የተወደዳችሁ የዩኒቨርሲቲ ወንጌላዊያን ክርስቲያን ተማሪዎች፣
-------------------------
ሰላም ለእናንተ ይሁን...!
ወቅቱ #በኮሮና_ቫይረስ [COVID-19] ወረርሽኝ ምክንያት የትምህርት ሁኔታ በሀገረ-አቀፍ ደረጃ ጊዜያዊ መቀያየር ከመደረጉ የተነሳ የተለያዩ መርሃ ግብሮች እንደተለመደው ያልቀጠለበት ሁኔታ ላይ እንገኛለን። ብዙዎች በብዙ ስጋትና ፍርሃት እያሳለፉ ያሉበት ወቅት ላይ ነን። በእንዲህ ዓይነት ጊዜና ሁኔታ እንደ #አማኝና #ባለአደራ፣ ራሳችንን እንዲሁም ሕዝባችንን ከበሽታው ለመጠበቅ የራሳችን የሆነ ድርሻ እግዚአብሔር በሰጠን ጥበብና የመንፈስ ቅዱስ ምሪት መወጣት ይጠበቅብናል።
ሁልጊዜም ቢሆን በምንም ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ብንሆን ቅዱስ ቃሉ፣ “እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት።” 1ኛ ጴጥ 5፡7 እንደሚል በእግዚአብሔር ፊት በፀሎት መሆንና ሀሳባችንን በእርሱ ላይ ማድረግ አለብን። ዓለም በነውጥ ውስጥ ብትሆንም እኛ ግን የምናመልከው ስለእኛ መስቀል ላይ ደሙን ያፈሰሰው፣ የሞተው፣ በሦስተኛው ቀን የተነሳው፣ ዳግም የሚመጣው ዘለዓለማዊ ጌታ በዙፋኑ አለልን። በፍጹም አባት እንደሌለን #አንፈራም #አንሸበርምም። ይልቅስ ቀኑ እየቀረበ ሲሄድ ዕለት ዕለት ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን ወደመምሰል እናም የወንጌሉን ሥራ እየሰራን የተፈጠርንበትን ብሎም የተጠራንበትን ዓላማ እየፈጸምን መኖር ይሁንልን።
ሞተን የጀመርነውን ዘለዓለማዊ የሕይወት ጉዞ ጊዜያዊ ሞትን በመፍራት ከዓላማችንና ሕልማችን መስተጓጎል የለብንም። ጌታ በቃሉ የሚለንን እናምናለን። እርሱን እንከተለዋለን። በቃሉ እግዚአብሔር ከጅምሩ ለዳዊት “እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።”—(መዝ 27፥14) በማለት ሲያበረታታው ነበር። ይህ እግዚአብሔር ዛሬም ሕያው ነው ከእኛ ጋር አሁንም ኣለ። እንደ ፅኑ ዓለት በሆነው ተስፋችን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የጸና ተስፋና እምነት ሁልጊዜም ይኑረን።
#ሕብረት
-----------
በጉዳይ የመጣ ስብሰባ ጉዳዩ ሲያልቅ ይበተናል፤ በፍቅር የተገመደ ንጹህ #ሕብረት ግን ተግዳሮት አይበግረውም። አይበተንም።
#ሕብረታችን በነበርንበት ትናንሽ ቡድኖች ሊቀጥሉ ይገባል። ወደ ቤተሰብ ያልሄዳችሁ (የሄዳችሁም ጭምር) ተማሪዎች ትንንሽ ቁጥር ባለው ሕብረት በመሰብሳብና በሚዲያ ቡድን በመፍጠር [Create group] ሌሎችን በማያሰናክል ሁኔታ መፀለይና በቃሉ መነጋገር መትጋት አለብን። #ሕብረቶቻችን [fellowships] በትልቅ ቁጥር ብቻ መሰብሰብን ዋና አድርጎ ያልቆመ መሆኑ ግልጽ ነው። አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ጥቂት ቁጥር ባለው መሰባሰብም ቢሆን መቀጠል ይችላል። ሁላችን አንድነታችንንና ሕብረታችንን በጥንቃቄ እንድጥለው ዘንድ በታላቅ ትህትና እመክራለሁ።
#ወንጌል
-----------
በሌላ በኩል ይህ ጊዜ ብቸኛው [unique] የሆነውን #የወንጌልን_መልዕክት የምንናገርበትና ቃሉን በጥልቀት የምንቆፍርበት ቢሆን ይመረጣል። የሰው ልጅ ያለ ኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል፣ በኃጢአት ምክንያት የሞተ ነው። የእግዚአብሔር ቃልና የመንፈሱ ኃይል በሌለበት ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ብስለት ማደግ አይኖርም። የሞት ስጋት፣ የጠላት ከንቱ ሸክምና ቀንበር የሚሰበረው በኢየሱስ ክርስቶስ መልካም ዜና በሆነው ወንጌል ብቻ ነው።
በተሰጠን ጊዜና ዕድል ቢያንስ ለቅርብ ሰው ወይም ጓደኛ #የወንጌሉን የምስራች ያለፍርሃት እንናገረው። በዘመናት ሁሉ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ከሚሞቱት ሰዎች ይልቅ ከነ ኃጢአታቸው የሞቱት ይበዛሉ። የሚከፋውም ሞት ደግሞ በኃጢአት ምክንያት የሚመጣው ሞት ነው። ብቸኛው መድኃኒትም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ኢየሱስ እርሱ ጌታና መሲህ ነው። ተባረኩ! እጅግ ወዳችኋለሁ።
----
አገልጋይ ገዛኸኝ ሹመሮ፣
ደቡብ-ኢቫሱ ክልል

#ሕብረት ያወጀው የንስሃና ምልጃ ጽሎት ዛሬ ተጀምሯል።
የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ሕብረት ከየካቲት 9-12/2015 ዓ.ም እንዲቆይ ያወጀው የንስሃና ምልጃ ጽሎት በትላንትናው እለት በሕብረቱ ጽ/ቤት ያስጀመረ ሲሆን በመላው ሀገሪቱ እና ከሀገር ውጪ ደግሞ ከዛሬ የሚጀምር ይሆናል።
"እግዚአብሔር ሆይ ተስፋ ባደረግንህ በእኛ ላይ ምህረትህ ትሁን"
በሚል መዝ 33:22 መሪ ቃል በማድረግ የተጀመረው የንስሃና ምልጃ ጽሎት
1. ስለ ፈሰሰው የንጹሃን ደም የእግዚአብሔርን ምህረትን መለመን
2. በጭንቀት ላይ ላሉ አረጋውያን፣ ወላጅ አጥ የሆኑ ህጻናትን፣ በችግር ውስጥ ለሚገኙ ወገኖች በሙሉ እግዚአብሔር በቃችሁ ብሎ እንዲያሳርፋቸው ምህረትን መለመን።
3. ለሃይማኖት እና ለሃገር መሪዎች ጥበብና ማስተዋል እንዲሰጣቸውና ፣ለሚመሩት ህዝባቸው የተሻለውን ፈጥነው የሚወስኑበትን ማስተዋል እንዲበዛላቸው መለመን።
ከላይ የተዘረዘሩት ነጥቦች ላይ የሚያተኩር ይሆናል።

#አዲስ
#የሰቆቃ ፈዉስ
#የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት #ሕብረት የሰላም ግንባታ እና ሰቆቃ ፈዉስ ፕሮጀክት ማጠቃለያ ፕሮግራም እያከናወነ ነዉ።
በሸራተን እየተካሔደ በሚገኘዉ የማጠቃለያ ፕሮግራሙ #የኢፌዴሪ የሰላም ሚኒስትር ክቡር አቶ ታዬ ደንደዓን ጨምሮ #የሕብረቱ ፕሬዝደንት መጋቢ ፃዲቁ አብዶ እና ጥሪ የተደረገላቸዉ የአብያተ ክርስቲያናት መሪዎች እና ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛል።
The Christian News - የክርስቲያን ዜና በስፍራው የምንገኝ ሲሆን ዝርዝር መረጃ ይዘን የምንመለስ ይሆናል....
Photo @Hossana Photo & Video Production