The Christian News
5.37K subscribers
3.08K photos
29 videos
730 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
#news
#ማስተዋል_ተመረቀ

ማስተዋል የተሰኘውና በቦሌ አማኑኤል ቤተ ክርስቲያን ዋና መጋቢ አመሉ ጌታ የተጻፈው መጽሐፍ እሁድ ሰኔ 27/2013 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሆቴል በድምቀት ተመርቋል፡፡

የምረቃው ስነስርዓት በፓስተር ፍጹም የተመራ ሲሆን በምረቃው ላይ የቤተክርስቲያን መሪዎች፣ መጋብያን፣ ጸሐፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

የተመረጡ የመጽሐፉ ክፍሎች በተለያዩ አንባብያን በንባብ ቀርበዋል፡፡ የመጽሐፉ ዳሰሳ በፓስተር መስፍን እና በፓስተር ሳሙኤል ቀርቧል፡፡

በመጨረሻም በአንጋፋው አባት ፓስተር ጎሳ የተመራ ጸሎት ተደርጎ መጽሐፉ ተባርኳል፡፡ መጽሐፉ በ243 ገጽ የተቀነበበ ሲሆን ዋጋውም 100 ብር ብቻ ነው፡፡

ፈጣን ወቅታዊ ታማኝ ሀገርኛ እና አለማቀፍ የክርስቲያናዊ ዜናዎችን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናሌን በዚህ ሊንክ ይቀላቀሉ።
https://t.me/TCNEW
በኢንስታግራም ቤተሰብ እንሁን
https://www.instagram.com/thechristiannews1/
አዳዲስ ዜናዎች በምስል እና ድምጽ ለማግኘት የዩቲዩብ ቻናላችንን በዚህ ሊንክ ይጎብኙ እና ቤተሰብ ይሁኑ!!!
https://www.youtube.com/channel/UCeHRJCDJ0wUDaBfAFmuMa7A?sub_confirmation=1
#News
#Jps_መልካምነት

በዛሬው ዕለት ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ የእግዚአብሔር ሰው ነብይ ሔኖክ ግርማ ከJps ቤተክርስቲያን አገልጋዮች ጋር በመሆን በቡልቡላ አካባቢ የችግኝ ተከላ አካሂደናል ። ከዚያም በተጨማሪ Jps ቤተክርስቲያን የ 5 ( አምስት ) አቅመ ደካሞችን ቤት ለማደስ እና መልሶ ለማቋቋም ቃል በገባችው መሰረት ዛሬ ቤቶቹን ፈረሳ በማድረግ ግንባታው ተጀምሯል ።

ፈጣን ወቅታዊ ታማኝ ሀገርኛ እና አለማቀፍ የክርስቲያናዊ ዜናዎችን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናሌን በዚህ ሊንክ ይቀላቀሉ።
https://t.me/TCNEW
በኢንስታግራም ቤተሰብ እንሁን
https://www.instagram.com/thechristiannews1/
አዳዲስ ዜናዎች በምስል እና ድምጽ ለማግኘት የዩቲዩብ ቻናላችንን በዚህ ሊንክ ይጎብኙ እና ቤተሰብ ይሁኑ!!!
https://www.youtube.com/channel/UCeHRJCDJ0wUDaBfAFmuMa7A?sub_confirmation=1
#news

በተቀባ የእግዚአብሔር ቃል አገልግሎት ቤተክርስቲያን የስነ መለኮት ኮሌጅ ላለፉት ሶስት አመት በዲፕሎማ ሲማሩ የቆዩትን ሃያ አራት ተማሪዎችን ሐምሌ 4/11/2013 የቤተክርስቲያኗ ምዕመናን በተገኙበት አስመርቃለች፡፡

በዕለቱ መጋቢ ፃድቁ አብዶ የእግዚአብሔር ቃል በማካፈል ያገለገሉ ሲሆን መጋቢ ሚካኤል ወንድሙ ቤተክርስቲያኗ ባጀት መድባ የስነ መለኮት ኮሌጅ መክፈቷ ጥሩና ጠቃሚ ነው በማለት ተናግረዋል።

በመቀጠል የኮሌጁ የበላይ ጠባቂ በሆኑት በመጋቢ ሚካኤል ወንድሙ እና በመጋቢ ቴዎድሮስ አዲስ የዲፕሎማ ሰርተፍኬት አሰጣጥ ስርዓት የተከናወነ ሲሆን በመጋቢ ሚካኤል ወንድሙ ለምሩቃን ተማሪዎች ፀሎት ተካሂዷል::

ተመራቂ ተማሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ ፡፡

ፈጣን ወቅታዊ ታማኝ ሀገርኛ እና አለማቀፍ የክርስቲያናዊ ዜናዎችን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናሌን በዚህ ሊንክ ይቀላቀሉ።
https://t.me/TCNEW
በኢንስታግራም ቤተሰብ እንሁን
https://www.instagram.com/thechristiannews1/
አዳዲስ ዜናዎች በምስል እና ድምጽ ለማግኘት የዩቲዩብ ቻናላችንን በዚህ ሊንክ ይጎብኙ እና ቤተሰብ ይሁኑ!!!
https://www.youtube.com/channel/UCeHRJCDJ0wUDaBfAFmuMa7A?sub_confirmation=1
#NEWS
የሃይማኖት አባቶች በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ ውይይት አደረጉ።
በውይይት መድረኩም ባለ 11 ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥተዋል።

የአዲስ አበባ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ “ወቅታዊ የሃገራችን አሁናዊ የከተማችን ሁኔታ እና ቀጣይ አቅጣጫ” በሚል ርዕስ ከተቋሙ መስራች አባል ቤተእምነቶች ከተወጣጡ የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች ጋር ውይይት አካሂደ፡፡

በውይይት መድረኩ ላይ ተገኝተው መልእክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ክብርት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ሀገራችን አሁን የገጠማት ፈተና በአይነቱ ውስብስብ ቢሆንም ለዘመናት በብዙ ፈተና ውስጥ አልፋ እዚህ የደረሰች ጠንካራ ሀገር እንደመሆንዋ ክብሯን ለማስቀጠል የሁላችንንም ሀላፊነት እንደሚጠይቅ ተናግረዋል፡፡
ክብርት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ አክለው እንደገለጹት የሀይማኖት ተቋማት በየቤተ እምነቶቻቸው ስለሀገራችን ሰላምና አብሮነት በመስበክ ፥ በስነምግባርና በሰላም እሴት ግንባታ ላይ እያደረጉ ያሉትን አስተዋጽኦ ይበልጥ አጠናክረው በማስቀጠል ሀላፊነታቸውን እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል::

የከተማችንን ሰላም አስተማማኝ ለማድረግ የከተማችን ነዋሪዎች እና የሃይማኖት ተቋማት እያደረጉ ያሉት ትብብር እጅግ የሚያስደስት ነው አሁንም ሳንዘናጋ አጠናክረን ማስቀጠል ይገባል ያሉት ደግሞ የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ጸሐፊ መጋቢ ታምራት አበጋዝ ናቸው።

በዛሬው እለት በነበረው ውይይት የአዲስ አበባ ከተማ የሰላም እና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ቢሮ ሃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የውይይት መነሻ ሃሳብ ያቀረቡ ሲሆን መሪዎቹም በመነሻ ሃሳቡ ዙሪያ ሰፋ ያለ ውይይት አድርገዋል።

በውይይቱ ላይ የተሳተፉት የሀይማኖት አባቶችም በሀገራችን ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን፤ የመቻቻልና የመከባበር እሴቶች እንዲጎለብቱ በየቤተ እምነቶቻቸው በማስተማር የጀመሩትን ስራ አጠናክረው በማስቀጠል ሀገራዊ አንድነትን በሚያጠናክሩና ለነገዋ ኢትዮጵያ ራእይ ያለው ትውልድ ለማነጽ በትኩረት እንደሚሰሩም ተናግረዋል።

በመረሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ የሰላም እና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ ክቡር ዶክተር ቀነዓ ያደታ በበኩላቸው ተሳታፊዎች ላነሱት የተለያዩ ጉዳዮች ምላሽ እና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በነበረው የውይይት መድረክ ከሁሉም ክ/ከተማ የተወጣጡ ቁጥራቸው 500 የሚደርሱ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አባላት የተሳተፉ ሲሆን የሃይማኖት ተቋማት በዚህ ሰዓት ስለ ሀገራችን እና ከተማችን ሰላም በየቤተእምነታቸው እንዲጸልዩ እና ተፈናቅለው በተለያዩ አከባቢዎች ለሚገኙ ወገኖች ድጋፍ እንዲያደርጉም ጥሪ ቀርቧል።

በመጨረሻም የጉባኤው ተሳታፊዎች ባለ 11 ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥተው የውይይት መድረኩ ተጠናቋል።

ህዳር 16 ቀን 2014 ዓ/ም
አዲስ አበባ
መካነ ኢየሱስ 23 አገልጋዮችን አቀሰሰች።

የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ በደቡብ ኢትዮጵያ ሲኖዶስ ለቃሉና የቅዱሳት ሚስጥራት አገልግሎት 23 አገልጋዮችን በምዕራብ ጉጂ፣ ቡሌ ሆራ ከተማ አቀስሳለች።

ከአገልግሎት ስምሪታቸውም ቀን አስቀድሞ “በመጋቢት አገልግሎት” አርዕስት ላይ ሰፊ ስልጠና ለአገልጋዮቹና ለትዳር አጋሮቻቸው ከግንቦት 2-5, 2015 ለአራት ተከታታይ ቀናት በቤተክርስቲያንቱ ምክትል ፕሬዚዳንት ተሰጦቷቸዋል።

አገልጋዮቹን የማቀሰስ መርሃግብር ሲኖዶሱ ባዘጋጀው የምስጋና ኮንፍረንስ በሶስተኛ ቀን ላይ የተከናወነ ሲሆን በእለቱም ለአለም አቀፍ የወንጌል አገልግሎት ከፍተኛ ድጋፍ ላደረጉ ሰበካዎች እውቅና ተሰጥቷል ።

#Ethiopia #AddisAbaba
#news #ኢትዮጵያ #ኢየሱስ
#new #ክርስቲያን #ዜና
#አሁን

የመካነ ኢየሱስ ሴሚናሪ የሙዚቃ እና ሚዲያ ት/ቤት ኦዲዮ እና ቪዥዋል ስቱዲዮ የመክፈቻ መሰናዶ እየተከናወነ ነዉ።

#Ethiopia #ኢትዮጵያ
#AddisAbaba #ኢየሱስ
#news #new #ክርስቲያን
#ዜና #መረጃ
#እንዝፈን ወይስ #እንዘምር?

ከዘፈኑ ዓለም ወደ ክርስቶስ ከመጡ ከነ ሙሉቀን መለሰ ፤ ሒሩት በቀለ ፤ አብተው ከበደ ፤ ጥበቡ ወርቅዬ ምስክርነት ያየነውና የሰማነው ጌታን አውቀው ከዘፋኝነት ሙያና አብሮት ካለው ገፈትና ግሳንግስ ጋር ተጣብቀው መቆየት አለመቻላቸውን ነው።

ጥበቡ ወርቅዬ ከምስክርነቱ እንደሰማሁት ወደ ዘፈን የሚመልሰውን ድልድይ ሰብሮ ነበር የተሻገረው።

ከዘፈን ወጥመድ ወጥተው ወደጌታ የመጡ እንደኖሩ ሁሉ ከቤተክርስቲያን ኮብልለው የጠፉ ዘፋኞች ሊኖሩ ይችላሉ። በዚህ ዘመን ዘፋኞች ወደ ክርስቶስ ሲመጡ ዘማሪዎች ደግሞ ወደ ዓለመኛ የዘፈን ሙያ ሲሄዱ ተስተውሏል።

ይህ የሙያ ቅይይር ብቻ ተደርጎ ከተወሰደ ስህተት ነው። ይህ የማንነት ልውውጥ እንጂ የሙያ ዝውውር አይደለም። አንድ ክርስቲያን ወደ ዘፈንና ዘፋኝነት ሲሄድ ስረዓተ እሴቱን ንቆ ነው። ያ ስረዓተ እሴት ደግሞ መሰረቱ ቅሉ ነውና ቃሉንና በውስጡ የተጻፈውን ዋና እውነት ጥሎና ረግጦ መሄድ ነው።

@Zelalem Mengistu #እንዝፈን ወይስ #እንዘምር? ዘፈናምነትና ቤተክርስቲያን ከተሰኘው መጽሃፍ ከተወሰኑ ገጾች ተቀንጭቦ የተወሰደ ሃሳብ ነው።

ዝማሬ ችሎታ ለሚመስላቸው ሰዎች ግን መዝሙር ከአምላክ የሚሰጥ ስጦታ እንደሆነ የሳሚን መዝሙር እና ዘፈኑን ያዳመጠ በትክክል መለየት ይችላል።

“ስለዚህ እንደ ቆመ የሚመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ።”
( 1ኛ ቆሮንቶስ 10፥12 )

አሁንም ልባችን ሳይዝል እንጸልይለት።

#Ethiopia #AddisAbaba
#ኢየሱስ #ኢትዮጵያ
#news #new
#ክርስቲያን #ዜና
#መረጃ
#ድንቅ #ስራ
#Fbi_Church_good #news አጥቢያ በቦሌ ክፍለ ከተማ በወረዳ 6 የአንዲት እናታችንን ቤት አፍርሳ #ሙሉ በሙሉ #በአዲስ መልክ ለማስረከብ የማስጀመሪያ ፕሮግራም አድርጋለች::

ይህ መልካም ስራ ነው ተባረኩ
#NewsUpdate

#ማሳሰቢያ

ከትላንት በስቲያ በቀድሞው አጎና ሲኒማ ህንጻ ላይ በደረሰው የእሳት አደጋ የተለያዩ ተቋማት ንብረቶች መዉደማቸዉ ይታወሳል።

#ይህንን #ዜና በማስመልከት The Christian News - የክርስቲያን ዜና የሕይወት ምንጭ ኢየሱስ ዓለም አቀፍ ቤ/ክ በሚል መጠርያ የምትጠራዉ ቤተክርስቲያን በአደጋዉ ጉዳት እንደደረሰባት የአዲስ አበባ የእሳት እና ድንገተኛ አደጋ ኮሚሽን መረጃን ዋቢ በማድረግ የተዘገቡ ከተለያዩ የግል ሚዲያ ያገኘነዉን #መረጃ ማሰራጨታችን ይታወሳል።

ሆኖም የቤተክርስቲያን መሪዎች በአጎና ሲኒማ ህንጻ በሚገኘው አዳራሽ አምልኮ ካቆሙ #አንድ አመት ያለፋቸዉን መሆኑን ጠቅሰዉ መረጃዉ የተሳሳተ እንደሆነ ገልፀዋል።

በዘገባዉ በቴሌቪዥን ስቲዲዮዉ ለድምጽ መከላከያ ተብሎ በህንጻዉ ግድግዳ ላይ የተገነባዉ እስፖንጅና በቤተክርስቲያኑ ውስጥ የነበረው በርካታ የፕላስቲክ ወንበሮች ለቃጠሎዉ መስፋፋት አስተዋጾኦ እንዳደረጉ የተቋሙ ኮሙኒኬሽን አቶ ንጋቱ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን መናገራቸው ተካቷል።

የቤተክርስቲያኒቱ መሪዎች በበኩላቸው ወንበሮቹ የራሱ የህንፃው ባለቤቶች የመሰብሰቢያ አዳራሽ ንብረት እንደሆነ ተናግረዋል።

አደጋዉን በተመለከተ በዘገባዉ ጎልቶ የወጣዉ የሌላ ተቋማት ጉዳት ስለነበር በዚህ ዉስጥ ቤተክርስቲያን ጉዳት ደርሶባት ከነበር እንደ ክርስቲያን ሃላፊነታችንን ለመወጣት በሚል ዘገባዉን አሰራጭተናል።

በተሰራጨዉ የተሳሳተ ዘገባ #The #christian #news ይቅርታ እየጠየቅን ዘገባዉን ከገፃችን ማንሳታችንን እናሳዉቃለን።
#የትግራይ የሀይማኖት አባቶች ፖለቲከኞች ልዩነቶችን ከማባባስ እንዲቆጠቡ አሳሰቡ።

አባቶቹ አክለዉ አለመግባባቶችን ለመፍታት #ውይይት እንዲደረግ ጠይቀዋል።

የትግራይ #ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ #ቤተክርስቲያን የሀይማኖት አባቶች የህዝባዊ ወያነ ሐርነት ትግራይ (#ህወሓት) አመራሮች #እና የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ልዩነታቸውን ሊያባብሱ ከሚችሉ መግለጫዎች እንዲቆጠቡ ጠይቀዋል።

በትላንትናዉ #እለት በሰጡት መግለጫ፣ በተለይም በክልሉ ወቅታዊ ፈተናዎች #ውስጥ የፖለቲካ ልዩነቶችን በውይይት መፍታት አስፈላጊ መሆኑን አሳስበዋል ሲል #አዲስ እስታንዳርድ አስነብበዋል።

"አባቶቹ ጥሪውን ያቀረቡት የአሜሪካው አምባሳደር ሁለቱንም ቡድኖች በመቀሌ ካነጋገሩ በኋላ ነው"

#Ethiopia #addisababa #news #NewsUpdate #BREAKING #BreakingNews