The Christian News
5.37K subscribers
3.08K photos
29 videos
730 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
#የኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናት ምክር #ቤት ሊቋቋም ነው ተባለ።

የኢትዮጵያ #ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን፣ የኢትዮጵያ #ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን እና የኢትዮጵያ #ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ናቸው በኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤትን ለማቋቋም የተስማሙት።

ምክር ቤቱን ለማቋቋም ያስፈለገው፣ በሃገሪቱ አስፈላጊ የሆነውን አስቸኳይ ሰብዓዊ ድጋፍ፣ #ሰላም እና ማህበራዊ መስተጋብርን ለማጠናከር መሆኑ ተገልጿል።

#በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት #ወደ 20 ሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎች በግጭትና ተፈጥሮአዊ ችግሮች ሳቢያ አስቸኳይ ሰብዓዊ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል።

በአብያተ ክርስቲያናቱ መሪዎች መካከል ከህዳር 17-20 ድረስ ሰፊ ውይይት ሲካሄድ ቆይቷል ነው የተባለው።

ከስምምነቱ የተገኘ ቃለ ጉባኤ እንደሚያሳየው፣ ህብረቱ የተነጠሉ ተቋማት ቡድን ብቻ እንዲሆን የታሰበ አይደለም ይላል። ነገር #ግን ደግሞ ማንም አካል ያለ መመዘኛ መጥቶ የሚገባበትም አይሆንም ሲል ያስቀምጣል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ወክለው አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) ፣ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስን ወክለው ቄስ ዮናስ ዮናስ ይገዙ (ዶ/ር)፣ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያንን ወክለው ካርዲናል ብርሃነ ኢየሱስ ሱራፌል ተፈራርመዋል።

ህብረቱን #ወደፊት ለማስኬድ ይረዳ ዘንድ ግብረ ሃይልም ተቋቁሟል።

“እውን የሆነው የኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት፣ ለረጅም አመታት በውይይት ላይ የነበረ ነው፣ ለዚህ ስትሰሩ የነበራችሁ መሪዎች፣ ምስጋና ይገባቸዋል” ሲሉ ቄስ ዶ/ር ዮናስ ይገዙ ምስጋናቸውን ችረዋል።

አክለው #አሁን በክርስቶስ የምናምን ሁላችን በአንድ #ጥላ ስር ሆነን የህዝባችንን የሰላም፣ ፍትህ እና እርቅ ጥሪ በጋራ መልስ የምንሰጥበት አጋጣሚ ነው ብለዋል።