The Christian News
5.37K subscribers
3.08K photos
29 videos
730 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
#ሰበር_መረጃ
#ህብረቱ_አስቸኳይ_መግለጫ_እየሰጠ_ነዉ

#ህብረቱ_በመግለጫዉ_በካዉንስሉ_አዳዲስ_አመራሮች_ዙሪያ_ያለዉን_ቅሬታ_አቅርቧል

በተጨማሪም ከካዉንስሉ ጋር ያለንን ግንኙነት እንዳቋረጥን እንዲታወቅልን እንፈልጋለን ብለዋል።

በተደጋጋሚ ልንነጋገር ብንሞክርም ምላሽ እና ማስተካከያ ማግኘት አልቻልንም ያሉት አመራሮች አካሄዳቸዉ በአንጋፋው የወንጌላዉያን አብያተ ክእስቲያናት ህብረት ላይ ተፅዕኖ ያደረገ እና የተሳሳተ አካሄድ እንደሆነ ተናግረዋል።

መግለጫቸውን እየሰጡ የሚገኙት የኢትዮጵያ ሙሉወንጌል ፣ የኢትዮጵያ ህይወት ብረሃን፣ መሰረተክርስቶስ እና ገነት ቤተክርስቲያን አመራሮች ናቸዉ።

ተጨማሪዉን ሙሉ ዝርዝሩን መረጃ ምሽት ላይ በቪዲዬ ይዘን የምንመለስ ይሆናል።

አዳዲስ እና ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስቲያን ዜና እንዲደርሳችሁ የቴሌግራም ገፃችንን ይቀላቀሉ።

https://t.me/TCNEW
#Breaking_NEWS
#ሰበር_መረጃ
The Christian News - የክርስቲያን ዜና

ዶ/ር ጣሰው ገብሬ የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ።

በወላይታ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን እየተደረገ የሚገኘው የቤተክርስቲያኒቱ 61ኛው ጠቅላላ ጉባዔ ላይ በተደረገው የመሪዎች ምርጫ የቀድሞ የቃለ ህይወት ቤተክርስቲያን ም/ፕሬዝደንት የነበሩት ዶ/ር ጣሰው ገብሬ በፕሬዝዳንትነት ቀጣይ የስራ ጊዜያትን እንዲያገለግሉ ተመርጠዋል።

በአሁኑ ሰዓት ም/ፕሬዝደንት እና ም/ዋና ጸሐፊ ምርጫ እየተከናወነ ይገኛል።
#ሰበር_መረጃ
@The Christian News

ከደቂቃዎች በፊት በ61ኛው የቃለሕይወት ቤተክርስቲያን ጠቅላላ ጉባዔ ላይ

ዶ/ር ጣሰው ገብሬ ፕሬዘዳንት
ዶ/ር ስምዖን ሄሊሶ ም/ፕሬዘዳንት
ዶ/ር ኤርሚያስ ማሞ ም/ዋና ጸሐፊ ሆነው እንዲያገለግሉ ተመርጠዋል።

ጉባኤው ለመጪዎቹ ሦስት ዓመታት ቤተ ክርስቲያኒቱን የሚመሩ የቦርድ እና የሥራ እአስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትንም መርጧል።

ምንጭ @EKHC Communication
#ሰበር_መረጃ
The Christian News - የክርስቲያን ዜና

#የመካነኢየሱስ_ዋና_ፅህፈት_ቤት_አስቸኳይ_መግለጫ_እየሰጠች_ነዉ

በትላንትናዉ እለት በቤተክርስቲያናችን የደረሰዉ አደጋን በተመለከተ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ልታወግዝ ይገባል።

ቄሶቻችን እና ምዕመኖቻችን ለተጨማሪ አደጋ እንዳይጋለጡ እስካሁን ወደቤታቸዉ አልገቡም ተደብቀዉ ይገኛሉ።

በሰቃ ማህበረ ምዕመናን በስፍራዉ ከ20 ዓመት በላይ ያገለገለች ቤተክርስቲያን ነች።

የክርስቲያን ዜና በስፍራዉ ተገኝተን መረጃዉን እየተከታተልን ሲሆን ከደቂቃዎች በኋላ ሙሉ ዝርዝሩን ይዘን እንመለሳለን።

አዳዲስ እና ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስቲያን ዜና እንዲደርሳችሁ የቴሌግራም ገፃችንን ይቀላቀሉ።

https://t.me/TCNEW
#ሰበር_መረጃ
The Christian News - የክርስቲያን ዜና

የተሐድሶ አለማቀፋዊ አብያተክርስቲያናት ሕብረት ጋዜጣዊ መግለጫ እየሰጠ ነዉ።

መግለጫዉ ባለ 13 ነጥብ የያዘ ሲሆን በዋናነት ከካዉንስሉ ጋር ስላላቸዉ ግንኙነት ያተኮረ ነዉ።

በዚህም መግለጫ ካዉንስሉ ሊያስተካክላዉ እና ሊያርማቸዉ ይገባል ያሏቸዉን ነጥቦች የጠቀሱ ሲሆን ጉዳዩ መፈታት የማይችል ከሆነ ወደሚመለከተዉ አካል እንደሚሄድ ተናግረዋል።

በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን ቤተል ተመሳሳይነት ያለዉ መግለጫ እየሰጠች ነዉ።

በዚህም ላለፉት 3 ዓመታት ያቀረብነዉ ጥያቄ ሊመለስልን አልቻለም ብለዋል።

ሙሉ የመግለጫዉን ሃሳብ The Christian News - የክርስቲያን ዜና Group በስፍራዉ ተገኝተን እየተከታተልን ሲሆን ከደቂቃዎች በኋላ ሙሉውን ሃሳብ ይዘን የምንመለስ ይሆናል።
#ሰበር_መረጃ

መጋቢ ጻዲቁ አብዶ እውቅና ተሰጣቸው።

የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ሕብረት ፕሬዝደንት መጋቢ ጻዲቁ አብዶ በቀጠና ሁለት ሙሉ ወንጌል በነበረው እውቅና የመስጠት ፕሮግራም ላይ ለኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን በተለይም ምዕመናንን ከስህተት ትምህርት በመጠበቅ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ልዩ ተሸላሚ አድርጓቸዋል።

መጋቢ ጻዲቁ አብዱ ከልጅነት እስካሁን ድረስ ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን ውስጥ በተለያዩ የሃገራችን ክፍሎች እውነተኛውን ትምህርት በማስተማር ለአገልጋዮች በስደት ውስጥ እና በመከራ ውስጥ ጸንተው በረሃብ በእጦት ሳይሸነፉ ምሳሌ በመሆን ሲያገለግሉ የነበሩ እና የኖሩ።

መጋቢ ጻዲቁ በእስር ቤት ስለ ወንጌል በመታሰር የልጅነታቸውን ጊዜ ዋጋ የከፈሉ ላለፉት አስርት አመታት በተለያዩ ሃላፊነቶች በአጥቢያ ፤ በቀድሞ ቀጠና ፤ በቤተዕምነት ደረጃ ብሎ በአብያተክርስቲያናት በተለያዩ ሃላፊነቶች ያገለገሉ ግልጽ አስተምህሮ እና አመራር በመስጠት በምሳሌነት የሚታወቁ ናቸው።

ማዕከላዊ ክልልም ያለፉትን ጊዚያት በማሰብ ልዩ የክብር ተሸላሚ እና እውቅና የሚሰጣቸው ሰው አድርጎ በመምረጥ ሸልሟቸዋል።
#ሰበር_መረጃ!!!!

የአባታችን የቄስ በልና ሳርካ ሽኝትና የቀብር ስነ ስርአት ቀደም ሲል በተገለጸው መሰረት የፊታችን ሰኞ ከአምስት ሰአት ጀምሮ የሚከናወን ይሆናል።

በስርአተ ቅዳሴ የሚከናወነው አገልግሎት በእንጦጦ መካነ አኢየሱስ ማህበረ ምእመናን መሆኑ እንዳለ ሆኖ በቤተ ክርስቲያን የሚደረገው አገልግሎት እንዳበቃ ሌሎች ፕሮግራሞች ሁሉ በወዳጅነት ፓርክ (Friendship Park) የሚከናወኑ መሆኑን እንገልጻለን።

የስርአቱ ዝርዝርና የአፈጻጸም ቅደም ተከተል የጊዜ ሰሌዳን ጨምሮ በነገው እለት ለህዝብ ይፋ ይደረጋል።