The Christian News
5.37K subscribers
3.08K photos
29 videos
730 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
የኢትዮጵያ ቃለ ህይወት ቤተ ክርስቲያን ልማት ኮሚሽን በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች የ25 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

የኢትዮጵያ ቃለ ህይወት ቤተክርስቲያን ልማት ኮሚሽን በጦርነቱ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው በሰሜን ወሎ ዞን ለሚገኙ ወገኖች 25 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር የሚየወጣ የአይነት ድጋፍ አድርጓል፡፡

ድጋፉ በሃብሩ፣ ጉባላፍቶ እና ቆቦ ከተማ አካባቢ ችግር ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች እየተሰራጨ መሆኑን የልማት ኮሚሽኑ ኮሚሽነር ተፈራ ቴሌሮ ተናግረዋል።

ኮሚሽኑ በጦርነት ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች የዕለት ምግብ ድጋፍ ቅድሚያ ሰጥቶ እያደረሰ መሆኑንም ኮሚሽነሩ አስረድተዋል፡፡

በቀጣይ አገልግሎት ሰጭ ተቋማትንና በግብርና ልማት ሥራ መልሶ ማቋቋም የሚስችል ለ2 ዓመት የሚቆይ 68 ሚሊየን ብር በላይ በጀት በመመደብ ከ68 ሺህ በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ወደ ስራ መገባቱን አንስተዋል፡፡

ድጋፉ በኢትዮጵያ ቃለ ህይወት ቤተክርስቲያን ልማት ኮሚሽን በኩል ከተለያዩ ረጅ ድርጅቶች የተገኘ መሆኑን የሰሜን ወሎ ዞን ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

#ዳጉ_ጆርናል
በሃይማኖት መገናኛ ብዙኃን የሚፈጸሙ የሥነ ምግባር ጥሰቶች በአስቸኳይ እንዲቆሙ የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን አሳሰበ

ከተቋቋመበት መርህና አላማ በተቃረነ አኳኋን በተለያዩ የሃይማኖት መገናኛ ብዙኃን የሚፈጸሙ ህጋዊና ሙያዊ የሥነ ምግባር ጥሰቶች በአስቸኳይ እንዲቆሙ የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን አሳሰበ።

ባለስልጣኑ ለዋልታ በላከው መግለጫ የሃይማኖት መገናኛ ብዙኃን ለኢትዮጵያውያን መልካም ዕሴቶች መጎልበት ወሳኝ ሚና እንዳላቸው መንግስት እንደሚያምን ገልጿል።

መንግስት የመገናኛ ብዙኃኑ ያላቸውን አወንታዊ ሚና በማመን ለተቋማቱ ህጋዊ እውቅና በመስጠት ድጋፍና እገዛ እያደረገ እንደሚገኝም ገልጿል፡፡

የሃይማኖት መገናኛ ብዙኃን ሃይማኖታዊ አስተምህሯቸውን ለተከታዮቻቸው ሲያስተምሩ የሌሎችን ሃይማኖትና እምነት አክብረው እንዲያስተምሩ፣ ከተቋቋሙበት ሃይማኖታዊ ጉዳይ ውጭ ሌሎች ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸው ጉዳዮች እንዳያስተላልፉ እና ከጥላቻ፣ በዜጎች መካከል አብሮ መሆንን ከሚያውክ በማንኛውም አግባብ ሁከትና ግጭት ሊቀሰቅስ ከሚችል በዜጎች ላይ ሥነ ልቦናዊም ሆነ አካላዊ ጥቃት እንዲደርስ ከሚያነሳሳ ንግግር እና ከመሰል አሉታዊ መልዕክቶች እንዲታቀቡ ይጠበቅባቸዋል ብሏል።

በተጨማሪ ሃይማኖት ተኮር ፕሮግራም ሲያሰራጩ በተለያዩ ሃይማኖት ተከታዮች መካከል የእርስ በእርስ ግጭት ማነሳሳት፣ የሌሎችን ሃይማኖት ማንኳሰስ እንዲሁም በሃይማኖቶች ተከታዮች መካከል አለመቻቻል እንዲፈጠር መቀስቀስም የተከለከለ መሆኑንም አብራርቷል፡፡

#ዳጉ_ጆርናል
በትግራይ ክልል በጦርነቱ ወቅት የቄስ ትምህርት መደበኛዉን የትምህርት ስርዓት በመተካት አስተዋጽዖ ያደርግ እንደነበር ነዋሪዎች ተናገሩ

በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል በነበረው ጦርነት ምክኒያት በተለይ በትግራይ ክልል ዜጎች ማግኘት የነበረባቸዉን መሰረታዊ አገልግሎቶች ለማግኘት ተቸግረው ቆይተዋል። አስተያየታቸውን ለብስራት ራዲዮ የሰጡ የክልሉ ነዋሪዎች የትምህርት ፣ የጤና እና ሌሎች መሰረታዊ አገልግሎቶች ተቋርጠዉ የነበረ ቢሆንም በተለይ በትምህርት ዘርፉ ላይ ህጻናት ማግኘት የነበረባቸዉን እዉቀት ሳያገኙ ቀርተዋል ብለዋል።

ኮቪድ - 19 በኢትዮጵያ ከተከሰተበትና ይህንኑ ተከትሎ ከተቀሰቀሰው ጦርነት ወዲህ ለሶስት አመታት ገደማ ተቋርጧል በተባለዉ መደበኛ ትምህርት ፤ ህጻናት እዉቀት ካለማግኘታቸዉ በተጨማሪ በሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች ከሚገኙ የእድሜ እኩዮቻቸዉ ወደ ኋላ እንዲቀሩ አድርጓቸዋል።አስተያየታቸውን ለጣቢያችን የሰጡን የክልሉ ነዋሪች እንደገለጹት ፤ ጦርነቱ አይሎ በነበረባቸዉ ወቅት የቄስ ትምህርት ተቋርጦ የነበረዉን መደበኛ ትምህርት በመተካት እድሜያቸዉ ለትምህርት የደረሱ ህጻናት ሲማሩ ቆይተዋል።

በተለይ እድሜያቸዉ ለጦርነት ያልደረሱና  ከሰባት እስከ አስራ አምስት አመት የሆኑ ህጻናት ትምህርቱን በስፋት ሲከታተሉ ነበር። በተጨማሪ በክልሉ የሚገኙ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ርቀዉ ዓመታትን ያስቆጠሩ እንደመሆናቸዉ የስነልቦና ጫና ይታይባቸዋል ብለዋል። እንደ አስተያየት ሰጪዉ ገለጻ " ህጻናት ከትምህርት ይልቅ ስለ ብረት እና ጦርነት ያወራሉ" ሲሉ ተናግረዋል። አክለዉ በተለያዩ ትምህርት ቤቶች ወደ መኖሪያ ቀዬአቸዉ መመለስ ያልቻሉ በርካታ ተፈናቃዮች ይገኛሉ ብለዋል።

በበረከት ሞገስ
#ዳጉ_ጆርናል
#አስደሳች_ዜና

ተማሪ ሊዲያ አበራ የዋስትና መብቷ እንዲከበር ይግባኝ ተጠየቀ

በሀላባ ከተማ በጊዜ ቀጠሮ መዝገብ በስር ላይ የምትገኘው ተማሪ ሊዲያ አበራ  የዋስትና መብቷ እንዲከበር ይግባኝ ተጠየቀ። የይግባኝ ጥያቄዉን የቀረበው ለሃላባ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው።

ይግባኙን ካቀረቡት 4 ጠበቆች መካከል ጠበቃ አበባየሁ  ጌታ አንዱ ሲሆኑ  ''ተማሪ ሊዲያ አበራ የ10 ኛ ክፍል ተማሪና  እድሜዋ 15 አመት እንደሆናት ጠቁመው ከዕድሜዋ አንጻር በስር ቤት ልታሳልፍ እንደማይገባ ገልጸዋል''

በዚህም መነሻ የዋስትና መብቷ ተከብሮ ከስር ተፈታ በውጭ ሆና ጉዳይዋን እንድትከታተል ይግባኝ መጠየቃቸውን አብራርተዋል።

ፍርድ ቤቱም ይግባኙን ለመልክቶ ብይን ለመስጠት ለመጋቢት 6 ቀን 2015 ዓ/ም ቀጥሯል።

Via ታሪክ አዱኛ
#ዳጉ_ጆርናል
#ካውንስሉ
#ሃላባ

በተማሪ ሊዲያ ጉዳይ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያን ካውንስል ያወጣዉን መግለጫ የሀላባ ዞን አስተዳደር አጣጣለ

👉🏼 አስተዳድሩ ፤ ቤተክርቲያኒቷ በምዕመናን ላይ ይደርሳል ያለችዉ ጫና የተጋነነ ነዉ ቢልም ምዕመናን ጫና አንደማይደርስባቸዉ ግን ማረጋገጫ መስጠት አልቻለም

በትናንትናዉ እለት የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያን ካውንስል የሀላባ ዞንን በተመለከተ ያወጠው መግለጫ ፍጹም ዞኑን የማይገልጽና ለዘመናት ተቻችለው የኖሩ ማህበረሰቦችን ወደ ግጭት የሚያመራ ነው ሲል የሀላባ ዞን አስተዳደር አጣጥሎታል።

በመግለጫው የተጠቀሱት የምዕመናን እንግልቶች የሌሉና እጅግ የተጋነኑ ናቸዉ ሲል አስተዳድሩ የተናገረ ሲሆን ምዕመናን ጫና እንደማይደርስባቸዉ ግን ማረጋገጫ መስጠት አልቻለም።

በተጨማሪም እንግልቶቹ ከቤተ እምነቶች ቦታ ጋር በተያየዘ የሀገራችን ህግ በማይፈቅድ መልኩ ቤተ ዕምነቶችን ለመምራት በሚፈልጉ እና የህዝብን ሰላምና ደህንነት ለማደፍረስ በሚንቀሳቀሱ ቡድኖች እየተራገበ ያለ ሐሰተኛ ድርጊት የመጣ ነው ብሏል።

ከሰሞኑም ከሊዲያ አበራ ጋር በተያየዘ ያለ ዕድሜዋ ታሰረች የሚባለው ግለሰቧ በህክምና በተረጋገጠው መሠረት ከ17 - 19 የዕድሜ ክልል የምትገኝ ስሆን በወቅቱ አምስት ግለሰቦች በከሰሱት ክስ መሠረት ጉዳዮዋ በህግ ሂደት ላይ መሆኑን ብስራት ራዲዮ ከመግለጫው ተመልክቷል።

በአመራሮች ጫና ህጻን የሆነች ያለክስና ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ታስራለች የሚባሉ እጅግ ስሜት ቀስቃሽ ውንጀላዎች ህዝቡን በሐይማኖት ለማጋጨት ሆን ተብሎ የተፈበረካ ዕኩይ ሴራ ከመሆኑም በላይ ህግና ስርኣትን ለመናድ ያለመም መሆኑ ሊታወቅ ይገባል ብሏል በመግለጫው።

በአጠቃላይ የካውንስሉ መግለጫ ዞኑን የማይገልጽና የዞኑን መልካም ገጽታ ለማበላሻት ያለመ መሆኑን እያሳወቅን የዞናችን ማህበረሰብ በሰከነ መልኩ ጉዳዩን በመገንዘብ የሴረኞችን ዕኩይ አላማ በጋራ እንድናከሽፍ ጥሪ አድርጓል።

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል በአዋጅ ቁጥር 2008/2012 በአዋጅ ሕጋዊ ሰውነት ያለው የወንጌል አማኞች ምክር ቤት መሆኑ ይታወቃል።

#ዳጉ_ጆርናል
የኬንያ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን አስራት ለቤተክስርቲያን የማይሰጡ ሰራተኞች ላይ ክትትል እንደሚያደርጉ አስታወቁ

በኬንያ የናንዲ ግዛት ገዥ አዲስ የተሾሙ ስራ አስፈፃሚዎች 10 በመቶ ገቢያቸውን ለቤተክርስትያ እንዲሰጥ ትዕዛዝ ማስተላለፋቸዉን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።የናንዲ ግዛት አስተዳዳሪ እስጢፋኖስ ሳንግ መመሪያው ያስፈለገው አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ከመሪዎች እና ከግዛቲቱ መንግስት ድጋፍ ስለሚያስፈልጋቸው ነው ብለዋል።

በዴይሊ ኔሽን ድህረ ገጽ ዘገባ መሰረት "በመጨረሻ የስራ ዘመኔ የምሾማቸዉ ዋና የስራ ኃላፊዎች በተለየ መንገድ መስራት እና ለህብረተሰቡ ማገልገል አለባቸው" ሲል ተናግረዋል።ርዕሰ መስተዳድሩ ይህንን ያሉት የቤተ ክርስቲያኒቱ መሪዎች በተገኙበት በተካሄደው የባለሥልጣናቱ ቃለ መሃላ ወቅት ነው።

ገዥው የአስራት ትእዛዙን እንዴት ለማስፈጸም እንዳቀዱ ባይታወቅም አስራት በማይሰጡ  የመንግስት ሰራተኞችን የስም ዝርዝር ከሀይማኖት አባቶች ጋር በመሆን ክትትል እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።አሥራት ለቤተ ክርስቲያን የመስጠት ልማድ የክርስትና የጥንት አካል ቢሆንም የግዴታ መሆን አለበት በሚለው ጉዳይ ላይ እርስ በእርሱ የሚጋጩ አስተያየቶች ተሰንዝረዋል፡፡

በኬንያ ያሉ ገዥዎች እና የስራ አስፈፃሚ ሰራተኞቻቸው ለትምህርት ቤቶች፣ ለመንገዶች እና ለሆስፒታሎች የታሰበ የህዝብ ገንዘብ ላይ ከፍተኛ ቁጥጥር ያደርጋሉ።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
#አሳዛኝ  #ዜና
#የሃሰተኛ #አስተማሪዎች #ዉጤት

በኬንያ ክርስቶስን ቶሎ ለማግኘት በረሃብ አድማ ላይ የነበሩ አራት  ሰዎች #ሞቱ

በኬንያ የባህር ጠረፍ ኪሊፊ አውራጃ አራት ሰዎች ህይወታቸው አልፈው የተገኙ ሲሆን በርካቶች ደግሞ ክፉኛ መጎዳታቸው የተሰማ ሲሆን የምግብ አድማ በማድረግ የዓለምን ፍጻሜ ሲጠባበቁ እንደነበረ ተጠቁሟል።

#ፖሊስ እንዳስታወቀው ለተከታታይ ቀናት በጫካ ውስጥ ግለሰቦቹ በፃም "ኢየሱስን ለማግኘት እንዲጠበቁ በኃይማኖት አባት" ከተነገራቸው በኋላ ይህው ድርጊት አጋጥሟል።

ፖሊስ ባደረገው የነፍስ አድን ጥረት 11 ሰዎችን በህይወት ማትረፍ ችሏል። በህይወት ከተረፉት መካከል ስድስቱ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን በከፋ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ተጠቁሟል ። ሌሎች የቀሩ ሰዎች በጫካ ውስጥ እንዳሉ መነገሩን ተከትሎ ፖሊስ ዛሬ ጠዋት ተጨማሪ ኃይል በማሰማራት ፍለጋ እንደሚቀጥል ገልጿል።

ፖሊስ በጫካው ውስጥ በቅርብ ቀናት የተቀብሩ ሰዎች አስክሬን ማግኘቱን አስታውቋል። ግለሰቦቹ ፈጥነው ወደ መንግሥተ ሰማያት ለመድረስ በረሃብ እንዲሞቱ ያደረገው የጉድ ኒውስ ኢንተርናሽናል #ቤተክርስቲያን መሪ መሆኑ ተነግሯል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል

#share
#ShareThisPost
#likeforlikes
#ኢትዮጵያ
#አሳዛኝ #ዜና

በአሜሪካ አንዲት እናት #ክርስቶስ #ወደ ምድር በቶሎ ለፍርድ እንዲመጣ በሚል #ሁለት ልጆቿን ገደለች።

በዩናይትድ ስቴትስ የምትኖር አንዲት እናት በአፖካሊፕቲክ ሃይማኖታዊ እምነቷ መሰረት ሁለት ልጆቿን በመግደል እና የባሏን የቀድሞ ሚስት ለመግደል በማሴር የእድሜ ልክ እስራት ተፈርዶባታል።

ሎሪ ቫሎው የተባለችዉ ይህችዉ #ሴት በግንቦት ወር የ16 ዓመቷን ሴት ልጇን ታይሊ ራያን እና የሰባት ዓመት በማደጎ የወሰደችዉን #ወንድ ልጇን ኢያሱ "ጄጄ" ቫሎውን በመግደል ጥፋተኛ ተብላለች፡፡

የእናታችን ኃጢአት (Sins of Our Mother) በሚል የዚህችዉ ሴት የህይወት #ታሪክ በኔትፍሊክስ እውነተኛ የወንጀል ዘጋቢ #ፊልም የቀረበ ሲሆን የኢየሱስ ክርስቶስን ዳግም ምጽዓት እንዲሆን ልጆቿን መግደሏ ከአምላክ የተሰጠ ራዕይ መሆኑን ትናገራለች፡፡

ዳኛ ስቲቨን ደብሊው ቦይስ በቫሎው የወንጀል ድርጊት ላይ ባሳለፉት የጥፋተኛነት ዉሳኔ በሶስት ተከታታይ የእድሜ ልክ እስራት በይነዋል፡፡ በወላጅ የተፈጸመውን የልጅ ግድያ “በእርግጥ መገመት ከምችለው በላይ አስደንጋጭ ነገር” ሲሉ ዳኛዉ ገልጸዋል።

ቫሎው ልጆቿን ከገደለች በኃላ #እንኳን እንደጠፉ ገልጻ ባታዉቅም በፖሊስ አስክሬናቸዉ ተገኝቷል፡፡

#ዳጉ_ጆርናል
#ቀራጩ ዘኪዮስ

የኬንያ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ በታክስ ፖሊሲያቸው የተነሳ በመፅሃፍ ቅዱስ ውስጥ በተገለፀው ስግብግቡ ቀራጭ ዘኪዮስ በመባል እየተጠሩ ይገኛል


የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስግብግቡ ቀራጭ ከሆነው ዘኪዮስ ጋር ስማቸውን እየተነፃፀረ እየተጠራ ይገኛል።

በክርስትና አማኞች ዘንድ በቅዱስ መጽሐፍ ኢየሱስን ለማየት ዛፍ ላይ የወጣው ስግብግብ ቀራጭ ዘኪዮስ ይታወቃል።

ሩቶ በዚህ ስም ሊጠሩ የቻሉት እ.ኤ.አ. በነሐሴ 2022 ፕሬዝዳንት ሆነው ከተመረጡ ወዲህ አዳዲስ ታክስ ዓይነቶችን በማስተዋወቅ እና ቀድሞ የነበሩት ላይ ጭማሪ በማድረግ በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት የገቡትን ቃል የካዱ መሪ ናቸው በሚል ተተችተዋል።

ሩቶ የግብሩ ጭማሪ ከፍተኛ ህመምን የሚያስከትል መሆኑን አምነዋል። ነገር ግን ባለፈው ሳምንት በተከበረው የኬንያ የነጻነት ቀን ንግግራቸው ላይ ህዝቡ እየከፈለ ያለው መስዋዕትነት "የነጻነት ታጋዮቻችንን የሚያኮራ ነው" ብለዋል።

የመንግስት ብድርን ለመቀነስ እና ወደ 10 ትሪሊዮን ሽልንግ ወይም 65 ቢሊዮን ዶላር ያደገውን ብሄራዊ ዕዳ ለማውረድ ከፍተኛ ግብር መጣሉ አስፈላጊ ነው ብለዋል። ኬንያ ካለባት የዕዳ ጫና አንፃር በጣም ከባድ እና አሳማሚ ውሳኔዎችን ወስደናል ብለዋል።

እንዲሁም ፕሬዚዳንቱ ከመጽሐፍ ቅዱሱ ዘኪዮስ ጋር መነፃፀራቸው ብዙም እንዳላሳሰባቸው ተናግረዋል። በአንዳንድ አካባቢዎች ዘኪዮስ ተብዬ ተጠርቻለሁ ምናልባት በግንቦት ወር የግብር ሰብሳቢዎች ቀን ይኖረናን ይሆናል ሲሉ ተናግረዋል። በርካታ ኬንያውያን ግን ከፕሬዝዳንቱ ሀሳብ ጋር ስምምነት የላቸውም።

በተለይ የኑሮ ውድነቱ እየጨመረ ባለበት ወቅት የግብር ጭማሪው የዕለት ተዕለት ኑሮአቸውን እንዳከበደው ይገልጻሉ።

በተጨማሪም የታክሱ ጭማሪ የህዝብ አገልግሎቶችን ከማሻሻል ይልቅ በመንግስት ውስጥ ያለውን የሀብት ብክነት እና የስልጣን ብልግና ለመደገፍ ብቻ እየረዳ ነው ይላሉ።የኬንያ የበጀት ተቆጣጣሪ ግን የህዝብ ገንዘብ አጠቃቀምን የሚቆጣጠር ገለልተኛ ቢሮ  በማቋቋም የመንግስት ባለስልጣናት የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገራት ጉዞን ጨምሮ ለብክነት የሚዳርገውን ገንዘብ እንዲቀንስ ማድረጉን ይገልጻል።

በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ከ40 በላይ የውጭ ሀገር ጉዞዎችን ያደረጉት ፕሬዝዳንት ሩቶ በአባካኝነት ስማቸው ቢነሳም የውጭ ኢንቨስትመንቶችን እና የስራ እድልን ለኬንያውያን እየፈለጉ መሆናቸውን በመግለፅ ጉዟቸውን ተከላክለዋል።

በኬንያ አሰሪዎች ፌዴሬሽን የቅርብ ጊዜ ዘገባ መሠረት በተመሳሳይ ጊዜ ውስጥ 70 ሺ የግሉ ዘርፍ ሥራዎች በከፍተኛ የሥራ ማስኬጃ ዋጋ መጨመር እየታገሉ መሆናቸውን እና አንዳንድ የንግድ ሥራዎች መዘጋታቸውን ጠቁመዋል።

#ዳጉ_ጆርናል
#ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በየትኛዉም መልክ የተመሳሳይ #ጾታ ጋብቻን አትፈቅድም።

#የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት #ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ጉባኤ ጠቅላይ ጽ/ቤት ከሰሞኑ ርዕሳነ ሊቀ ጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስ ለተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎች የፈቀዱት ቡራኬ ላይ ማብራሪያ ሰጠ።

ከሰሞኑ የሮማዉ ሊቀ ጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስ ቤተክርስቲያኗ ለተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎች ቡራኬ እንዲሰጡ ፈቃድ መስጠታቸዉን የተለያዩ #መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

ይህንኑ ተከትሎም የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ጉባኤ #ጠቅላይ ጽ/ቤት በጉዳዩ #ላይ #መግለጫ አዉጥቷል። ጠቅላይ ጽ/ቤቱ ከካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ስርዓተ አምልኮ ጋር የሚጻረር ወይንም ዉዥንብርን ሊፈጥር የሚችል ስርዓተ አምልኮን ያወግዛል ብሏል።

ሆኖም የጳጳሱ መልዕክት በተቃራኒው ተወስዷል የሚል ሃሳብ ያለዉን መግለጫ ያወጣ ሲሆን ለተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎች ጋብቻን #ግን ጳጳሱ ፈቃድ አልሰጡም ብሏል።

አክሎም የመፅሐፍ ቅዱስ ጥቅስን በማስቀመጥ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በየትኛዉም መልክ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻን አትፈቅድም ፤ አታጸድቅምም ማለቱን ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ከመግለጫው ተመልክቷል።

ቤተክርስቲያኒቱ ሀጢያትን አትባርክም ታወግዛለች #እንጂ ያለዉ መግለጫዉ የተመሳሳይ ጾታ #ጋብቻ የኢትዮጵያ ባህል #እና እሴትን የሚጥስ በመሆኑ ተቀባይነት እንደማይኖረዉም በመግለጫው አስታዉቋል።

በበረከት ሞገስ
#ዳጉ_ጆርናል