #ሰዎች #እግዚአብሔር ከሰጣቹ መሪዎች ለመለየት ሲፈልጉ #እንዲህ አይነት ፕሮፓጋንዳ ይዘራሉ ።

✝️ ሰውዬው ከልጅነቱ ጦርነት የለመደ ተክለ ሰውነቱና ትጥቁ አስፈሪ ነበርና ለአርባ ቀንና ሌሊት ጠዋትና ማታ በተናገራቸው ቁጥር ሳዖልም እስራኤልም እጅግ ይደነግጡ ነበር::

👉ይሄኔ በንጉሡ በሳዖል በኩል ጎሊያድን የሚገድል እንዲህ ይደረግለታል የሚል አዋጅ ቢወጣም አንድም ሰው ግን አልተገኘም ነበር::

ጦርነቱ የውክልና ጦርነት ነው የእውነተኛ አምላክና የአማልእክት ጦርነት ነው:: #ስለዚህ ጎሊያድ ዳዊትን በአማልክቶቹ ስም ነው የረገመው #ነገር ግን ይሄንን እውነተኛ #አምላክ የሚወክል ጀግና ሰው አልተገኘም

👉ቀጥሎ ባሉት ቁጥሮች የእሴይ ስምንተኛና የመጨረሻ ስለሆነው ልጅ ስለ ዳዊት ማስተዋወቅ ይጀምራል::

✝️ እግዚአብሔር በስውር ያዘጋጀው ማንም የማያውቀው ከእግዚአብሔር ጋር ግን የሚተዋወቅ ቤተሰቡ የረሳው ጌታ ድል ያለማመደው:: ዳዊትን ወንድሙ እብሪተኛ አለው ቢያሳድገውም ቀዳሚው ቢሆንም አልተረዳውምና::

✝️ ዳዊት ስለ ጎሊያድ ጥያቄን ሲጠይቃቸው ንጉሱ ሳዖልን ጨምሮ ከራሳቸው በላይ ስለ ጎሊያድ አስፈሪነት እንደሰው አወሩት አትችለውም አሉት የአምላክን ጣልቃ ገብነት እረስተዋል::

✝️ ጎሊያድ ላቀረበው እስራኤል ግን ለማያውቀው አዲስ የጦር ስልት የሚገጥም ጀግና በታጣበት ጊዜ እግዚአብሔር በድብቅ ያዘጋጀውን ሰው አመጣ:: ዳዊትም ይህ ያልተገረዘ ማን ነው? አለ‼️

#ይህም ንግግሩ ለሳዖል ደረሰ ሳዖልም ዳዊትን አስጠራው የራሱን ልብስ አለበሰው ። #ይህ የሚያሳየን #ዳዊት በሚያመጣው ድል ተቀባይነትንና ስምን ለራሱ ለመውሰድ በመፈለግ ነበር ። አንዳንድ ሰዎች አሉ በሰው ድካም ድሉን የነሱ አድርገው የሚወስዱ ። ዳዊት ግን በዚህ መንገድ አልለመድኩም አለ::

እግዚአብሔር ባለማመደው ስልት ገባ በአምላኩ በእግዚአብሔር ስም ሊዋጋው #ወደ ጦር ሜዳው ገባ ገደለው በራሱ ሰይፍ አንገቱን ቆረጠው ።

      👉👉 መልእክቴ ይህ ነው ‼️

✝️ ዛሬም በህይወት ጉዞአችን ውስጥ ያልለመድነው ፣ ያላወቅነው፣ ያልጠበቅነው ፣ ያልተዘጋጀንበት #እኛ በፍጹም የማንችለው #ፈተና  ቢገጥመንም ነገር ግን #ጌታ ከእኛ ጋር አለና ጌታ ባለማመደን መንገድ #ድል ይሰጠናል ያድነናል ይታደገንማል::

✝️ ካፈጠጠብኝ  በአለም ካለው
     እጅግ ይበልጣል በእኔ ያለው
     የፍጥረት ገዢ ተቆጣጣሪው
     ጌታ ኢየሱስ ከእኔ ጋራ ነው‼️

#መጋቢ ጻድቁ አብዶ
በ18 አመቴ ሀኪም ትሞታለህ እንጅ አትተርፍም ከሆስፒታል ውጣ አለኝ።

#እኔ ደግሞ #ዛሬ በ78 ዓመቴ ኢየሱስ ያድናል እላለሁ!

ዶ/ር ቤተ መንግስቱ

ስንመለከታቸዉ እረጋ ያሉ በአገልግሎት ከኬኒያ እስከ አሜሪካ ከአሜሪካ እስከ ኢትዮጵያ የጉባኤ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ምስረታ ቀዳሚ የነበሩ።

ዶ / ር ቤተ መንግስቱ በአሁኑ ሰዓት በተልይ "አፍሪካ ተነሺ" በሚል አለም አቀፋዊ ጉባኤ የምትታወቀዉን የቤዛ ኢንተርናሽናል ቤተክርስቲያን እየመሩ ይገኛሉ።
#የዛሬ -ሃምሳ #ዓመት

#እኔ #በጌታ ምሪት #ወደ ባሌ ጎባ ገብቼ ቤተክርስቲያን ለመትከል ቤት የተከራየውበት ቀን #በሮቤና በአጋርፋ ይሠሩና ይኖሩ ከነበሩት ሁለት ወንድሞች #አያና መኳንንና #ከአባተ ወላኒዎሰ ጋር ከሮቤ አንድ ታጣፊ አልጋ ከነፍራሹ በ28 ብር ገዝተን ቤቱን ደግሞ በ10 ብር ተከራይተን የኪራይ ውል ፈጸምን።

ኪራዩን ከሁለቱ ወንድሞች ማን እንደከፈለ ትዝ አይለኝም ። ቤቱ ወንዝ ደር ከመሆኑም በላይ ንፋስ ያስገባል እና በጣም ይበርዳል።

በተለይም በማያውቁት አገር ሌሊቱን ለብቻ ማደር እንዴት ያስፈራል። ሃምሳ ዓመት ወደ ኋሊት አሰብኩ ። የአምላኬ ምህረትና ማደን ቸርነቱም ገረመኝ ደነቀኝም።

ስሙ ለዘለዓለም የተባረከ ይሁን ። 🙏🙏🙏

ከመጋቢ ጻድቁ አብዶ (የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ኅብረት ፕረዚዳንት) ገጽ የተወሰደ
#እንዴት ልንሆን እንችላለን? #ነገ #ምን ይሆናል ?
ጊዜው የማይገቡን ነገሮች የሚነገሩበት ነው።

አለም የምትለው ሌላ ነው እኛ የምንለው ደግሞ #እግዚአብሔር አለልን ነው።

ጠዋትና #ማታ በሚዲያ የምንሰማው #አለም በብዙ ፍረሃት #ውስጥ ያለችበት #ጊዜ ነው።

#እምነት ሁኔታን መካድ አይደለም ከሁኔታ በላይ የሆነውን #አምላክ ከፍ ማድረግ ነው።

ምንዛሬ ከፍ አለ ዝቅ አለ። ኑሮ ተወደደ እረከሰ ስለዘመኑ የሚወራው አብዛኛው አይገባንም።

#እኔ ግን እንዲህ እላችኋለው ለእግዚአብሔር ዘመን ከፍ አይልም ዝቅ አይልም። ኑሮ ስለረከሰ አልኖርንም ኑሮ ስለተወደደ አንጠፋም።

በሰው ካልኩሌሽን አልኖርንም አሁንም አንኖርም። ምንም እንኳን ምድረበዳ ቢሆን #ኢየሱስ አለ።

ዘመኑ አስጨናቂ ነው ? እውነት ነው ግን ኢየሱስ አለ።