The Christian News
5.15K subscribers
3.04K photos
25 videos
714 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
#በዚህ #ሳምንት #አስደናቂ የቤተሰብ #ፕሮግራም ይከናወናል።
#ኢየሱስ #ኢትዮጵያ #ድንቅ #ወንጌል #አዲስ #አዲስአበባ

ለመጀመሪያ ጊዜ በ2011ዓ.ም "ቅድሚያ ለቤተሰብ" በሚል ርዕስ በተዘጋጀዉ መሰናዶ እና ከ270 በላይ ጥንዶች በተሳተፉበት መድረክ (በድሮዉ አዳራሽ) የመካፈል ዕድል ገጠመኝ በወቅቱ ቅድሚያ ለቤተሰብ መኖር ወሳኝ መሆኑን ተጠቅሶ ቤተክርስቲያን ጤናማ ማህበረሰብ ለመገንባት እንዲህ አይነት ፕሮግራም እንደምታዘጋጅ የቤተክርስቲያኒቱ መሪ ፓስተር ሚኪ ተናግረዉ ነበር።

ቀጥሎ ደግሞ "ፍቅር ለዘወትር አይወድቅም" በሚል በ2014ዓ.ም በተካሔደው እና 300 ጥንዶች በተገኙበት ተወዳጅ ፕሮግራም የመገኘት እድል ነበረኝ።

በወቅቱ መጋቢ ቴዎድሮስ አዲስ ይህ መረሃ ግብር የተዘጋጀው በጋብቻቸው ፍጹም ለሆኑ ሰዎች አይደለም ቤት ሁሌም እየተሰራ ነው የሚሄደው "ይህ ፕሮግራምም የሰዎች ቤት የሚሰራበት ነው" ሲሉ የፕሮግራሙን አላማ ጠቅሰዉ ነበር።

እነሆ አሁን ደግሞ 13ኛ ልዩ የባለ ትዳሮች ቀን ደረሰ ባሳለፍነዉ ዓመት በመረሃ ግብሩ ላይ ቃል ኪዳንን የማደስ መሰናዶ ተከናዉኖ የዓመቱ ምርጥ እናት ከሆኑ እናት የሕይወት ምስክርነት ተሰምቶ ባለትዳሮች በጋራ የማዕድ ጊዜ እንዲያሳልፉ ተደርጓል።

በምስክርነት እጅግ ብዙዎች ተነክተዉ የብዙ ሰዎች የማንቂያ ደዉል ሆኖ ነበር።

በየአመቱ በተቀባ የእግዚአብሔር ቃል አገልግሎት ቤተክርስቲያን አዘጋጅነት በሚሰናዳዉ ይህ ደማቅ ስነስርአት እነሆ #ደረሰ ደረሰ

የዘንድሮው ደግሞ ከሌሎቹ ጊዜያት እጅግ ደማቅ እንደሚሆን አምናለሁ።

ቀን :- አርብ ሚያዚያ 27-2015ዓ.ም
ሰዓት :- ከቀኑ 8:00 ሰዓት
ቦታ :- ቦሌ የተቀባ የእግዚአብሔር ቃል አገልግሎት ቤተክርስቲያን

#ጋብቻ #መልካም #ነዉ
#መልካም
#መልካም #እለተ ሰንበት ይሁንልን 🙏🙏🙏

ቴክኒካሊ ብልጥ ሆነን የማናልፍበት ዘመን መጥቷል።

ዘመኑን ለማለፍ መንፈሳዊ መሆን የግድ ነዉ። እሱም ከኢየሱስ ጋር #ብቻ መሆን #ነዉ የሚያዋጣዉ።

በመፅሐፍ #ቅዱስ #ብዙ ታሪክ የሰሩ ሰዎችን ብንመለከት #እንኳን አለም እነሱን አይታ ተሸናፊዎችነዉ ያለቻቸዉ። ማንም አይፈልጋቸዉም ነበር።

በዘመናቸዉ #ሁሉ #ኢየሱስ ሲሉ ነበር ካለፉ በኋላ ግን ሁሉም ሰዉ ስለ ኢየሱስ ከ2ሺህ ዘመናት በላይ ይናገራል።

ኢየሱስ ካልክ የዚህ ድንቅ መፅሐፍ አካል ትሆናለህ። መፅሐፍ ቅዱስ የአንድ ታሪክ መፅሐፍ ነዉ። እነዚህ ሁሉ ሰዎች ስለ አንድ ታሪክ ሲናገሩ ነዉ የታሪክ አካል የሆኑት።

#ነብይ ጥሌ
#መንገድ #ዝግ #ነዉ

#የኢትዮጲያ #ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል በመስቀል አደባባይ የሚያከናውኑት የፀሎት ፕሮግራም ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የተወሰኑ መንገዶችን ለተሸከርካሪ ዝግ እንደሚደረጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ

አሽከርካሪዎች እንደ ተለመደው ለትራፊክ ፖሊሶች ትዕዛዝ ተባባሪ እንዲሆኑ ተጠይቋል፡፡

#ነገ ዕሁድ መጋቢት 8 ቀን 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ በመስቀል አደባባይ ከሰዓት በሗላ ከቀኑ 7፡30 እስከ 12፡00 ሰዓት ድረስ የኢትዮጲያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል የፀሎት መርሐ-ግብር ስለሚያከናውኑ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚደረጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

አሽከርካሪዎች መረጃው አስቀድሞ ኖሯቸው ሌሎች አማራጭ መንገዶችን በመጠቀም ለትራፊክ ፖሊስ አባላት ትዕዛዝ ተባባሪ እንዲሆኑ ፖሊስ ጥሪውን እያስተላለፈ፡-

• ከቅዱስ ኡራኤል አደባባይ #ወደ መስቀል አደባባይ ለሚጓዙ ተሽከርካሪዎች ኡራኤል አደባባይ ላይ

• ከቦሌ ጌቱ ኮሜርሻል አቅጣጫ ወደ መስቀል አደባባይ ኦሎምፒያ አደባባይ በታች እና በላይ እንዲሁም ግራና ቀኝ

.የቀድሞው አራተኛ ክፍለጦር (ጥላሁን አደባባይ ላይ )

• ከለገሀር መብራት ወደ መስቀል አደባባይ ለሚጓዙ ለገሀር መብራት ላይ

• ከሀራምቤ መብራት ወደ መስቀል አደባባይ ሃራምቤ መብራት ላይ

• ከብሔራዊ ቤተ መንግስት ወደ መስቀል አደባባይ ብሔራዊ ቤተ መንግስት አጠገብ ዕሁድ መጋቢት 8/16 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡ 00 ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ መንገዶቹ ለጊዜው ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ፡፡

ፕሮግራሙ በሚከበርበት ዙሪያ እና በአካባቢው በግራና በቀኝ ለረጅምም ሆነ ለአጭር ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጨምሮ ገልጿል፡፡