The Christian News
5.06K subscribers
3.01K photos
23 videos
710 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
#የነገዉ ልዩ የትንሳኤ ፕሮግራም ዝግጅቱ እየተጠናቀቀ ነወ።
#በአዲስ_አበባ_እስታዲየም
The Christian News - የክርስቲያን ዜና

የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት የ2014 ዓ.ም የትንሣኤ በዓል ምክንያት በማድረግ የምልጃና የጸሎት ፕሮግራም በአዲስ አበባ ስታዲየም ያካሂዳል።

ለአገራችን በሚደረገው በዚህ የምልጃና የጸሎት ፕሮግራም ላይ እሑድ ሚያዝያ 16 ቀን 2014 ዓ.ም ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ በስፍራው በመገኘት አብረን የእግዚአብሔርን ፊት እንድንፈልግ ኅብረቱ ጥሪ ያደርጋል።

በአሁኑ ሰዓት ሙሉ ዝግጅቱ በመጠናቀቀ ላይ ሲሆን በነገዉ እለት ሁላችሁም ተጋብዛችኋል።
የመዘምራን የጋራ የምክክር #ጊዜ ተካሄደ፡፡

#በኢትዮጵያ #ሙሉ ወንጌል አማኞች #ቤተክርስቲያን #በአዲስ #አበባ እና አከባቢው ሶስት ክልሎች ውስጥ ከሚገኙ አጥቢያዎች የተሳተፉበት የጋራ የምክክር ጊዜ ተከናወነ።

በቀጠና ሁለት ሙሉወንጌል ቤተክርስቲያን በተካሔደዉ መረሀ ግብር መዘምራን፣ የሙዚቃ ተጫዋቾች እና የሶሎ ዘማርያን የተገኙ ሲሆን አገልግሎት የበለጠ ፍሬያማ ለማድረግ እንዲሁም በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ካሉ የቀድሞና አሁን በማገልገል ላይ ካሉ የሙሉ #ወንጌል መዘምራን #አባላት ጋር ሕብረትን ለማጠናከርና ያሉንን ጠንካራ እሴቶች ለማስቀጠል ቃል ተገብቷል ፡፡

በፕሮግራሙ የጎተራ ሙሉ ወንጌል አጥቢያ D መዘምራን እና የስድስት ኪሎ ሙሉ ወንጌል አጥቢያ አሳፍ መዘምራን ያገለገሉ ሲሆን ፓስተር ደበበ ለማ ( ጋሽ ደቤ )፣ ፓስተር ሳሙኤል ወንድሙ ከአትላንታ እና ፓስተር ኤርሚያስ ገ/መድህን ልዩ ልዩ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል፡፡
#ድንቅ #ስራ
#Fbi_Church_good #news አጥቢያ በቦሌ ክፍለ ከተማ በወረዳ 6 የአንዲት እናታችንን ቤት አፍርሳ #ሙሉ በሙሉ #በአዲስ መልክ ለማስረከብ የማስጀመሪያ ፕሮግራም አድርጋለች::

ይህ መልካም ስራ ነው ተባረኩ
#ነገ #በአዲስ #አበባ #እስታዲየም
#ኑ አዲስ አመትን አብረን እንቀበል።
ከማለዳዉ 12:00 ጀምሮ

መስከረም 1 በአዲስ አበባ እስታዲየም የአምልኮ ፕሮግራም ይካሄዳል።

በኢትዮጵያ ወንጌላውያውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት የ2016ዓ.ም #አዲስ #ዓመት ምክንያት በማድረግ በ "አዲስ አበባ እስታዲየም" ልዩ የበዓል #ፕሮግራም ይካሔዳል።

የጳጉሜ ወር በሙሉ ለሃገራችን ሰላም እና ለምድራችን እረፍት እንዲሆን ጸሎት ሲደረግ እንደ ነበር ይታወሳል።

#ነገ በመስከረም 1/2016ዓ.ም በአዲስ አመት የጾም ጸሎቱ ማጠቃለያ እና የጋራ የአምልኮ እና የምስጋና መረሃ ግብር በአዲስ አበባ እስታዲየም የሚደረግ ሲሆን በመረሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው አብረን አዲስ ዓመትን እንቀበል።
#በአዲስ #አመት #ሌላ #በረከት
ከግማሽ #ሚልዮን በላይ .. በማዉጣት ለአቅመ ደካሞች ..

የፌይዝ ባይብል ኢንተርናሽናል ቸርች ሚራክል አጥቢያ ከጉድለቷ በመቆረስ ከ550,000 ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ሶስት የአቅመ ደካሞች ቤት አስመረቁ።

በፕሮግራሙ ላይ የፌይዝ ባይብል #ኢንተርናሽናል ቸርች መሪ የሆነው ቢሾፕ ዳዊት ሞላልኝ እንዲሁም የልደታ ክፍለ ከተማ አፈ ጉባኤ አቶ ዘሪሁን እና የወረዳ 8 አፈጉባኤ እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት አስመርቀን አስረክበናል::

በዚህ በጎ ተግባር ላይ በገንዘባችሁ እና በሙያችሁ የተሳተፋችሁ የቤተክርስትያናችን አባሎች #ሁሉ #እግዚአብሔር ይባርካችሁ::

Fbi Church Miracle Chaple Mekanisa
#አስደሳች #ዜና ለወንጌል አማኞች #በሙሉ

#በመስቀል #አደባባይ የንስሐ፣ የምልጃና የምስጋና ፕሮግራም መዘጋጀቱ ተገለጸ።

በዛሬው እለት #የኢትዮጵያ #ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል መሪዎች በአዲስ አበባ በመስቀል አደባባይ የንስሐ፣ የምልጃና የምስጋና ፕሮግራም መዘጋጀቱን ለሚዲያዎች መግለጫ ሰጥተዋል።

በተሰበረ #ልብ፣ በንስሐ መቅረብ የመጀመሪያ ተግባራችን መሆን እንዳለበት የጠቀሱት መሪዎቹ “#ወደ ደጆቹ በመገዛት ወደ አደባባዮቹም በምስጋና ግቡ፣ አመስግኑት፣ ስሙንም ባርኩ” (መዝ 100)፤4 በሚለው ቃለ #እግዚአብሔር መሠረት መጋቢት 8 ቀን 2016 ዓ/ም ከቀኑ 7፡00 ጀምሮ #በአዲስ አበባ #መስቀል አደባባይ የንስሐ፣ የምልጃና የምስጋና በዓል ለማካሄድ አስፈላጊው ዝግጅት #ሁሉ ተጠናቋል ብለዋል።

አሁንም የእርስ በርስ መጠፋፋቱ አልቆመም ያሉት መሪዎቹ መደማመጥና መከባበር በመካከላችን እንዲኖርና ለይቅርታና ለፍቅር ልባችን የቀና እንዲሆንና ፀጋውንም እንዲያበዛልን #እግዚአብሔርን የምንማጸንበት #ጊዜ ይኖራል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በፕሮግራሙ የሚካፈለው የሕዝብ #ብዛት እጅግ ብዙ ስለሆነ ስብሰባው የሚካሄደው በመስቀል አደባባይ ነው፡፡

በመሆኑም መላው የወንጌል አማኝ በነቂስ ወጥቶ #በእግዚአብሔር ፊት የንስሐ፣ የምልጃና የምስጋና ፕሮግራሙ ተካፋይ እንዲሆን ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

The Christian News - የክርስቲያን ዜና በስፍራው ተገኝተን ዝርዝሩን አሰናዳንላችሁ።

#photo Christian tube - ክርስቲያን ቲዩብ

ዝርዝር መረጃ ምሽት ላይ በቪዲዮ ይዘንላችሁ የምንመለስ ይሆናል።
https://www.youtube.com/channel/UCeHRJCDJ0wUDaBfAFmuMa7A?sub_confirmation=1
#እግዚአብሔር ይመስገን 🙏🙏🙏

ክፉውን ነገር ተጸየፉት፤ ከበጎ ነገር ጋር ተባበሩ፤
ሮሜ 12:9

#FBI #church (ፌይዝ ባይብል ኢንተርናሽናል #ቤተክርስቲያን) በአንድ #አመት ውስጥ #በአዲስ አበባ በሁለት ክፍለ ከተሞች የአምስት አቅም የሌላቸውን ቤተሰቦች #ቤት ሰርተን አስረክበናል።

የረዳን #እግዚአብሔር የተመሰገነ ነው::
#ቤተ #በአዲስ አበባ

በሆሳዕና ለረጅም አመት እያገለገለች የምትገኘዉ ቤተምህረት #አሁን ደግሞ በአዲስ አበባ የቤተ ክርስቲያን ተከላና- የመክፈቻ ፕሮግራም ከግንቦት 21-25 / ከእሮብ እስከ ቅዳሜ ከ 10:00 ጀምሮ እሁድ ጠዋት ይከናወናል።

#አድራሻ ፦ ከቡልጋሪያ #ወደ ቄራ ሲወርዱ ስካኒያ አካባቢ የቤተ ምህረት ማስታወቂያ ባለበት 100 ሜትር ገባ ብሎ ያገኙናል።

#ቤተ ምህረት እንገናኝ 🙏🙏