The Christian News
5.32K subscribers
3.06K photos
27 videos
720 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
#Breaking_news

የመሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አዲስ ፕሬዝዳንት መረጠች።

በዛሬው እለት በዋና ጽ/ቤት አዲስ የተመረጡት ፕሬዝዳንትን አቀባበል የማድረግ እና የቀድሞ ፕሬዝዳንትን የመሸኘት መሰናዶ ተከናውኗል።

በዚህም መሰረት ቤተክርቲያኒቷን ለ5ዓመታት የመሯት ወንድም ቴዎድሮስ በየነ ተሸኝተው አቶ ደሳለኝ አበበን ደግሞ እንኳን ደህና መጣቹ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

የመሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የተመሰረተችው በ1943ዓ.ም ሲሆን ከጋሽ ሚሊዮን በለጠ ጀምሮ ላለፉት 76ዓመታት በርካታ መሪዎች መርተዋታል።

ለቀድሞ መሪዋ አቶ ቴዎድሮስ ምስጋና በማቅረብ ለአቶ ደሳለኝ ደግሞ መልካም የአገልግሎት ዘመን እንዲሆንላቸው መልካም ምኞታችን ነው።
#Breaking_news

የመጽሀፍ ቅዱስ ማህበር በ56 ሚሊዮን ብር ያስገነባውን ህንጻ አስመረቀ።

በዛሬው እለት የመጽሀፍ ቅዱስ ማህበር የተለያዩ የአብያተ ክርስቲያናት መሪዎች እና ከመላው አለም የመጡ አጋር የመጽሀፍ ቅዱስ ማህበር መሪዎች በተገኙበት አዲሱን ሁለገብ ህንጻ አስመርቋል።

በምርቃቱ ስነ-ስረዓት ላይ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ከኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን እና ከኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት የተመከሉ አመራሮች ተገኝተዋል።

በሌላ በኩል ከተባበሩት መጽሀፍ ቅዱስ ማህበር ከእንግሊዝ መጽሀፍ ቅዱስ ማህበር ከአሜሪካ መጽሀፍ ቅዱስ ማህበርን ጨምሮ በርካታ አለም አቀፍ አጋር ማህበራት መሪዎች ተገኝተው መርቀውታል።
#Breaking_News

የአዲስ ኪዳን ካህናት ቤተክርስቲያን አገልጋይ እና የማር ሲል ቴሌቪዥን ዋና ስራ አስፈጻሚ አገልጋይ ዮናታን አክሊሉ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ወደ እስራኤል ተጓዘ።

አገልጋይ ዮናታን አክሊሉ ለመልካም ወጣት የስብዕና ማዕከል የስራ ጉብኝት ከትናንት በስቲያ ቅዳሜ ወደ እስራኤል አቅንቷል፡፡

ይህም ጉብኝት ባሳለፍነው ጥቅምት ወር መጀመሪያ በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር የሆኑት ራፋኤል ሞራቪያ በአዲስ አበባ ማርሲል ቴሌቪዥን ጽህፈት ቤት በመገኘት አገልጋይ ዮናታን አክሊሉ በሀገሪቱ በወጣቶች የስብዕና ግንባታ ላይ እየሰራ ያለውን ስራ አድንቀው መንግስታቸው በዚሁ ተግባር በቀጣይነት አብሮ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን ገልጸው እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡

አያይዘውም በሀገረ እስራኤል ተገኝተው ይህንን እና መሰል በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ እንዲጎበኙ በጋበዟቸው መሰረት ነው አገልጋይ ዮናታን አክሊሉ ወደ እስራኤል ያቀናው፡፡

አገልጋይ ዮናታን አክሊሉ በእስራኤል በሚኖረው ቆይታም በሀገሪቱ የሚገኙ ልዩ ልዩ የሱስ ማገገሚያ ማዕከሎችን ይጎበኛል፣ የልምድ ልውውጥም ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ከዚህ ባለፈም ከእስራኤል የመንግስት ባለስልጣናት ጋር በመልካም ወጣት ፕሮጀክትና በሌሎች መሰል ጉዳዮች ዙሪያ ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል።

https://www.youtube.com/channel/UCeHRJCDJ0wUDaBfAFmuMa7A?sub_confirmation=1
#Breaking_Christian_NEWS

አዲሱ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል መቋቋሙን በተመለከተ ለሚዲያዎች በሸራተን ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ እየሰጠ ነው።

መግለጫው በዋናነት የካውንስሉ መመስረት አስፈላጊነት እና ባለፉት 9 ወራት የተሰሩትን ስራዎች የሚጠቅስ ነው።

የወንጌላውያን አማኞች በእምነታቸው ምክንያት ከመነሻው ጀምሮ ይደርስባቸው የነበረውን እንግልት የሚጠቅሰው መግለጫ አዲሱ ካውንስል በህግ ማዕቀፍ እንደ ዜጋ የተቀመጠላቸው መብት እንዲጠቀሙ ይረዳቸዋል ተብሏል።

የምክረ ሀሳብ አቅራቢው ኮሚቴ ይህንን ተግባር ሲያከናውን አስፈላጊውን ድጋፍ ላደረጉለት ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር አብይ አህመድ ምስጋና አቅርበዋል።

የዜናውን ሙሉ ሀሳብ ምሽት ላይ በዮቱብ ቻናላችን ላይ እናደርሳችኋለን።

https://www.youtube.com/channel/UCeHRJCDJ0wUDaBfAFmuMa7A?sub_confirmation=1
#Breaking_Christian_NEWS

በሃገሪቱ የተከሰተውን የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል ህዝበ ክርስቲያኑ እና ምእመኑ በጸሎት ቦታዎች ቁጥሩን ሊቀንስ እና የጤና ባለሙያዎችን ትዕዛዝ ሊተገብር እንደሚገባም የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጥሪ አቀረበ።

https://www.youtube.com/channel/UCeHRJCDJ0wUDaBfAFmuMa7A?sub_confirmation=1

https://t.me/TCNEW
#Breaking_News
#ሰበር_መረጃ
The Christian News - የክርስቲያን ዜና

#ካውንስሉ_አዲስ_ፕሬዝደንት_እየመረጠ_ነው

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል 1ኛ መደበኛ ስብሰባ ጠቅላላ ጉባኤውን ዛሬ ጥቅምት 26 ቀን 2014 ዓ.ም በመካነ ኢየሱስ ሴሚናሪየም ግቢ ውስጥ እየተካሄደ ይገኛል።

በጠቅላላ ጉባኤው አዲስ ፕሬዝደንት ምክትል ፕሬዝደንት እና ጠቅላይ ጸሐፊ ይመረጣል ተብሎ ይጠበቃል።

በሌላ በኩል 2 አዳዲስ ህብረቶች ካውንስሉን ይቀላቀላሉ ተብሎ ይጠበቃል። ዝርዝሩን እየተከታተልን የምናደርሳችሁ ይሆናል።

ፎቶ ምንጭ @Council_Media
#Breaking_News
The Christian News - የክርስቲያን ዜና
#ቄስ_ደረጀ_ተመርጠዋል

የቀድሞ የካውንስሉ ጠቅላይ ጸሐፊ ቄስ ደረጀ ጀምበሩ በተሰበሰበው ድምጽ መሰረት ከ232 መራጮች 224 ከፍተኛ ድምፅ በማግኘት የካውንስሉ ጠቅላይ ጸሐፊ ሆነው ለቀጣይ 5ዓመት እንዲቀጥሉ ተወስኗል።

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል በመካነ ኢየሱስ ሴሚናሪ እያደረገ ባለው 1ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አዳዲስ መሪዎችን እየመረጠ ነው።

ቀጣዩ የካውንስሉ ፕሬዝደንት እና ም/ፕሬዝደንት የሚሆኑት ምርጫ እየተከናወነ ነው።
#Breaking_News
#ሰበር_መረጃ
The Christian News - የክርስቲያን ዜና
#የካውንስሉ_አዲስ_ፕሬዝደንት_ዶክተር_ጣሰው_ገብሬ_ሆነው_ተመርጠዋል
#ዶክተር_ቤተመንግስቱ_የካውንስሉ_ምክትል_ፕሬዝደንት_ሆነው_ተሹመዋል

የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ም/ፕሬዝደንት ዶ/ር ጣሰው ገብሬ በተሰበሰበው ድምጽ መሰረት ከ232 መራጮች 225 ከፍተኛ ድምፅ በማግኘት የካውንስሉ አዲስ ፕሬዝደንት ሆነው ተመርጠዋል።
የፍቅር አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ፕሬዝደንት እና የቤዛ አለም አቀፍ ቤተክርስቲያን መስራች እና አገልጋይ ዶ/ር ቤተመንግስቱ ደግሞ ቀጣይ የካውንስሉ ም/ፕሬዝዳንት በመሆን ተመርጠዋል።
#Breaking_NEWS
#ሰበር_መረጃ
The Christian News - የክርስቲያን ዜና

ዶ/ር ጣሰው ገብሬ የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ።

በወላይታ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን እየተደረገ የሚገኘው የቤተክርስቲያኒቱ 61ኛው ጠቅላላ ጉባዔ ላይ በተደረገው የመሪዎች ምርጫ የቀድሞ የቃለ ህይወት ቤተክርስቲያን ም/ፕሬዝደንት የነበሩት ዶ/ር ጣሰው ገብሬ በፕሬዝዳንትነት ቀጣይ የስራ ጊዜያትን እንዲያገለግሉ ተመርጠዋል።

በአሁኑ ሰዓት ም/ፕሬዝደንት እና ም/ዋና ጸሐፊ ምርጫ እየተከናወነ ይገኛል።
#የትግራይ የሀይማኖት አባቶች ፖለቲከኞች ልዩነቶችን ከማባባስ እንዲቆጠቡ አሳሰቡ።

አባቶቹ አክለዉ አለመግባባቶችን ለመፍታት #ውይይት እንዲደረግ ጠይቀዋል።

የትግራይ #ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ #ቤተክርስቲያን የሀይማኖት አባቶች የህዝባዊ ወያነ ሐርነት ትግራይ (#ህወሓት) አመራሮች #እና የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ልዩነታቸውን ሊያባብሱ ከሚችሉ መግለጫዎች እንዲቆጠቡ ጠይቀዋል።

በትላንትናዉ #እለት በሰጡት መግለጫ፣ በተለይም በክልሉ ወቅታዊ ፈተናዎች #ውስጥ የፖለቲካ ልዩነቶችን በውይይት መፍታት አስፈላጊ መሆኑን አሳስበዋል ሲል #አዲስ እስታንዳርድ አስነብበዋል።

"አባቶቹ ጥሪውን ያቀረቡት የአሜሪካው አምባሳደር ሁለቱንም ቡድኖች በመቀሌ ካነጋገሩ በኋላ ነው"

#Ethiopia #addisababa #news #NewsUpdate #BREAKING #BreakingNews