The Christian News
5.37K subscribers
3.08K photos
29 videos
730 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
#ጋና ግብረሰዶምን ህገወጥና በወንጀል ተጠያቂ ልታደርግ ነው።

ለሃገሪቱ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቀረበው ረቂቅ ህግ መሰረት ግብረሰዶምን ህገወጥና ወምጀል የሚያደርግ ነው።

የጋና ፕሬዝዳንት የሆኑት አኩፎ አዶ ይሄንን ውሳኔ ማሳለፍ ከውጪ ሃገራት ዘንድ ትልቅ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጫና ሊያመጣባቸው ይችላል እየተባለ ነው።
ይሁን እንጂ ውሳኔው በብዙሃኑ የጋና ምክር ቤት አባላት ተቀባይነት ይኖረዋል እየተባለ ነው።

የጋና ክርስቲያኖች ምክር ቤት (ቆንስላ) ይሄ ህግ ሆኖ እንዲጸድቅ #በሙሉ ድምጽ እንደግፋለን፣ እንጸልያለን ብለዋል።

ሙሉ ዝርዝር መረጃ ምሽት በቪዴዮ The Christian News - የክርስቲያን ዜና ይዘንላችሁ እንመለሳለን። ሊንኩን ይጠቀሙ።

https://www.youtube.com/@TheChristianNews/videos
“የሰማይ #አምላክ ያከናውንልናል እኛም ባሪያዎቹ ተነስተን እንሰራለን" ክብርት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

“እግዚአብሄር ታላቅ ነገር አደረገልን እኛም ደስ አለን” ክብርት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

የአዲስ አበባ #ከተማ ከንቲባ ክብርት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በዛሬዉ እለት በአዲስ አበባ እስታዲየም ተገኝተዉ ያስተላለፉት #መልዕክት #እግዚአብሔር ተግዳሮት በሚመስል መንገድ ውስጥ በርካታ ነገሮችን አሳክቶ ስራችንን ፍሬያማ አድርጎታል።

#ብዙ የምንወድቅባቸው የሚመስሉ መንገዶችን አልፈናል ዳገቶች ፤ ሸለቆዎች ነበሩ ብዙ ሰላም የሌለባቸውን ሀገሮች ታሪክ ስንመለከት እግዚአብሔር ስለ ሰጠን ሰላም እናመሰግነዋለን።

ፍጹም ስላማችን እንዲደፈርስ እርስ በእርሳችን እንዳንቀባበል እንድንበታተን ወንድም ወንድሙን እንዲገድል ፈጽሞ መበታተን እንዲሆን ያልተሰራ ነገር የለም ከውስጥም ከውጪም ብዙ ጫናዎች ነበሩብን #ነገር #ግን ከእግዚአብሔር ጋር ጸንተን ቆመናል።

በእነዚህ የውጣ ውረድ መንገዶች በጸሎታችሁ አብራችሁን ለነበራችሁ በብዙ መንገድ ስትለፉ ስትደክሙ በልማት ፤ በበጎ አድራጎት ፤ በሰላም ስራዎች ያልተለያችሁን ለትውልዱ መልካሙን ዜና በመንገር ተስፋ እንዲኖረው ይልቁንሙ ከሁኔታዎች በላይ #እግዚአብሔር የሚለውን ለሃገራችን ያለውን እንዲመለከት በማድረግ ብዙ ዋጋ የከፈላችሁ እና የሰራችሁ #በሙሉ እናመሰግናችኋለን።

በአዲሱ አመትም በርካታ ውጥኖች አሉን በርትተን እንሰራለን አንሰንፍም ፤ ፈጽሞ ስንፍናን አልተማርንም በመጽሐፍ #ቅዱስ ተጽፎ ያነበብነው አባታችሁ ተግቶ ሲሰራ ነው። እኛም ልጆቹ ተግተን እንሰራለን።

በፍቅር ወንድማማችን በማስታረቅ ፤ በማቀራረብ የሰላሙን #ዜና እየተናገርን የሰላም ስራተኞች በመሆን እየታወቅን ይልቁንም ለምድራችን ብዙ ፍሬ እንዲበዛ እግዚአብሔር ለምድራችን የወደደውን ያለመከልከል መስራት እንዲችል ምቹ ሁኔታን በመፍጠር ብርቱ ሰራተኞች በመሆን ለመልካም ስራ እጅ ለእጅ ተያይዘን ለምድራችን አብረን እንድንተጋ በዚህ አጋጣሚ ጥሪዬን አቀርባለሁ።

እያየነው ያለነው ፍሬ ተስፋ የሚያስቆርጥ ሳይሆን የሚያበረታ ነው አባቶቻችን ልጆቻችን ይሰሩታል ብለው ያሳለፉትን ይህ ትውልድ እግዚአብሔር እረድቶን በራሳችን እውቀት እና ገንዘብ አባይን ገድበናል ብዙም ፍሬ አግኝተናል ይህ ቀላል አይደለም።

አንድ ላይ ሆነን ከሰራን እና ከተደጋገፍን የያዝነው ስራ በጸድቅ ከፈጸምን ይከናወንልናል ነህምያ “የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል እኛም ባሪያዎቹ ተነስተን እንሰራለን" እንዳለው እኛ ተነስተን እንሰራለን የሰማይ አምላክም ያከናውንልናል።

#ዛሬ የጀመርነው አዲሱ አመት ለሁሉም የሃገራችን ክፍል ሞልቶ የሚፈስበት ወንድማማቾች ተጸጽተው የሚተቃቀፉበት ፤ ለምድራቸው ሰላም በጋራ የሚሰሩበት የኢትዮጵያ እሴት ደምቆ የሚታይበት ብዙ ውድቀቷን የሚፈልጉ #ኢትዮጵያን በሰላማዊነቷ በብዙ ለውጥ እና የልማት ስራዎች የሚሰራበት አመት እንደሚሆንልን እናምናለን።

#መልካም #አዲስ #አመት

Photo 📷 Hossana Photo & Video Production
#ፍትህ ግን ምንድነው? 🤔 የትስ #ነው ያለው? 🤔
#እኛ ጥያቄያችን #አንድ እና ግልጽ  ነው።

#የቤተክርስቲያናችን_ንብረት_ይመለስልን!!! 🙏🙏🙏

37 ዓመታት በእንባ እና በጸሎት የጸሎት ቤቷን ለማስመለስ ፍትሕን ፍለጋ የተነከራተተችው #ቤተክርስቲያን ዛሬም ፍትህን ፍለጋ ላይ ነች።

የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ከ1950ዎቹ #መጀመሪያ ጀምሮ በተለይ ትምህርትን ከማስፋፋት አንጻር #ለሀገር እና #ለሕዝብ ጥቅም ላበረከተችው አስተዋጽዖ በወቅቱ የነበረው የመንግስት ስረዓት ከምስጋና ይልቅ ት/ቤቶቻችንና ጸሎት ቤቶቻችንን መውረስ ቀሏቸዋል።

በደርግ #መንግስት በግፍ የተወረሰው የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የኦሎምፒያው ጸሎት ቤታችን በአዲስ አበባ የመጀመሪያው የመሰረተ ክርስቶስ የማምለኪያ ስፍራ ነው።

#ይህ የመሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ንብረት #ማለት የሙሉ #ወንጌል ምዕመን እና የሙሉ ወንጌል ቤ/ክ ንብረት ማለት ነው። የመካነ ኢየሱስ ማለት ደግሞ የቃለ ሕይወት ነው። የቃለ ሕይወት ማለት የሕይወት ብረሃን የሕይወት ብረሃን ማለት የገነት የገነት ማለት የጉባኤ እግዚአብሔር ... በአጠቃላይ የወንጌል አማኞች #በሙሉ ነው።

ይህ ከ66 ዓመት በላይ የተሻገረው የጸሎት ስፍራ ንብረት ብቻ አይደለም ይልቁንም ለወንጌል የተሰደዱ ፤ ለወንጌል ዋጋ የከፈሉ የወንጌላውያን አማኞች #ታሪክ እና ቅርስም ጭምር ነው።

በ1943ዓ.ም የተመሰረተችው የመሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ከቀደምት የወንጌል አማኞች ቤተዕምነት መካከል አንዷ ብቻ ሳትሆን እውነተኛው የክርስቶስ ወንጌል ለአዲሱ #ትውልድ  እንዲሸጋገር ከ70 ዓመት በላይ #በኢትዮጵያ በሚመችም በማይመችም ሁኔታ #ውስጥ ስትሰራ ቆይታለች።

#ዛሬ ላይ መዲናችን #አዲስ አበባ ከሌሎች #አለም ላይ ከሚገኙ ከተሞች መካከል ለመወዳደር ሌት ተቀን እየተጋች ትገኛለች። በዚህ ውስጥ ታዲያ በከፊሉ አዳዲስ ሲገነባ በከፊሉ ለተቸገሩት ሲደረስ በሌላ አቅጣጫ ግን እንሳኩን ያልተመለሱ #ብዙ ጥያቄዎች እንዳሉ የአደባባይ ሚስጥር ነው።

ታዲያ በመዲናችን #ዛሬም ፍትህን ከሚጠይቁ ተቋማት መካከል አንጋፋዋ የመሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አንዷ ነች።

ስለዚህ ህጋዊ የሆነው የቤተክርስቲያን ታሪክ ፤ ቅርስ እና ንብረታችን የሆነው የጸሎት ቤቶቻችን ይመለሱልን የማያቋርጥ ጥያቄያችን ነው!!!

ይህ #መልዕክት የሚደረሳችሁ ምዕመናን እና ኢትዮጵያውያን በሙሉ የቤተክርስቲያናችን ንብረት እስኪመለስ ድረስ ሁላችንም #SharePost በማድረግ ለሁሉም እናድርስ!!!

The Christian News - የክርስቲያን ዜና በዚህ ዙሪያ ተጨማሪ ዘገባዎችን በተለያየ ጊዜ ይዘን የምንመለስ ይሆናል።

#share #share #share #share
#ወደ #ጌታ #ሄዱ

ላለፋት ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ በኦሮሚያ ክልል በጂማ ዞን በጎማ ወረዳ በኪሎሌ ቀበሌ ውስጥ በምትገኘው ቃለ ሕይወት #ቤተክርስቲያን በወንጌል #አገልግሎት መስዋዕትነት የከፈሉ የሕይወት ዘመናቸውን #በሙሉ ለወንጌል አገልግሎት የሰጡት ወንጌላዊው ሀይሉ ሌታሞ ወደ ሚወዱት እና ወዳገለገሉት ጌታ ሄደዋል።

ለብዙዎቻችን በረከት የሆኑ እና ብዙዎቻችንን በቃሉ ያሳደጉና ያፈሩ አባታችን ወንጌላዊ ሀይሉ ሌታሞ ዛሬ ህዳር 25 ቀን2016 ዓ/ም ወደሚወዱትና ወደ ሚናፍቁት ጌታቸው በመሰብሰባቸው The Christian News - የክርስቲያን ዜና የተሰማንን ሀዘን እየገለጽን ለቤተሰብ፣ ለወዳጆች እና ለመላው ቃለ ሕይወት ቤተክርስትያን ምዕመናን መጽናናትን እንመኛለን

የተወዳጁ አገልጋይ ስረዓተ ቀብር በነገዉ እለት የሚፈፀም ይሆናል።
#አስደሳች #ዜና ለወንጌል አማኞች #በሙሉ

#በመስቀል #አደባባይ የንስሐ፣ የምልጃና የምስጋና ፕሮግራም መዘጋጀቱ ተገለጸ።

በዛሬው እለት #የኢትዮጵያ #ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል መሪዎች በአዲስ አበባ በመስቀል አደባባይ የንስሐ፣ የምልጃና የምስጋና ፕሮግራም መዘጋጀቱን ለሚዲያዎች መግለጫ ሰጥተዋል።

በተሰበረ #ልብ፣ በንስሐ መቅረብ የመጀመሪያ ተግባራችን መሆን እንዳለበት የጠቀሱት መሪዎቹ “#ወደ ደጆቹ በመገዛት ወደ አደባባዮቹም በምስጋና ግቡ፣ አመስግኑት፣ ስሙንም ባርኩ” (መዝ 100)፤4 በሚለው ቃለ #እግዚአብሔር መሠረት መጋቢት 8 ቀን 2016 ዓ/ም ከቀኑ 7፡00 ጀምሮ #በአዲስ አበባ #መስቀል አደባባይ የንስሐ፣ የምልጃና የምስጋና በዓል ለማካሄድ አስፈላጊው ዝግጅት #ሁሉ ተጠናቋል ብለዋል።

አሁንም የእርስ በርስ መጠፋፋቱ አልቆመም ያሉት መሪዎቹ መደማመጥና መከባበር በመካከላችን እንዲኖርና ለይቅርታና ለፍቅር ልባችን የቀና እንዲሆንና ፀጋውንም እንዲያበዛልን #እግዚአብሔርን የምንማጸንበት #ጊዜ ይኖራል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በፕሮግራሙ የሚካፈለው የሕዝብ #ብዛት እጅግ ብዙ ስለሆነ ስብሰባው የሚካሄደው በመስቀል አደባባይ ነው፡፡

በመሆኑም መላው የወንጌል አማኝ በነቂስ ወጥቶ #በእግዚአብሔር ፊት የንስሐ፣ የምልጃና የምስጋና ፕሮግራሙ ተካፋይ እንዲሆን ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

The Christian News - የክርስቲያን ዜና በስፍራው ተገኝተን ዝርዝሩን አሰናዳንላችሁ።

#photo Christian tube - ክርስቲያን ቲዩብ

ዝርዝር መረጃ ምሽት ላይ በቪዲዮ ይዘንላችሁ የምንመለስ ይሆናል።
https://www.youtube.com/channel/UCeHRJCDJ0wUDaBfAFmuMa7A?sub_confirmation=1