The Christian News
5.37K subscribers
3.08K photos
29 videos
730 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
ዘማሪ ሳሚ አበበ ሙሉ በሙሉ ከቤተክርስቲያን ተሰናብቷል።

ዉድ የክርስቲያን ዜና ቤተሰቦቻችን ዛሬ የሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን በዘማሪ ሳሚ አበበ ላይ የሰጠችዉ የመጨረሻ መግለጫ ቢሆንም እዚህ ከመደረሱ አስቀድሞ ላለፉት 6 ወራት በርካታ ስራዎች እንደተሰሩ ተገልጿል።

ምንም እንኳን ዜናዉ አሳዛኝ ቢሆንም ቤተክርስቲያን ይህ እንዳይፈጠር በርካታ ስራዎችን ብትሰራም አልተሳካም።

ነገር ግን ምንም እንኳን ቤተክርስቲያን ከዘማሪዉ ጋር ያላት ግንኙነት ቢቋረጥም ባለቤቱን እና ልጁን ግን ሙሉ ሃላፊነት በመዉሰድ አስፈላጊውን እገዛ እንደምታደርግላቸዉ በመግለጫው ተጠቅሷል።

ላለፉት 6 ወራት ዘማሪው የፅሞና ጊዜ ወስዶ ልጁን እና ቤተሰቡን እየተንከባከበ በንሰሃ እንዲመለስ ቤተክርስቲያን እና መሪዎች ከፍተኛ ጥረት ቢያደርጉም ዘማሪው ፍቃደኛ ባለመሆኑ ምክንያት ሳይሳካ ቀርቷል።

ይልቁንም ባለቤቱ ከቤት እንዳበረረችዉ እና ቤተክርስቲያን ድጋፍ እያደረገችልኝ አይደለም በሚል ቤተክርስቲያንን ከሷል።

ሙሉ ዝርዝር መረጃዉን

በቪዲዬ መመልከት ትችላላችሁ። https://youtu.be/AilX6O9IC24
#አባባ #ሴባ #ዋባሎ #ከዚህ #አለም #ድካም #አረፉ!

አባባ በ1901ዓ.ም በወላይታ ዞን ኦፋ ወረዳ ሳዶዬ ቀበሌ የተወለዱ ሲሆን በ1952 ዓ.ም ከተወለዱበት ከኦፋ ወረዳ ወንጌልን ለማገልገል ወደ ኪንዶ ኮይሻ ወረዳ ማንአራ ቀበሌ አቀኑ።

በተያዘም ከጤፓ ቀበሌ ጀምሮ በጨራቼ አድርጎ እስከ ጫው ካሬ ገበረ ማህበር ድረስ በቁጥር 13 የቃለህይወት ቤቴክርስቲያንን የመሠረቱና የተከሉ እኔን ጨምሮ በርካቶች ወንድሞቼና እህቶቼ ወደዚህ ዓለም እንዲንመጣ በረከት የሆኑ ታላቅ የእምነት አባት እና የሥጋ አያቴን በሞት ማጣት ምነኛ የሚያሳዝን ብሆንም ወዳገለገሉ ጌታ መሄዳቸው ከባድ መታደል ነው።

አባባ በበጉ ሠርግ በዳግም ምጻት እንገናኝ ቻው መልካም እረፍት።

Taway lo"uwan da!!
ልጃቸዉ
#ከዚህ ቀደም የተወረሱ ቦታዎች እንዲመለሱ ተደርጓል። መጋቢ ታምራት አበጋዝ

የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ጸሐፊ መጋቢ ታማራት አበጋዝ ከWBN ጋር በነበራቸው ቆይታ የስረዓተ አምልኮ ቦታዎችን #እና የስረዓተ መቃብር ቦታዎችን ፍተሃዊ በሆነ #መንገድ እንዲያገኙ ተሰርቷል ብለዋል።

የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከዚህ ቀደም የነበረው ተግዳሮት እንዲፈታ እና #ሁሉም በፍትሃዉነት እንዲስተናገዱ ሰርቷል።

ከቅርብ አመታት ወዲህ የሃይማኖት ተቋማት #ህጋዊ ሰውነት እንዲያገኙ ተስርቷል ያሉት መጋቢ ታማራት አበጋዝ የስረዓተ አምልኮ ቦታ እንዲያገኙ ተደርጓል።

በሌላ በኩል በአግባቡ ፍትሃዊ በሆነ መንገድ እንዲስተናገዱ እና #ከዚህ ቀደም የተወረሱ ቦታዎች እንዲመለሱ ተደርጓል አሁንም ቀሪዎቹ እንዲመለሱ እና እንዲስተካከል እየተሰራበት ነው ብለዋል።

#ሙሉ ቃለ መጠይቁን የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በሚል የፌስ ቡክ ገጽ ላይ ይመልከቱ።

የክርስቲያን ዜና በከፊል ዝርዝሩን ይዘን የምንመለስ ይሆናል።