The Christian News
5.37K subscribers
3.08K photos
29 videos
730 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
#Christian_NEWS

#ሌላ_አስቸኳይ_የጾም_ጸሎት_ጥሪ
በሀገራችን ኢትዮጵያ ከተፈጠረው የኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ የተነሳ ለህዝብ ጥንቃቄ ሲባል ሰብሰባዎችን እንዳያደርጉ መወሰኑ ይታወቃል።
በዚህ አግባብ መጠንቀቅ አለማመን አለመሆኑ ግምት ውስጥ ገብቶ ለሚቀጥለው ሁለት ሳምንታት የእሁድ አምልኮ ባይኖር፤ ኮንፍራንስ፤ ስልጠናዎችና፤ ሰብሰባዎች በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ እንዳይካሄዱ ስትል መልዕክት አስተላልፋለች።
በተጨማሪም የመጽሀፍ ቅዱስ ጥናትን በተመለከተ ከ15 ያልበለጡ አባላት ከሆኑ እና የሚጠናበት ቤት ባለቤቶች ፈቃደኝነታቸው ተጣርቶ ከበቂ ጥንቃቄ ጋር እንዲደረግ አሳስባለች።
በመጨረሻም የቤተክርስቲያኒቱ አባላት በሙሉ ከመጋቢት 11-13 ቀን 2012 ዓ.ም ሁሉም በያሉበት በጾም እና በጸሎት ሰለዚህ ወረርሺኝ ጉዳይ ወደ እግዚያብሄር እንድንጸልይ በጌታ ፍቅር አሳስባለች።
https://t.me/TCNEW
#ሌላ_መልካም_ዜና
#ደማቅ_ሕይወት
#ዘማሪ_መሉነህ_ጩፋሞ_ትላንትና ከቤተሰቦቹ ጋር እርቁን በሰላም ጨርሰዋል ስትፀልዩ የነበራቹ ቅዱሳን እንኳን ደስ አላቹ🙏🙏🙏
#ሌላ_መረጃ
#የቤተክርስቲያን_መሪዎች_ድምጻቸውን_ማሰማት_ቀጥለዋል
#ሁላችንም_Share_Share_Share_Share_Share_እናድርግ
#ካውንስሉ_የጋራ_ድምጽ_ነው!!!
#በካቢኔ_የተፈቀደልን_20ሺህ_ካ.ሜ
#የተወረሱ_የቤተእምነት_የጸሎት_ቦታዎች_ይመለስልን!!!

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ሁላችንንም የሚወክል ጥላ ነው። ሁላችንም ከካውንስሉ ጎን ልንቆም እና ልንደግፍ ይገባል። ኢትዮጵያ ውስጥ የምትገኙ ሁላችሁም አንድ ሆነን የእግዚያብሄርን ስራ እየሰራን መብታችንን እናስከብራለን ግዴታችንንም እንወጣለን!!!

መጋቢ እሸቱ ወርቄ
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስተ ክርስቲያናት ካውንስል የቦርድ አባል እና የኢትዮጵያ ፔንቴኮስታል አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ፕሬዝደንት

ጊዜ ይወስድብናል እንጂ ይሄንን ነገር ከማግኘት አንጻር ምንም የሚያጠራጥረን ነገር የለም። ካውንስሉ በሀገር አቀፍ ብቻ ሳይሆን በአለም አቀፍ ይወክለናል ብለን በአዋጅ የተቋቋመ ተቋም ነው። ስለዚህ የተለያዩ አብያተክርቲያናት መሪዎች እና ምዕመናን የሚወክለን ተቋም እንደመሆኑ መጠን በተለያየ መንገድ ድምጻችንን ልናሰማ ይገባል።

መጋቢ ታምራት ታሪኩ
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስተ ክርስቲያናት ካውንስል የቦርድ አባል እና የኢትዮጵያ ገነት ቤተክርስቲያን ፕሬዝደንት

ስልጣን ላይ የተቀመጠው የትኛውም መንግስት በህዝብ የተሾመ ነው። የተሾመው ደግሞ ህዝብን ለማገልገል ነው። ይህን ለማስፈጸም የትኛውም የመንግስት መዋቅር ውስጥ የተቀመጡ ሃላፊዎች ህዝብን ያለ ምንም አድሎ በእኩልነት ማገልገል ይኖርባቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ አባይ ሚዛን አጸያፊ ነው እንደሚል የትኛውም ነገር የእግዚያብሄርን መንግስት ተገዳድሮ ማስቆም አይችልም።

ሪቨረንድ አማኑኤል ቶማስ
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስተክርስቶ
#ሌላ_ሰበር_መረጃ

መጋቢ እና ዘማሪ ተስፋዬ ጋቢሶ ተሸልመዋል።

ቀጠና ሁለት ቤተክርስቲያን በነበረው መረሃ ግብር በዘመን ተሻጋሪ ፤ ገሳጭ ፤ መካሪ ፤ አጽናኝ እና ክርስቶስ ተኮር በሆኑ ሰማይ ተኮር ህይወት ህይወት በሚሸቱ ዝማሬዎቻቸው የሚታወቁት መጋቢ እና ዘማሪ ተስፋዬ ጋቢሶ እንዲሁ እውቅና ተሰቷቸዋል።

በሁሉም አብያተክርስቲያናት ዘንድ እጅግ ተወዳጅ እንዲሁም ትውልድን እንደ ድልድይ በመሆን በማገናኘት በትሁትነታቸው የሚታወቁት መጋቢ እና ዘማሪ ተስፋዬ ጋቢሶ የሙሉ ወንጌል ብቻ ሳይሆን የአብያተክርስቲያናት ሁሉ እንቁ ሃብት የሆኑ ሰው ናቸው።

እግዚአብሄር የሰጣቸው ዝማሬዎች ዘመን ተሻጋሪ እና ልብን እና ህይወትን አዳሾች ሲሆኑ በተጨማሪ በማስተማር እና በማሰልጠን ይታወቃሉ።

ለኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ዘመን ተሻጋሪ በሚል ተሸላሚ ሆነዋል።

የክርስቲያን ዜና በቦታዉ ተገኝተን የተከታተልን ሲሆን ለመጋቢ እና ዘማሪ ተስፋዬ ጋቢሶ እንኳን ደስ አሎት እንላለን🙏🙏🙏🙏
#በአዲስ #አመት #ሌላ #በረከት
ከግማሽ #ሚልዮን በላይ .. በማዉጣት ለአቅመ ደካሞች ..

የፌይዝ ባይብል ኢንተርናሽናል ቸርች ሚራክል አጥቢያ ከጉድለቷ በመቆረስ ከ550,000 ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ሶስት የአቅመ ደካሞች ቤት አስመረቁ።

በፕሮግራሙ ላይ የፌይዝ ባይብል #ኢንተርናሽናል ቸርች መሪ የሆነው ቢሾፕ ዳዊት ሞላልኝ እንዲሁም የልደታ ክፍለ ከተማ አፈ ጉባኤ አቶ ዘሪሁን እና የወረዳ 8 አፈጉባኤ እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት አስመርቀን አስረክበናል::

በዚህ በጎ ተግባር ላይ በገንዘባችሁ እና በሙያችሁ የተሳተፋችሁ የቤተክርስትያናችን አባሎች #ሁሉ #እግዚአብሔር ይባርካችሁ::

Fbi Church Miracle Chaple Mekanisa