The Christian News
5.37K subscribers
3.08K photos
29 videos
730 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
#አለም_በችግር_ውስጥ_ስትገባ_ተስፋችን_በኢየሱስ_ክርስቶስ_ላይ_ብቻ_እንዳለ_እርግጠኞች_ነን
The Christian News - የክርስቲያን ዜና

ወጣት ለክርስቶስ ከ169ሺህ ዶላር በላይ በማሰባሰብ በጦርነት በተመታች ዩክሬን ውስጥ ለተፈናቀሉ ሰራተኞች ድጋፍ ተደረገ።

ዩዝ ፎር ክሪስቶስ የተባለ አገልግሎት ሩሲያ በዩክሬን ላይ በወረረችበት ወቅት ቤታቸውን ጥለው ለመሰደድ ለተገደዱ ሰራተኞች እና በጎ ፈቃደኞች 170,000 ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ አሰባስቧል ሲል በዛሬው እለት ክርስቲያን ፖስት አስነብቧል።

የአገልግሎት ቡድኑ “ለህፃናት እና ወጣቶች አገልግሎት የመስጠት ታማኝ ታሪክ አለው። ያሉት የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር የሆኑት ጆ ቤክለር ናቸው።

ቤክለር አክለው ሌሎች ደግሞ በምስራቅ አውሮፓ ሰላም እና ጥበቃ እንዲደረግልን አብረውን ይጸልዩ ነበር። ዓለም በችግር ውስጥ ስትገባ ተስፋችን በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ብቻ እንዳለ እርግጠኞች ነን ሲሉ ተናግረዋል።

በዩክሬን እና ሩሲያ መካከል ጦርነት ከተጀመረ አንስቶ በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ያሉ ብዙ አብያተ ክርስቲያናት እና ሚኒስቴሮች በግጭቱ በቀጥታ የተጎዱትን ለመርዳት ፍላጎታቸውን እንዳሳዩ ዘገባው አክሎ አስነብቧል።

ምንጭ The Christian Post
#አለም_አቀፍ_ሚሽነሪዎች

ኢትዮጵያን ግሎባል ሀርቨስት አሊያንስ በይፋ እየተመሰረተ ነው።

የኢትዮጵያ ግሎባል ሀርቨስት ኔትወርክ እና የኢትዮጵያ ግሎባል ሚሽን አሊያንስ ውህደት የሆነው ኢትዮጵያን ግሎባል ሀርቨስት አሊያንስ በዛሬው እለት የአብያተክርስቲያናት መሪዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በሸራተን ሆቴል በይፋ የምስረታ መሰናዶውን እያከናወነ ይገኛል።

ሚኒስትሪው ሚስዮናውያንን በወንጌል ወዳልተደረሱ ወደ አለም አቀፍ ለመላክ እቅዶችን ይዞ የተነሳ እንደሆነ በመድረኩ ተጠቅሷል።

ጥምረትን የፈጠሩት ሁለቱ ሚኒስትሪዎች ከዚህ ቀደም በግል ለጌታ ታልቁ ተልዕኮ ምላሽ በመስጠት በግል ይሰሩ የነበረ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት አቅማቸውን በማጠናከር የበለጠ እንደሚሰሩ በመድረኩ ተገልጿል።

The Christian News - የክርስቲያን ዜና በስፍራው የምንገኝ ሲሆን ዝርዝር መረጃዎችን ይዘን የምንመለስ ይሆናል።
#እንኳን #አደረሳችሁ!!!!

#ተነስቷል ግን በዚህ የለም !!!

... “አትደንግጡ፤ የተሰቀለውን የናዝሬቱን ኢየሱስን ትፈልጋላችሁ፤ ተነሥቶአል፥ በዚህ የለም፤ እነሆ እርሱን ያኖሩበት ስፍራ።”

— ማርቆስ 16፥6

በመላዉ #አለም የምትገኙ #ዉድ #የክርስቲያን #ዜና ቤተሰቦች እንኳን ለ2015ዓ.ም የትንሳኤ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!!

#መልካም #የትንሳኤ #መታሰቢያ #በዓል ይሁንልን!!!
#አባባ #ሴባ #ዋባሎ #ከዚህ #አለም #ድካም #አረፉ!

አባባ በ1901ዓ.ም በወላይታ ዞን ኦፋ ወረዳ ሳዶዬ ቀበሌ የተወለዱ ሲሆን በ1952 ዓ.ም ከተወለዱበት ከኦፋ ወረዳ ወንጌልን ለማገልገል ወደ ኪንዶ ኮይሻ ወረዳ ማንአራ ቀበሌ አቀኑ።

በተያዘም ከጤፓ ቀበሌ ጀምሮ በጨራቼ አድርጎ እስከ ጫው ካሬ ገበረ ማህበር ድረስ በቁጥር 13 የቃለህይወት ቤቴክርስቲያንን የመሠረቱና የተከሉ እኔን ጨምሮ በርካቶች ወንድሞቼና እህቶቼ ወደዚህ ዓለም እንዲንመጣ በረከት የሆኑ ታላቅ የእምነት አባት እና የሥጋ አያቴን በሞት ማጣት ምነኛ የሚያሳዝን ብሆንም ወዳገለገሉ ጌታ መሄዳቸው ከባድ መታደል ነው።

አባባ በበጉ ሠርግ በዳግም ምጻት እንገናኝ ቻው መልካም እረፍት።

Taway lo"uwan da!!
ልጃቸዉ
#ፍትህ ግን ምንድነው? 🤔 የትስ #ነው ያለው? 🤔
#እኛ ጥያቄያችን #አንድ እና ግልጽ  ነው።

#የቤተክርስቲያናችን_ንብረት_ይመለስልን!!! 🙏🙏🙏

37 ዓመታት በእንባ እና በጸሎት የጸሎት ቤቷን ለማስመለስ ፍትሕን ፍለጋ የተነከራተተችው #ቤተክርስቲያን ዛሬም ፍትህን ፍለጋ ላይ ነች።

የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ከ1950ዎቹ #መጀመሪያ ጀምሮ በተለይ ትምህርትን ከማስፋፋት አንጻር #ለሀገር እና #ለሕዝብ ጥቅም ላበረከተችው አስተዋጽዖ በወቅቱ የነበረው የመንግስት ስረዓት ከምስጋና ይልቅ ት/ቤቶቻችንና ጸሎት ቤቶቻችንን መውረስ ቀሏቸዋል።

በደርግ #መንግስት በግፍ የተወረሰው የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የኦሎምፒያው ጸሎት ቤታችን በአዲስ አበባ የመጀመሪያው የመሰረተ ክርስቶስ የማምለኪያ ስፍራ ነው።

#ይህ የመሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ንብረት #ማለት የሙሉ #ወንጌል ምዕመን እና የሙሉ ወንጌል ቤ/ክ ንብረት ማለት ነው። የመካነ ኢየሱስ ማለት ደግሞ የቃለ ሕይወት ነው። የቃለ ሕይወት ማለት የሕይወት ብረሃን የሕይወት ብረሃን ማለት የገነት የገነት ማለት የጉባኤ እግዚአብሔር ... በአጠቃላይ የወንጌል አማኞች #በሙሉ ነው።

ይህ ከ66 ዓመት በላይ የተሻገረው የጸሎት ስፍራ ንብረት ብቻ አይደለም ይልቁንም ለወንጌል የተሰደዱ ፤ ለወንጌል ዋጋ የከፈሉ የወንጌላውያን አማኞች #ታሪክ እና ቅርስም ጭምር ነው።

በ1943ዓ.ም የተመሰረተችው የመሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ከቀደምት የወንጌል አማኞች ቤተዕምነት መካከል አንዷ ብቻ ሳትሆን እውነተኛው የክርስቶስ ወንጌል ለአዲሱ #ትውልድ  እንዲሸጋገር ከ70 ዓመት በላይ #በኢትዮጵያ በሚመችም በማይመችም ሁኔታ #ውስጥ ስትሰራ ቆይታለች።

#ዛሬ ላይ መዲናችን #አዲስ አበባ ከሌሎች #አለም ላይ ከሚገኙ ከተሞች መካከል ለመወዳደር ሌት ተቀን እየተጋች ትገኛለች። በዚህ ውስጥ ታዲያ በከፊሉ አዳዲስ ሲገነባ በከፊሉ ለተቸገሩት ሲደረስ በሌላ አቅጣጫ ግን እንሳኩን ያልተመለሱ #ብዙ ጥያቄዎች እንዳሉ የአደባባይ ሚስጥር ነው።

ታዲያ በመዲናችን #ዛሬም ፍትህን ከሚጠይቁ ተቋማት መካከል አንጋፋዋ የመሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አንዷ ነች።

ስለዚህ ህጋዊ የሆነው የቤተክርስቲያን ታሪክ ፤ ቅርስ እና ንብረታችን የሆነው የጸሎት ቤቶቻችን ይመለሱልን የማያቋርጥ ጥያቄያችን ነው!!!

ይህ #መልዕክት የሚደረሳችሁ ምዕመናን እና ኢትዮጵያውያን በሙሉ የቤተክርስቲያናችን ንብረት እስኪመለስ ድረስ ሁላችንም #SharePost በማድረግ ለሁሉም እናድርስ!!!

The Christian News - የክርስቲያን ዜና በዚህ ዙሪያ ተጨማሪ ዘገባዎችን በተለያየ ጊዜ ይዘን የምንመለስ ይሆናል።

#share #share #share #share
#አሳዛኝ #ዜና

12ኛ አመቱን በያዘው የሶርያ እርስ በእርስ ጦርነት ምክኒያት የክርስቲያኖች #ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እያሽቆለቆለ #ነው ተባለ።

በተለይ በበሰሜናዊ ሶርያ የምትገኘው አሌፖ #ከተማ በርካታ ክርስቲያኖች ይገኙባታል የነበረች ከተማ ነች።

ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ 250ሺህ የነበረው የክርስቲያኖች ቁጥር፣ አስደንጋጭ በሆነ ሁኔታ #ወደ 50ሺህ ወርዷል።

በከተማዋ ያሉ ክርስቲያኖች አሌፖ በጦርነቱ ፍርስርሷ ከመውጧቷ በተጨማሪ፣ በአይ ኤስ አይ ኤስ፣ የኩርድ ታጣቂዎች፣ አማጺ ሃይሉና የሶርያ #መንግስት መካከል በሚደረግ ጦርነት የመጀመሪያዎቹ ገፈት ቀማሾች መካከል ናቸው።

ከ200ሺህ #በላይ ክርስቲያኖች ከአሌፖ #ብቻ መሰደዳቸው፣ በሃገሪቱ ጥቂት የሆኑ ክርስቲያኖችን ቁጥርን አደጋ #ላይ ጥሎታል ሲል #አለም አቀፉ #ክርስቲያን ኮንሰርን አስነብቧል።

አሌፖ ከጦርነቱ በፊት በሰሜናዊ ሶርያ የንግድ ማዕከል የነበረችና ጥንታዊ ከተማ ስትሆን፣ ከጦርነቱ ማግስት ተከስቶ በነበረው ርዕደ #መሬት ሳቢያም ሁኔታዋ ከድጡ ወደ ማጡ ሆኗል።

በ2023 የኦፕን ዶርስ ዝርዝር መሰረት ሶርያ 12ኛ ለክርስቲያኖች የማትመች ሃገር ናት።
#እንዴት ልንሆን እንችላለን? #ነገ #ምን ይሆናል ?
ጊዜው የማይገቡን ነገሮች የሚነገሩበት ነው።

አለም የምትለው ሌላ ነው እኛ የምንለው ደግሞ #እግዚአብሔር አለልን ነው።

ጠዋትና #ማታ በሚዲያ የምንሰማው #አለም በብዙ ፍረሃት #ውስጥ ያለችበት #ጊዜ ነው።

#እምነት ሁኔታን መካድ አይደለም ከሁኔታ በላይ የሆነውን #አምላክ ከፍ ማድረግ ነው።

ምንዛሬ ከፍ አለ ዝቅ አለ። ኑሮ ተወደደ እረከሰ ስለዘመኑ የሚወራው አብዛኛው አይገባንም።

#እኔ ግን እንዲህ እላችኋለው ለእግዚአብሔር ዘመን ከፍ አይልም ዝቅ አይልም። ኑሮ ስለረከሰ አልኖርንም ኑሮ ስለተወደደ አንጠፋም።

በሰው ካልኩሌሽን አልኖርንም አሁንም አንኖርም። ምንም እንኳን ምድረበዳ ቢሆን #ኢየሱስ አለ።

ዘመኑ አስጨናቂ ነው ? እውነት ነው ግን ኢየሱስ አለ።