The Christian News
5.37K subscribers
3.08K photos
29 videos
730 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
#ፀድቄአለሁ:: #አራት_ነጥብ::

እንግዲህ ምን እንላለን አለ መፀሃፉ::
ከመደነቅ ከመገረም ከማመስገን ውጪ::

#ዘርፌ የዘፈኑን አለም በቃኝ ብላ ወደ መንፈሳዊው አለም ከመጣች ጀምሮ በብዙዎች የምትደመጥ በሚያስደንቅ የድምፅ ስጦታዋ ስትዘምር ተፅኖ የፈጠረች አሁን ደግሞ ጌታ መንፈስ ቅዱስ እረድቷት ለመፅደቅ ሳይሆን ፅድቋን ትዘምረው ጀመር::

እኛንም ኑ ፅድቃችንን ኢየሱስን አብረን እንዘምረው እናክብረው ብላናለች::

እኛም #አሜን ብለናል::

እሁድ ግንቦት 14 በቀጠና ሁለት ሙሉወንጌል ቤተ ክርስትያን እንገናኝ #ሼር አድርጉ::

እንወዳችሁዋለን ተባርካችሁዋል::

አዳዲስ እና ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስቲያን ዜና እንዲደርሳችሁ የቴሌግራም ገፃችንን ይቀላቀሉ።
#live እየገባችሁ በልሳን የምትፀልዮ ሰዎች ስህተት ውስጥ ናችሁ። ዘማሪት ሶፊያ ሽባባዉ

#መጽሀፍ #ቅዱስ ድርጊታችሁን ስህተት ነው ስለሚል እኔም ስህተት ነው እላለሁ።

በየ ሚዲያውና በየ ቲቪ ቻናሎች በልሳን የሚጸለይበት አላማው ምንድነው? ይህን በማድረጋችሁ እምነቱን ከማሰደብና ማላገጫ ከማድረግ ውጭ አንዳች የምታመጡት ጥቅም የለምና እባካችሁ ስሜታዊነትን አስወግዱና ቃሉ እንደሚል እንሁን።

የሚመለከታቸው #ክርስቲያን #ሁሉ #አሜን እያለ ከማደፋፈር ይልቅ ልክ አለመሆናቸውን በማሳወቅ ማስተው ያስፈልጋል። ማንም ሰው ከቃሉ አይበልጥም።

አንዳንድ አገልጋዮች የማያምኑ ሰዎች በጉባኤው እንዳሉ እያወቁ እስኪ ሁላችሁ በልሳኖቻችሁ ጸልዩ ብለው ጭራሽ ትዛዝ ሲሰጡ ግራ ይገባኛል።ሰውም እነሱ ያሉትን ተከትሎ በሚያምንም በማያምንም ፊት በልሳን እየጮኸ ይጸልያል።

#የእግዚአብሔር #ቃል ነው መከበር ያለበት ወይስ የአገልጋዩ ትዕዛዝ? የሁልጊዜ ጥያቄዬ ነው።

1ቆሮንጦስ 14:23
እንግዲህ ማኅበር ሁሉ አብረው ቢሰበሰቡ ሁሉም በልሳኖች ቢናገሩና ያልተማሩ ወይም የማያምኑ ሰዎች ቢገቡ፡— አብደዋል አይሉምን?
#አስቸኳይ...

ሞትን ለማምለጥ የሚደረግ የሞኞች እሩጫ 🏃‍♂️🏃‍♀️🏃‍♂️🏃‍♂️

ከሰሞኑ #አንድ ዘገባ አነብብኩኝ ዝገባው #ቃል በቃል "የፌስቡክ መስራቹ ማርክ ዙከርበርግ ራሳቸውን ከዓለም ፍጻሜ ለመጠበቅ በሚል መጠለያ እየገነቡ መሆኑ ተገለጸ" ይላል #እንደ ርዕሱ ቢሆን ሁላችንም ፈገግ ብለን ብናልፈው መልካም #ነበር #ግን አይሆንም።

#ሁሉም #ሰው እንደሚሞት እንዲሁም የአለም ፍጻሜ እንዳለ እርግጠኛ ነው። ግን የሚመጣውን ጥፋትም #ይሁን የሚጠብቀውን የዘላለም #ሞት #እንዴት ማምለጥ እንዳለበት የተረዳ አይመስለኝም።

ለዚህም ይመስለኛል ባለጸጋው በአንድ ደሴት #ውስጥ ባለ #መሬት ውስጥ በ100 ሚሊዮን ዶላር መጠለያ በመገንባት #ላይ መሆናቸው የተሰማው።

አንዳንዴ ግን አጠቃቀሙን ካላወቅነው ሃብታም መሆን ከባድ ይመስለኛል።

ከ120 ቢሊዮን ዶላር በላይ የተጣራ ሀብት እንዳላቸው የሚነገረው ቱጃሩ የፌስቡክ መስራች ዙከርበርግ የደሴቲቱን ስፍራ በ170 ሚሊዮን ዶላር ከዓመታት በፊት የገዙት ሲሆን አሁን #ደግሞ #በዚህ ስፍራ ላይ ቅንጡ የክፉ #ጊዜ መኖሪያ #ቤት እየገነቡ ነው፡፡

#ይህ ስፍራ ለኑሮ አስፈላጊ የሚባሉ ምግቦችን ማምረት፣ የኤሌክትሪክ ሀይል፣ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ማድረጊያ ሜዳ፣ ውሃ ዋና #እና ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ አገልግሎቶችን #ሙሉ ለሙሉ ከዚሁ ስፍራ ማግኘት በሚያስችል መልኩ በመገንባት ላይ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

#ክፉ ጊዜ ግን መቼ #ነው? ይህ ክፉ ጊዜ ሲመጣ እንዴት በደሴቶች ተሸሽገን ማለፍ እንችል ይሁን?

#መጽሐፍ #ቅዱስ የጌታ ምጽዓት እና የአለም ፍጻሜ በቀረበ ጊዜ በመጨረሻው ዘመን ጦርነት እና የጦር ወሬ ፤ የተፈጥሮ አደጋ መብዛት እንዳለ ይነግረናል በራዕይ መጽሀፍ ደግሞ ደሴቶችም #ሁሉ ሸሹ ተራራዎችም አልተገኙም ይላል።

ታዲያ ቱጃሩ ወዳጃችን ደሴትም ፈልፍሎ ለክፉ #ቀን የሚሆን ማምለጫ የሚያዘጋጀው ከማን ለመሸሽ ነው?

#ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ #እውነት እውነት እላችኋለሁ ባለጠጋ #ወደ #እግዚአብሔር መንግስት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢገባ ይቀላል ያለው ቃል ግልጽ ይመስላል።

ስለ ስሙ ያላቸውን ሁሉ ትተው የተከተሉት ግን የዘላለምን ሕይወት ይወርሳሉናል።

ለማንኛውም ወዳጄ ማርክን እና ሌሎች ባለጠጎች ከክፉ ቀን ማንም ሸሽቶ አያመልጥም እና መሸሸጊያ ዋሻ ወደ ሆነዉ ኢየሱስ ተሰብስበኝ በተሰጠን ጊዜ ተጠቅመን መጽሀፍ "እነሆ በደመና ይመጣል አይንም ሁሉ ያየዋል" እንደሚል ያንን ለማየት እንናፍቅ "ማራናታ" #አሜን መልዕክታችን ነው።