The Christian News
5.37K subscribers
3.08K photos
29 videos
730 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
#NewsUpdate

#ማሳሰቢያ

ከትላንት በስቲያ በቀድሞው አጎና ሲኒማ ህንጻ ላይ በደረሰው የእሳት አደጋ የተለያዩ ተቋማት ንብረቶች መዉደማቸዉ ይታወሳል።

#ይህንን #ዜና በማስመልከት The Christian News - የክርስቲያን ዜና የሕይወት ምንጭ ኢየሱስ ዓለም አቀፍ ቤ/ክ በሚል መጠርያ የምትጠራዉ ቤተክርስቲያን በአደጋዉ ጉዳት እንደደረሰባት የአዲስ አበባ የእሳት እና ድንገተኛ አደጋ ኮሚሽን መረጃን ዋቢ በማድረግ የተዘገቡ ከተለያዩ የግል ሚዲያ ያገኘነዉን #መረጃ ማሰራጨታችን ይታወሳል።

ሆኖም የቤተክርስቲያን መሪዎች በአጎና ሲኒማ ህንጻ በሚገኘው አዳራሽ አምልኮ ካቆሙ #አንድ አመት ያለፋቸዉን መሆኑን ጠቅሰዉ መረጃዉ የተሳሳተ እንደሆነ ገልፀዋል።

በዘገባዉ በቴሌቪዥን ስቲዲዮዉ ለድምጽ መከላከያ ተብሎ በህንጻዉ ግድግዳ ላይ የተገነባዉ እስፖንጅና በቤተክርስቲያኑ ውስጥ የነበረው በርካታ የፕላስቲክ ወንበሮች ለቃጠሎዉ መስፋፋት አስተዋጾኦ እንዳደረጉ የተቋሙ ኮሙኒኬሽን አቶ ንጋቱ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን መናገራቸው ተካቷል።

የቤተክርስቲያኒቱ መሪዎች በበኩላቸው ወንበሮቹ የራሱ የህንፃው ባለቤቶች የመሰብሰቢያ አዳራሽ ንብረት እንደሆነ ተናግረዋል።

አደጋዉን በተመለከተ በዘገባዉ ጎልቶ የወጣዉ የሌላ ተቋማት ጉዳት ስለነበር በዚህ ዉስጥ ቤተክርስቲያን ጉዳት ደርሶባት ከነበር እንደ ክርስቲያን ሃላፊነታችንን ለመወጣት በሚል ዘገባዉን አሰራጭተናል።

በተሰራጨዉ የተሳሳተ ዘገባ #The #christian #news ይቅርታ እየጠየቅን ዘገባዉን ከገፃችን ማንሳታችንን እናሳዉቃለን።
#የትግራይ የሀይማኖት አባቶች ፖለቲከኞች ልዩነቶችን ከማባባስ እንዲቆጠቡ አሳሰቡ።

አባቶቹ አክለዉ አለመግባባቶችን ለመፍታት #ውይይት እንዲደረግ ጠይቀዋል።

የትግራይ #ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ #ቤተክርስቲያን የሀይማኖት አባቶች የህዝባዊ ወያነ ሐርነት ትግራይ (#ህወሓት) አመራሮች #እና የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ልዩነታቸውን ሊያባብሱ ከሚችሉ መግለጫዎች እንዲቆጠቡ ጠይቀዋል።

በትላንትናዉ #እለት በሰጡት መግለጫ፣ በተለይም በክልሉ ወቅታዊ ፈተናዎች #ውስጥ የፖለቲካ ልዩነቶችን በውይይት መፍታት አስፈላጊ መሆኑን አሳስበዋል ሲል #አዲስ እስታንዳርድ አስነብበዋል።

"አባቶቹ ጥሪውን ያቀረቡት የአሜሪካው አምባሳደር ሁለቱንም ቡድኖች በመቀሌ ካነጋገሩ በኋላ ነው"

#Ethiopia #addisababa #news #NewsUpdate #BREAKING #BreakingNews