The Christian News
5.37K subscribers
3.08K photos
29 videos
730 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
#ወይ_ጉድ_አሜሪካ፡.እግዚአብሔር ሆይ እርዳን! የገጠመኝን ጉድ እነሆ፡...
===(ከ2 ዓመት በፊት በፌስቡክ የተለጠፈ)
#ለአምልኮ ወደ ቤተ ክርስቲያን ለመሄድ ከዶርሜ ወጣሁ፡፡ ገና የግቢው በር ጋ ሲደርስ አንድ ፈረንጅ ከግቢያችን 'Security' ጋር ያወራል፡፡ 'Security'ው ጠራኝና ፈረንጁን እንዲረዳው ነገረኝ፡፡ እኔም ተቀበልኩኝና አነጋገርኩት፡፡ ፈረንጁም፡ ከአሜሪካን (USA) ሀገር እንደመጣ፡ ቤተ ክርስቲያን መሄድ እንደሚፈልግ ነገረኝ፡፡ እኔም መጀመሪያ ሊሄድ ካሰብኩበት ቤ/ክ ሃሳቤን ቀየርኩና ወደ አንድ ታሪካዊት ቤ/ክ ሊወስደው ወሰንኩኝ፡፡ ወደተኮናተረው ታክሲ ገባን፡፡ ሁለት ልጆች፡1 ወንድና 1 ሴት ታክሲው ውስጥ ነበሩ፡፡ ዕድሜያቸው ከ 14-16 አይበልጥም፡፡ የዛሬ 11 ዓመት ከኢትዮጵያ ላሳድጋቸው የወሰድኳቸው ልጆቼ ናቸው፡ ወላጆቻቸውን እንዲያናግሩ ይዤአቸው መጥቼ ነው ብሎ አስተዋወቀኝ፡፡ ጤና ይስጥልኝ ስላቸው፡ Ohhh...no Amharic, just English...አሉኝ፡፡ Ok፡ welcome to your homeland...ብዬ ሰላም አልኳቸው፡፡ ለባለ ታክሲውም የእንኳን ለጌታችን ትንሳኤ በዓል አደረሰህ ሰላምታዬን ካቀረብኩለት በኃላ እየተጫወትን ጉዞ ወደ ቤተ ክርስቲያን፡፡ ከጥቂት ደቂቃዎች በኃላ ደረስን፡ ገባን፡፡ ጸለይን፡ ስለ ጌታችን ትንሳኤ ቃል ሰማን፡ በዝማሬም አምልከን ጨርሰን ወጣን፡፡ እንደወጣን ስለ አሜሪካን ሀገር ክርስትና አንድ አንድ ጥያቄዎችን መጠየቅ ጀመርኩኝ፡፡ እንዴት ነው ክርስትና በአሜሪካ? ከማነበውና ከሚሰማው ሲረዳ እያሽቆለቆለ እንደሆነ ነው፡ ለዚህም ደግሞ የhomosexuality(ተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ), እንዲሁም የአንድ አንድ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ልምምዶች በዋናነት እንደምክንያትነት ይጠቀሳሉ ሲባል አምብቤያለሁ፡ ሰምቼአለሁ፡ እስቲ አንተም አውራኝ ስለዚህ ጉዳይ ብዬ ሳበቃ፡ እያየሁት ፊቱ ጠቆረ፡ ምነው ምን ሆንክ ብዬ ስለው፡ ቀጠለና እንዲህ አለኝ፡ 'እንዴት ነው homosexuality ምክንያት ሊሆን የሚችለው? Homosexual መሆኑ ምኑጋ ነው ጥፋቱ፡...'ወዘተ ብሎ ተናገረ፡፡ በጣም አዘንኩኝ፡ በጣም ደነገጥኩኝ፡፡ አግብተሃል ስለው፡ አዎን፡ የታለች በለቤትህ ስለው፡ 'አሜሪካ አለኝ' (ወንድ ይሁን ሴት ትሁን አልገለጸም):: ልጆችስ አሏችሁ ስለው 'ይኼው የምታያቸው ናቸው' ስለኝ፡ no no...ማለቴ ከናንቴ አብራክ የወጡ ስለው፡ 'አይ የለንም' አለኝ፡፡ ክርስቲያን ነህ ስለው፡ 'ይኼው እያየሄኝ፡ አብረን አምልከን እየወጣን' አለኝ፡፡ Ok አልኩኝ የማጣራት ሥራዬን ከሠራሁ በኃላ፡፡ ከዚያም እንዲህ አልኩት፡ የክርስትና መሰረቱ የእግዚአብሔር ቃል ነው፡ ቃሉ ደግሞ በብሉይም፡ በአዲስም ኪዳን፡ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ ሀጥያትና ርኩሰት እንደሆነ ይናገራል (በ2ቱም ኪዳኖች የተፃፈውን እየጠቀስኩ), ታድያ ቅዱስ ቃሉ እንዲህ ካለ፡ አንተም ደግሞ ክርስቲያን ነኝ ካልክ፡ ቃሉ የሚለው አንተ ከምትለው እንዴት ተጋጨ? ወይስ ሌላ መጽሐፍ ጻፋችሁ ስለው፡ አይ መፅሐፉ እራሱ ነው፡ ያነበብክልኝን ጥቅሶች ሁሉንም አውቃቸዋለሁ፡ የዛ ዘመን አውድ(context) እና የዚህ ዘመን ይለያያል፡፡የጥቅሶቹን Context ስናይ ስለ ተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ አይደለም ብሎ ተከራከረኝ በግልፅ ቋንቋ የተፃፈውን፡፡ ከሁሉም ያሳዘነኝ ያስደነገጠኝና ያናደደኝ፡ የጉድፈቻ ልጆቹ በተኩራራና በቁጣ ስሜት እንዲህ አሉኝ፡ 'የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ ምን ችግር አለው? ሰው የፈለገውን ማግባትና አብሮ መኖር ይችላል፡ እናንተ የሰውን መብት ለምን ትጋፋላችሁ? አንተ የዘረዘርካቸው ጥቅሶች ሁሉ ሀጥያት ስለመሆኑ አይናገሩም፡ አውዳቸው ሌላ ነው፡...'' አሉኝ በማከታተል፡፡ ወዮ ወየው፡...ጉድ ስሙ ይኼው ፡፡(በውጪም በሀገር ውስጥም ያላችሁ ወላጆች፡ ልጆቻችሁን ታውቃላችሁን ፡ ዬት ነው የሚማሩት፡ ዬት ነው የሚውሉት፡ ከማንስ ጋር፡...ምንድነው የሚማሩት፡ በስልካቸውና በኮምፒዩተራቸውስ ምንድነው የያዙት፡...አደራ ተከታተሏቸው፡ ልጅን በሚሄድበት መንገድ መምራት የወላጆች ሀላፊነት ነው: ይኼን ጽሁፍ ቀድሜ በአፋን ኦሮሞ ጽፌ፡ እንዲህ የሚል comment አነበብኩ፡ " homosexual የሆኑ ነጮችም ጥቁሮችም ልጅ መውለድ ስለማይችሉ፡ በስመ ጉድፈቻ ከሀገራችንና ከሌሎች ድሃ ሀገሮች ልጆችን እየሰበሰቡ አሳድገው፡ እነሱንም እንደዚሁ ያረጓቸውና በዚህ ክፉ መርዝ በክለው ይህን እርኩሰት እንዲያባብሱ በጀት መድበውላቸው ይልኩብናል፡,...ጉድ እየሆነ ነው ብሎ ጻፈልኝ)
አሁን ውስጤ ከማዘን አልፎ ተቆጣ፡ የሆነ ሀይል መጣብኝና የእግዚአብሔርን ቃል በድፍረት መናገር ጀመርኩኝ፡ እንዲህም አልኳቸው፡ ገና በመጀመሪያ በዘፍ. 1 ላይ፡ እግዚአብሔር ሰውን ወንድና ሴት አድርጓ፡ አዳምና ሔዋንን ፈጠረ ይላል እንጂ ወንድና ወንድ አድርጓ አዳምና አብርሃምን ወይም ሴትና ሴት አድርጓ ሔዋንና ሣራን ፈጠራቸው አይልም፡፡ ሰውን ብቻ ሳይሆን ሌሎች እንስሳትንም እንደዚሁ አድርጓ ፈጠራቸው፡ ብዙ ተባዙም አላቸዉ፡፡ እግዚአብሔር ደግሞ በሥራው ትክክል ነው፡፡ የእግዚአብሔርን አሠራር የሚቃወም ደግሞ ሴይጣንና መልዕክተኞቹ ናቸው፡፡ የእግዚአብሔር ቃል ርኩሰት ነው የሚለውን እነሱ ኖርማል ነው፡ መብት ነው፡ ፍላጓት ነው...እያሉ ያስፋፋሉ፡፡ ከእግዚአብሔር በተቃራኒው ይሄዳሉ፡፡ ብዙ ካወራሁላቸው በኋላ እንዲህ ብዬ ደመደምኩላቸው፡ ቤተ ክርስቲያን መመላለስ እና ክርስቲያን ሆኖ መኖር የተለያዪ ነገሮች ናቸው፡፡ ክርስትና ክርስቶስን መኖር ነው፡ እርሱን የመከተል ህይወት ነው፡፡ እግዚአብሔር አይለዋወጥም፡ ያኔ ሀጥያት ነው ያለዉን ዛሬ አይቀይረውም፡፡ ነገር ግን፡ እርሱ የፍቅር አምላክ ስለሆነ ማንም እንዲጠፋ፡ ከሴይጣን ጋር በገሃነም እንዲጣልና ለዘለዓለም እንዲሰቃይ አይፈልግም፡፡ የመዳንን መንገድ አዘጋጅቷል፡ መንገዱም አንድና አንድ ብቻ ነው፡
ጌታ ኢየሱስን በማመን፡ በፈሰሰው ደሙ መጽዳት ነው፡ ደሙ ዛሬም ትኩስ ነው፡ ከሀጥያት ሁሉ ያነፃል፡፡ እግዚአብሔር ዛሬ ይኼን እንዲነግራችሁ አገናኘን፡ ከጥፋት ጓዳና ውጡ፡ የርኩሰትን አጀንዳ አታራምዱ፡ መጨረሻችሁ እንዲያምር ክርስቶስን በህይወታችሁ አንግሱት፡ ተከተሉት፡፡ እርሱን በህይወታችሁ ካነገሳችሁና በእውነት ከተከተላችሁ፡ በዘላለማዊው ቤታችን በመንግስተ ሰማያት እንገናኛለን ብዬ ተሰናበተኳቸዉ፡፡

#በመጨረሻም ወንድሜ፡ አንቺም እህቴ፡ ዓለም በክፋት እየባሰች እየሄደች ነው፡፡ ሴይጣን አጭር ጊዜ እንደቀረው አውቆ የጨለማውን ሥራ በመገናኛ ብዙሃን፡ በማህበረሰብ ሚድያ፡ በተለያዪ የቴክኖሎጂ ውጤቶች፡ በአካል ሰዎችንም በመጠቀም የጥፋት አጀንዳውን ሌት-ተቀን እያስፋፋ ይገኛል፡፡ እባክህን ሴይጣንንና መልዕክተኞችን አትስማቸው፡ የሰማይና የምድር ጌታ የሆነውን ኢየሱስን ግን ስማው፡ ከጥፋት ትድናለህ፡ በህይወት ትኖራለህ፡ መንግስተ ሰማያትንም ትወርሳለህ!
#ወንድማዊ ግዴታዬ ነውና ጊዜዬን ሰጥቼ ፃፍኩልህ፡ ውድ ጊዜህን ሰውተህ ስላነበብክልኝ አመሰግናለሁ!
#እኔ በመፃፍ ድርሻዬን ተወጥቼአለሁ፡ ትውልዱን ለመታደግ SHARE ማድረግ ያንተ ፈንታ ነው፡፡
ሌሎች ተመሳሳይ ትምህርቶችን በ t.me/wondmagegnudessa ቴሌግራም ቻናል ማግኘት ትችላለህ፡፡
#ጤና ይስጥልኝ!